No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ሰናይት አድነው ደጀኔ አያንሳ አመልካች፡- አቶ ነስሬ መሐመድ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዘምዘም መሐመድ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የመጥፊት ውሳኔን እና የጋብቻ ንብረት ክርክርን የተመለከተ ነው። ክርክሩ የጀመረው በስር የቡታጀራ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪ ተከሳሽ፣ በዚህ መዝገብ የላለት አማል ሁሴንና ወ/ሮ ፊጡማ ሀሰን ደግሞ ጣ/ገቦች ነበሩ።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው የአሁን አመልካች ባቀረቡት ክስ ተጠሪ በመ/ ባቀረበችው የመጥፊትና የፍቺ ውሳኔ ይሰጥልኝ አቤቱታ መነሻነት ፍርድ ቤቱ ከሳሽን ጠፍቷል ሲል ወስኖ አያይዞ በከሳሽና ተከሳሽ መሀከል የነበረው ጋብቻ ፈርሷል ሲል መወሰኑን ከምኖርበት ሳውዱ አረቢያ በተመለስኩበት ጊዜ ማወቅ ችያለሁ። ይሁን እንጂ ተከሳሽ ፍ/ቤቱን በማሳሳት የጋራ የሆኑ ንብረቶቻችን በግሎ አዙራ አላግባብ ለመበልጸግ በማሰብ ከሳሽ ሳላውቅ ጥልኝ ጠፍቷል በማለቷ የተገለጸውን ፍርድ እንዱሰጥ ብታስደርግም ከሳሽና ተከሳሽ በ1992 ዓ.ም ተጋብተን 2 ልጆች ከወለድን በኋላ ኑሯችንን ለማሻሻል በጋራ ተመካክረን በ1997 ዓ.ም ወደ አረብ ሀገር ለስራ ተሰድጄ ስሄድ ተከሳሽ ሸኝታኝ ከሄድኩ በኋላም በስልክ ስንደዋዋል ከመቆየታችንም በላይ በተለያዩ ግዜያት ለእሷና ለልጆቻችን ገንዘብ ስልክላት ቆይቻለሁ። ከዚህም ባሻገር ወደ አረብ ሀገር እንድትመጣ መንገድ አመቻችቼላት በነበራት አጋጣሚ የጋራ ቤታችንን የምትሰራበትን ገንዘብ ጨምሬ በመስጠት ወደ አገር ቤት አስቀድማ ተመልሳ ከእሷ ጋር ከመጋባታችን በፉት ከሳሽ በ1982 ዓ.ም አቶ መሀመድ ሁሴንና ፊጡማ ኢብሮ ከተባለ ግለሰቦች ገዝቼው የነበረውንና ተሰርቶ ይገኝ የነበረውን በቡታጀራ ከተማ የሚገኝ መጠኑ 487.34 ካ/ሜ ቦታ ላይ የነበረውን 30 የቆርቆሮ ክዲን ቤት በማፍረስ በምትኩ ግምቱ ከብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሉየን) በላይ የሆነ አንድ ባለ 90 ቆርቆሮ ክዲን ትልቅ መኖሪያ ቤት በጋራ ገንዘባችን ተሰርቶ ይገኛል። እንዱሁም በዚሁ ክ/ከተማ በተከሳሽ ስም ከቀበላ ተከራይተን በጋራ ስንጠቀምበት የነበረ አንድ ክፍል ንግድ ቤት እና ከዚሁ ይዞታ ተያይዞ የሚገኝ በግምት 150 ካ/ሜ የሚሆን አስቀድሞ በሰነድ አልባ ይዞታነት ይዘነው የምንጠቀምበትን ተከሳሽ በስውር ወደ ራሷ ስም በማዞር ወደ ላላ 3ኛ ወገን ለማዛወር ስትል ከሳሽ ደርሼ ያሳገድኩት ይዞታና በላዩ ላይ የሚገኙ 4 ክፍል ሰርቪስ ቤቶች የከሳሽና ተከሳሽ የባልና ሚስት ሀብት ነው። በመሆኑም በመ/ የተሰጠው የመጥፊትና የፍቺ ውሳኔ ተሰርዞ የጋራ ሀብቶቻችን ወደነበሩበት እንዱመለሱ፤ ተከሳሽ በፍቺው የምትጸና ከሆነ የፍቺ ውጤት የሆኑትና ከሳሽ በጋራ ያፈራናቸውን ቤትና ቦታዎች እንዱሁም የቤት ቁሳቁሶች በንብረት አጣሪ ተለይተው እኩል እንድንካፈል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። ተከሳሽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር መልስ ያቀረቡ ሲሆን ጣልቃ ገቦችም የበኩላቸውን ክርክር አቅርበዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በመ/ በቀን 23/01/2004 ዓ.ም የተሰጠው የፍቺ ውሳኔ ሉሰረዝ አይገባም። ንብረትን በተመለከተ በይዞታው ላይ የነበረው 30 የቆርቆሮ ክዲን ቤት ፈርሶ ከውሳኔው በኋላ ተከሳሽ አሁን ያለውን ትልቁን ቤት የሰራች በመሆኑ በዚህ ቤት ላይ ከሳሽ መብት ባይኖረውም ተያይዞ ያለው ባድ ይዞታ መሬት ተለክቶ 50% ለከሳሽ የቀረውን 50% ደግሞ ትልቁ ቤት ያረፈበትን አካቶ ተከሳሽ ላሆን ይገባል በማለት ወስኗል። በ150 ካ/ሜ ላይ የተሰሩት ቤቶችና ይዞታ መሬት በተመለከተ የከሳሽና ተከሳሽ በጋብቻ ጊዜ ያፈሩት መሆኑ ስለተረጋገጠ የጋራ ሀብት ነው እኩል ሉካፈለት ይገባል። በዚህ 150 ካ/ሜ ላይ የተሰሩት ቤቶችን በተመለከተ እነ አማል ሁሴን ከተከሳሽ ወኪል ወ/ሮ ሸምሲ መሀመድ ጋር ያደረጉት የሽያጭ ውል ስምምነት በፍ/ህ/ቁ 1723 እና 1815 መሰረት መፍረሱን በማረጋገጥ ወደ ነበሩበት ይመለሱ። ከሳሽ በተከሳሽ ላይ ተንቀሳቃሽ ንብረት በተመለከተ ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለቡታጅራ አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱሁም የሰበር አቤቱታ ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው።
አመልካች ባቀረቡት ማመልከቻ በመ/ የተላለፈው የመጥፊትና የፍቺ ውሳኔ ተሰርዞ የአመልካችና ተጠሪ ጋብቻ ወደነበረበት እንዱመለስ እና በፍቺ ውጤቶች ላይ እንድንከራከር ተብል እንዱወሰንልኝ፤ በቡታጀራ ከተማ ቀበላ 04 የሚገኘው 487.34 ካ/ሜ ይዞታና ባለ 90 ቅጠል ቆርቆሮ ቤትም የግል ሀብት ነው ተብል እንዱወሰንልኝ በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
No topics extracted.
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ የፍ/ብ/ህ/ቁ 170 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎች በተገቢው ያገናዘበ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለዚህ ችልት እንዱቀርብና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪ ባቀረቡት መልስ አመልካችና ተጠሪ በ1992 ዓ.ም ጋብቻ የመሰረትን ሲሆን ልጆች እንደወለድን ተጠሪ አመልካችን በምንኖርበት የቀበላ ኪራይ ቤት ውስጥ ጥልኝ በ1997 ዓ.ም በመጥፊቱ ለረጅም አመታት ሳስፈልገው ብቆይም ያለበትን ላውቅ ባለመቻላ ልጆቼን ብቻዬን ሳሳድግ ቆይቼ በ2003 ዓ.ም ለቡታጀራ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት የመጥፊት ውሳኔ እንዱሁም ጋብቻ ይፍረስልኝ አቤቱታ አቅርቤ ለ7 አመታት መጥፊቱ በመረጋገጡ የመጥፊት ውሳኔ ተሰጥቶ ጋብቻችን ፈርሷል። የመጥፊት ውሳኔ ከተሰጠ 6 አመት በኋላ ተመልሶ ከጠፊበት በመምጣት የጋራ ንብረት ታካፍለኝ ክስ ያቀረበ ሲሆን የጋራ ንብረቴ ነው ብል ያቀረበው በቡታጀራ ከተማ 04 ቀበላ ውስጥ የሚገኘውና በ487 ካ/ሜ ቦታ ላይ የተሰራው ቤት የመጥፊት የፍቺ ውሳኔ ከተሰጠ ከ2 አመት በኋላ በተጠሪ የግል ጥረት የተፈራ ስለመሆኑ የራሱ የአመልካች ምስክሮች ጭምር አረጋግጠው መስክረውበታል። ይህም ሆኖ አመልካች ቦታውን ከመጥፊቱ በፉት የገዛሁት ነው የሚል የሀሰት የሽያጭ ውል አቅርቦ የነበረ በመሆኑ ቤቱ የተጠሪ ነው ተብል ተወስኖ ትርፈን ይዞታ እኩል ይካፈለ ሲል ፍ/ቤቱ ወስኗል። አመልካች ለረጅም አመታት ልጆቹንና ትዲሩን ጥል ጠፍቶ የራሱን ህይወት ሲመራ የኖረ ለመሆኑ ባልካደበትና ጋብቻ በተጋቢዎች ነጻ ፈቃድ ላይ የሚመሰረትና አንደ የትዲር አጋር ባልፈለገ ግዜ የሚፈርስ በመሆኑ የፍቺ ውሳኔ ተነስቶ ወደ ነበርንበት ጋብቻ እንመለስ ብል መጠየቅ የህግም ሆነ የሞራል መሰረት የለውም።
የመጥፊት ውሳኔ መነሳትም ሆነ አለመነሳት በጋብቻችን መፍረስ ላይ የሚያመጣው የተለየ ህጋዊ ውጤት ስለላለ ያቀረበው ጥያቄ የህግ መሰረት የለውም፤ የስር ፍ/ቤቶችም የፈጸሙት ምንም አይነት የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም ክርክራቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ነው። በበኩላችን የግራ ቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በውሳኔው የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
እንደመረመርነው የአሁን አመልካች ቀዲሚ ቅሬታ የመጥፊትና የፍቺ ውሳኔ ተሰርዞ የአመልካችና ተጠሪ ጋብቻ ወደ ነበረበት እንዱመለስ የሚጠይቅ ነው። በፍ/ብ/ህ/ቁ 163(1) ስር እንደተመለከተው የጠፊ ሰው ጋብቻ የመጥፊቱ ማስታወቅ ፍርድ የመጨረሻ በሆነበት ቀን የሚፈርስ ሲሆን በአንፃሩ ጠፍቷል የማለት ማስታወቅ ውጤት መስጠቱ የሚቀረው ጠፊ የተባለው ሰው የመጣ እንደሆነ ስለመሆኑ በዚሁ ህግ አንቀጽ 170(1)(ሀ) ስር ተደንግጓል። ይህም ቢሆን ግን ጋብቻን በተመለከተ ወደ ነበረበት እንዱመለስ የማድረግ ውጤት ይኖረዋል ተብል የሚወሰድ አይደለም።
ስለሆነም የፍቺ ውሳኔው ተነስቶ ከተጠሪ ፈቃድ ውጪ ወደ ነበሩበት ጋብቻ እንዱመለሱ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ንብረቱን በተመለከተም ጠፊ የተባለው ሰው በተመለሰ ጊዜ ንብረቶቹን በሚገኙበት አኳኋን፤
እንዱሁም የተሸጡትን ንብረቶች ዋጋና እነዚህንም ዋና ገንዘቦች በሥራ ላይ በማዋል የተገኙትን ንብረቶች ሁለ መልሶ እንደሚወስድ፤ ይሁንና ንብረቶች የሚያስገኙትን ገቢ በተመለከተ ንብረቶቹ በይዞታ ተሰጥቷቸው እነዚህን ገቢዎች ላገኙ ሰዎች ገቢ እንደሆኑ እንደሚቀሩ በፍ/ብ/ህ/ቁ 171(1) እና (2) ስር ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዲይ የስር ፍርድ ቤት የፍሬ ነገር ክርክርና ማስረጃውን መርምሮ መጠኑ 487.34 ካ/ሜ የሆነው ይዞታ ላይ የነበረው 30 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት አለመኖሩንና አሁን ሰፍሮ የሚገኘው 90 ቅጠል ቆርቆሮ የለበሰ መኖሪያ ቤት መሆኑን፤ ይህም ቤት በተጠሪ ጥረት ብቻ የተፈራ መሆኑን በማረጋገጥ ይዞታውን አመልካችና ተጠሪ እኩል ይካፈለ፤ ቤቱ የተጠሪዋ ስለሆነ በእኩላታው ውስጥ መኖሪያ ቤቱ ያለበትን ይዞታ ተጠሪ እንድትወስድ ቀሪውን የእኩላታ ድርሻ ደግሞ አመልካች እንዱወስደ፤ እንዱሁም መጠኑ 150 ካ/ሜ የሆነውን ይዞታና ቤት ግን በጋራ የተፈራ መሆኑ ስለተረጋገጠ እኩል እንዱካፈለ በማለት ወስኗል። የንብረት ክርክሩ በዚህ መልኩ መወሰኑ ደግሞ ከፍሲል የተጠቀሱትን የህጉን ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የተከተለ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም። በአጠቃላይ ውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚሰኝ ሆኖ ስላላገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
የቡታጀራ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 11/04/2011 ዓ.ም፣ የቡታጀራ አካባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 28/05/2013 ዓ.ም እንዱሁም የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 24/10/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።