No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነጻነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ አፈወርቅ መንግስቱ ተጠሪዎች፡- ወጋገን ባንክ አ.ማ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረበዉ ክስ በተጠሪ ባንክ ዉስጥ ከሐምል 20 ቀን 1996 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ፤ በኋላም ከስራ እስከ ተሰናበትኩበት ታህሳስ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የባንኩ የቱለ ቦል ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ደረጃ 3 የስራ መደብ ላይ በወር ብር 23,750.00 እየተከፈለኝ በማገልገል ላይ እያለሁ እንደ አዉሮፒዉያን አቆጣጠር በሴፔቴምበር 06 ቀን 2018 በቅርንጫፈ በባለ መቶ እና በባለ ሃምሳ ብር ኖት እሽግ ዉስጥ የባለ አስር ብር ኖት ተቀላቅል በመታሸጉ ምክያት ለተከሰተ የብር 469,000.00 ጉድለት ተጠያቂዉም አንተ ነህ በማለት ተጠሪ በቀን 23/04/2011 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ ከስራዬ ያሰናበተኝ በመሆኑ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነዉ ተብል ልዩ ልዩ ክፍያዎች እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀዉን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ።
ተጠሪ በበኩለ በሰጠዉ መልስ የአመልካች የስራ ዉል የተቋረጠዉ እንደ አዉሮፒዉያን አቆጣጠር ሴፔቴምበር 06 ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገ ምርመራ በባንኩ ቱለ ቦል ቅርንጫፍ በባለ መቶ እና ባለ ሃምሳ ብር ኖት እሽግ ዉስጥ የባለ አስር ብር ኖት ተቀላቅል የብር 469,000.00 ጉድለት በመከሰቱ እና ጉደለቱ ከመከሰቱ በፉት የቅርንጫፈ ዋና ገንዘብ ያዥ እረፍት ሲወጡ እ.አ.አ. በኦገስት 31 ቀን 2018 ዓ.ም የተደረገዉ የገንዘብ ርክክብ የባንኩን መመሪያ በመጣሱ ሲሆን ይህም ጥፊት ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሉያሰናብት የሚችል የዱሲፔሉን ጥፊት በመሆኑ ነዉ፤ ጉዲዩም በዱሲፔሉን ኮሚቴ ታይቶ ከስራ እንዱሰናበት የተደረገ ስለሆነ ስንብቱ ህጋዊ ነዉ፤ ሉከፈለዉ የሚገባ ክፍያም የለም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት የስር መጀመሪያ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ጉድለቱ የተፈጠረዉ በአመልካች ቸልተኝነት ስለመሆኑ ተጠሪ በማስረጃ ያላረጋገጠ በመሆኑ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነዉ በማለት ካሳን ጨምሮ የተለያዩ ክፍያዎችን በጠቅላላዉ ብር 415,624.99 ተጠሪ ለአመልካች ይክፈለዉ በማለት ወስኗል። በዚህ ዉሳኔ ቅር የተሰኘዉን ተጠሪ ይግባኙን ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በጉዲዩ ላይ ግራ ቀኙን ካራከር በኋላ ተጠሪ አመልካች የስራ መሪ መሆኑን በመጥቀስ ያቀረበዉን መቃወሚያ ዉድቅ በማድረግ ግራ ቀኙን አከራክሮ ዉሳኔ መስጠቱ የፍደራል ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ እና በላልች በርካታ መዛግብት ላይ የሰጠዉን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ይቃረናል፤የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለዉም በማለት ዉሳኔዉን ሽሮታል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነዉ የሰበር አቤቱታ በአመልካች የቀረበዉም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
አመልካች ሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤት ተፈጽመዋል ያላቸዉን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረምለት ጠይቋል። የአቤቱታዉ ይዘትም በአጭሩ በተጠሪ ባንክ የተቀጠርኩት በተራ ሰራተኛነት ሆኖ እያለ እና ከተቀጠርኩ በኋላም በመካከላችን የተሻሻለ የስራ ዉል ባልተፈፀመበት ተጠሪ የስራ መሪ እንደሆንኩ አስመስል ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት አግኝቶ በዚሁ አግባብ ዉሳኔ መሰጠቱ፤ ተጠሪ ባንክ አስራ አንድ አባላት ባለት የዲይሬክተሮች ቦርድ የሚመራ ሲሆን ባንኩን የሚያስተዲድሩት ለቦርደ ተጠሪ የሆኑ አንድ ፔሬዝዲንት እና አምስት ምክትል ፔሬዝዲንቶች አለት፤አመልካች የምሰራበት ቅርንጫፍ በአነስተኛ ደረዲ የተመደበ በመሆኑ እኔም ደረጃ ሶስት ስራ አስኪያጅ የስራ መደብ ተሰጥቶኝ በዚሁ የስራ መደብ ላይ ሳገለግል ቆይቻለሁ፤ ከአጠቃላይ የባንኩ መዋቅር የአልካች የስልጣን ደረጃ ከአራት መቶ ሰዎች በኋላ ሲሆን ይህም እንደ ክፍል ኃላፉ ስልጣን የሚቆጠር ነዉ፤ በስሬ የማስትዲድራቸዉ ሰራተኞች አስራ አምስት የማይሞለ ሲሆን እነዚህን ሰራተኞች ከማስተዲደር ባለፈ ፕሉሲ የማዉጣት፤ የመፈፀም፤ ሰራተኛ የመቅጠር፤የማዘዋወር፤
የመመደብ፤ የማባረር፤ የማገድ፤ እርምጃ የመዉሰድ፤ የመቀነስ እና የመሳሰለት ስልጣኖች እንደላለኝ እየታወቀ የስራ መሪ ነዉ ተብል መወሰኑ፤ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ የስራ አስኪያጅ የስራ መዘርዝር በእንግሉዝኛዉ እና በአማርኛዉ መካከል ያለዉን የትርጉም መዛባት አመልካች ማብራሪያ እንዱሰጥበት ጥያቄ አቅርቤ በዝምታ ታልፍ የስራ መሪ ነዉ ተብል የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነዉ።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ አመልካች የስራ መሪ ነዉ? ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ ከአዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና በዚህ ሰበር ችልት ከሰጡት የህግ ትርጓሜዎች አንፃር ተጠሪ ባለበት መጣራት ያለበት መሆኑ ታምኖበት ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቧል። በዚሁም መሰረት ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ህዲር 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፍ ባቀረባዉ መልስ አመልካች በተጠሪ መስሪያ ቤት ዉስጥ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ መደብ ላይ ሲሰራ እንደነበረና ውለም የተቋረጠው ስራ አስኪያጅ ሆኖ ሲያገልግል የቆየ መሆኑ ከስር ፍ/ቤት ጀምሮ የተረጋገጠ ሲሆን እንደ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅነቱ ደግሞ የቅርንጫፈን እቅድና ዓላማዎች ማዘጋጅትና የማስፈፀም፣ የቅርንጫፍ በጀት ማዘጋጅት እና አፈፃፀማቸው የመከታተል፣ በቅርንጫፍ ያለ ሰራተኞች ውጤታማ እንዱሆኑ ማሰልጠን፣ በስሩ ያለ ሰራተኞችን የስራ ውጤት መሙላት፣ የሰራተኞችን የስነ-ምግባር ሁኔታ መከታተል፣ ቅርንጫፈን የሚመለከቱ ውሳኔዎችን በተመለከተ በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ በመሳተፍ ውሳኔ የማሳለፍ ኃላፉነት እንዲለበት በስራ መዘርዝሩ ላይ የተቀመጠ ሲሆን ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም ይህንኑ በማረጋገጥ የሰጠው ውሳኔ ተገቢ በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቶ ተከራክሯል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ የክርክር ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታውን ለማስቀረብ በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኙ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሮታል። እንደመረመረዉም የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች የስራ መሪ ነው በሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰው አመልካች በተጠሪ ባንክ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ የሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት የቅርንጫፍ ግብአቶችን ለማሳደግ ማሰባሰብ፣ እቅድና ፔሮግራሞችን ማዘጋጀት እና መተግበር፣ የቅርንጫፍን የኦፔሬሽን ፕሉሲ እና አስራሮች እንዱሁም ውጫዊ የደንብ መስፈርቶች ተገዥነት መቆጣጠር እንዱሁም አስፈላጊ ሲሆን የለውጥ ማሻሻያ ምክሮችን መስጠት፣ የቅርንጫፍ እቅድ እና ዓላማዎች ማዘጋጀት እና ተግባራቸውን መምራት፣ በስራቸው የሚገኙትን ሰራተኞች የስነ ምግባር ሆኔታዎች ማስተዲደር እና በቅርንጫፍ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ የተለያዩ ኮሚቴዎች አባል በመሆን መሳተፍ ስለመሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች “በአማርኛው የቅርንጫፈ የኦፔሬሽን ፕሉሲ” በሚል የተገለፀው ትክክለኛ ትርጉም አይደለም በሚል የሚከራከር ቢሆንም በመሰረታዊነት የስራ ድርሻው ከላይ የተመለከተው ስለመሆኑ ክድ አይከራከርም። የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሻው መሰረታዊ ነጥብ አመለካች እንደ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ እንዱያከናውን የሚጠበቁበት ከላይ የተመለከቱት ተግባራት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አግባብ አመልካችን የስራ መሪ የሚያሰኝ መሆን አለመሆኑ ነው።
በአዋጁ አንቀጽ 2(10) ላይ እንደተመለከተው የስራ መሪ ማለት በሕግ ወይም እንደ ድርጅቱ የስራ ጠባይ በአሰሪው በተሰጠው የውክልና ስልጣን መሰረት የስራ አመራር ፕሉሲዎችን የማውጣትና የማስፈፀም ስልጣን ያለው ወይም ሰራተኛን የመቅጠር፣ የማዘዋወር፣ የማገድ፣ ማሰናበት ወይም የመመደብ ተግባሮችን የመወሰን ስልጣን ያለው ግለሰብ ሲሆን እነዚህን የስራ አመራር ጉዲዮች አስመልክቶ የአሰሪውን ጥቅም ለመጠበቅ አሰሪው ሉወስድ ስለሚገባው እርምጃ በማንም ሳይመራ የራሱን ውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ የህግ አገልግልት ኃላፉንም ይጨምራል በማለት ትርጉም ሰጥቷል።
ከዚህ መረዲት የሚቻለዉ አንድ ሰራተኛ የሥራ አመራር ፕሉሲዎችን የሚያወጣና የሚያስፈጽም ወይም ሰራተኛን የሚቀጥር እና የማሰናበት ዔርምጃ የመዉሰድ ተግባራትን የሚያከናዉን የሥራ መሪ ልባል የሚችል መሆኑን ነዉ። ሰራተኘዉ ከእነዚህ አንደን ወይም ከዚያ በላይ ሥራዎችን የሚሰራ መሆኑ በማስረጃ መረጋገጥ ያለበት ሲሆን ተግባራቱ መኖራቸዉ ከተረጋገጠ ደግሞ በአሰሪዉ እና በሰራተኛዉ መካከል ያለዉ ግንኙነት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ጉዲይ የሚገዛበት አግባብ አይኖርም። ህግ አዉጪዉ ይህንን ልዩ ሁኔታ ወይም ማግለያ በአዋጁ ያስቀመጠበት መሰረታዊ ዓላማ የሰራ መሪ አሰሪዉን ወክል የድርጅቱን ፕሉሲ የሚያቅድና የሚያስፈጽም ነዉ ተብል ስለሚገመት ከላላዉ ሰራተኛ መብት ጋር የጥቅም ግጭት እንዲይፈጠር በሚል መነሻ ሃሳብ እንደሆነ ይታወቃል። ስለዚህም አንድ ቀጣሪ የስራ መሪ ነዉ ተብል ሉፈረጅ የሚችለዉ በህጉ የሥራ የመሪ ተግባራት ተብለዉ የተዘረዘሩትን ስራዎች ለማከናዉን ስልጣን የተሰጠዉ መሆኑ መረጋገጥ አለበት።
በተያዘዉ ጉዲይ በአመልካች ድርጅት መዋቅር መሰረት ተጠሪ የ3ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ሆነዉ ሲሰራ እንደነበር አላከራከረም። በልላ በኩል ተጠሪ ስራ አስኪያጅ የሚል ስያሜ መያዙ በራሱ የስራ መሪ የሚያሰኝ አለመሆኑን ከህጉ አነጋገር የምንገነዘበዉ ጉዲይ ሲሆን ዋናኛ መስፈርቱ የስራ መሪ የሚያሰኙ ጉዲዮችን በሚመለከት የመወሰን ስልጣንና ተግባር መኖሩ አለመኖሩ ላይ የሚመሰረት መሆኑን ነዉ። ሆኖም የአመልካች የስራ ድርሻ መሆናቸዉ የተረጋገጠዉ ከላይ የተመለከቱት ተግባራት አመልካች የተጠሪ ባንክ ፕሉሲ ጉዲዮች ላይ የማቀድ እና የመወሰን እንዱሁም ሰራተኛ የመቅጠርም ሆነ የማሰናበት ተግባራትን የሚያካትት አይደለም። ይልቁንም እነዚህ ተግባራት በበላይ አካላት የሚወሰኑ ሆኖ የአመልካች ኃላፉነት ከዚህ በመለስ ያለ የእለት ከእለት አስተዲደራዊ ስራዎች ላይ የተገደበ ስለመሆኑ ለመገንዘብ ተችሎል። ይህም የሚያሳየዉ ተጠሪ በሚመራዉ ቅርንጫፍ ባንክ የእለት ስራዎችን መምራትና ሰራተኛ ማስተዲደር ስልጣን ቢኖረዉም ሰራተኞችን የመቅጠርና ማሰናበት ስራዉ በበላይ አካላት የሚሰራ መሆኑን ነዉ።
በአጠቃላይ አመልካች እንደ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ የተሰጠዉ ኃላፉነት የስራ መሪን አስመልክቶ በአዋጅ አንቀጽ2(10) ላይ የተመለከተዉን ትርጓሜ ያማያሟላ ሆኖ እያለ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ በማስረጃ የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር እንዱሁም ለጉዲዩ አግበብነት ያለዉን ድንጋጌ ይዘት ያላገናዘበ በመሆኑ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/4/እና 10 ድንጋጌ መሰረት በዚህ ችልት ሉታረም የሚገባ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘግቶ የነበረዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ አመልካች ከስራዉ የተሰናበተበትን አግባብ ህጋዊነት ከግራ ቀኝ ክርክር አንፃር በመመርመር የመሰለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 341(1) መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.