No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- አቶ አብርሃም ጌታሁን፡- ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኃይለሥላሴ አስረስ፡- ከጠበቃ መለሰ ግርማይ ጋር ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የተያዘው ክርክር ከንግድ ምልክት ጋር የተገናኘ ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም አመልካች በቀን 08/10/2013 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 12/02/2012 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 26/09/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር የአሁን ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ።
ተጠሪ ባቀረቡት ክስ Sunland International Hotel የሚለውን ቃልና ምስል በንግድ ምልክትነት ያስመዘገብኩ ሲሆን ከ25/01/2009 ዓ.ም እስከ 25/01/2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የአዔምሯዊ ንብረት ጥበቃ ተሰጥቶኛል። ይሁን እንጂ ተከሳሽ ያለእኔ ፈቃድ እና እውቅና ያስመዘገብኩትን የንግድ ምልክት እየተጠቀሙበት የሚገኙ በመሆኑ ተከሳሽ ይህን ድርጊታቸውን እንዱያቆሙ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተከሳሽ በሰጡት መልስ የምጠቀመው የንግድ ስም Sunland international Hotel የሚል ሳይሆን Sunland Hotel የሚል ነው፤ International የሚለው ቃል በተከሳሽ የንግድ ስም ውስጥ የለም፤ በጋዜጣ ላይ የወጣው የከሳሽ ንግድ ምልክት በኢታሉክስ አጻጻፍ Sunland የሚል ነው፤ ነገር ግን የተከሳሽ የንግድ ስም በካፑታል ላተር SUNLAND HOTEL የሚል በመሆኑ ከከሳሽ የንግድ ምልክት ጋር ተቀራራቢ እንጂ ተመሳሳይ ነው ልባል አይችልም፤ በጋዜጣ የወጣው የከሳሽ ንግድ ምልክት ምስል እና ከሳሽ ከክሱ ጋር አያይዞ በማስረጃነት ያቀረበው ምስል ተመሳሳይነት የላላቸው ናቸው፤ ከሳሽ የንግድ ምልክቱን በስማቸው ያስመዘገቡ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት አላቀረቡም፤ ይህን ባላቀረቡበት የንግድ ምልክቱ በ3ኛ ወገኖች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም። ተከሳሽ sunland hotel የሚለውን የንግድ ስም ስልጣን ባለው በንግድ እና ኢንደስትሪ ጽ/ቤት አስመዝግቤያለሁ። አዔምሯዊ ንብረት የንግድ ምልክትን ምዝገባ የሚያካሂድ ሲሆን ንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ደግሞ የንግድ ስም ለመመዝገብ ስልጣን የተሰጠው ነው። በዚህ ምክንያት አንደ በአንደ ላይ የበላይ ላሆን የሚችልበት አግባብ የለም። አለ ቢባል እንኳ መብቱን ቀድሞ ያገኘው ማን ነው የሚለው ነጥብ መታየት አለበት። ተከሳሽ የንግድ ስም የምስክር ወረቀት ያገኘው በ10/05/2009 ዓ.ም ሲሆን ከሳሽ በዚህ ጊዜ የንግድ ምልክቱን በጋዜጣ ማስታወቂያ አሳውጆ ተቃዋሚ የሚቀርብ ከሆነ ሲጠባበቅ ነበር፤
የምስክር ወረቀት ሉያገኝ የሚችለውም ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው። ከሳሽ የንግድ ምልክት አስመዝግቤያለሁ በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም በንግድ ስሙ የከፈተው ሆቴል ወይም የሚያንቀሳቀሰው ንግድ የለም።
በአንጻሩ ተከሳሽ ባስመዘገብኩት የንግድ ስም በስራ ላይ የምገኝ ሲሆን ተከሳሽ በንግድ ስሙ እንዲልጠቀም የምከለከል ከሆነ ያገኘሁትን መልካም ስም አጣለሁ፤ በመሆኑም ክሱ ውደቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት ክርክሩንና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተከሳሽ የሚጠቀመው የንግድ ምልክት ከከሳሽ የንግድ ምልክት ጋር ተመሳሳይ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል፤
ተከሳሽ የሚጠቀመው የንግድ ምልክት/ስም አማካይ የሆነ ተጠቃሚን ሉያሳስት የሚችል ሲሆን ከሳሽ እና ተከሳሽ ከሚሰጡት አገልግልት አንጻር ተከሳሽ የሚጠቀመው የንግድ ምልክት ህብረተሰቡን የሚያሳክር ነው፤ ከሳሽ የንግድ ምልክታቸውን ያስመዘገቡት ለሆቴል አገልግልት በመሆኑ ከዚህ አገልግልት ጋር በተያያዘም የንግድ ምልክቱን ቃልም ሆነ ምስል መጠቀም የብቸኝነት መብት ያላቸው በመሆኑና ተከሳሽ በከሳሽ የንግድ ምልክት ላይ ጥሰት የፈፀሙ መሆኑ ስለተረጋገጠ ተከሳሽ ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ የከሳሽን የንግድ ምልክት እንዲይጠቀሙ፤ የሰቀለትንም የንግድ ምልክት ከሆቴላቸው ላይ እንዱያነሱ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ተከሳሽ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ ክርክሩን መርምሮ በህግ ስልጣን ከተሰጠው ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዲቤ ከሳሽ ከ25/01/2009 ዓ.ም እስከ 25/01/2016 ዓ.ም ድረስ ለንግድ ምልክቱ ጥበቃ የተሰጣቸው መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል በማለት ቅሬታውን ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ አፅንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች በቀን 08/10/2013 ዓ/ም ባቀረቡት ማመልከቻ ተፈፀመ የሚለትን የህግ ስህተት በመዘርዘር የስር ፍ/ቤቶች አመልካች በህጋዊ መንገድ ያገኘሁትን የንግድ ስም እንዲልጠቀም የሰጡት ውሳኔ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብል እንዱታረም በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች የተጠሪን ንግድ ምልክት ከሆቴለ ላይ እንዱያነሱ የወሰኑበትን አግባብነት እንዱሁም የንግድ ምልክቱን ማን ቅድሚያ እንዲስመዘገበው የተጣራበትን አግባብ ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪ ባቀረቡት መልስ ክርክራቸውን አጠናክረው የስር ፍርድ ቤቶች ተከሳሽ የንግድ ስሙን በማስመዝገብ ከቅን ልቦና ውጭ ሉጠቀሙት አይችለም፤ ለክሱ ምክንያት በሆነው የንግድ ስምና ምልክት ከሳሽ የቀደምትነት መብት አላቸው በማለት የሰጡት ውሳኔ ተገቢነት ያለው በመሆኑ እንዱጸና ብለዋል። አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ነው። በበኩላችን የግራ ቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የተፈፀመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
አንደመረመርነው የአመልካች መሰረታዊ መከራከሪያ ተጠሪ ለንግድ ምልክቱ የህግ ጥበቃ አግኝቼበታለሁ ባለት የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/98 መሰረት አመልካችን ለመቃወም የሚያስችል መብት የላቸውም፤ እንዱሁም ቀደምትነት ያለው የአመልካች የንግድ ስም ሆኖ እያለ በኋላ የተመዘገበው የተጠሪ የንግድ ምልክት በምዝገባ ቅደም ተከተል ሳይሆን የአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በጻፈው ደብዲቤ ቀደምትነት አለው መባለ ስህተት ነው በሚል ነው።
በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀጽ 2(12) የተሰጠው ትርጉም እንደሚያመለክተው “የንግድ ምልክት” ማለት የአንድን ሰው ዔቃዎች ወይም አገልግልቶች ከላልች ሰዎች ዔቃዎች ወይም አገልግልቶች ለመለየት የሚያስችል የሚታይ ምስል ነው። ምልክቱ ቃላቶችን፣ ዱዛይኖችን፣ ፉደልችን፣ ቁጥሮችን፣ ቀለሞችን ወይም የዔቃዎችን ወይም የመያዣዎቻቸውን ቅርጽ ወይም የእነዚህኑ ቅንጅት ሉይዝ ይችላል።
ከዚህም ላላ ምልክቱ በአዋጁ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች የማያሟላ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም። በአዋጁ የተጠቀሱት ሁኔታዎች ደግሞ በክፍል ሁለት ከአንቀጽ 5 እስከ 7 ድረስ ተዘርዝረዋል። ከድንጋጌዎቹ መረዲት እንደሚቻለው ማንኛውም የንግድ ምልክት የአንድን ሰው ዔቃዎች ከላልች ዔቃዎች በግልፅ ለመለየት የሚያስችል ከሆነ (capable of clearly distinguishing) ሉመዘገብ እንደሚችል፤ ነገር ግን ከአንድ አይነት ዔቃዎች ጋር የተያያዘ የላላ ሰው ቀዲሚ የንግድ ምልክት ጋር አንድ አይነት የሆነ ወይም መሳከርን ሉያስከትል የሚችል ተመሳሳይነት ያለው ከሆነ (where it is identical ………. Or if it so nearly resembles such a trademark as to be likely to deceive or cause confusion) ሉመዘገብ እንደማይገባ ተመልክቷል። (የአዋጁን አንቀጽ 5(1) እና 7(1) ይመለከቷል)።፡ በልላ በኩል እነዚህን መመዘኛዎች አልፍ በባለስልጣኑ ምዝገባ የተደረገለት የንግድ ምልክት ጥበቃ ያገኛል።
ከፍ ሲል ከተጠቀሱት የአዋጁ ድንጋጌዎች እና ከአዋጁ ጠቅላላ ይዘት እንዱሁም በዘርፈ ከዲበረው ዔውቀት መገንዘብ እንደሚቻለውም የአንድን በማመልከቻ በምዝገባ የገባ የንግድ ምልክት መሰረተዊ ባህሪ (essential feature) በመውሰድ ወይም የንግድ ምልክቱን እንዲለ ወስድ በምልክቱ ላይ የተወሰነ ጭማሪ ወይም ለውጥ በማድረግ የቀረበ የንግድ ምልክት መሳከርን ሉያስከትል የሚችል ተመሳሳይነት ያለው ነው ልባል ይችላል።
በተያዘው ጉዲይ የስር ፍ/ቤት አመልካች የሚጠቀሙበት የንግድ ምልክት ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 501/98 ያገኙትን መብት እና ጥበቃ የሚጥስ መሆን አለመሆኑን በጭብጥነት ይዞ ከቀረበው ማስረጃ አንፃር በመመርመር የተጠሪ የንግድ ስምና ምልክት የሆነው Sunland International Hotel በተጠሪ ጠያቂነት የአዋጁን መስፈርት አሟልቶ ከ 25/01/2009 ዓ.ም እስከ 25/01/2016 ድረስ ለንግድ ምልክቱ ጥበቃ የተሰጣቸው መሆኑንና የንግድ ምልክቱም ለሆቴል አገልግልት ምድብ 13 የተመዘገበ መሆኑን፤ እንዱሁም አመልካች በተጠሪ የንግድ ምልክት ላይ ጥሰት የፈፀሙ መሆኑን በፍሬ ነገር ደረጃ በማረጋገጥ ወስኗል።
ይህ የፍሬ ነገር መደምደሚያ ተጠሪ በህጉ ስልጣን በተሰጠው አካል ዘንድ በመዝገብ ያስገቡት የንግድ ምልክት መሰረተዊ ባህሪ (essential feature) አመልካች በንግድ ሚ/ር በንግድ ምዝገባ አስመዝግቤዋለሁ በሚለት የንግድ ምልክት የተወሰነ ለውጥ ተደርጎ መወሰደን የሚያሳይ ነው።
በአጠቃላይ የአመልካች የሚጠቀሙበት Sunland Hotel የሚለው ምልክት በተጠሪ በተገቢው ጽ/ቤት የተመዘገበውንና ጥበቃ ያገኘውን Sunland International Hotel የሚል የንግድ ምልክት መሰረታዊ ባህሪ በመያዝ የተወሰነ ለውጥ የሚያደርግ በመሆኑና የሁለቱ ንግድ ምልክቶች ተመሳሳይነት መሳከርን የሚፈጥር መሆኑ ፍሬ ነገርን ለማጣራትና ማስረጃን ለመመዘን ስልጣን ባለው የስር ፍርድ ቤት ተረጋግጦ አመልካች የተጠሪን የንግድ ምልክት እንዲይጠቀሙ፤ የሰቀለትንም የንግድ ምልክት ከሆቴላቸው ላይ እንዱያነሱ ተብል በመወሰኑ የተፈፀመ የህግ ስህተት የለም ብለናል።
ተከታዩንም ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 12/02/2012 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 26/09/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የተሰጠው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
ለሰበር ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.