No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ይስሀቅ ጥጋቡ - ጠበቃ ጌታነው ሙንየ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የከተማ ቦታ የሉዝ መብት በሽያጭ የሚተላለፍበትን አግባብ የሚመለከት ነዉ። አመልካች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ በአዱስ አበባ ከተማ ቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 10 ክልል ዉስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር አዱስ የካርታ ቁጥሩ ቦላ10-1/100/3/7/30914 የሆነ ለቅይጥ አገልግልት እንዱዉል በሉዝ ለ1ኛ ተጠሪ የተሰጣቸዉን 883 ካሬ ሜትር ቦታ በወኪላቸዉ 2ኛ ተጠሪ አማካኝነት በቀን 11/06/2013ዓ/ም በተደረገ ዉል በብር 4,500,000.00 አመልካች ገዝቻለሁ።2ኛ ተጠሪ የሉዝ ክፍያ መፈጸም አልቻልኩም በማለታቸዉ አመልካች ግዥ የፈጸምኩበትን 50% ብር 2,250,000.00 ከፍያለሁ።ቀሪዉን በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ቀርበን ሰነድችን ስንረካከብ ለመክፈል ተስማምተናል።በወቅቱ የሉዝ ይዞታዉ ለሰባት ዓመታት የሉዝ ክፍያ ስላልተከፈለበት ይዞታዉ ወደ መሬት ባንክ እና ማስተላለፍ ጽ/ቤት ገብቶ ስለነበር ዉለን በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጅንሲ ቀርቦ ለመፈጸም አልተቻለም።ይዞታዉን ከመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽ/ቤት ለማዉጣት አመልካች ብር 700,000.00 ለሉዝ ክፍያ በ1ኛ ተጠሪ ስም ለቦላ ክፍለ ከተማ መሬት ባንክና ሉዝ ጽ/ቤት በዲሽን ባንክ በኩል ከፍያለሁ።2ኛ ተጠሪ ከጽ/ቤቱ ደረሰኝ አስቆርጠዉ እንዱያመጡ ብጠይቃቸዉ ፈቃደኛ አልሆኑም።እንዱሁም ብር 50,000.00 በ2ኛ ተጠሪ ስም ገቢ አድርጌያለሁ። በድምሩ ብር 3,000,000.00 ክፍያ ለተጠሪዎች ማስጠንቀቂያ ብሰጣቸዉም በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ቀርበዉ የሽያጭ ዉለን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆኑም። ስለሆነም በዉለ የተመለከተዉን መቀጮ ብር 1,000,000.00 እንዱሁም በዉለ መሰረት ባለመፈጸማቸዉ ለደረሰብኝ ጉዲት ካሳ ብር 250,000.00 ከፍለዉ የሉዝ መብት በሽያጭ የማስተላለፍ ዉለን ተገደዉ እንዱፈጽሙ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መልስ 1ኛ ተጠሪ ዉለን አላዉቅም።የሉዝ መብቴን ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ የሚያስችል ዉክልና አልሰጠሁም።1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር የፈጸምኩት የሉዝ መብት ማስተላለፍ ዉል የለም።አመልካች በልላቸዉና ባልተፈጠረ መብት ላይ ተመርኩዘዉ ያለምንም ሕጋዊ መሰረት ያቀረቡት ክስ የሕግ መሰረት የላለዉ በመሆኑ ተገድጄ የሉዝ መብቴን የማስተላልፍበት ምክንያት የለም።የሉዝ መብት በማይንቀሳቀስ ይዞታ መነሻነት የሚገኝ በመሆኑ ይህንን መብት ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 እና 2878 መሰረት መደረግ ሲገባዉ በዚህ አግባብ የተደረገ ዉል አልቀረበም።የሉዝ መብት የሚተላለፈዉ በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 24/2 መሰረት አግባብ ባለዉ አካል ቁጥጥር ተደርጎበት ግልጽ የሽያጭ ስርዓት ተከትል የሚደረግ በመሆኑ 1ኛ ተጠሪም ሆንኩ የመንግስት አካል በማያዉቀዉ ሁኔታ ተዘጋጅቶ በቀረበ የሽያጭ ዉል 1ኛ ተጠሪ የሉዝ መብቴን የማጣበት ምክንያት የለም።ስለሆነም ዉል የለም ተብል ክሱ ዉድቅ ላሆን ይገባል።የዉል ግንኙነት ስለላለኝ 1ኛ ተጠሪ በክሱ የተጠቀሰዉን መቀጮ እና ኪሳራ የምከፍለበት ምክንያት የለም። አመልካች ብር 700,000.00 በ1ኛ ተጠሪ ስም አልከፈለም።ለምን ዓላማ እንደከፈለም ማስረጃዉ አያሳይም።ይህ ክፍያ ከሉዝ ክፍያዉ ጋርም ግንኙነት የለዉም።በመሆኑም በዚህም ረገድ ያቀረቡት ጥያቄ ዉድቅ ላሆን ይገባል።2ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር የሉዝ መብት ለማስተላለፍ በክሱ የተጠቀሰዉን ዉል አልተዋዋልኩም።ዉለ ላይ አልፈረምኩም።በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 መሰረት የተደረገ ዉል በማስረጃነት አልቀረበም።በመካከላችን የዉል ግንኙነት በላለበት መቀጮና ኪሳራ ለአመልካች የሚከፈልበት ምክንያት የለም።ዉል ሳይኖር አመልካች የሉዝ ክፍያ ሉከፍለ ስለማይችለ ብር 700,000.00 ከፍያለሁ ያለት ተቀባይነት የለዉም ተብል ክሱ ዉድቅ እንዱደረግ በመጠየቅ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎችን መርምሮ በቀን 06/04/2014ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ 1ኛ ተጠሪ በክሱ ካርታ ቁጥሩ የተጠቀሰዉን ቤት እንዱሸጡ በቀን 13/11/2020ዓ/ም ለ2ኛ ተጠሪ የዉክልና ሥልጣን መስጠታቸዉ ተረጋግጧል።ለክሱ መነሻ የሆነዉ በቀን 11/06/2013ዓ/ም የተደረገዉ ዉል የ1ኛ ተጠሪን የሉዝ መብት በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገ ነዉ።2ኛ ተጠሪ የዉክልና ሥልጣናቸዉን በመጠቀም የ1ኛ ተጠሪን የሉዝ መብት ለአመልካች በዉል ማስተላለፊቸዉ ተረጋግጧል።አመልካች ቀሪዉን 50% ክፍያ ዉል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፉት ቀርበዉ ዋናዉን የሽያጭ ዉል ሲዋዋለ እና ቤቱን የሚመለከቱ ልዩ ልዩ ሰነድችን ርክክብ ሲፈጽሙ እንደሆነ ተስማምተዋል።በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት ግራ ቀኝ ዉል ሥልጣን ባለዉ አካል ፉት ቀርበዉ ለመዋዋል የገቡትን ግዳታ ተፈጻሚ ማድረግ ካልቻለ የተዘጋጀዉ ስምምነት ረቂቅ እንጂ ከጅምሩ ዉል አይደለም በማለት በወሰነዉ መሰረት በግራ ቀኙ መካከል ያለዉ ስምምነት ረቂቅ በመሆኑ ተጠሪዎች ተገደዉ ሉፈጽሙ አይገባም።ዉለ ረቂቅ በመሆኑ በክሱ የተጠየቀዉን መቀጮና ኪሳራም ተጠሪዎች ሉከፍለ አይገባም።ነገር ግን አመልካች ለተጠሪዎች የከፈለትን ብር 2,250,000 እና ለ2ኛ ተጠሪ ገቢ ያደረጉትን ብር 50,000.00 በድምሩ ብር 2,300,000.00 ተጠሪዎች ባልተነጣጠለ ኃላፉነት ለአመልካች ሉከፍለ ይገባል።አመልካች ለሉዝ ክፍያ ብር 700,000.00 ከፈልኩኝ ያለትን ገንዘብ ለሉዝ ክፍያ ስለመክፈላቸዉ ያላስረደ በመሆኑ ከሚመለከተዉ ላላ አካል መጠየቅ ይችላለ እንጂ ተጠሪዎችን መጠየቅ አይችለም በማለት ወስኗል።
አመልካች በዉሳኔዉ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ በቀን 07/07/2014ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞባቸዋል።
አመልካች በቀን 21/08/2014 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ፡- 2ኛ ተጠሪ በ1ኛ ተጠሪ በተሰጣቸዉ የዉክልና ሥልጣን በጽሁፍ በተደረገ የሽያጭ ዉል የሉዝ ይዞታ ለአመልካች አስተላልፈዋል።ዉለ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ዉል ሳይሆን የሉዝ መብትን በሽያጭ የማስተላለፍ ዉል ነዉ።የሉዝ መብት በሽያጭ ማስተላለፍ በይዞታዉ ላይ ያለዉን መብት በልላ አካል መተካት እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ የሉዝ መብትን በሽያጭ የማስተላለፍ ዉል ደግሞ በከተማ መሬት ሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 24፣ደንብ ቁጥር 49/2004 አንቀጽ 38 እና 39 እንዱሁም መመሪያ ቁጥር 93/2014 አንቀጽ 7.4 ከመንግስት አካል ጋር ዉል በመዋዋል የሚገኝ መብት ነዉ።ከዚህ ዉጭ ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 መሰረት እንዱፈጸም የሚያስገድድ ድንጋጌ የለም።የሉዝ መብት ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል በተመለከተ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉ አስገዲጅ ትርጉም ተፈጻሚ ላሆን ይገባል።የስር ፍርድ ቤት በሕግ ፉት የሚጸና ዉል አለ ወይስ የለም የሚለዉን ከዚህ አኳያ ሳይመረምር በግራ ቀኙ መካከል የጸና ዉል የለም ሲል የደረሰበት ድምዲሜ ስህተት ነዉ።ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ዉል ሥልጣን ባለዉ አካል ላደረግ አይችልም ስላልተባለና ይህንን ማድረግም ግዳታ ስላልሆነ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት የላለዉን በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን ዉሳኔ በመጥቀስ ዉለ እንደ ረቂቅ ይቆጠራል ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ የሕጉን መንፈስ የተከተለ አይደለም።2ኛ ተጠሪ በሽያጭ ዉለ መሰረት ገንዘቡን መቀበላቸዉን ስለአመኑ ዉለ መኖሩን ማመናቸዉን ያሳያል።በዚህ መልኩ ዉለ መኖሩን እስከአመኑ ድረስ የዉለን ፍርማሉቲ በመከራከሪያነት በማንሳት የሚያቀርቡት ክርክር በሰ/መ/ ላይ ከተሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም አንጻር ተቀባይነት የለዉም።አመልካች በ1ኛ ተጠሪ ስም ለሉዝ ክፍያ ብር 700,000.00 መክፈለን በምስክሮች ለማስረዲት የቆጠርኩትን ምስክሮች ሳይሰማ በዚህ ረገድ የጠየቅሁትን ዲኝነት ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉን የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነዉ። እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ወለድ ተጠሪዎች ገንዘቡን ከተቀበለበት ጊዜ ጀምሮ እንዱከፍለ አለመወሰኑ እና ወጪና ኪሳራ አመልካች ለዲኝነት በከፈልኩት እንዱሁም ለጠበቃ አበል በከፈልኩት ልክ አለመወሰኑ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት አቤታቸዉን አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ በተሰጣቸዉ ዉክልና ከአመልካች ጋር በቀን 11/06/2013ዓ/ም የሉዝ ይዞታ መብትን በሽያጭ ለማስተላለፍ ዉል ተዋዉለዉ ብር 2,300,000.00 ከአመልካች የተቀበለ መሆኑ በተገለጸበት ዉለ ረቂቅና ያልተመዘገበ በመሆኑ ተጠሪዎች ይዞታዉን ለማስተላለፍ በዉል ሉገደደ አይገባም በሚል የተወሰነበትን አግባብ በሰ/መ/ ላይ ከተሰጠዉ የሕግ ትርጉም፣ከፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ከሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 24 እንዱሁም አዋጁን ተከትለዉ ከወጡ ደንብና መመሪያ አንጻር ተጠሪዎች ባለበት እንዱመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በቀን 09/10/2014ዓ/ም በተናጠል የተጻፈ መልስ አዘጋጅተዉ አቅርበዋል።
የመልሳቸዉም ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች በሰር ፍርድ ቤት የተሰጠዉን ዉሳኔ በማስፈጸም የተፈረደላቸዉን ገንዘብ ከተቀበለ በኋላ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት ሉኖረዉ አይገባም።አመልካች ዉል ነዉ በሚል ያቀረቡትን ሰነድ ተጠሪዎች የማናዉቀዉ እና የሉዝ መብት ለማስተላለፍ የተደረገ ዉል እንደላለ በመግለጽ ተከራክረናል።የሉዝ መብት ማስተላለፍ የሚቻለዉ በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 24፣ በደንብ ቁጥር 49/2004 እና በመመሪያ ቁጥር 11/2004 መሰረት ከሚመለከተዉ የመንግስት ተቋም ተገቢዉ ፈቃድ ሲገኝ ብቻ ነዉ።ይህም የሚያሳየዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 ስር ከተደነገገዉ ፍርማሉቲ በተጨማሪ ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ መሟላት እንዲለበት ነዉ።ዉል የለም እንጂ አለ ቢባል እንኳ ዉለ የተደረገዉ የሉዝ መብትን ለማስተላለፍ በሚቻልበት ደረጃ ግንባታ ሳይከናወን ነዉ።ስለሆነም የዉለ ጉዲይ ሕጋዊ ካለመሆኑም በተጨማሪ ሉፈጸም የማይችል ነዉ።ይህም ዉለን ፈራሽ የሚያደርግ ነዉ።የሉዝ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል በማይንቀሳቀስ ይዞታ ላይ የሚደረግ ዉል እንደመሆኑ መጠን ከቤት ሽያጭ ዉል የተለየ አይደለም።ስለሆነም ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት ላደረግ ይገባል።2ኛ ተጠሪ ከአመልካች ገንዘብ መቀበላቸዉ ብቻዉን የሉዝ መብትን ለማስተላለፍ ዉል ፈጽመዋል የሚያስብል አይደለም።በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በትክክል በተደረገና ስለመደረጉም በተከራካሪ ወገኖች በታመነ ዉል ላይ ብቻ እንጂ ከጅምሩ ዉል የለም ተብል ክርክር በቀረበበት ጉዲይ ላይ ተፈጻሚነት የለዉም።ዉለ በተዋዋይ ወገኖች ያልታመነና በሰ/መ/ ላይ በተሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት ሕጋዊ ዉጤት የላለዉ በመሆኑ ምስክሮች አለመስማት በዉጤት ደረጃ የሚያመጣዉ ለዉጥ የለም።እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ወለድ፣ ወጪና ኪሳራ ተጠሪዎች በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት እንድንከፍል መወሰኑ አመልካችን የሚጠቅም ከመሆኑም በተጨማሪ አመልካች አለአግባብ አጋነዉ በመጠየቅ ያወጡትን ወጪ ቀንሶ በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም የመልስ መልሳቸዉን በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኙ ክርክርና በስር ፍርድ ቤት እና በይግባኝ ሰሚዉ ችልት የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም በግራ ቀኙ መካከል ሕጋዊ ዉጤት በሚኖረዉ አኳኋን የተደረገ ዉል የለም በሚል በተሰጠዉ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም የክርክሩ ሥረ ነገር 2ኛ ተጠሪ በ1ኛ ተጠሪ በተሰጣቸዉ የዉክልና ሥልጣን በ1ኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የከተማ ቦታ የሉዝ መብት ለአመልካች በሽያጭ ለማስተላለፍ ተደረገ የተባለዉን የሽያጭ ዉል መነሻ ያደረገ ነዉ። ተጠሪ በክሳቸዉ ላይ የሽያጭ ዉለ በቀን 11/06/2013ዓ/ም እንደተደረገ እና የቤቱም ሽያጭ ዋጋ ብር 4,500,000.00 ሆኖ በዉለ ደረሰኝነት የዋጋዉን 50% ብር 2,250,000.00 መክፈላቸዉን፣ብር 50,000.00 ለ2ኛ ተጠሪ ገቢ ማድረጋቸዉን እንዱሁም ብር 700,000.00 ለሉዝ ክፍያ እንዱዉል ለቦላ ክፍለ ከተማ መሬት ባንክና ሉዝ ጽ/ቤት በ1ኛ ተጠሪ ስም በዲሽን ባንክ በኩል ገቢ ቢያደርጉም ተጠሪዎች በዉለ መሰረት ሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ዘንድ በመቅረብ ዉለን ለመዋዋልና ተገቢዉን ሰነድ ለማስረከብ ፈቃደኛ እንዲልሆኑ በመግለጽ ተገደዉ እንዱፈጽሙና በዉለ የተመለከተዉንና ክስ የቀረበበትን መቀጮና ኪሳራ እንዱከፍለ እንዱወሰንላቸዉ ዲኝነት ጠይቀዋል። ተጠሪዎች ከላይ በተመለከተዉ አግባብ አመልካች በክሱ የጠቀሱትን ዉል እንዲልተዋዋለ በመግለጽ ክደዉ ከመከራከራቸዉም በተጨማሪ አመልካች በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት የተደረገ የሽያጭ ዉል በማስረጃት ያላቀረቡ መሆኑን ጭምር በመጥቀስ ተገደዉ እንዱፈጽሙ የሚያደርግ የጸና ዉል የለም ሲለ ተከራክረዋል።
በመርህ ደረጃ ተዋዋይ ወገኖች በፈለጉት አይነት ፍርም እና ሁኔታ ዉል ቢዋዋለ ዉላቸዉ የሕግ ደረጃ ተሰጥቶት የሚያስገድዲቸዉ ይሆናል። ሕግ በልዩ ሁኔታ አንድ ዉል መደረግ ስላለበት የአጻጻፍ ስርዓትና (ፍርምና) ምዝገባ በተመለከተ የደነገገዉ ካለ ይሄዉ የአጻጻፍ ስርአት(ፍርም) ተፈጻሚ መሆን ይኖርበታል። የአንድን ዉል ጉዲይ መሰረት በማድረግ ዉለ ልዩ የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትል እንዱደረግ በሕግ የተደነገገ እንደሆነ ተዋዋይ ወገኖች ዉላቸዉን በሕግ በተወሰነዉ ፍርም መሰረት የማድረግ ግዳታ እንዲለባቸዉ እና ይህን ካላደረጉ ዉለ ሕጋዊ ዉጤት እንደማያስከትል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1678፣1719 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ የተመለከተዉ ያሳያል።ልዩ የአጻጻፍ ሥርዓትን ተከትለዉ እንዱደረጉ በሕግ ከተለዩት የዉል ጉዲዮች ዉስጥ አንደ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ባለቤትነት ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል ነዉ።በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1130 ስር እንደተደነገገዉ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች የሚባለት መሬትና ቤት ናቸዉ። በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት የማይንቀሳሰቀስ ንብረት ባለቤትነትን በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚደረግ የሽያጭ ዉል በጽሁፍ ሆኖ ዉል ለማዋዋል በሕግ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፉት መደረግና መረጋገጥ (መመዝገብ/ authentication) እንዲለበት ተደንግጓል።
ይህንን አጻጻፍ ተከትል ያልተደረገ የቤት ሽያጭ ዉል እንደ ረቂቅ እንደሚቆጠርና ሕጋዊ ዉጤት እንደማያስከትል ከፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1720/1 እና 1723/1 ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል።የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ (በቀጽ 4 ላይ እንደታተመዉ) የሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉምም ይህንኑ የሚያሳይ ነዉ።
በልላ በኩል የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ዉል መደረጉን ግራ ቀኙ የተማመኑ እንደሆነ ወይም ተዋዋዮች የሽያጭ ዉል በመካከላቸዉ መኖሩን ያልተካካደ እንደሆነ ዉለ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር በተደነገገዉ መሰረት በሕግ ዉል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፉት ተደርጎ ያልተረጋገጠ ቢሆንም እንኳን ዉለ ሕጋዊ ዉጤት እንደሚኖረዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ (ቅጽ 13 ላይ እንደታተመዉ) እና በላለች መዛግብት ላይ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የሽያጭ ዉል የተደረገዉ የከተማ ቦታ የሉዝ መብት ለማስተላለፍ በመሆኑ ዉለ መደረግ ያለበት በሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 24 መሰረት በመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገዉ የአጻጻፍ ሥርዓት ተፈጻሚ ላሆን አይገባም በማለት የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪዎች ደግሞ የሉዝ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል የማይንቀሳቀስ ንብረት በሽያጭ ከማስተላለፍ የተለየ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገዉን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትል መደረግ ብቻ ሳይሆን በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 24 ስር በተደነገገዉ መሰረት በሚመለከተዉ የመንግስት አካል ሉፈቀድ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 18 እና 19 ስር እንደተደነገገዉ በሕጉ በተደነገገዉ አግባብ ሉራዘም የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሉዝ የሚገኝ የከተማ ቦታ የመጠቀም መብት ጸንቶ የሚቆይበት ዘመን እንደ ቦታዉ አገልግልት አይነት ከ15 ዓመት እስከ 99 ዓመት ድረስ ነዉ። በዚህ አግባብ የተገኘዉን የሉዝ መብት በአዋጁ አንቀጽ 24/1 ስር በተደነገገዉ መሰረት ማንኛዉም የሉዝ ባለይዞታ መብቱን ለማስተላለፍ ወይም በከፈለዉ የሉዝ ክፍያ መጠን በዋስትና ለማስያዝ ወይም በካፑታል አስተዋጽኦ ለመጠቀም እንደሚችል ተደንግጓል።እንዱሁም ማንኛዉም የሉዝ ባለይዞታ ከዉርስ በስተቀር ግንባታ ከመጀመሩ በፉት ወይም የግንባታዉን ግማሽ ከማጠናቀቁ በፉት የሉዝ መብቱን ማስተላለፍ የሚችለዉ አግባብ ባለዉ አካል ቁጥጥር ተደርጎበት ግልጽ የሽያጭ ሥርዓትን በመከተል (…shall be required to follow transparent procedures of sale to be supervised by the appropriate body.) እንደሆነ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 24/2 ስር የተደነገገዉ ያሳያል።በአዋጁ አንቀጽ 2/6 ስር በተመለከተዉ ትርጓሜ መሰረት አግባብ ያለዉ አካል ማለት የከተማ ቦታን ለማስተዲደርና ለማልማት ሥልጣን የተሰጠዉ የክልል ወይም የከተማ አስተዲደር አካል ነዉ።
በልላ አግባብ ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር በመሬት የመጠቀም መብት…ሲተላለፍ በመሬቱ ላይ የተገነባዉ ሕንጻና ከሕንጻዉ ጋር የተያያዙ መገልገያዎች መብት አብሮ እንደሚተላለፍ…በአዋጁ አንቀጽ 24/6 ላይ ተመልክቷል።
እንዱሁም የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ባወጣዉ የከተማ መሬት ሉዝ ደንብ ቁጥር 49/2004 ከአንቀጽ 38 እስከ 41 ስር ግንባታ ያልተጀመረበትን እና ግማሽ ግንባታ ያረፈበትን ቦታ የሉዝ መብት በሽያጭ ማስተላለፍ የሚቻልበት አግባብ በዝርዝር ተደንግጓል።በሽያጭ የሚተላለፈዉ ግንባታ ያልተጀመረበት ቦታ ከሆነ የሉዝ መብት ሽያጩ ዋጋ የሚወሰነዉ አግባብ ባለዉ አካል እንደሆነና ዋጋዉም ወቅታዊ የመሬት ሉዝ መብት መሸጫ ዋጋ እንደሚሆን፣ ባለመብቱ በዋጋዉ ካልተስማማ መሬቱ ለጨረታ እንደሚወጣና ለጨረታ እንዱወጣ ካልተስማም አግባብ ያለዉ አካል በአዋጁ አንቀጽ 24(3/ሀ) መሰረት ክፍያ በመፈጸም አግባብ ያለዉ አካል ክፍያ በመፈጸም ቦታዉን መልሶ እንደሚወስድ፣የሉዝ መብት የሽያጭ ዉል እና የስም ዝዉዉሩ የሚፈጸመዉ የሉዝ ክፍያ ለመፈጸም ገዥ ዉል ከተዋዋለ እና የሉዝ ቅድመ ክፍያ ከፈጸመ በኋላ እንደሆነ፤ግማሽ ግንባታ የተከናወነበት ሲሆን ደግሞ አግባብ ባለዉ አካል የመሬት ሉዝ መብት ዋጋ እና የግንባታ ዋጋ በሚል ተለይቶ ቀርቦ ባለመብቱ በዚህ አግባብ በቀረበዉ የመሬት ሉዝ መብት መሸጫ ዋጋ ሲስማማ እና የመሬት ሉዝ ዋጋዉን ገዥ አግባብ ላለዉ አካል ገቢ ሲያደርግ፣ የሉዝ ዉል መዋዋል ሲቻል እና የሉዝ ቅድመ ክፍያ ሲፈጸም ብቻ እንደሆነ ተመልክቷል፤የሉዝ መብት የተሸጠበት ገንዘብ ለሻጭ የሚከፈለዉ አግባብ ባለዉ አካል በኩል እንደሆነም በዚሁ ደንብ ተደንግጓል።(የደንቡ አንቀጽ 38 እና 39 ይመለከቷል።) ከዚህ በላይ በዝርዝር እንደተገለጸዉ በሉዝ አዋጅ እና ደንብ ላይ ከተደነገገዉ መረዲት የሚቻለዉ የሉዝ መብት በሽያጭ የሚተላለፈዉ ግንባታ ያልተጀመረ ቦታ ከሆነ በሕግ በተመለከተዉ አግባብ የሉዝ ዘመኑ ሉራዘም የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የሉዝ ዘመኑ እስከሚያልቅ ድረስ በቦታዉ የመጠቀም መብት እንደሆነ፤የሉዝ መብት የተላለፈዉ በቦታዉ ላይ ግማሽ ግንባታ ከተከናወነ በኋላ ከሆነም የሚተላለፈዉ ለሉዝ ዘመኑ በቦታዉ የመጠቀም መብት ብቻ ሳይሆን በቦታዉ ላይ ከተሰራዉ ሕንጻ ጭምር በመሆኑ አመልካች የሉዝ መብት ማስተላለፍ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንደማስተላለፍ የሚቆጠር አይደለም በማለት ያቀረቡት ክርክር የሕግ መሰረት ያለዉ አይደለም።እንዱሁም በሉዝ የተገኘ የከተማ ቦታ ግንባታ ሳይከናወን እና ግማሽ ግንባታ ተከናዉኖ በባለመብቱ ለሶስተኛ ወገን ሲተላለፍ ከላይ በተገለጸዉ አግባብ ባለመብቱና ገዥ በሚያደርጉት የሽያጭ ዉል ብቻ ግብይቱ የሚፈጸም ሳይሆን ከዋጋዉ ጀምሮ የዉል አፈጻጸሙ ጭምር አግባብ ባለዉ የመንግስት አካል ቁጥጥር የሚመራ ነዉ።
በዚህ ሥርዓት ለማሳካት የታቀደዉ የፕሉሲ ምክንያቶችም የከተማም ሆነ የገጠር መሬት ባለቤትነት የሕዝብና የመንግስት በመሆኑና ዉስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዱዉል ማድረግ፣ በመሬቱ ላይ እሴት ሳይጨመር አየር በአየር የሉዝ መብት በማስተላለፍ አለአግባብ መበልጸግ እንዲይኖርና የኢኮኖሚ አለመረጋጋት የሚያባብስ ምክንያት እንዲይሆን ለመከላከል፣ በማይገባ አኳኋን ዋጋ በገበያ ብቻ በመመራት እየተወሰነ የመሬት ተጠቃሚነትና ምርታማነት እንዲይቀንስ ለመከላከል እና ላልች ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፕለቲካዊ ምክንያቶችን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ይታመናል።
በተያዘዉ ጉዲይ አመልካች ተጠሪዎች የሉዝ መብት በሽያጭ የማስተላለፍ ዉለን ተገደዉ እንዱፈጽሙ ይወሰንልኝ በማለት ለጠየቁት ዲኝነት መሰረት ያደረጉትን ዉል ተጠሪዎች አልተዋዋልንም በማለት በግልጽ ክደዉ ተከራክረዋል።የሉዝ መብት ማስተላለፍ ማለት ደግሞ ከላይ እንደተገለጸዉ መብቱ የተመሰረተበትን የከተማ ቦታና በእላዩ ላይ የሰፈረ ሕንጻ(ግንባታ) ጭምር የሚመለከት ነዉ። ስለሆነም የሉዝ መብቱ የሚሸጥበትን ዋጋ ከመወሰን፣ መብቱን ለሦስተኛ ወገን ከማስተላለፍ አኳያ ሉሟለ የሚገባቸዉ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸዉን በማረጋገጥ የሉዝ ዉል ከገዥ ጋር ከመዋዋልና ስመ ሀብቱን ወደገዥ ከማስተላለፍ አንጻር የሚመለከተዉ የመንግስት አካል የሚኖረዉ ተሳትፍ እንደተጠበቀ ሆኖ በባለመብቱና በገዥ መካከል የሚደረገዉ ዉል ግልጽ የሽያጭ ሥርዓትን በመከተል (…shall be required to follow transparent procedures of sale…) መደረግ ይኖርበታል። ይህም ግልጽ የሽያጭ ሥርዓት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር የማይንቀሳቀስ ንብረት በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደነገገዉ ነዉ።በዚህ መሰረት የሉዝ መብት በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚደረገዉ ዉል አግባብ ባለዉ አካል ቁጥጥር ተደርጎበት በጽሁፍ መሆንና በሕግ ዉል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፉት ተረጋግጦ የተመዘገበ መሆን ይኖርበታል። የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ መደረጉን እና የሽያጭ ዉለን ይዘት አስመልክቶ ተክድ ክርክር በቀረበ ጊዜ እንዱህ አይነት ክርክር ለማስረዲት ላቀርብ የሚገባዉ ማስረጃ ዉል ለማማዋል ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፉት ተደርጎ መመዝገቡን ወይም መረጋገጡን (Authentication) የሚያሳይ ዉል ላሆን ይገባል እንጂ በምስክር ወይም በልላ ማስረጃ ማስረዲት አይቻልም።
ሲጠቃለል በያዝነዉ ጉዲይ አመልካች ከተጠሪዎች ጋር ተዋዋልኩኝ ያለትን ዉል ተጠሪዎች ክደዉ የተከራከሩ በመሆኑ አመልካች በሚመለከተዉ የመንግስት አካል ቁጥጥር ተደርጎበት በዉል አዋዋይ ፉት የተደረገ የሉዝ መብት ሽያጭ ዉል በማስረጃነት በማቅረብ በሕግ አግባብ የተደረገ ዉል መኖሩን ማስረዲት አልቻለም።በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት በሕግ ፉት ዉጤት ያለዉ ዉል በግራ ቀኙ መካከል አልተደረገም በሚል ተጠሪዎች ከአመልካች የተቀበለትን ገንዘብ ሉመልሱ ይገባል ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ ከዉጤት አንጻር ሲታይ በዚህ ችልት ሉታረም የሚችል ስህተት የተፈጸመበት አይደለም።እንዱሁም መቀጮና ወለድ በተጨማሪም ለሉዝ ተከፈለ የተባለዉ ብር 700,000.00 በሕግ አግባብ የተደረገ ዉል ሕጋዊ ዉጤት በመሆኑ በግራ ቀኙ መካከል ሕጋዊ ዉጤት ያለዉ ዉል የለም የሚል ድምዲሜ ላይ ተደርሶ ዉድቅ መደረጉ እና ተጠሪዎች የተቀበለትን ብር 2,300,000.00 እና ከዚህ ጋር በተያያዘ ክሱ ያስከተለዉ ወጪ እንዱከፍለ በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም ብለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 06/04/2014 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 07/07/2014 ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንተዋል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ት ዔ ዛ ዝ
የውሳኔው ግልባጭ ለግራ ቀኙ ይሰጣቸዉ፤ለሥር ፍርድ ቤቶችም ይተላለፍ።
የፍርድ አፈጻጸም እንዱታገድ የተሰጠው ትእዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.