No summary available.
ቀን 25/08/2008 ዓ/ም ዳኞች፡-
ጉዲዩ የቀረበው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰበር ችልት አመልካች ከተጠሪ በኪራይ ውል የያዘውን መኖሪያ ቤት እንድለቅ የሰጡት ውሳኔ አግባብነት ያላቸውን የህግ ማዔቀፍች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የተያዘው በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በስር ፍርድ ቤት፣ አመልካች በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዲ 5 የቤት ቁጥር የሆነውን የመንግስት ቤት ከተከሳሽ ጋር የካቲት 15 ቀን 2004 ዓ/ም በፈጸምኩት የኪራይ ውል ተከራይቼ በመኖር ላይ እገኛለሁ፣ ከሳሽ የተከራይነት ግዳታዬን እየተወጣሁ እያለሁ የኪራይ ውለን ለማቋረጥ የሚስችል ህጋዊ ምክንያት በላለበት ሁኔታ ህዲር 15 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ ደብዲቤ የተከራየሁትን ቤት በአምስት ቀን ውስጥ ለቅቄ እንድወጣ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶኛል።በመሆኑም በተከራያሁት ቤት የመኖር መብቴ እንዱከበርልኝና ተከሳሽ እየፈጠረ ያለው ሁከት ይወገድልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርቦ የፍርድ ቤቱን የዲኝት ስልጣን አለመኖርና ከሳሽ ተከሳሽን ለመክሰስ የሚያስችለው ምክንያት የለም የሚል የክስ መቃወሚያ አቅርቧል። የስር ፍርድ ቤት የተጠሪን የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያ ውድቅ አድርጎታል። ተጠሪ አመልካች የእናቱ ወ/ሮ እታገኘ ለገሰ የኮንደሚኒየም ቤት፣ በውርስ አግኝቶ እየተጠቀመ ነው። በመሆኑም ከሳሽ በውርስ ያገኘው ኮንደሚኒየም ቤት ያለው በመሆኑ ከመንግስት የተከራየውን ቤት ማስረከብ አለበት። ለዚህ ምክንያት የኪራይ ውለን በማቋረጥ ቤቱን እንዱያስረክብ የወሰድኩት እርምጃ በአግባቡ ነው በማለት ተክራክሯል። የስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ከእናቱ ወረሰ የተባለው ኮንደሚኒየም ቤት ዘጠኝ የሟች ልጆች በጋራ የወረሱትና ከሳሽ ብቻውን ቤተሰቡን ይዞ ገብቶ ሉኖርበት የማይችል በመሆኑ፣ ተከሳሽ የከሳሽን የቤት ኪራይ ውል ያቋረጠው ከህግ አግባብ ውጭ ነው በማለት፣ ከሳሽ የተከራየውን ቤት ለተከሳሽ የማስረከብ ግዳታ የለበትም በማለት ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮ፣ አመልካች የተከራየውን ቤት ለተጠሪ ሉያስረክብ ይገባል በማለት ወስኗል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርቧል። የከተማው አስተዲደር ሰበር ችልት አመልካችን የሰበር አቤቱታ አልተቀበለውም።
አመልካች ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ሟች እናቴ የደረሳት ባለ አንድ መኝታ ቤት ኮንደሚኒየም ቤት ነው። ይህንን ቤት የሟች ዘጠኝ ወራሾች በውርስ አግኝተናል።
የኮንደሚኒየም ቤቱን አመልካች ብቻዬን በውርስ አላገኘሁትም። የላልች ሰዎች የጋራ ሀብት በሆነ ኮንደሚኒየም ቤት ገብቼ ለመኖር የሚያስችለኝ መብት የለኝም። ስለዚህ የተጠሪ እርምጃ የከተማው አስተዲደር ያወጣውን መመሪያ የሚጻረርና የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ በሰበር ታይቶ እዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ ሀምላ 27 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ መልስ ተጠሪ የተከራየውን ቤት እንዱለቅ የተጠየቀው የከተማ አስተዲደር ባወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2003 መሰረት ነው። ለዚህ ሰበር ችልት የተያዘው ጭብጥ የፍሬ ጉዲይ እንጂ የህግ ጭብጥ አይደለም የሚል ይዘት ያለው ክርክር አቅርቧል። አመልካች ነሐሴ 28 ቀን 2007 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ጉዲዩን መርምረናል፤ የአመልካች ወላጅ እናት ኮንደሚኒየም ቤት የደረሳቸው ቢሆንም፣ የአመልካች እናት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው በደረሳቸው ኮንደሚኒየም ቤት ላይ ያላቸው መብትና ጥቅም በፍታብሓር ህግ ቁጥር 826 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ለሟች ወራሾች የሚተላለፍ መሆኑ ግልጽ ነው። የአመልካች እናት ከአመልካች ላላ ስምንት ወራሾች ያላቸው መሆኑ በስር ፍርድ ቤትና ግራ ቀኙ ባቀረቡት ክርክር ተረጋግጧል። አመልካች ከተጠሪ ጋር ኪራይ ውል ተዋውል እየኖር ባለበት ሁኔታ እናትህ ኮንደሚኒየም ስለደረሳቸውና ኮንደሚኒየም ቤት በውርስ ስላገኘህ የተከራየከውን ቤት ልትለቅ ይገባል በማለት ተጠሪ ያቀረበው ጥያቄ አመልካች በውርስ ከላልች ወራሾች ጋር ባገኘው ኮንደሚኒየም ቤት ላይ ያለው መብት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1060 ንዐስ አንቀጽ 2 እና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1266 እና ተከታይ ደንጋጌዎች መሰረት የጋራ ባለሀብትነት መብት መሆኑን ያገናዘብ ሆኖ አላገኘነውም።
አመልካች የኮንደሚኒየም ቤቱ ብቸኛ ወራሽ ካልሆነ ከእናቱ ከላልች ጋር በወረሰው ኮንደሚኒየም ቤት ገብቶ ለመኖር የሚያስችለው መብት የለውም። ይህ ከሆነ ተጠሪ ከላይ የጠቀሰናቸውን የህግ ደንጋጌዎችና የመመሪያ ቁጥር 3/2003 አንቀጽ 14 እና አንቀጽ 15 ንዐስ አንቀጽ 3 በሚቃረን ሁኔታ የኪራይ ውለን በመሰረዝ አመልካች የተከራየውን ቤት እንድለቅ ያቀረበው ጥያቄ ህጋዊ ነው በማለት አዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት ተቀብለው አመልካች ቤቱን ለቅቆ እንዱወጣ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ሰህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና የከተማው አስተዲደር የሰበር ችልት በመዝገብ ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ መጋቢት 3 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ። መዝገቡ ወደ መዝግብ ቤት ይመለሰ።
No topics extracted.