No summary available.
ቀን፡- ጥቅምት 04 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፕሬሽን - የርብ ግድብ መስኖ ልማት ፔሮጀክት - ነ/ፈጅ መኳንንት ደግነት - ቀረቡ ተጠሪ፡-
የሰበር መዝገቡ የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ተከሳሽ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጣልቃ ገብ ነበሩ። 1ኛ ተጠሪ ግንቦት 11 ቀን 2009 ዓ/ም በተጻፈ ያቀረቡት ክስ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓ/ም ሕፃን አብርሃም ግዛቸው ከአዱስ ዘመን ወደ ርብ ግድብ እየተጓዘ እያለ ንብረትነቱ የአመልካች የሆነ ኮድ 3-47221 ቶዮታ መኪና በ3ኛ ተጠሪ እየተሽከረከረ እግሩን በመግጨት ከጉልበቱ በታች ባደረሰበት ጉዲት እግሩ ከጥቅም ውጭ ሲሆን በሕክምና 30% ጉዲት መድረሱ ተረጋግጧል።
ሕፃን አብርሃም ግዛቸው ጉዲቱ ሲደርስበት 5 ዓመቱ ሲሆን እስከ 62 ዓመት ድረስ ሉኖር ስለሚችል ሉያገኝ የሚችለውና በጉዲቱ የሚያጣው ጥቅም በቀን 30 ብር በወር 900 ሲሆን 900 ብር x 12 ወራት x 57 ዓመት ብር 615,600.00፣ የሞራል ካሣ ብር 1,000.00 እና የሕክምናና የትራንስፕርት ወጪ ብር በድምሩ ብር 617,502.00 አመልካች እንዱከፍል እንዱወስንላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካች ያቀረበው መልስ ክሱ በፍ/ሕ/ቁ. 2143(1) መሰረት በይርጋ የታገደ ነው። ጥፊት ያጠፊው ሾፋር ነው መጠየቅ ያለበት፤ ባለንብረት ኃላፉነት የለበትም። የ5 ዓመት ሕፃን እስከ 18 ዓመት ድረስ ሥራ አይሰራም። ጉዲቱ በሂደትም ስለዲነ አለታዊ ጉዲት አላስከተለም። 30% ቋሚ ጉዲት የተባለው ያልተብራራ እና በተጎጂው ሕይወት ላይ የሚያስከትለው የመሥራት ችግር ያልተገለጸ ስለሆነ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል። ለተሽከርካሪው 3ኛ ወገን ኃላፉነት ሽፊን የሰጠው 2ኛ ተጠሪ እና የተሽከርካሪው ሾፋር የነበረው 3ኛ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገቡ ጠይቋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጣልቃ እንዱገቡ ያዘዘ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ቀርቦ አደጋውን አመልካች ያላሳወቀኝ በመሆኑ ኃላፉነት የለብኝም በማለት የተከራከረ ሲሆን 3ኛ ተጠሪ መጥሪያ ደርሷቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት ታይቷል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዲዩን መርምሮ የይርጋ መቃወሚያውን ውድቅ ካደረገ በኋላ 2ኛ ተጠሪ ኃላፉነትን ክድ ተከራክሯል በማለት ከክርክሩ ውጭ አድርጓል። 3ኛ ተጠሪ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር በጥፊቱ በ1ኛ ተጠሪ ላይ ጉዲት በማድረሱ እና አመልካች የተሽከርካሪው ባለንብረት በመሆኑ ለጉዲቱ ኃላፉ ናቸው። የኃላፉነት መጠኑን በተመለከተ 1ኛ ተጠሪ 30% ቋሚ ጉዲት የደረሰበት ስለመሆኑ በሕክምና ተረጋግጧል። ይሕም ለወደፉት ሕይወቱ ላይ አለታዊ ተፅዔኖ የሚያሳድር ነው።
1ኛ ተጠሪ ዔድሜው 5 ዓመት በመሆኑ አሁን በጉዲቱ ሳቢያ ሉያጣው የሚችል ነገር ባይኖርም ለወደፉት የሚያጣው ጥቅም መካስ እንዲለበት በፍ/ሕ/ቁ. 2092 የተመለከተ ስለሆነ ነገር ግን የሚቋረጠውን ጥቅም በእርግጠኝት ማወቅ ስለማይቻል በርትዔ ብር 250,000.00 ካሣ፣ የሞራል ካሣ ብር 1,000.00 እና የሕክምናና የትራንስፕርት ወጪ ብር 902.00 በድምሩ ብር 251,902.00 ከወጭና ኪሣራ ጋር አመልካች እና 3ኛ ተጠሪ በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት ለ1ኛ ተጠሪ እንዱከፍለ ወስኗል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአመልካችን ይግባኝ ባለመቀበል ሰርዟል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ክሱ የቀረበው ጉዲቱ ከደረሰ ከሁለት ዓመት በላይ ስለሆነ በፍ/ሕ/ቁ. 2143(1) በይርጋ ቀሪ ላሆን ይገባል። አመልካች የተሽከርካሪው ባለንብረት ስለሆነ የፍ/ሕ/ቁ. 2143(2) ተፈጻሚ አይደለም። 2ኛ ተጠሪ የ3ኛ ወገን ኃላፉነት የመድን ሽፊን የሰጠ ሆኖ እያለ ከክሱ ውጭ መደረጉ ተገቢ አይደለም። ጥፊቱ የ3ኛ ተጠሪ ሆኖ እያለ የኃላፉነት መጠኑ ሳይለይ በአንድነትና በነጠላ ኃላፉ ልንባል አይገባም። የማይሰራ ልጅ፣ ጉዲቱ ሳይረጋገጥ በርትዔ ካሣ መወሰኑ ስህተት ያለበት ነው የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ 2ኛ ተጠሪ ከክሱ ውጭ መደረጉ ሕጋዊነቱን ለማጣራት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ በማዘዙ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ክሱ በጊዜው የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ ቀርቦ ነበር፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ሥልጣን የለውም በማለት በመሻሩ እንደገና ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክሱ ሲቀርብ ነው የዘገየው፤ በይርጋ ሉታገድ አይገባም። ጉዲቱ በሆስፑታል ተረጋግጦ ቀርቦ የተወሰነ ነው።
ውሳኔው ሉጸና ይገባል ብለዋል። 2ኛ ተጠሪ በበኩለ ክሱ በይርጋ ቀሪ ቢሆን እንደሚስማማ በመግለጽ በይርጋ ቀሪ ካልሆነ ግን አመልካች አደጋውን በጊዜው ያላሳወቀው በመሆኑ ከክሱ ውጭ መደረጉ ተገቢ ነው በሎል። አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታውን አጠናክሮ ተከራክሯል። 3ኛ ተጠሪ ተጠርተው ያልቀረቡ በመሆኑ ጉዲዩ በላለበት ታይቷል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር፣ በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘው ጭብጥ፣ በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው 1ኛ ተጠሪ ግንቦት 11 ቀን 2009 ዓ/ም በተጻፈ ያቀረቡት ክስ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓ/ም ሕፃን አብርሃም ግዛቸው ከአዱስ ዘመን ወደ ርብ ግድብ እየተጓዘ እያለ ንብረትነቱ የአመልካች የሆነ ኮድ 3-47221 ቶዮታ መኪና በ3ኛ ተጠሪ እየተሽከረከረ እግሩን በመግጨት ከጉልበቱ በታች ባደረሰበት ጉዲት እግሩ ከጥቅም ውጭ ሲሆን በሕክምና 30% ጉዲት መድረሱ ተረጋግጧል። የጉዲት ካሣ ብር በድምሩ ብር 617,502.00 አመልካች እንዱከፍላቸው እንዱወስንላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች በበኩለ ክሱ በፍ/ሕ/ቁ. 2143(1) መሰረት በይርጋ የታገደ ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል። በፍ/ሕ/ቁ. 2143(1) መሰረት ጉዲት ከደረሰ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ የካሣ ክስ በይርጋ የታገደ እንደሚሆን አስቀምጧል። 1ኛ ተጠሪ ክሱን ያቀረበው ግንቦት 11 ቀን 2009 ዓ/ም ሲሆን ጉዲቱ የደረሰው ደግሞ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓ/ም ነው። ይሕም ክስ የቀረበው በሕጉ ከተመለከተው የሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ እንደሆነ ያስገነዝባል። በፍ/ሕ/ቁ. 2143(2) ላይ ጉዲቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ከሆነ የይርጋ ዘመኑ በወንጀል ይርጋ ጊዜው ልክ ይሆናል በሚል ተደንግጓል። የሥር ፍርድ ቤት 3ኛ ተጠሪ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር በጥፊቱ በ1ኛ ተጠሪ አካል ላይ በቋሚነት ጉዲት ማድረሱን አረጋግጧል። ይሕም ድርጊቱ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 559(2) መሰረት በወንጀል ስለሚያስቀጣ እና የወንጀለ ይርጋ በወ/ሕ/ቁ. 217(1)(ሰ) መሰረት አምስት ዓመት ነው። 1ኛ ተጠሪ ክሱን በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ አቅርበዋል። የክሱ ምክንያት ከውል ውጭ ካሣ እንዱከፈል በመሆኑ የጉዲት አድራሹ ተሽከርካሪ ባለቤት ላይ ክሱ ሲቀርብ የፍ/ሕ/ቁ. 2143(2) ለጉዲዩ ተፈጻሚ ነው። በተጨማሪም ክሱ በጊዜው የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ ቀርቦ በይግባኝ ሥልጣን የለውም ተብል በመሻሩ እንደገና ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክሱ ሲቀርብ ነው የዘገየው በሚል 1ኛ ተጠሪ ያቀረበውን ክርክር አመልካች አልካደውም። ይሕም ይርጋ ጊዜውን የሚያቋርጥ በመሆኑ የጉዲት ካሣ ክሱ በይርጋ የታገደ አይደለም መባለ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
የጉዲት ካሣውን በተመለከተ ግራ ቀኙ ባላቸው ከውል ውጭ ኃላፉነት የጉዲት ካሣ ክርክር የሥር ፍርድ ቤቶች የጉዲት ካሣውን ጉዲት አድራሹን መኪና ሲያሽከረከር የነበረውን 3ኛ ተጠሪና የተሽከርካሪው ባለንብረት የሆነው አመልካችን ኃላፉ በማድረግ የ1ኛ ተጠሪ ዘለቄታዊ የአካል ጉዲቱ 30% መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ተጠሪ ለወደፉት ይኖራለ ተብል በተገመተው ዔድሜ ልክ በርትዔ ካሣ እንዱከፈላቸው ወስነዋል። 3ኛ ተጠሪ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር በጥፊታቸው በፍ/ሕ/ቁ.
2027(1) እና 2028 መሰረት እና አመልካች የጉዲት አድራሹ ተሽከርካሪ ባለንብረት በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ.
2081(1) መሰረት ለጉዲቱ ኃላፉ መሆናቸው ተገቢ ነው። ካሣ በፍ/ሕ/ቁ. 2090(1) እንደተመለከተው ከደረሰው ጉዲት ጋር ተመዛዛኝ ወይም ተመጣጣኝ መሆን እንዲለበት መርህ የተቀመጠ ሲሆን በፍ/ሕ/ቁ.
2092 አግባብ ደግሞ ካሣው የተረጋገጠ ለወደፉት የሚደርስን ጉዲትም ማካተት እንዲለበት ተመልክቷል። የአካል ጉዲትን ወደ ገንዘብ መተመን አስቸጋሪ ቢሆንም በተጎጂው ወደፉት የመስራት አቅም ላይ አለታዊ ተፅዔኖ ካለው ለወደፉት የሚደርስ ጉዲት (future damage) መወሰን እንደሚገባ ሰበር ችልቱ በ
ቅጽ 5 ላይ እና በ
ቅፅ 9 ላይ አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል። ለወደፉት የሚደርስ ጉዲት ለመወሰን የደረሰው የአካል ጉዲት ዘላቂና የመስራት አቅም ላይ አለታዊ ተፅዔኖ ያለው ስለመሆኑ የሚረጋገጠው በዋነኛነት በህክምና ማስረጃ ነው። በተያዘው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ ከጉልበቱ በታች እግሩ ላይ ጉዲት የደረሰበት ሲሆን የአካል ጉዲቱም በህክምና 30% ስለመሆኑ በሥር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። 1ኛ ተጠሪ ጉዲቱ ሲደርስበት ሥራ መስራት ያልጀመረ ሕጻን በመሆኑ አሁን ተቀጥሮ የሚሰራና ገቢ የሚያገኝ አይሆንም። በልላ በኩል ሥራ ለመስራት በሚደርስበት ዔድሜ ላይ የደረሰበት ቋሚ የአካል ጉዲት በአጠቃላይ የመሥራት ኃይል በመቀነስ ለወደፉት የሚደርስ ጉዲት (future damage) እንደሚያስከትል የሚታወቅ ሲሆን ትክክለኛ ጉዲቱ ግን ለማወቅና ለመለየት ስለሚያስቸግር በፍ/ሕ/ቁ. 2102 እንደተመለከተው ጉዲት መድረሱ ተረጋግጦ ነገር ግን የጉዲት መጠኑን ማወቅ ካልተቻለ ካሣውን በርትዔ መወሰን ይችላል። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች ካሣውን በርትዔ በመወሰን ለ1ኛ ተጠሪ ብር 250,000.00 ካሣ በርትዔ እንዱከፈል መወሰናቸው ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለናል።
አመልካች በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 43 መሰረት የጉዲት ካሣ ኃላፉነቱን እንዱጋራው 2ኛ ተጠሪ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ጣልቃ ገብቶ እንዱከራከር ጠይቋል። 2ኛ ተጠሪ ቀርቦ አደጋውን አመልካች ያላሳወቀኝ በመሆኑ ኃላፉነት የለብኝም በማለት የተከራከረ ሲሆን ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ጉዲዩን መርምሮ 2ኛ ተጠሪ ኃላፉነትን ክድ ተከራክሯል በማለት ከክርክሩ ውጭ አድርጓል።
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 43 መሰረት የተከሳሽን ኃላፉነት ሉጋሩ የሚችለ ወገኖች ወደክርክሩ እንዱገቡ የሚደረገው ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ ክርክሩን አጠቃል ለመምራት እንዱያስችል ሲሆን ከውል ውጭ ኃላፉነት ተከትል ከሚመጣ ክርክር ጋር በተያያዘ ተጎጂው ካሣውን የሚጠይቅበት እድል የሚያሰፊ ነው። በተያዘው ጉዲይ ክርክሩ በዚህ ሰበር ችልት ደረጃ ከደረሰ በኋላ መመለስ የተጎጂውን ካሣውን ሳያገኝ እንዱቆይ የሚያደርግ ሲሆን ከአመልካች መብት አኳያም ካሣውን በራሱ ከከፈለ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በገባው የሦስተኛ ወገን መድን ውለ መሰረት 1ኛ ተጠሪ የከፈለውን ካሣና 2ኛ ተጠሪ ባለበት ኃላፉነት ልክ የውል ግዳታ መሰረት በማድረግ ለመጠየቅ ሕጋዊ መፍትሓ አለው።
በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች ለ1ኛ ተጠሪ ሉከፈል የሚገባውን የጉዲት ካሣ አመልካች ከ3ኛ ተጠሪ ጋር እንዱከፍል በመወሰናቸው በዚህ ሰበር ችልት ደረጃ የሚመረመር መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አላገኘንበትም።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ/ም እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሐምል 20 ቀን 2012 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
አፈጻጸሙ ላይ የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.