No summary available.
መ/ቁ/ 199697 ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ሰሃኔ አህመድ አብዱ - ጠበቃ ጌቱ ሶሬሳ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሙሁሙድ አብዱ መድቤ - አልቀረቡም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የገጠር መሬት ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በሶማላ ክልል በደቡብ ጅጅጋ ወረዲ ፍ/ቤት ላይ የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩበት ነዉ።አመልካች ያቀረበው ክስ ይዘት ባጭሩ በሸቤላ ወረዲ በለድካ ቀበላ የሚገኝ 200 ጋሻ መሬት ከአባቴ የወረስኩና ለመሬቱም በፍ/ብ/ህ/ቁ 1195 መሰረት በሃይለስላሴ ዘመን የይዞታ ካርታ ማረጋገጫ ያለኝ ሲሆን ቦታው በ4 ቤተሰብ ይዞታ ስር የሚገኝ ጫትና ማሽላ የሚመረትበት ሲሆን ያልታረሰ መሬት የቤተሰብ አባላት መኖሪያ መንደር እና ለእንስሳት ግጦሽ የሚውል ተጠሪ እንዱለቅልኝ ይወሰንልኝ የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩለ በመካከላችን የቦታ ይገባኛል ጥያቄ ጉዲይ በሽማግላዎች ለመዲኘትና ውሳኔያቸውን ለመቀበል በፊርማችን አረጋግጠን በቀን 30/07/2012ዓ.ም ተስማምተናል።ቦታው የእኔ ከመሆኑም በላይ የሸቤላ ወረዲ አስተዲደርም በቁጥር 534/012 በቀን 01/08/2012 ዓ.ም የሽማግላዎቹን ውሳኔ ያፀደቀ ሲሆን የጎሳ መሪው ጋራድ ኩልሚዬ በ03/08/2012 ዓ.ም እንዱሁም የሲን ቀበላ አስተዲደርም በ06/08/2012 ዓ.ም ደብዲቤ የሽማግላዎችን ውሳኔ ያፀደቁ ናቸዉ።ስለዚህ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 244(1/ሀ) መሰረት ጉዲዩ በአዱስ መልክ መታየት የለበትም በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆን ሲል መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል።
ፍ/ቤቱም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በፍሬ ነገር ላይ አከራክሮ የግራ ቀኝ የሰነድና የሰው ምስክሮች ቃል መርምሮ ለክሱ ምክንያት የሆነው ቦታ የተጠሪ ይዞታ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፊፈን ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍ/ቤቱም ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት መዝገቡን መርምሮ አመልካች ያቀረበው መሬት ባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አግባብ አልነበረም ምክንያቱም በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የተሻረ እና ያለአግባብ የተዘጋጀ ነው፣መሬቱ ላይ የጫት ምርት አለኝ የሚለው ከእውነት የራቀ ነው፣ ስለዚህ የተጠሪ ማስረጃ አብላጫ ያለው ነው በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቷል።አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበዉን አቤቱታ ችልቱ መርምሮ በውሳኔው ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት አልተፈፀመም በማለት አቤቱታው ውድቅ አድርጎታል።
በዚህ ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች ለዚህ ችልት ያቀረበው አቤቱታ ይዘት ባጭሩ ሲታይ ማንኛውም ክርክር ሉወሰን የሚገባው በቀረበው ማሰረጃ እና በህጉ መሰረት ብቻ መሆኑን፤ይህ ታልፍ የሚሰጥ ውሳኔ ህጋዊ ላሆን እንደማይችል፤የስር ፍ/ቤት ማስረጃዎቹ ምን እንዲስረደ፣ የአመልካች ማስረጃዎች በምን ምክንያት ውድቅ እንደተደረጉ፣በአካባቢው ተገኝቶ ምን እንደተገነዘበ ለውሳኔ ያበቃዉ ማስረጃ የትኛው እንደሆነ ሳይጠቅስ እንዱሁም የተያዘው ጭብጥ ምን እንደሆነ እና የፍርድ ሐተታ ሳይቀመጥ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፣የተጠሪ ምስክሮች የተጠሪ ነው ብል አዋሳኝ ጠቅሶ የመሰከሩት የተለየ ቦታ ሆኖ እያለ መሬቱ የተጠሪ ነው በማለት የሰጠዉ ውሳኔ የስነ ስርዓት ደንብ የተከተለ አይደለም፣በአስተዲደር እና በሽማግላዎች ለተጠሪ ተወስኗል ተብል የቀረበው ሰነድ ሰመተር ፊራህ እና ሂርሲ ፊራህ በሚባል ጎሳዎች መካከል የተነሳ ክርክር እንጂ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል እንዲልሆነ ተጠቅሶ እያለ የፍ/ብ/ህ/1195 ጠቅሶ ውሳኔ ማሳለፈ እና የገጠር መሬት ህግና አዋጅ መሰረት በማድረግ ውሳኔ መሰጠት ሲገባ ይህንን ሳያደርግ ህግን እና መደበኛ የሙግት አመራር ሥነ ሥርዓት በመጣስ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ውሳኔው በመሻር ተጠሪ ያለአግባብ የወሰደው መሬት እንዱመልስ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል።
የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ በስር ፍ/ቤቶች የተደረገው ክርክርና የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ስርዓትን እና የማስረጃ ምዘና መርህን የተከተለ መሆን አለመሆን ተጠሪ ባለበት ለማጣራት ጉዲዩ ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዟል።
ተጠሪ ባቀረበው መልስ በአዋጅ ቁ/456/1997 አንቀጽ 12 መሰረት ከእርሻ መሬት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ግጭትና አለመግባባት በግራ ቀኝ በተመረጡ ሽማግላዎች ታይቶ ውሳኔ ማግኘት እንዲለበት በሚገልጸዉ መሰረት ክርክር ያስነሳው መሬት ከአያታችን የተላለፈልን በእጄ የሚገኝ ይዞታ መሆኑ አረጋግጦ በሽማግላዎች እና በጎሳ መሪ ጋራድ ኩልሚዬ እና የቀበላው አስተዲደር ጽ/ቤት የሽማግላዎች ውሳኔ በመደገፍ ያጸደቀ በመሆኑ አመልካች በስር ፍ/ቤት ይህንን ሃቅ ማስተባበል ባለመቻለ ተወስኖበታል።አመልካች ስርዝ ድልዝ ያለበት በኃይለስላሴ ዘመን የተሰጠ ተአማኚነት የጎደለው ሰነድ አቅርቦ ቢከራከርም በቁጥር 31/67 በወጣው የመሬት አዋጅ መሰረት መሬት ለአራሹ ድንጋጌ መሰረት የተሰረዘና የተሻረ በመሆኑ ማስረጃው ተቀባይነት የለዉም፤የስር ፍ/ቤት ማስረጃዉን ውድቅ ማድረጉ ትክክለኛ ነው።የስር ፍ/ቤት ጭብጥ በመመስረት መሬቱ የሚገኝበት የመስክ ምልከታ በማድረግ አጣርቶ የግራ ቀኝ ማስረጃ መርምሮ የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት የህግ ምክንያት የለም፣በየደረጃው ያለ ፍ/ቤቶች ይህንኑ በማገናዘብ ውሳኔውን ያፀደቁ በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ ወጪና ኪሳራ ተወስኖልኝ በነፃ እንዱሰናበት በማለት ተከራክረዋል።አመልካች አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ አመልካች ክስ ያቀረበበት የገጠር መሬት ተጠሪ ያለአግባብ ይዟል በሚል በፍርድ ሃይል ተገድ እንዱለቅ ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ ይዞታዉ በእጁ የገባዉ በዉርስ የተላለፈለት ስለመሆኑ እና ክስ የቀረበበት ይዞታ ላይ አመልካች መብት የላለዉ መሆኑን መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል።ይሁንና ፍሬ ነገር የማጣራትና ማስረጃ የመመርመር ስልጣን በህግ የተሰጣቸዉ የሥር ፍርድ ቤቶች ጉዲዩ አስቀድሞ በግራ ቀኙ ስምምነት በተመረጡ ሽማግላዎችና የጎሳ መሪ ታይቶ የተጠሪ ይዞታ ስለመሆኑ ተወስኖ በወረዲዉ መሬት አስተዲደር አካል የጸደቀ መሆኑን አረጋግጠዉ የአመልካችን ክስ ዉድቅ ስለማድረጋቸዉ ተገንዝበናል።አመልካች አሁንም አጥብቆ የሚከራከረዉ የሥር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የክርክር አመራር እና የማስረጃ ምዘና ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት ነዉ።በዋናነትም አከራካሪዉ ይዞታ የአመልካች ስለመሆኑ በሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የተሰጠ የግል ይዞታ ማረጋገጫ እያለኝ ለተጠሪ መወሰኑ የማስረጃ ምዘና ስህተት ነዉ በማለት ይከራከራል።እኛም ይህንኑ መሰረት በማድረግ በስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን እንደሚከተለዉ መረምረናል።
አንድ መብት ወይም ግዳታ አለ ብል የሚከራከር ወገን መብቱ ወይም ግዳታው ስለመኖሩ የማስረዲት
ሸክም (one who alleges in the affirmative shall prove it) እንዲለበት የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 258
እና 259 እና የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2001 ድንጋጌዎች ይዘት ያሳገነዝባል።አከራካሪዉን ፍሬ ነገር
ለማስረዲት ላቀርብ የሚገባዉ ማስረጃ ዓይነት በሚመለከት ሰነድ/ጽኁፍ/፣ምስክር፣የህሉና
ግምት፣በተከራካሪ ወገን እምነት ወይም በመሓላ ቃል ማስረዲት እንደሚቻል የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ
2002 በግልጽ ይደነግጋል።በፍትሓብሕር ክርክር ቅቡልነት ያለዉ የማስረጃ ምዘና መርህ
standard of proof የክርክርሩን ፍሬ ነገር ማን በተሻለ ሁኔታ/ደረጃ/ በማስረጃ
አሰረድቷልpreponderance of evidence የሚል መሆኑም ልብ ይለዋል።የክርክሩን ጭብጥ
በመለየት እና ማስረጃ የማቅረብና የማስረዲት ግዳታን፤የቀረበዉን ማስረጃ አግባብነትና ተቀባይነት
መለየት እና የማስረጃዉ ብቃት/ምዘና/ መርህን አስመልክቶ ቅቡልነት ያላቸዉን መርሆዎች
ተከትል የክርክሩን ፍሬ ነገር ማጣራት እና ማስረጃ በመመዘን ሚዛናዊና ፍትሃዊ ድምዲሜ ላይ
ለመድረስ በሚያስችል ሁኔታ ክርክሩን በአግባቡ መምራት የፍርድ ቤቱ ሃላፉነትና ተግባር
ስለመሆኑ ስለፍትሓብሕር ክርክር አመራር ስርዓት የሚደነግገዉ የስነ ስርዓት ህግ የሚያስገነዝበን
ጉዲይ ነዉ።
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ ተጠሪ የያዘዉን መሬት ለአመልካች እንዱለቅ በሚል ዲኝነት በመጠየቁ ተጠሪ መብት ሳይኖረዉ የያዘዉ ስለመሆኑ የማስረዲት ሸክም አመልካቹ ነዉ።ፍርድ ቤቱም በአከራካሪዉ መሬት ላይ የይዞታ መብት ያለዉ ማነዉ የሚል ጭብጥ በመያዝ የግራቀኙን ማስረጃ ከመስማት ባሻገር በአካልም ጭምር በቦታዉ ተግኝቶ ምልክታ ያደረገ ስለመሆኑ ዉሳኔዉ ያሣያል።መሬቱ የአመልካች ስለመሆኑ ያስረዲልኛል በማለት ያቀረበዉ ሁነኛ ማስረጃ አዋጅ ቁጥር 31/67 ከመዉጣቱ በፉት የተሰጠዉ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ነዉ።አመልካች ያቀረበዉ የይዞታ ማረጋገጫ ተቀባይነት የለዉም የተባለዉ የገጠር መሬት የግል ሀብት መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 31/67 የተሻረ መሆኑ ተጠቅሶ ነዉ።የዉሳኔዉ ምክንያት ተገቢ መሆን አለመሆኑ የሚወሰነዉ በዚህ ዙሪያ ያለዉን ህግ በማጤን ነዉ።የሀገራችን የመሬት ስሪት ስርዓት ከስርዓተ መንግስት ጋር እየተለዋወጠ የመጣ መሆኑን ማየት ይቻላል።በዘዉዲዊዉ ስርዓት መሬት በአብዛኛዉ በከበርቴዎች እና መንግስት ይዞታ ስር የነበረ ሲሆን ከሞላ ጎደል የግል ሀብት ሆኖ ቆይቷል።ይህንን ስርዓት የተካዉ ዋጅ ቁጥር 31/67 እና አዋጅ ቁጥር 47/67 በማወጅ የገጠር እና የከተማ መሬት የህዝብ እና የመንግስት ሀብት እንዱሆን አድርጓል።ከእነዚህ አዋጆች በኋላ በወጣዉ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት እንደተደነገገዉ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት የመንግስት እና የህዝብ ሀብት ተደርጓል።(የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40/3/ ይመለከቷል)።ይህም የመሬት ስሪት ለዉጥ መደረጉንና መሬት የግል ሀብት መሆኑ ሙለ በሙለ ቀሪ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ።ይህንኑ ተከትል ግለሰቦች የገጠር መሬትም ሆነ የከተማ መሬት የመጠቀም የይዞታ መብት እንጂ የባለቤትነት መብት እንደላላቸዉ ከህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።የገጠር መሬት የመጠቀም የይዞታ መብት የሚገኘዉም በመንግስት በሚደረግ ድልድል፣በዉርስ ወይም በስጦታ ወይም የግል ባለሀብት ከሆነ ደግሞ በኢንቨስትመንት ዉል እንደሚሆን ህገ መንግስቱን ተከትል የወጣዉ የፋዳራል የገጠር መሬት አስተዲደር አዋጅ ቁ/456/97 አንቀጽ 5/3/ ይዘት ያስገነዝባል።በዚህ ዙሪያ ሶማላ ክልል ከዚህ የተለየ የገጠር መሬት አስተዲደር አዋጅ ስለመኖሩ በስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ አልተገለጸም።ስለሆነም በገጠር መሬት የመጠቀም የይዞታ መብት አለኝ የሚል ሰዉ ከእነዚህ በአንደኛዉ አግባብ ይዞታዉን ያገኘ ስለመሆኑ ማስረዲት ይጠበቅበታል።
በዚህ ጉዲይ ለክርክር ምክንያት የሆነዉ መሬት ተጠሪ በዉርስ ያገኘዉ መሆኑን እና ጉዲዩ አስቀድሞ በግራ ቀኙ መካከል በተደረገ ስምምነት በሽማግላዎች እና ጎሳ መሪ ታይቶ የተጠሪ ህጋዊ ይዞታ ነዉ ተብል ጉዲዩ በሚመለከተዉ አስተዲደር አካልም ተቀባይነት ያገኘ ስለመሆኑ ከስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ይዘት መገንዘብ ተችሎል።በአዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀጽ 12 እንደተደነገገዉ የገጠር መሬት በተመለከተ የሚነሳ አለመግባባት አስቀድሞ ግራ ቀኙ በሚያደርጉት ዉይይትና ስምምነት ወይም በመረጡት ሽማግላዎች እንዱታይ በማድረግ ወይም በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር ህግ በሚወሰነዉ መሰረት ላታይ የሚቻል ሲሆን ከዚህ ላላ አቤቱታዉን ለሚመለከተዉ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይቻላል።አለመግባባቱ አስቀድሞ በሽምግልና እንዱታይ መስማማት የሚቻል ቢሆንም የሽማግላዎቹ ዉሳኔ የመጨረሻ እና አስገዲጅ እንደማይሆን የድንጋጌዉ ይዘት ያስገነዝባል።ስለዚህም ዉሳኔዉ የመጨረሻ እንደሆነ አድርጎ ተጠሪ ያቀረበዉን መቃወሚያ የስር ፍርድ ቤቶች ዉድቅ ማድረጋቸዉ ስህተት የለዉም።ነገር ግን ጉዲዩ ለፍርድ ቤት ሲቀርብ ፍርድ ቤቱ በሽማግላዎቹ ዉሳኔ እና ማስረጃ ይዘት ሳይወሰን ላልች አግባብነት ያላቸዉን ማስረጃዎችን በመስማትና በመመርመር የበኩለን ዉሳኔ መስጠት ይችላል። በዚህም ጉዲይ የተደረገዉም ይኸዉ ነዉ።የስር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ማስረጃ የመረመረ ስለመሆኑ የዉሳኔዉ ይዘት የሚያሳይ ሲሆን አመልካች ያቀረበዉ የገጠር መሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ የተሰጠዉ አዋጅ ቁ/31/67 ከመዉጣቱ በፉት በመሆኑና የዚህ ሰነድ የማስረጃ ጠቀሜታ ወይም ብቃት ከአዋጅ ቁጥር 31/67 አንጻር በማየት ከላልች ማስረጃዎች ጋር በማገናዘብ እና በማመዛን የደረሰበት ድምዲሜ ላይ ማስረጃ ምዘና ስህተት ተፈጽሟል የሚያሰኝ ምክንያት አልተገኘም።
ባጠቃላይ ክስ የቀረበበት መሬት ላይ የባለይዞታነት መብት ያለዉ ተጠሪ ወይስ አመልካች ነዉ?
የሚለዉን ጭብጥ በመወሰን ረገድ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን የሰነድና የምስክሮችን ቃል በመመርመርና በማመዛዘን ተጠሪ በተሻለ ማስረጃ ማስረዲቱን አረጋግጦ ዉሳኔ የሰጠ መሆኑን መገንዘብ ተችሎል።ስለሆነም ዉሳኔዉ የክርክሩን ጭብጥ በመለየት እና ማስረጃ የማቅረብና የማስረዲት ግዳታን፤የቀረበዉን ማስረጃ አግባብነትና ተቀባይነት በመለየት እና የማስረጃዉን ብቃት/ምዘና/ መርህን አስመልክቶ ቅቡልነት ያላቸዉን መርሆዎች ተከትል የተወሰነ ነዉ ከሚባል በስተቀር በኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/4/ ና 10 ድንጋጌዎች መሰረት ለሰበር ችልቱ ከተሰጠዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም ስልጣን አንጻር በዉሳኔዉ ሉታረም የሚገባ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚባልበት ምክንያት አላገኘንም።በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/በዚህ ጉዲይ የሶማላ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ የህግ ስህተት የለዉም በማለት በመ/ቁ/05-1-68/13 ላይ በ22/03/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/መሰረት ጸንቷል።
2ኛ/በዚህ መዝገብ ላይ በ04/06/2013 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረዉ የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።ይጻፍ።
3ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል፡
No topics extracted.