366 በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁ (3) ስር የተመለከተው በቅጣት ውሳኔ ላይ በይግባኝ የመከራከር መብት ተከሳሹ ባይኖርም በህግ ረገድ ፍርድ ቤት በራሱ ተነሳሽነት በቅጣት ማቅለያነት መያዝ ሲገባው ያልያዘውን አልያም በቅጣት ማክበጃነት መያዝ ሳይኖርበት በተሳሳተ የህግ አተረጓጎም የተያዘ የቅጣት ማክበጃ ምክንያትን ብቻ የሚመለከት ስለመሆኑ
No summary available.
ሚያዝያ 28/2013 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ ገ/መድህን ብርሃነ ተጠሪ፡- የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በላለበት ታይቶ የተወሰነ የወንጀል ክስ እንዱነሳ ኤቤቱታ ቀርቦ ውድቅ በመደረጉ በቅጣት አወሳሰን ረገድ የቀረበ የሰበር ቅሬታን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በወ/መ/ቁ/178997 ላይ መስከረም 30/2012 ዓ.ም በዋለው ችልት የአመልካችን የይግባኝ ቅሬታ ውድቅ በማድረግ የሰጠውን የመጨረሻ ውሳኔን በመቃወም ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1(ሀ))፣ 27(2) እና 539(1(ሀ)) ድንጋጌን ጠቅሶ አመልካችን ጨምሮ በሶስት ተከሳሾች ላይ በትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው። በቀረበው ክስ ላይ የአሁን አመልካች ሁለተኛ ተከሳሽ ነበር። የክሱም ጭብጥ ተከሳሾች ሰውን ለመግደል አስቀድመው በማሰብ አባሪ ተባባሪ ሆነው አቶ ክብሮም ፃድቃን የተባለውን የግል ተበዲይ የስር 3ኛ ተከሳሽ የነበረው ተበዲዩን እየመራ ከተቀጣጠሩበት ስፍራ ሲደርሱ አመልካች እና የስር 1ኛ ተከሳሽ በሽጉጥ ተኩሰው ሲመቱት ተበዲዩ እንደሞተ ሰው መስል ያሳለፊቸው እና በደረሰበት ጉዲት ምክንያት ተበዲዩ ላይ 100% የአካል ጉዲት የደረሰበት ለመሆኑ በህክምና ምርመራ የተረጋገጠ በመሆኑ ከባድ የግድያ ሙከራ ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ነው።
አመልካች እና የስር 3ኛ ተከሳሽ በአድራሻቸው ተፈልገው ባለመገኘታቸው እና በኢትዮጵያ ሄራልድ ጋዜጣም በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ባለመቅረባቸው ክሱ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል። በዚሁ አግባብ የዐቃቤ ህግ ክስ እና ማስረጃ ከተሰማ በኋላ የስር 1ኛ ተከሳሽ ባቀረበው መከላከያ ማስረጃ የዐቃቤ ህግ ማስረጃን አላስተባበለም፤ አመልካች እና 3ኛ ተከሳሽ ቀርበው አልተከራከሩም በሚል በተከሰሱበት ወንጀል ጥፊተኛ ተብለዋል። ከቅጣት አንፃርም በተከሳሾቹ ላይ የወንጀል ሪኮርድ አለመቅረቡ እንዱሁም የስር 1ኛ ተከሳሽ የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆኑ በቅጣት ማቅለያነት ተይዞ እና የቅጣት ውሳኔው በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 01/2002 መሰረት ተሰልቶ 1ኛ ተከሳሹ በ15(አስራ አምስት) ዓመት ፅኑ እስራት፤ አመልካች እና ቀሪው ተከሳሽ እያንዲንዲቸው በ19(አስራ ዘጠኝ) ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጡ ተወስኗል።
ይህ ከሆነ በኋላ አመልካች እርሱ በላለበት የተወሰነው የወንጀል ጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ተነስቶ ክሱ በድጋሚ ላታይ ይገባል ያለበትን ምክንያት ጠቅሶ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 197 መሰረት ፍርደን ለሰጠው ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም በአቤቱታው ላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማ በኋላ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። አመልካችም በቅጣት ማቅለያነት ሉያዙልኝ ሲገባ አልተያዙልኝም ያላቸውን ነጥቦች ዘርዝሮ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁር 195(1) መሰረት ተሰርዞበታል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ታህሳስ 09/2012 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤት ተፈፅሟል ያላቸውን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሶ በዚህ ችልት እንዱታረምለት ጠይቋል። ፍሬ ቃለም ጥፊተኛ የተባልኩበት የወንጀል ድርጊት በሙከራ ደረጃ የቀረ በመሆኑ፣ ከባድ የጤና እክል ያለብኝ እና የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆኔ እንዱሁም ከተበዲይ ጋር መታረቄን ገልጬ እያለሁ በቅጣት ማቅለያነት ተይዘውልኝ ቅጣቱ ቀልል ሉወሰን ሲገባ መታለፈ አግባብ ባለመሆኑ ሁኔታዎቹ ከግንዛቤ ገብተው ቅጣቱ ተሻሽል ሉወሰን ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ጥፊተኛ ከተባለበት የወንጀል ህግ ድንጋጌ አንፃር የቅጣት ውሳኔው አግባብነት ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 01/2002 አንፃር በዚህ ችልት ቀርቦ እንዱመረመር በመታዘዙ ምክንያት ተጠሪ የፅሁፍ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል።
በዚሁ አግባብ ተጠሪ የካቲት 30/2012 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ድርጊቱ በሙከራ ደረጃ መቅረቱ እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ ቢያዝ የማይቃወም መሆኑን፤ ቀሪዎቹ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ግን በስር ፍርድ ቤት ያልቀረቡ እና ክርክር ያልተደረገባቸው በመሆናቸው በዚህ ችልት ሉቀርቡ አይችለም በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ በማቅረብ ሞግቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ይህ ችልትም ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ነጥብ አኳያ የግራ ቀኙን ክርክር ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንግዱህ ከክርክሩ አመጣጥ በግልፅ መረዲት እንደሚቻለው የአመልካች የሰበር አቤቱታ መነሻው በላለሁበት የተላለፈብኝ የወንጀል ጥፊተኝነት ውሳኔ እንዱነሳ ያቀረብኩት አቤቱታ ውድቅ ቢደረገም በቅጣት ማቅለያነት መያዝ ሲኖርባቸው ያልተያዙ ምክንያቶች እንዱያዙልኝ ያቀረብኩት የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ መደረጉ አግባብ አይደለም የሚል ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል።
በእርግጥ በላለበት የተሰጠ የወንጀል ጥፊተኝነት ውሳኔ እንዱነሳለት አቤቱታ አቅርቦ ውድቅ የተደረገበት አመልካች በተሰጠው የቅጣት ውሳኔ ላይ ብቻ ይግባኝ ማለት የሚችል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 202(3) ይደነግጋል። ሆኖም “በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 202(3) ድንጋጌ ስር የተመለከተው የይግባኝ መብት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን አቅርቦ መከራከርን ያጠቃልላልን?” የሚለው ትኩረት ሉሰጠው የሚገባው ነጥብ ነው።
በወንጀል ቅጣት አወሳሰን ውስጥ የሚቀርቡት የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ምክንያቶች ላይ የግራ ቀኙ መከራከሪያ ሉሰማ እንደሚገባ የወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 149(3) ይደነግጋል። ይህ እንዱሆን የተፈለገውም የሚቀርበው የቅጣት አስተያየት የተያዘውን መነሻ የወንጀል ቅጣት ከፍ አልያም ዝቅ የማድረግ ውጤት ያለው በመሆኑ ምክንያት ስለትክክለኛነቱ በተገቢ አክኋን ለማጥራት እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። የሚቀርበው የቅጣት አስተያየትም የህግ ወይም የፍሬ ነገር ላሆን ይችላል። የቅጣት አስተያየቱ የህግ ከሆነ እንደየሁኔታው በፍርድ ቤት ግምት የሚወሰድበት በመሆኑ ያን ያክል የግራ ቀኙን መገኘት እና ክርክር ማቅረብ ላይፈልግ ይችላል። ሆኖም አስተያየቱ የፍሬ ነገር ከሆነ የተባለው ምክንያት ስለመኖሩም ሆነ ስላለመኖሩ ግልፅ ጥያቄ እና ክርክር መቅረብ ያለበት በመሆኑ በቅጣት አወሳሰን ሂደት የተከራካሪ ወገኖችን መቅረብ/መገኘት/ የግድ የሚል ነው። ከዚህ አኳያ ተገቢውን መከራከሪያ ለማቅረብ ደግሞ ከመነሻውም የክርክሩ አካል መሆንን የሚጠይቅ በመሆኑ ጉዲዩ በላለበት የተወሰነበት ተከሳሽ የፍሬ ነገር የቅጣት አስተያየት አቅርቦ የሚከራከርበት የህግ አግባብ የለም። እናም በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 202(3) ስር የተመለከተው በቅጣት ውሳኔ ላይ በይግባኝ የመከራከር መብት ተከሳሹ ባይኖርም በህግ ረገድ ፍርድ ቤት በራሱ ተነሳሽነት በቅጣት ማቅለያነት መያዝ ሲገባው ያልያዘውን አልያም በቅጣት ማክበጃነት መያዝ ሳይኖርበት በተሳሳተ የህግ አተረጓጎም የተያዘ የቅጣት ማክበጃ ምክንያትን ብቻ የሚመለከት ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች በቅጣት ማቅለያነት ሉያዙልኝ ሲገባ አልተያዙልኝም ብል ከዘረዘራቸው ውስጥ የወንጀል ድርጊቱ በሙከራ ደረጃ ስለመቅረቱ ተጠቅሶ ከቀረበው ውጭ ያለት ምክንያቶች የፍሬ ነገር መከራከሪያዎች ናቸው። ይህ ከሆነ ደግሞ ቀድሞውኑ ጉዲዩን ለያዘው ፍርድ ቤት ሉቀርቡ እና ተገቢው ክርክር ላደረግባቸው የሚገባቸው እንጂ ፍርድ ቤት በራሱ አስተያየት ሉያነሳቸው የሚችላቸው ጉዲዮች አይደለም። አመልካች በዚህ መልኩ መከራከሪያውን እንዲያቀርብ ደግሞ ጉዲዩ በላለበት የታየ በመሆኑ እና እድለም ያልነበረ በመሆኑ ከጊዜ በኋላ በይግባኝ ደረጃ መከራከሪያ ላቀርብባቸው የሚገባ አይደለም። በመሆኑም አመልካች ከዚህ አንፃር ያቀረበው መከራከሪያ ለአቤቱታው መሰረት ከሆነው የወንጀል ሀግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 202(3) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ውጭ በመሆኑ ችልቱ አልተቀበለውም።
ሆኖም ድርጊቱ በሙከራ ደረጃ የመቅረቱ ጉዲይ በወንጀል ህግ አንቀፅ 27(3) እና 31 መሰረት ከቅጣት አወሳሰን ረገድ ፍርድ ቤት በራሱ አስተያየት ከግንዛቤ ሉያስገባው የሚችል የህግ ነጥብ ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት ከዚህ አንፃር ጉዲዩን ያለማየቱ ሉታረም የሚገባው መሰረታዊ የህግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ አግባብ የሙከራ ወንጀል ድርጊት በመሰረቱ ሉፈፀም ለነበረው ወንጀል በተቀመጠው ቅጣት መደብ የሚያስቀጣ ነው። ሆኖም የነገሩ ሁኔታዎች ታይተው እና ተመዝነው በወንጀል ህጉ አንቀፅ 179 ስር በተመለከተው መደበኛው የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ቅጣቱ ሉቀል ወይም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቅጣትን መወሰን ጨርሶ ለመተው የሚቻል መሆኑን የወንጀል ህጉ አንቀፅ 27(3) እና 31 ድንጋጌ ያስገነዝባል። በዚሁ መሰረት በስር ፍርድ ቤት የተያዘው የእስራት ቅጣት እርከን በአንድ እርከን እንዱቀንስ ተደርጎ በእርከን 32 ስር መቀጣት እንዲለበት ታምኗል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
No topics extracted.