No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ ቀናዓ ቂጣታ ብርሃኑ መንግሥቱ ማርታ ተካ አመልካች- አቶ አየለ ዲመና ተጠሪ- የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአመልካች የዋስትና መብት ይከበርልኝ ጥያቄ ዉድቅ ተደርጎ በመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ለማሳረም የቀረበ የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ። አመልካች በተጠረጠሩበት ወንጀል ምርመራ እየተደረገ ቆይቶ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕግ በአመልካች ላይ በ15 ቀናት ዉስጥ ክስ እንዱመሰርት ጊዜ ሰጥቶ መዝገቡን መዝጋቱን፤በዚህ መልኩ በተሰጠዉ ጊዜ ዉስጥ በአመልካች ላይ የወንጀል ክስ አለመመስረቱን ምክንያት በማድረግ አመልካች ለፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸዉ እንዱጠበቅላቸዉ ጠይቀዋል።ፍርድ ቤቱም ዐቃቤ ሕግ መልስ እንዱሰጥ አዝዞ በሰጠዉ መልስ አመልካች በፈጸሙት የእምነት ማጉደል እና ከባድ ማታለል ወንጀል የተጠረጠሩና ድርጊቱም በተለያዩ 12 ሰዎች ላይ የተፈጸመ በመሆኑ፣በማታለል ብር 924,814 በባንክ ሂሳባቸዉ ማስገባታቸዉ የተደረሰበት በመሆኑ፤የኦዱት ሥራዉ ስላልተጠናቀቀ በተባለዉ ጊዜ ዉስጥ ክስ መመስረት አንችልም።ስለሆነም አመልካች ከዚህ ቀደም ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ዉድቅ ስለተደረገ በድጋሚ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ዉድቅ ይደረገልኝ በማለት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ በቀን 10/11/2015ዓ/ም በሰጠዉ ትዕዛዝ አመልካች እምነት የማጉደል እና የማታለል ወንጀል ፈጽመዋል ተብል ከመጠርጠራቸዉ ጋር በተያያዘ ከዚህ በፉት የዋስትና መብት ጥያቄ አቅርቦ በቀን 23/09/2015 ዓ/ም ዉድቅ ከተደረገ በኋላ አሁን በድጋሚ የዋስትና መብት ጥያቄ ማንሳታቸዉ ተቀባይነት የለዉም።ጉዲዩ ላይ አስቀድሞ የመጨረሻ ዉሳኔ ስለተሰጠበት በይግባኝ ካልተስተካከለ በስተቀር በድጋሚ ሉጠይቁ አይችለም። በልላ በኩል በአመልካች ላይ እየተደረገ ያለዉን ምርመራ በተመለከተ የኦዱት ሂደቱ ያልተጠናቀቀ መሆኑንና በሂደት ላይ መሆኑን በመግለጽ ዐቃቤ ሕግ የቀረበዉ በቂ ምክንያት ስለሆነ ዐቃቤ ሕግ ክሱን በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዱመሰረት በማለት የአመልካችን የዋስትና መብት ጥያቄ ዉድቅ በማድረግ ወሰነ።
አመልካች በዉሳኔዉ ቅር በመሰኘት በየደረጃዉ ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ አመልካች የተጠረጠሩበት ወንጀል በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32/2 ስር የተደነገገዉን ተላልፈዋል በሚል በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 3/1 መሰረት ለአመልካች የዋስትና መብት መከልከለ በአግባቡ ነዉ በማለት ሰርዞባቸዋል።
አመልካች በቀን 10/12/2015ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ አጭር ይዘት፡- ዐቃቤ ሕግ በአመልካች ላይ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 109 መሰረት በ15 ቀን ጊዜ ዉስጥ ክስ እንዱመሰርት ቢታዘዝም ክስ ባልመሰረተበት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19/6 ጥበቃ የተደረገልኝን የዋስትና መብት ተከልክያለሁ። የዋስትና መብት ጥያቄ አንድ ጊዜ ተጠይቆ በልላ ጊዜ የተለየ ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ የዋስትና መብት መጠየቅ እንዲይቻል የሚከለክል ሕግ በላለበት አመልካች አስቀድሞ የዋስትና ጥያቄ አቅርበዉ ዉድቅ ተደርጓል በሚል ምክንያት ዐቃቤ ሕግ በ15 ቀን ዉስጥ የወንጀል ክስ እንዱመሰርት በተሰጠዉ ጊዜ ክስ አለመመስረቱ ተረጋግጦ እያለ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን የዋስትና ጥያቄ ዉድቅ ማድረጉ ስህተት ነዉ።በምርመራ መዝገቡ በቀረበዉ ማስረጃ መሰረት አመልካች ሉከሰስ የሚችለዉ በወንጀል ሕግ ቁጥር 676 እና 692 መሰረት ሆኖ እያለ በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32 መሰረት ሉከሰስ ይችላል በሚል የዋስትና መብት ጥያቄዬ ዉድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ።አንድን ሰዉ በወንጀል ተጠርጥሯል በሚል ምክንያት ብቻ በአስር ላይ ማቆየት በራሱ የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት የሚጥስ ነዉ ተብል የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ ተሽሮ የዋስትና መብቴ ይጠበቅልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ አመልካች በተጠረጠሩበት ወንጀል ክስ ሳይቀርብባቸዉ የሚከሰሱት ዋስትና ሉያስከለክል በሚችል ድንጋጌ ነዉ በሚል ምክንያት ብቻ የዋስ መብታቸዉ የተከለከለበትን አግባብ ተጠሪ ባለበት እንዱመረመር ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 07/01/2016ዓ/ም የተጻፈ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል። የመልሱም አጭር ይዘት፡- አመልካች የአቢሲኒያ ባንክ ቦሩ ጃዊ ቅርንጫፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነዉ ሲሰሩ ከተለያዩ 13 የሚሆኑ የባንኩ ደንበኞች ላይ ብር 1,024,817.00 ስብስበዉ ወደ ደንበኞች ሂሳብ ቁጥር ሳያስገቡ ለራሳቸዉ ጥቅም በማዋላቸዉ በከባድ የእምነት ማጉደልና የማታለል የሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል።ይህ ጉዲይ ከባንክ ጋር የተያያዘ ከመሆኑ አንጻር የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የለዉም።ክስ መመስረቻ ጊዜ እንዱሰጠን ሳንጠይቅ የስር ፍርድ ቤት በ15 ቀን ዉስጥ ክስ እንድንመሰርት ያዘዘዉ ሥልጣን ሳይኖረዉ ነዉ።ይህ ጊዜ የተሰጠዉ የምርመራ መዝገቡ ለተጠሪ ከመላኩ በፉት ነዉ።ጉዲዩ ተጨማሪ የማጣራት ሥራ የሚያስፈልገዉ ነዉ።አመልካች አቢሲኒያ ባንክ ከመግባታቸዉ በፉት የዘመን ባንክ ሰራተኛ የነበሩ ቢሆንም ከዚህ ባንክ የተሰናበቱት በዱሲፔሉን ግድፈት ቢሆንም ከዚህ ባንክ ባልተጻፈ ማስረጃ በአቢሲኒያ ባንክ ስለተቀጠሩ በተጨማሪነት በሀሰተኛ ሰነድ በመገልገል የሙስና ወንጀል ለመክሰስ እየተጣራ ይገኛል። አመልካች በገቢ ደረሰኝ ላይ ሲያትሙ የነበረዉ ማህተም በባንኩ ለማን የተሰጠ እንደሆነ ከባንኩ ተጠይቆ ማስረጃ ተገኝቷል።በደረሰኞቹ ላይ ያለዉ ፊርማ በፍረንሲክ እንዱመረመር ተደርጎ ዉጤቱ እየተጠበቀ ይገኛል። ስለሆነም አመልካች በከባድ ማታለል፣በከባድ እምነት ማጉደልና ሀሰተኛ ሰነድን በማዘጋጀትና በመገልገል ተደራራቢ ወንጀልች የተጠረጠሩ በመሆኑ የጉዲዩ ክብደት ከግምት ገብቶ የአመልካች የዋስትና ጥያቄ ዉድቅ በመደረጉ የተፈጸመ ስህተት የለም ተብል የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ይጽናልኝ በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የመልስ መልሳቸዉን በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተገለጸዉ የግራ ቀኙን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም ሰበር አጣሪ ችልት የያዘዉን ጭብጥ ከግምት በማስገባት አመልካች የዋስትና መብት እንዱጠበቅላቸዉ ያቀረቡት ጥያቄ ዉድቅ ተደርጎ በመወሰኑ በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈጸም አለመፈጸሙን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም አመልካች የዋስትና መብት ጥያቄ ያቀረቡት ስር ፍርድ ቤት ምርመራ ተጠናቋል በሚል ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዱመሰርት በተሰጠዉ 15 ቀን ዉስጥ ክስ እንዲልመሰረተባቸዉ፣ በተጠረጠሩበት ወንጀል ክስ ላቀርብባቸዉ የሚችለዉ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 676 እና 692 መሰረት ስለሆነ የተጠረጠሩበት ወንጀል የዋስትና መብት የሚያስከለክል እንዲልሆነ እና ክስ ሳይመሰረትባቸዉ ከሕግ አግባብ ዉጭ በእስር ላይ እንደሚገኙ በመግለጽ ነዉ።በዚህ መልኩ ያቀረቡትን የዋስትና መብት ይጠበቅልኝ ጥያቄ የስር ፍርድ ቤቶች ዉድቅ በማድረጋቸዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ተከራክረዋል። ተጠሪ ደግሞ አመልካች በእስር ላይ የሚገኙት በፋዳራል መንግሥት በተመዘገበዉ ባንክ (ሕዝባዊ ድርጅት) ላይ ከባድ የማታለል፣ ከባድ የእምነት ማጉደል እና ሀሰተኛ ሰነድ የማዘጋጀትና የመገልገል ተደራራቢ ወንጀልችን ፈጽመዋል በሚል በመጠርጠራቸዉ እንደሆነ፣ ምርመራዉ ሳይጠናቀቅና የምርመራ መዝገብ ለዐቃቤ ሕግ ሳይተላለፍ ክስ መመስረቻ ተብል 15 ቀን መሰጠቱ ስህተት እንደሆነ፣ ይህንን ትእዛዝ የሰጠዉ ፍርድ ቤት ሥልጣን እንደላለዉና ክስ መመስረቻ ጊዜ እንዱሰጠዉም እንዲልተጠየቀ በመግለጽ በአመልካች ላይ ተደራራቢ የወንጀል ክስ ላቀርብባቸዉ የሚችለዉ የሙስና ወንጀልችን ለመደንገግ በወጣዉ አዋጅ መሰረት በመሆኑ የዋስትና ጥያቄያቸዉ ዉድቅ መደረጉ በአግባቡ ነዉ ሲል ተከራክሯል።
በዚህ መልኩ ግራ ቀኙ ካሰሙት ክርክር እና ከስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ግልባጭ እንደተረዲነዉ የስር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመዲኘት ሥልጣን አለዉ ወይስ የለዉም የሚለዉን ቀጥለን የምንመለከተዉ ሆኖ ፍርድ ቤቱ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 109/1 መሰረት ዐቃቤ ሕግ በ15 ቀናት ዉስጥ በአመልካች ላይ ክስ እንዱመሰርት የሰጠዉ ጊዜ አመልካች የዋስትና ጥያቄ ከማቅረባቸዉ በፉት እንደተጠናቀቀ የግራ ቀኙ ክርክር ያሳያል። የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስቀድሞ ለምርመራ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ መስጠት እንደማይገባ አምኖበት ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ እንዱመሰርት የ15 ቀናት ጊዜ ከተሰጠ በኋላ እና ይህ ጊዜ ካለቀ በኋላ አመልካች በቀን 06/11/2015ዓ/ም ለሁለተኛ ጊዜ የዋስትና ጥያቄ ማቅረብ አይችለም በማለት የአመልካችን የዋስትና ጥያቄ ዉድቅ ሲያደርግ የወንጀል ምርመራ አለመጠናቀቁን መረዲቱን ገልጾ ተጠሪ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በአመልካች ላይ ክስ እንዱመሰርት አዝዞ መዝገቡን መዝጋቱን የትዔዛዙ ይዘት ያሳያል።በዚህ መልኩ በቀን 10/11/2015ዓ/ም ትዕዛዝ ተሰጥቶ የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ከተዘጋ በኋላ በዐቃቤ ሕግ መልስ ላይ እንደተመለከተዉ አመልካች ላይ እስካሁን ወይም ቢያንስ ዐቃቤ ሕግ ለዚህ ችልት መልሱን እስካቀረበበት ቀን 07/01/2016ዓ/ም ድረስ የወንጀል ክስ አለመመስረቱን ተገንዝበናል።
በኢፋዱሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17/2 ስር ማንኛዉም ሰዉ በሕግ ከተደነገገዉ ሥርዓት ዉጭ ሉያዝ፣ክስ ሳይቀርብበት ወይም ሳይፈረድበት ሉታሰር እንደማይችል በመደንገግ ለነጻነት መብት ጥበቃ ተደርጓል።ይህ መብት የሀገራችን የሕግ አካል በሆነዉ በተባበሩት መንግሥታት የሲቪልና የፕለቲካ መብቶች ቃል ኪዲን አንቀጽ 9/1 ላይ በግልጽ እዉቅና የተሰጠዉ መብት ነዉ።በኢፋዱሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 19/6 ስር የተያዙ ሰዎች በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ጥያቄዎችን ላይቀበል የሚችልበት ወይም በገደብ መብታቸዉን የሚያስጠብቅበት ሁኔታ ሉኖር የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በመርህ ደረጃ በዋስ የመፈታት መብት እንዲላቸዉ ተደንግጓል።
በተያዘዉ ጉዲይ በአመልካች ከባድ አታላይነትና ከባድ የእምነት የማጉደል ወንጀል ተፈጽሞበታል የተባለዉ አቢሲኒያ ባንክ አ.ማ በመሆኑ የሙስና ወንጀልችን ለመደንገግ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 2/4 ትርጓሜ መሰረት ወንጀለ የተፈጸመዉ ሕዝባዊ ድርጅት ላይ ነዉ።አመልካች የዚህ ባንክ ቅርንጫፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ እንደነበሩ ከተገለጸዉ ጋር ተደምሮ ሲታይ ዐቃቤ ሕግ በአመልካች ላይ የወንጀል ክስ የሚመሰርት ከሆነ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 881/2007 ስር የተደነገገዉን ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ላሆን እንደሚችል ይገመታል። በተሻሻለዉ የፀረ ሙስና የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀጽ 7(1 እና 4) ስር እንደተመለከተዉ ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የሚነሱ የመያዝ፣ የብርበራ፣የቀነ ቀጠሮ፣በማረፉያ ቤት የማቆየት፣የዋስትና፣የዔግድ እንዱሁም ከምርመራ ጋር የተያያዙ ላልች ተመሳሳይ ጉዲዮች የሚታዩት የሙስና ወንጀልችን ክስ ለማየት ሥልጣን በተሰጠዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነዉ።እንዱሁም በኢፋዱሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 80/2 ስር እንደተመለከተዉ በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት የዉክልና ሥልጣናቸዉ ያልተነሳባቸዉ የክልልች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ይህ ሥልጣን ይኖራቸዋል።
ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በአዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀጽ 7/4 ስር የተደነገገዉ ቢኖርም ይህንን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 7/5 ስር እንደተደነገገዉ በአዋጁ የመያዣ፣ የብርበራ፣ የቀነ ቀጠሮ፣…የዋስትና መብት ጥያቄ የሚመለከቱ ሥነ ሥርዓታዊ ጉዲዮች የሙስና ወንጀለን የማየት ሥልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት እንዱታዩ መደረጉ የተከሳሹን መብት የሚያጣብብ ወይም ማስረጃ እንዱጠፊ ምክንያት የሚሆን ወይም ተገቢ ላልሆነ ወጪ የሚዲርግ መሆኑን አግባብ ያለዉ የሙስና ወንጀልን ለመመርመር እና/ወይም ለመክሰስ ሥልጣን የተሰጠዉ አካል ካመነበት እንደ ሁኔታዉ በአቅራቢያዉ በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዱታይ ሉወስን ይችላል።በያዝነዉ ጉዲይ በአመልካች ላይ የወንጀል ምርመራ ሲያደርግ የነበረዉ አካል ለስር ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካችን አቅርቦ ለምርመራ የሚያስፈልገዉን ጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ እንደነበርና በዚያዉ መዝገብ ላይ አመልካች የዋስትና መብታቸዉ እንዱጠበቅላቸዉ ጠይቀዋል።በዚህ አግባብ የቀረበዉን የወንጀል ምርመራ ለማድረግ የሚያስፈልገዉን ጊዜ ቀጠሮ ጉዲይ እና የአመልካች የዋስትና መብት ጥያቄ አይቶ ለመወሰን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 434/1997(በአዋጅ ቁጥር 882/2007 እንደገና እንደተሻሻለዉ) በአንቀጽ 7/5 ስር በተደነገገዉ መሰረት ሥልጣን አለዉ ብለናል።በመሆኑም ተጠሪ ጉዲዩ የታየዉ ሥልጣን በላለዉ ፍርድ ቤት ነዉ በማለት ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም።
እንዱሁም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 109/1 መሰረት ዐቃቤ ሕግ በአመልካች ላይ በ15 ቀናት ዉስጥ ክስ እንዱመሰርት ትእዛዝ ሰጥቶ መዝገቡን ዘግቷል።ተጠሪ በአመልካች ላይ የሚደረገዉ የወንጀል ምርመራ ሳይጠናቀቅ ክስ መመስረቻ ጊዜ ተሰጥቶ መዝገቡ መዘጋቱ ትክክል አይደለም የሚል ከሆነና በትእዛዙ ላይ ቅሬታ ካለዉ አግባብ ባለዉ ሕግ መሰረት ይግባኝ ጠይቆ ማሻርና በአመልካች ላይ ምርመራ ማድረጊያ ተጨማሪ ጊዜ እንዱሰጠዉ ማስፈቀድ ሲገባዉ ይህንን አላደረገም።ክስ እንዱመሰርት የተሰጠዉ ጊዜ ካለቀ በኋላ እስካሁን በአመልካች ላይ ክስ ሳይመሰርት አመልካች በሕግ ከተደነገገዉ ሥርዓት ዉጭ በማረፉያ ቤት ታስረዉ እንዱቆዩ መደረጉ ተረጋግጧል።ዐቃቤ ሕግ ወይም አመልካችን የያዘዉ የወንጀል መርማሪ አካል በዚህ አግባብ አመልካችን እስር ላይ እንዱያቆዩ የሚፈቅድላቸዉ ሕግ የለም።
አመልካች የዋስትና መብታቸዉ ተጠብቆ ከእስር ለመለቀቅ ለሁለተኛ ጊዜ ማመልከቻ ያቀረቡት አዱስ የተፈጠረዉን ሁኔታ ማለትም ዐቃቤ ሕግ በተሰጠዉ 15 ቀናት ዉስጥ ክስ ያልመሰረተባቸዉ መሆኑን መሰረት በማድረግ ነዉ።በመሆኑም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን የዋስትና ጥያቄ ተመልክቶ የዋስትና መብታቸዉ እንዲይጠበቅ የሚያደርግ ሕጋዊ ምክንያት መኖር አለመኖሩን መርመሮ መወሰን ሲገባዉ አመልካች የዋስትና ጥያቄ አቅርበዉ አስቀድሞ በተሰጠ ትእዛዝ ዉድቅ መደረጉን በመግለጽ ይህን ትእዛዝ አመልካች በይግባኝ ሳያሽሩ ለሁለተኛ ጊዜ ጥያቄዉን ማቅረባቸዉ ተገቢ አይደለም በማለት ዉድቅ ማድረጉ የክርክሩን ልዩ ባህርይና የተፈጠረዉን አዱስ ሁኔታ መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ጉድለት ነዉ። በተጨማሪም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕግበአጭር ጊዜ ዉስጥ በአመልካች ላይ ክስ ይመስርት በማለት መዝገቡን መዝጋቱ የጊዜዉን አጭርነት ዐቃቤ ሕግ በመሰለዉ እንዱወስን በሚፈቅድ አኳኋን የመወሰን ሥልጣኑን ለዐቃቤ ሕግ አሳልፍ መስጠቱን እና አመልካች ላልተገደበ ጊዜ በእስር ላይ እንዱቆዩ ሉያደርግ የሚችል ትእዛዝ መስጠቱን ያሳያል።ይህም የዲኝነት ሥራ አመራር የሚጠይቀዉን የገለልተኛነትና የዲኝነት ነጻነት መርሆዎችን የሚቃረንና ሕገ መንግሥታዊ ጥበቃ የተደረገለትን የአመልካችን የነጻነትና የዋስትና መብቶች የሚጥስ ነዉ። እንዱሁም ጉዲዩን በይግባኝና በሰበር ያየዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እነዚህን ስህተቶች ማረም ሲገባዉ ያልተረጋገጠ መነሻ ይዞ አመልካች ዋስትና በሚያስከለክል የሙስና ወንጀል ሉከሰሱ ይችላለ በማለት የአመልካችን ይግባኝና የሰበር አቤቱታዎች በትእዛዝ መሰረዙም ሉታረም የሚገባዉ ስህተት ነዉ።
ሲጠቃለል በወንጀል በተጠረጠረ ሰዉ ላይ ምርመራ ማድረጊያ ጊዜ በፍርድ ቤት እየተሰጠ ቆይቶ በወንጀል መርማሪ እና/ወይም በዐቃቤ ሕግ የተጠየቀዉን ተጨማሪ የምርመራ ማከናወኛ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ባለመፍቀድ እስከ 15 ቀን ድረስ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዱመሰረት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 109/1 መሰረት የሰጠዉ ትእዛዝ ጸንቶ እያለ እና የተሰጠዉ ክስ መመስረቻ ጊዜ ከአለቀ በኋላ በተጠርጣሪዉ ላይ ክስ ሳይመሰረት ተጠርጣሪዉን በእስር ላይ ማቆየት በኢፋዱሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17/2 እና በተባበሩት መንግሥታት የሲቪልና የፕለቲካ መብቶች ቃል ኪዲን አንቀጽ 9/1 የተከለከለዉን በሕግ ከተደነገገዉ ሥርዓት ዉጭ ወይም በዘፈቀደ አስሮ እንደማቆየት የሚቆጠር ነዉ። በወንጀል ምርመራ ሂደት የዋስትና መብት እንዱጠበቅለት ተጠርጣሪዉ ጥያቄ አቀርቦ ጥያቄዉ ተቀባይነት ከአጣ በኋላ የዋስትና ጥያቄ ለማቅረብ የሚያስችል አዱስ ሁኔታ ሲፈጠር ይህንኑ አዱስ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ለዚያዉ ፍርድ ቤት ተጠርጣሪዉ የዋስትና መብት ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ ሥነ ሥርዓታዊ መብት አለዉ ብለናል።በዚህ አግባብ አዱስ ሁኔታ በመፈጠሩ ወይም ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዱመሰረት የተሰጠዉ ጊዜ ክስ ሳይመሰረት በማለቁ ምክንያት የተያዘዉ (የታሰረዉ) ሰዉ በዋስትና ለመለቀቅ የሚያቀርበዉ ጥያቄ አግባብነት ካለዉ ሕግ አንጻር ሳይመረመር በደፈናዉ ጥያቄዉ ቀድሞ ተቀባይነት ያላገኘ ነዉ በሚል የተያዘዉ ሰዉ ክስ ሳይመሰረትበት ላልተወሰነ ጊዜ ታስሮ እንዱቆይ የሚያደርግ ትእዛዝ/ዉሳኔ መስጠት በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2(4/ሀ) እና 10(1/ሐ) ስር በተደነገገዉ መሰረት ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። ስለሆነም አመልካች ላይ የወንጀል ክስ እንዱመሰረት የተሰጠዉ የ15 ቀን ጊዜ ከአለቀ በኋላ አመልካች ላይ የወንጀል ክስ ሳይመሰረትባቸዉ በእስር ላይ የሚገኙት በሕግ ከተደነገገዉ ሥርዓት ዉጭ በመሆኑ የአመልካች የዋስትና መብታቸዉ ተጠብቆ ከእስር ሉፈቱ ይገባል ብለናል። በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 10/11/2015ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ፣ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ላይ በቀን 20/11/2015ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 02/12/2015ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አንቀጽ 9/1 መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ ብር) በዋስትና አስይዘዉ ወይም ለዚህ በቂ የሆነ መያዣ ሲያቀርቡ ከእስር እንዱፈቱ ታዟል።አመልካች በአዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀጽ 6/መ መሰረት ከአገር አንዲይወጡ ታግደዋል።ይጻፍ።በዚህ ትእዛዝ መሰረት አመልካች በዋስትና ከመለቀቃቸዉ በፉት ከአገር እንዲይወጡ የተሰጠዉ የዔግድ ትእዛዝ በሚመለከተዉ አካል ተመዝግቦ ዉጤቱ ሲገለጽ ከእስር እንዱለቀቁ ይጻፍ።
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ። ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.