No summary available.
መ/ቁ/ 203557 ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- 1ኛ/ አቶ መላኩ አብረሃ 2ኛ/ አቶ እርቅይሁን ባየ አልተጠሩም 3ኛ/ አቶ መሃመድ አሉ ተጠሪ፡- ኢትዮ ቴላኮም ሰሜን ምስራቅ ርጅን - ነ/ፈጅ አቶ ዲንኤል ገ/አናንያ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የስራ ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል ደቡብ ወል በደሴ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ በተጠሪ መ/ቤት ውስጥ በረዲት መስመር ሰራተኛነት 1ኛ አመልካች ሰኔ ወር 1991 ዓ.ም፣ 2ኛ አመልካች ጥቅምት ወር 1992 ዓ.ም፣ 3ኛ አመልካች ግንቦት ወር 1986 ዓ.ም ጀምሮ ተቀጥረን እያንዲንዲችን በወር ብር 3000 እየተከፈለን እያለ ተጠሪ የሰራተኞች ቅነሳ ምክንያት ሳይኖር በቀን 06/07/2011 ዓ.ም ከስራ እንደተቀነስን ገልጾ የስራ ውላችንን በህገ ወጥ መንገድ ያቋረጠ ስለሆነ ውዝፍ ደመወዛችን ተከፍል ወደ ስራ እንዱንመለስ ወይም በአዋጁ የተመለከቱት ክፍያዎች እንዱከፈለን ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።ተጠሪ በበኩለ አመልካቾች በተጠሪ መ/ቤት ውስጥ ሲሰሩ የነበረው በቀን ሰራተኛነት ሲሆን ሲሰሩት የነበረው ስራ የመ/ቤቱ ቋሚ ስራ ሆኖ እየተቆራረጠ ስራው በሚኖርበት ጊዜ ብቻ አልፍ አልፍ እየተጠሩ የሚሰሩ እንጂ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ባለመሆናቸው ከስራ መሰናበታቸው ህጋዊ ነው በማለት መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክር እና የቀረበለትን ማስረጃ መርምሮ አመልካቾች ስራ ሲኖር ብቻ የሚሰሩ የቀን ሰራተኞች በመሆናቸው ከአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ድንጋጌ አንፃር በተጠሪ ድርጅት በአንቀጽ 10 መሰረት ለተወሰነ ጊዜ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ የተቀጠሩ ሰራተኞች ናቸው ለማለት የማያስችል በመሆኑ አመልካቾች የተጠሪ ድርጅት ሰራተኞች ባለመሆናቸው በአዋጁ ሉያገኙ የሚገባቸው ክፍያ የለም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበዉ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አስቀርቦ ከመረመረ በኋላ አመልካቾች በተጠሪ ድርጅት በሚሰጣቸው የሥራ ትዕዛዝ የሚሰሩ እና ለሰሩበትም በየአስራ አምስት ቀን ክፍያ የሚከፈላቸው ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት በማስረጃ ተረጋግጧል፣ይህ ከሆነ ደግሞ በአዋጅ ቁ/1156/2011 አንቀጽ 4(1) መሰረት የስራ ውል ግንኙነት አለ በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር የስራ ውል ግንኙነቱ ለተወሰነ ጊዜ ነው ወይስ ላልተወሰነ ስራ ነው? ውለ የተቋረጠው በህግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ላይ አከራክሮ ውሳኔ እንዱሰጥበት ለስር ፍ/ቤት በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁ/ 343/1/ መሰረት መልሶታል።
ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን ችልቱም ቅሬታውን ተቀብል ካከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤት የሰማቸው ምስክሮችም ሆነ የተያያዙት ሰነድች አመልካቾች ስራ ሲኖር ከያለበት በስልክ ተጠርተው የስልክ መስመር ለማስገባት ወይም ብልሽት ሲገጥም መስላልና ላልች እቃዎችን ተሸክመው መጥተው የሚሰሩ ሆኖ የስራ ሰዓት ላይ የሚያደርገው ቁጥጥርና ክትትል አለመኖሩን ለስር ፍ/ቤት የቀረበው ፔሮል ‘Daily workers wage payment form’ በሚል የተዘጋጀ መክፍያ እንጂ ለመደበኛ ሰራተኞች የሚዘጋጅ ፔሮል አለመሆኑን ያስረዲል።ስለዚህ አመልካቾች ከተጠሪ ጋር ያላቸው የሥራ ውል ግንኙነት በአዋጅ ቁ/1156/2011 የሚሸፈን አይደለም፣ የስራ ውል ግንኙነት የላቸዉም በማለት የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር የወረዲ ፍ/ቤት ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ አጽንቷል።ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ ቀረበዉ በዚህ ላይ ነዉ።
አመልካቾች ይህ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፤በስር ወረዲ ፍ/ቤት ተጠሪ ባቀረበው ክርክር አመልካቾች ሲሰሩት የነበረው ስራ አልፍ አልፍ የሚሰራ ስራ ማለትም የተከሳሽ ቋሚ ስራ ሆኖ ስራዉ በሚኖርበት ጊዜ ብቻ ለመስራት የተቀጠሩ ናቸው በማለት መልስ መስጠቱ ሲታይ ከመነሻው አመልካቾች ከተጠሪ ጋር በአዋጅ ቁ/1156/2011 አንቀጽ 10(1)(ሰ) ድንጋጌ ላይ የተመለከተውን የሥራ ውል ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ የተደረገ የስራ ውል መኖሩን አምኖ መልስ ሰጥቶ እያለ ሰበር ችልቱ የስራ ውል የለም በማለት የሰጠው ውሳኔ ሉታረም ይገባል።በተጠሪ ድርጅት ከሚከፈለው ደመወዝ ላይ ግብር እየተቀነሰ እንዱሁም በስራ ሰዓት ሉያጋጥም ለሚችል አደጋ ተጠሪ የመድን ዋስትና እንዱኖረን ማድረጉ የተረጋገጠ ከመሆኑ አንፃር የስራ ውል ግንኙነት መኖሩን የሚያሳይ ነው።የስር ፍ/ቤት ቁጥጥርና ክትትል የለም በማለት የሰጠው ድምዲሜ በማስረጃ ያልተረጋገጠ በመሆኑ የስራ ግንኙነቱ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 1156/2011 አይሸፈንም መባለ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አመልክተዋል።
የአመልካቾች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካቾች ከተጠሪ ጋር የስራ ውል ግንኙነት የላቸውም መባለን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 10(1/ሰ) አንፃር ለማጣራት ጉዲዩ ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዟል።
ተጠሪ ድርጅት ባቀረበው መልስ አመልካቾች ሲሰሩበት የነበረው ስራ አልፍ አልፍ የሚሰራ ስራ ሆኖ የድርጅቱ ቋሚ ሥራ መደብ አይደለም፣ የስራ መደብ መጠሪያ የለውም፣ አመልካቾች ጋር የስራ ግንኙነት ስለላለን ስራ ሲኖር ብቻ በፈቃዲቸው መጥተው የሚሰሩና ድርጅቱም ማስገደድና መቆጣጠር የማይችል፣ እነሱም ስራ በላለ ጊዜ ለምን አልተጠራንም፣ለምን ደመወዝ አልተከፈለንም ማለት የማይችለ በመሆኑ የስራ ውል ግንኙነት የለም።የመስመር ዝርጋታ የሚሰሩ ቋሚ ባለሙያ ሰራተኞች አለ፣ አመልካቾች የመስመር ስራ ሉሰሩ አይችለም፣ አልሰሩም ከእውነት የራቀ አቤቱታ ነው።ተጠሪ ድርጅት የመድን ዋስትና የሚሰጠው በማንኛውም ሁኔታ ለሚሰራው ሰራተኛ የቀንም ይሁን መደበኛ ሰራተኞች በስራ ምክንያት ለሚመጣ አደጋ ዋስትና መውሰደ የሚጠበቅ ከህግ የመነጨ ግዳታ ሲሆን የስራ ውል አለ የሚያስብል አይደለም።በአዋጁ አንቀጽ 4 መስፈርት አሟልቶ በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት መኖሩ ያልተረጋገጠ ስለሆነ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ እንዱጸና በማለት ተከራክረዋል።አመልካቾች አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብ ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘበነዉ አመልካቾች ከተጠሪ ጋር የነበረን የስራ ዉል ከህግ አግባብ ዉጭ በተጠሪ አነሳሽነት ተቋርጧል በሚል ወደ ስራ እንዱመልሳቸዉ ወይም ተገቢዉን ክፍያ እንዱከፍላቸዉ የጠየቁት የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት በማድረግ ነዉ።አመልካች በበኩለ የስራ ግንኙነት እንደነበር ሳይክድ ግንኙነቱ ስራ ሲኖር ብቻ ሰርተዉ ክፍያ የሚከፈላቸዉ የቀን ሰራተኞች እንጂ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚሸፈን የስራ ግንኙነት ወይም ዉል የለንም በማለት ተከራክሯል።ጉዲዩን በየደረጃዉ የመረመሩት የስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃ አመዛዝነዉ ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚሸፈን ነዉ ወይም አይደለም በማለት የተለያየ አቋም ይዘዉ የሰጡትን ዉሳኔ በሰበር ስልጣኑ የመረመረዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ፍሬ ነገሩን መርምሮ አመልካቾች ከተጠሪ ጋር የነበራቸዉ የሥራ ግንኙነት አዋጁን መስፈርት የሚያሟላ አይደለም የሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል።የዚህ ሰበር ችልት ዉሳኔ የሚሻዉ አቢይ ነጥብ በአመልካቾች እና በተጠሪ መካከል በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚሸፈን የስራ ዉል ግንኙነት የለም ተብል በሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠዉ ዉሳኔ ላይ የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን የሚመለከት ነዉ።
ከመዝገቡ እንደሚታየዉ በአመልካቾችና እና በተጠሪ መካከል የስራ ዉል እንደነበር አላከራከረም።አከራካሪዉ ጉዲይ ስራ ዉለ በየትኛዉ ህግ ይሸፈናል የሚለዉ ነዉ።አንድ ሰራተኛ ወይም የሥራ ዉል በየትኛዉ ህግ ይተዲደራል የሚለዉን ጥያቄ ለመመለስ ሰራተኛ ማነዉ የሚለዉን መመርመር ግድ ይላል።ለዚህም የስራ ውል አመስራረትን አስመልከቶ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ የተደነገገውን በቀዲሚነት መመልከት ተገቢ ይሆናል።በመሰረቱ በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት ሁለ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚሸፈን አለመሆኑን የአዋጁ ተፈጻሚነት ወሰን የሚመለከተዉ አንቀጽ 3/2/ ድንጋጌ ያስገነዝባል።በልላ አገላለጽ በዚህ ድንጋጌ መሰረት በአዋጁ እንደማይሸፈኑ የተገለለ የስራ ዉል አይነቶች ካልሆነ በስተቀር በአሰሪዉና በሰራተኛዉ መካከል ዉል መኖሩ ከተረጋገጠ ዉለ የሚገዛዉ በዚሁ አዋጅ መሰረት እንደሆነ ይገመታል።በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የስራ ዉል የሚመሰረተዉ በአዋጁ አንቀጽ 4 ስር የተመለከቱት ሁኔታዎች ሲኖሩ ነዉ።በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ አንቀጽ 4/1/ ላይ፤
‹‹ ማንኛዉም ግለሰብ ደመወዝ እየተከፈለው በአሰሪው መሪነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ወይም የተወሰነ ስራ ለአሰሪው ለመስራት ቢስማማ በሁለቱ መካከል የስራ ውል ይመሰረታል››በማለት ይደነግጋል።ከዚህም መገንዘብ የሚቻለዉ የስራ ውል ማለት አንድ ሰዉ በአሰሪው የሚሰጠዉን ስራ ለመስራት እና ለሰራዉ ስራ ደግሞ ደመወዝ የሚከፈለዉ ሆኖ ዉለ ቆይታ እንደስራዉ ዓይነት በጊዜ ወይም በስራዉ መጠን በጊዜ ወይም በሥራ ዐይነት በመወሰን የሚያደርጉት ስምምነት ነዉ።በልላ በኩል ደግሞ የስራ ውል እንዳት መደረግ እንዲለበት እና ዉለ ሉይዛቸው ስለሚገባው ነገሮች በንኡስ ቁጥር 2 እና 3 ሥር ተመልክተዋል።በዚህም መሰረት የስራ ውለ ተዋዋይ ወገኖች የሚኖራቸው መብትና ግዳታ በማያጠራጥር አኳኋን በግልጽ ስምምነት መደረግ ያለበት ሲሆን ውለም የስራውን አይነትና ቦታ፣ለስራው የሚከፈለውን ደመወዝ መጠን፣ የስላቱን ዘዳ፣ የአከፊፈለን ሁኔታና ጊዜ እና ውለ ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ መያዝ እንደሚኖርበት ተመልክቷል።የስራ ውል በዚህ መልክ መደረግ የሚኖርበት ሲሆን በሕግ በተለየ አኳኋን ካልተደነገገ በቀር የተለየ ፍርም የላለው ስለመሆኑ በአንቀጽ አምስት ስር ተመላክቷል።ስለሆነም የስራ ውል የተለየ ፍርም እንዱኖረዉ ሕጉ ስላላስገደደ በማንኛውም አይነት ሁኔታ ሉቋቋም እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ በአመልካቾችና በተጠሪ መካከል የነበረዉ የስራ ግንኙነት ምን ይመስላል የሚለዉን ጉዲይ የመረመሩት የሥር ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ፍሬ ነገር የስልክ መስመር ዝርጋታ ወይም ብልሽት ጥገና ስራ ሲኖር እየተጠሩ የጉልበት ስራ ማለትም ምሶሶ እና ላልች መገልገያ እቃዎችን ከቦታ ቦታ መሸከም፤ጉድጓድ መቆፈርና ላልች ተዛማጅ ስራዎችን ማከናወን፤በሰሩት ስራ ልክ በየሁለት ሳምንቱ ከፍያ የሚፈጸምላቸዉ ስለመሆኑና የሚሰሩትም ሆነ ከፍያ የሚፈጸምላቸዉ ስራ ሲኖር ብቻ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ።በዚህ ላይ በግራ ቀኙ መካከል መካካድ የለም።ከላይ እንደተገለጸዉ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ መሰረት በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ዉል በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ተቋቁሟል ለማለት የሚቻለዉ ሰራተኛዉ ስራ መስራቱ እና ደመወዝ ወይም የሥራ ዋጋ መከፈለ ብቻ ሳይሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአሰሪዉ መሪነት የሚሰራ ሰራተኛ መሆኑም ጭምር መረጋገጥ እንዲለለበት ያሣያል።በዚህ ረገድ ይግባኝ ሰሚዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሰሪዉ በሚሰጣቸዉ ስራ ልክ ሰርተዉ በዚህም ልክ የሚከፈላቸዉ ስለመሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር መሰረት በማድረግና ከህጉ ጋር በማዛመድ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት አላቸዉ ነገር ግን የዉለ ዓይነት እና ዉለ የተቋረጠበትን ምክንያት ህጋዊነት የሥር ፍርድ ቤት እንዱመረምር በሚል መልሶለታል።
የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ይህን ዉሳኔ ለመሻር መሰረት ያደረገዉ አመልካቾች ስራ ሲኖር ብቻ የሚጠሩ ስለሆነ በአሰሪዉ በኩል ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ አይደለም፣ከስራ ለመቅረት ፈቃድ አይጠይቁም፤ረዲት የመስመር ሰራተኛ የሚባል የሥራ መደብ የለዉም፤መደበኛ ፔሮል የላቸዉም፤የበጀት ድጋፍ የለዉም እናም መመዘኛዉን አሟልተዉ በአሰሪዉ ስለመቀጠራቸዉ በምክሮቻቸዉ አላረጋገጡም፤በመቆጣጠር ረገድ ተጠሪ የነበረዉ ተግባር አልተረጋገጠም በማለት የቀን ሰራተኛ እንጂ የስራ ዉል ግንኙነት አላቸዉ የሚባል አይደለም በማለት ነዉ።ከክርክሩ እንደተገነዘብነዉ ስራዉ የድርጅቱ ቋሚ ስራ መሆኑ አከረካሪ አለመሆኑን ነገር ግን አመልካቾች ስራዉን የሚሰሩት አልፍ አልፍ የመስመር ዝርጋታ ወይም ጥገና ሲኖር ብቻ በመሆኑ ቋሚ የስራ መደብ አለመኖሩ መሰረታዊ መመዘኛ ሆኖ መዉሰደ ተገቢ አለመሆኑን ነዉ።ላላዉ አሰሪዉ ቁጥጥር እና ክትትል አያደርግም የሚለዉ የሰበር ችልቱ ዉሳኔ ምክንያት አግባብነት ሲታይ ቁጥጥርና ክትትል የሚለዉ ልክ እንደመደበኛ ሰራተኛ በማየት ከሆነ ስህተት ነዉ።ምክንያቱም በዚህ ጉዲይ የተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር የሚያሳየን ስራዉ አልፍ አልፍ የሚሰራ ስራ በመሆኑና አመልካቾችም በአሰሪዉ የተሰጣቸዉን ስራ ሰርተዉ በሰሩት ስራ ልክ በየአሰራ አምስት ቀን ደመወዝ የሚከፈላቸዉ በመሆኑ አሰሪዉ የስራዉን ዓይነትና መጠን በመወስንና በመምራት ረገድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ቁጥጥር የሚያደርግ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።ከዚህም በተጨማሪ ሰበር ችልቱ ለዉሳኔ መሰረት ያደረጋቸዉ ምክንያቶች ረዲት የመስመር ሰራተኛ የሚባል የሥራ መደብ የለዉም፤መደበኛ ፔሮል የላቸዉም፤የበጀት ድጋፍ የለዉም የሚለት በዋናነት የፍሬ ነገር ጉዲይ እና የማስረጃ ምዘና ላይ ተመሰረተ መሆኑን ነዉ።
እንደሚታወቀዉ የሰበር ሰሚ ችልት የተቋቋመበት ዋነኛ ዓላማ አንድ ወጥ የህግ አተረጓጎም እንዱኖር እና የዉሳኔዎችን ተገማችነት ለማረጋገጥ ነዉ።በፋዳራልም ሆነ በክልል ፍርድ ቤቶች ሰበር ሰሚ ችልት እንዱቋቋም ያስፈለገዉ በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 80(3)(ሀ ና ለ) ላይ እንደተደነገገዉ በመጨረሻ ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ለማረም ነዉ።ህገ መንግስቱን ተከትል የወጣዉ የፍደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 እንዱሁም ይህንን አዋጅ የተካዉ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 4/1/ እና 10 ድንጋጌዎች የሰበር ስልጣን የሚመለከቱ ሲሆን ሰበር ችልቱ ማስረጃ ማጣራትና መመዘን ሥልጣን እንደላለው ያስገነዝባለ።የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 223/2007 አንቀጽ 17 ተመሳሳይ ዓላማ እና ይዘት እንዲለዉ ግልጽ ነዉ።ስለዚህም የሰበር ችልት ዋና ተግባር የፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ተገማች እና ወጥ የህግ አተረጓጎም እና አተገባበር እንዱኖር ማድረግ በመሆኑ ማስረጃ የመመርመርና የመመዘን ጉዲይ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።በእርግጥ ማስረጃ ለመስማትና ለመመዘን ሥልጣን የለውም ማለት ግን ከማስረጃ ጋር የተያያዘ ጭብጥ የሰበር አቤቱታ አይመለከትም ማለት አይደለም።ማስረጃ ለመመዘን ሥልጣን የተሰጠው ፍርድ ቤት ማስረጃ ሲቀበል የተከራካሪዎችን እኩል የመደመጥ መብት ካላከበረ፣ የማስረዲት ሸክም (burden of production) የማን ነው የሚለውን ካልለየ፣ የማስረጃ ተቀባይነትና ተገቢነት ላይ መከተል የሚገባውን ሥርዓት ካልተከተለ፣ በምዘና ጊዜ የሁለንም ተከራካሪዎች ማስረጃ አብሮ ካልመዘነ፣ የተለየ የማስረዲት ደረጃ (standard of proof) የሚጠይቁ ጉዲዮችን በሚጠይቀው ደረጃ ልክ መረጋገጡን ካላሳየ እና በመሰረታዊ ሕግ ሆነ በሥነ-ሥርዓት ሕግ ያለትን የማስረጃ ሕጎችና መርሆች ካላከበረ ጉዲዩ የማስረጃ ምዘና ሳይሆን የሕግ አተረጓጎም ስህተትና ፍርድ ቤት ያለበትን ኃላፉነት አለመወጣት ስለሚሆን የሰበር ሰሚ ችልቱ የሚመለከተው ጉዲይ ይሆናል።
በተያዘዉ ጉዲይ ከላይ እንደተገለጸዉ የስራ ዉል በጽሁፍ ወይም በቃል ላደረግ ይችላል።ዉል መኖሩን ለማስረዲት የሚቀርበዉ ማስረጃ ዓይነትም እንደነገሩ ሁኔታ ሰነድ ወይም ምስክር ላሆን ይቻላል።አመልካቾች ከተጠሪ ጋር የነበራቸዉ ግንኙነት አሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት መሆኑን ለማስረዲት ያቀረቡት ማስረጃ የደመወዝ ክፍያ ፔሮል፣ በድርጅቱ የተሰጣቸዉ መታወቂያ እና የሰዉ ምስክር ሲሆን ተጠሪም በበኩለ ማስተባበያ ክርክር እና ማስረጃ ማቅረቡን መዝገቡ ያሣያል።እነዚህን ማስረጃዎች የመመርመር እና ፍሬ ነገር የማረጋገጥ ሃላፉነትና ስልጣን ያለዉ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ማስረጃዎቹን ይዘት መመርምሮና አመዛዝኖ ግንኙነታቸዉ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት መሆኑን አረጋግጧል።አመልካቾች እንደ ክርክራቸዉ አቀራረብ በዚህ ልክ ካስረደ ከተጠሪ የሚጠበቀዉ የስራ ዉለ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ የማይሸፈንበትን ምክንያት በአዋጅ አንቀጽ 3/2/ ስር ከተደነገጉት ማግለያ ሁኔታዎች በአንደ ወይም በልላዉ የሚጠቃለል መሆኑን ማስረዲት ነዉ።ይህ ስለመሆኑ ደግሞ በተጠሪ በኩል የቀረበ ክርክርም ሆነ ማስረጃ ስለመቅረቡ መዝገቡ አያሣይም።በመሆኑም በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ማስረጃ ተመዝኖ የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር ጉዲይ ይህ ሰበር ችልት የማይቀበልበት ምክንያት የለም።ይህ ከሆነ ደግሞ ስራዉ አልፍ አልፍ የሚሰራ ስራ በመሆኑም ሆነ ደመወዝ በየአስራ አምስት ቀን መከፈለ እንዱሁም ለስራዉ ቋሚ የስራ መደብ አለመኖሩ ብቻ ግንኙነታቸዉ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚሸፈን አይደለም ሉያሰኝ አይችልም።
ሲጠቃለል በክርክሩ የተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር አመልካቾች የሚሰሩት ስራ የተጠሪ ቋሚ ስራ መሆኑ፣ስራዉ አልፍ አልፍ የሚሰራ እና አመልካቾችም ስራዉ ሲኖር ተጠርተዉ ለሰሩት ስራ ደመወዝ በየአስራ አምስት ቀን የሚከፈላቸዉ መሆኑን ያሳያል።ተጠሪ በበኩለ አመልካቾች ቀን ሰራተኞች ናቸዉ ብል ቢከራከርም የሥራ ዉል መኖር የሚወሰነዉ በስራዉ ላይ እንጂ በቆይታዉ ጊዜ አለመሆኑን የህጉ ይዘት ያስገነዝባል።ስለሆነም በአመልካቾች እና በተጠሪ መካከል ያለዉ የስራ ዉል በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚሸፈን ነዉ በማለት ይግባኝ ሰሚዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዲሜ በማስረጃ የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር እና ህጉን ያገናዘበ ሆኖ እያለ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የፍሬ ነገር ክርክር እና ማስረጃ ምዘና ጉዲይ ላይ ተመስርቶ ዉሳኔዉን መሻሩ በህግ ለሰበር ሰሚ ችልት ከተሰጠዉ ስልጣን ዉጪ በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ ነዉ ብለናል።በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/አማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/7 ላይ በቀን 14/05/2013ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
2ኛ/የደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/47249 ላይ በቀን 25/02/2013ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ ጸንቷል።ይጻፍ 3ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.