የስራ ቅጥሩ በሚመለከተዉ አካል ይሁንታ የሚፈጸም መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ አሰሪ ከዉጭ አገር ሰራተኛ ጋር በሚያደርገዉ ውል ውለ ጸንቶ የሚቆይበትን ጊዜ በተመለከተ ተስማምተዉ የሚያስቀምጡት የጊዜ ገደብ ህጋዊ ዉጤት ያለዉ በመሆኑ አሰሪዉ የዉለ ጊዜ ሲያበቃ ዉለን አቋርጦ ሰራተኛዉን የማሰናበት መብት የሚኖረው አይካ አዱስ ጨርቃ ጨርቅ ኢንቨስትመንት ግሩፔ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አቶ ኢብራሑም አይድግደ
No summary available.
ቀን፡-30/02/2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አይካ አዱስ ጨርቃ ጨርቅ ኢንቨስትመንት ግሩፔ ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ጠበቃ ንጉሴ እሰየው - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኢብራሑም አይድግደ - አልቀረቡም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የስራ ዉል መቋረጥ የሚመለከት ነዉ።ክርክሩ የተጀመረው ኦሮሚያ ክልል በፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።ከመዝገብ እንደሚታየዉ ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ውስጥ የምግብ ባለሙያ ሁኜ በቀን 28/04/2000 ዓ.ም በወር 2500 ድላር ደመወዝ ተቀጥሬ እየሰራሁ እያለ በቀን 22/08/2011 ዓ.ም ያለጥፊት ከህግ ውጪ ውልህን ጨርሰሀል በማለት ከስራዬ አሰናብቶኛል፣ስለዚህ ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ ተብል የአገልግልት ክፍያ፣የካሳ ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ፣ ክፍያ የዘገየበት እና ለአውሮፕላን ቲኬት በአጠቃላይ 41,264.33 ድላር ወይም በኢትዮጵያ ብር 1,190,477.44 ከ10% የጠበቃ አበል ጋር እንዱከፈልኝ እንዱወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።አመልካች በበኩለ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገው የስራ ስምምነት ለተወሰነ ጊዜ ለአንድ አመት የሚቆይ ሆኖ ውለ እንደተጠናቀቀ ወዱያውኑ ሉቋረጥ እንደሚችል ተስማምተናል፣ተጠሪ ተቀጥሮ ሲሰራበት የቆየው የስራ መደብ ላይ የኢትዮጵያ ዜጋ በብቃት ሉሰሩ የሚችለት ነው።ለአንድ የውጪ ዜጋ ደግሞ ፈቃድ የሚሰጠው የሀገር ውስጥ ሰራተኞች ግንዛቤ እና ልምድ እስከሚያገኙ ብቻ ነው።ስለዚህ የሀገር ውስጥ ዜጎች መስራት እየቻለ የውጭ ዜጋ መስራት የለበትም።ውላችን ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ ሲሆን የውጭ ዜጋ ሆኖ ተጠሪ ላልተወሰነ ጊዜ መስራቱ ከህግ ውጪ በመሆኑ ውለ የተቋረጠው በህግ አግባብ በመሆኑ የተጠየቀው ክፍያ ሉከፈለው አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃ መርምሮ አመልካች እና ተጠሪ የተፈራረሙት የስራ ውል ከ23/04/2010 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት ጸንቶ የሚቆይ መሆኑን የሚያሳይ ቢሆንም በአዋጅ ቁ/377/96 አንቀጽ 10 ስር ከተገለጹት ምክንያቶች ውስጥ በየትኛው ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ የተገለጸ ነገር የለም።ውለ ለተወሰነ ጊዜ ስለተባለ ብቻ የህጉን መስፈርት አሟልቷል የሚያስብል አይደለም፣ተጠሪ ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ስራ ሲሰራ እንደቆየ የሚያሳይ ማስረጃ አመልካች አላቀረበም።ተጠሪ ተቀጥሮ ሲሰራበት የቆየው ስራ ደግሞ በባህሪው በቀጣይነት የሚሰራ ስራ በመሆኑ እና የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.43160 ላይ በሰጠው ዉሳኔ በአንቀጽ 10 ስር ተዘርዝረው ካለት ስራዎች ውጭ ከሆነ ይህ ውል የተወሰነ ጊዜ ነው ቢባል እንኳን የተወሰነ ጊዜ ዉል ላሆን አይችልም በማለት አስገዲጅ ውሳኔ ሰጥቷል።የውጭ ሀገር ዜጋ ስለሆነ ውለ የተወሰነ ጊዜ ነው የሚል ህግ የለም፣ስለዚህ የስራ ውለ ላልተወሰነ ጊዜ ነው፣አመልካች የውለ ጊዜ ስለተጠናቀቀ በማለት ውለን ማቋረጡ የህግ መሰረት የለውም፣ስንብቱ ከህግ ውጭ ነው በማለት የተጠየቁ ክፍያዎች ለተጠሪ እንዱከፈል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ ጉዲዩ አያስቀርብም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዟል።አመልካች ለኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ችልቱም ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኝ ክርክር ሰምቶ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለዉም በማለት አጽንቷል።ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ነዉ።
አመልካች ያቀረበው አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፤ዉለ ለተወሰነ ጊዜ ከውጭ ሀገር ዜጋ ጋር የተደረገ የቅጥር ውል የሚል ሲሆን ይህንን የሚያረጋግጥ በስር ፍ/ቤት ሰነደ ቀርቦ እያለ እና በቅጥር ውለ አንቀጽ 11(ሐ) መሰረት ከተዋዋይ ወገኖች መካከል አንደ ወገን ውለን በማንኛውም ጊዜ መቋረጥ እንደሚቻል ተመልክቷል፣በኢንቨስትመንት ደንብ ቁጥር 474/2012 አንቀጽ 19(1) መሰረት የውጭ ሀገር ዜጎችን የሚቀጥር ባለሀብት ለኢትዮጵያዊያን አስፈላጊውን የስራ ላይ ስልጠና እንዱሰጥ እና እውቀት እንዱተላለፍ በማድረግ የውጭ ዜጋ ተቀጣሪዎች በኢትዮጵያዊያን እንዱተኩ የማድረግ ግዳታ ያለበት ሲሆን በዚሁ መሰረት አመልካች የተጠሪ የስራ ውል በውላቸው መሰረት እንዱቋረጥ ማድረጉ ህጋዊ ስንብት ነው።ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ለ11 ዓመት የሰራው በጊዜያዊነት የስራ ቅጥር ውለ እየታደሰ እና የስራ ፍቃደም እንዱታደስ በማድረግ ነው።ተጠሪ በቋሚነት መቀጠሩን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አላቀረበም።ስለዚህ ለዜጎች ቅድሚያ የሥራ ዕድል ለመስጠት ሲባል በህጋዊ መንገድ የተቋረጠ ዉል ላይ ብር 1,190,477.44 እንዱከፈል የተወሰነው መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ውሳኔው እንዱሻር በማለት አመልክተዋል።
የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ ቅጥሩ ለተወሰነ ጊዜ መሆኑን የቅጥር ውለ ላይ ከመመልከቱ አንፃር የስር ፍ/ቤት ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የስራ ውል ነው በሚል መነሻ ስንብቱ ህገወጥ ነው ማለቱን አግባብነት ለማጣራት ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዟል።
ተጠሪ ባቀረበው መልስ በውላችን መሰረት አመልካች በቅድሚያ የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ እንዱሁም የውለ ቀን ሳይጠናቀቅ ውለን ማቋረጡ ስንብቱን ህገ ወጥ ያደርጋል። በተጠሪ ድርጅት ላልተወሰነ ጊዜ ተቀጥሬ ለ11 ዓመታት ሲሰራ መቆየቴ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጧል።አንድ ሰራተኛ ለተወሰነ ወይስ ላልተወሰነ ጊዜ ነው የተቀጠረው ለማለት የሚቻለው ሰራተኛው የተቀጠረበት ስራ ባህሪይ እንጂ በውለ ላይ ለጊዜያዊ ስራ ተቀጥረዋል ስለተባለ ብቻ እንደማይሆን ሰበር ችልቱ በመ/ቁ.43160 ላይ አስገዲጅ ውሳኔ ሰጥቷል፤ አመልካች ስራው እንዲልተጠናቀቀ እና በተጠሪ ስራ ቦታ ላላ ሰው መቅጠሩ ተጠሪ ላልተወሰነ ስራ እንደተቀጠረ ያረጋግጣል።ስለዚህ በድርጅቱ ለተከታታይ ለ11 ዓመት አገልግዬ ያለአገልግልት ክፍያ፣ ያለማስጠንቀቂያ፣ የቲኬት ክፍያ እና ያለምንም ክፍያ ያሰናበተኝ ስለሆነ የስር ፍ/ቤቶች ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ በማለት የሰጡት ውሳኔ ስህተት የላለበት በመሆኑ እንዱፀና በማለት ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እና ክርክሩን አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረዉ የስራ ዉል የተቋረጠዉ በአመልካች አነሳሽነት መሆኑ አላከራከረም።አመልካች አጥብቆ የምከራከረዉ ተጠሪ የዉጭ ሀገር ዜጋ በመሆኑና ዉለም ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ ስለሆነ ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ ልባል አይገባም በማለት ነዉ።
በመሰረቱ የስራ ዉል እንደማናቸዉም ዉል የግራ ቀኙን መብትና ግዳታ በሚመለከት በአሰሪዉ እና በሰራተኛዉ ነጻ ፈቃድና ስምምነት የሚደረግ ዉል ቢሆንም በህግ የተጠበቁ ዝቅተኛ የሥራ ሁኔታዎችን የሚቀንስ ወይም የሚቃረን ላሆን አይችልም።የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር1156/2011 አንቀጽ4 ድንጋጌ ስር የተመለከቱት ሁኔታዎች ይህንኑ ያስገነዝባለ።የስራ ዉል አይነት በተመለከለተ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ ላደረግ እንደሚችል የአዋጁ አንቀጽ 4/1/ ድንጋጌ ይዘት ያሣያል።ከዚህም የምንገዘነበዉ የስራ ዉለ ቆይታ በጊዜ ወይም እንደስራዉ ባህርይ በተዋዋዮች ሉወሰን የሚችል ስለመሆኑ ነዉ።ይሁን እንጂ የሰራተኛዉን የስራ ዋስትና እና የመደራደር አቅም ዉስንነት ከግምት በማስግባት የስራ ዉለን ቆይታ ጊዜ ወይም ባህርይ ለመወሰን የሚረደ ሁኔታዎች በህግ ተደንግጎ እናገኛለን።በዚህ ረገድ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ አንቀጽ 9 እና 10 ድንጋጌዎች እንደሚያሣዩን በመርህ ደረጃ የስራ ዉል ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ የሚገመት ሲሆን በተወሰኑ ሁኔታዎች እና ምክንያቶች ብቻ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ ተብል የሥራ ዉል ላደረግ የሚችል መሆኑን ነዉ።ስለዚህም አሰሪዉ እና ሰራተኛዉ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ በሚል መስማማት የሚችለ ቢሆንም ጉዲዩ አከራካሪ ሆኖ ከቀረበ ዉለ ከህጉ ጋር የሚጣጣም መሆን አለመሆኑ ሉመመርመር ይገባል።በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ችልት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ክርክር ዉሳኔ የሰጠባቸዉ ጉዲዮች ላይ እንዲመለካተዉ የሥራ ዉለ ቆይታ ጊዜ አስመልከቶ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ በሚል መዋዋላቸዉ ብቻ ሳይሆን ዉለ ከስራዉ ባህርይ ጋር ተገናዘቦ መታየት እንዲለበት ያስገነዝባል።ሰበር መ/ቁ11924፣መ/ቁ/ 25765፣መ/ቁ.43160 እና ላልች መሰል መዝገቦችን ማየት ይቻላል።
በተያዘዉ ጉዲይ በግራቀኙ መካከል የተደረገዉ ዉል ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ መሆኑን እና በየጊዜዉ እየታደሰ መቆየቱንና ለመጨረሻ ጊዜም በ23/04/2010ዓ.ም ለአንድ ዓመት የተራዘመ መሆኑን ዉለ የተቋረጠዉ በ22/08/2011ዓ.ም ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት አረጋግጧል።ፍርድ ቤቱም ዉለ ለተወሰነ ጊዜ ነዉ ቢባልም የስራዉ ባሕርይ ሲታይ የድርጅቱ ቋሚ ወይም ቀጣይነት ያለዉ ስራ ነዉ በሚል ምክንያት ሰበር ችልቱ በመ/ቁ/43160 ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ ድጋፍ በማድረግ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይቆጠራል በማለት ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ የሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል።ከክርክሩ እንደሚታየዉ ተጠሪ ለ11ዓመት በቋሚነት አገልግያለዉ በሚል ምክንያት የሥራ ዉለ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይቆጠራል በማለት የሚከራከር ቢሆንም ዉለ በየጊዜዉ እየታደሰ የቆየ መሆኑ በተጠሪም አልተካደም።በእርግጥ የስራ ዉል ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ የተደረገ ነዉ የሚያሰኘዉ የዉለ ይዘት ብቻ ሳይሆን በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 10 ስር የተዘረዘሩት ምክንያቶች ወይም ሁኔታዎች መኖራቸዉ መረጋገጥ እንዲለበት የህጉ አገላለጽ እና ይህ ሰበር ችልት በመ/ እና ላልች መሰል መዝገቦች ላይ የሰጠዉ ዉሳኔ ያስገነዝባል።ይሁንና የሰበር ችልቱ ዉሳኔ በዚህ መዝገብ ከቀረበዉ ክርክር አኳያ ተፈጻሚነት አለዉ ወይ የሚለዉ ከጉዲዩ ባህርይ አንጻር መመርመር አለበት።
ከመዝገቡ እንደሚታየዉ ተጠሪ የተቀጠረበት የሥራ መደብ የድርጅቱ ቋሚ ወይም ቀጣይነት ያለዉ ስራ አይደለም የሚል ክርክር የለዉም።የአመልካች ዋነኛ መከራከሪያ ነጥብ ተጠሪ ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠረዉ እና ዉለ እየታደሰ የቆየዉ የዉጭ ሀገር ዜጋ በመሆኑ በቋሚነት ሉቀጠር አይችልም የሚል ነዉ።ተጠሪ የዉጭ ሀገር ዜጋ መሆኑ አከራካሪ እስካልሆነ ድረስ የሥራ ዉለን ዓይነት በመወሰን ረገድ የሚኖረዉ ዉጤት ከአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ እና ላልች አግባብነት ካላቸዉ ህጎች ጋር ተገናዝቦ መታየት አለበት።
የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 የዉጭ አገር ሰራተኞች የሚቀጠሩበትን ሁኔታ የሚደነግግ ሲሆን በዚህም መሰረት የዉጭ አገር ዜጋ በማናቸዉም የስራ መስክ ተቀጥሮ ለመስራት የሚችለዉ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዲዮች ሚኒስቴር ወይም ክልል ሲሆን የክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዲዮች ቢሮ የሚሰጠዉን የስራ ፍቃድ ሲያገኝ እና የስራ ፍቃድ የሚሰጠዉም በአንድ የስራ መስክ ለማገልገል እስከ ሦስት ዓመት ሲሆን በየዓመቱ መታደስ ያለበት ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 174 ላይ ከተመለከተዉ ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።በዚህ ረገድ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ተመሳሳይ ይዘት ያለዉ መሆኑን ልብ ይለዋል።የአዋጁን አንቀጽ 171/1/ሰ እና 176 መመልከት ይቻላል።የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻልን አንደ ዓላማዉ ያደረገዉ (መግቢያዉን መመልከት ይቻላል) የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 769/2004 በአንቀጽ 37(2)፣ በዚህ አዋጅ የተተካዉ የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 280/94 አንቀጽ 36(2) እንዱሁም አሁን በስራ ላይ ያለዉ የእንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180/2012 አንቀጽ 22(4) የዉጭ ዜጎችን የሚቀጥር ባለሀብት ለኢትዮጵያዉያን አስፈላጊዉ ስልጠና እንዱዘጋጅ እና እንዱሰጥ በማድረግ በተወሰነ ጊዜ ዉስጥ የዉጭ አገር ዜጋ ሰራተኞችን እንዱተኩ ማድረግ እንዲለበት ይደነግጋለ። ቀደም ሲል በስራ ላይ የነበሩት ሁለቱ የእንቨስትመንት አዋጆችም ሆነ አሁን በስራ ላይ ያለዉ የእንቨስትመንት አዋጅ ዓላማዎች ናቸዉ ተብለዉ ከተዘረዘሩት ዉስጥ አንደ ለኢትዮጵያዉያን ሰፉ እና ጥራት ያለዉ የስራ ዕድል መፍጠር እና ለአገሪቱ ዕድገት የሚያስፈልገዉን የዕዉቀት፣ ክህልት እና ቴክኖልጂ ሽግግር ማሳለጥ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 280/94 አንቀጽ 4(6)፣ በአዋጅ ቁጥር 769/2004 እና አዋጅ ቁጥር 1180/2012 አንቀጽ 5 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለዉ በአገራችን የግል እንቨስትመንትን ማስፊፊት አስፈላጊ ከሆነባቸዉ ምክንያቶች ዉስጥ አንደ መንግስት ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በአገሪቱ ዉስጥ በማንኛዉም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራት እና ለመተዲደሪያ የመስራት መብት ለመተግበር በተለይም ሰፉ የሥራ እድል ለመፍጠር የሚያስችል ፖሉሲ መከተል እንዲለበት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 41 /1/ እና 4) በተጣለበት ግዳታ መሰረት ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ለዜጎች የስራ ዋስትና ማረጋገጥ መሆኑን ነዉ።አንድ ዓላማ ያላቸዉ የተለያዩ ህጎች በሚኖርበት ጊዜ በተለያዩ የህግ ክፍልች በሚገኙ ድንጋጌዎች ተደጋጋፉ ሆነዉ የጋራ ዓላማ የሚያሳኩበትን የህግ ትርጉም መሻት የህግ ባለሙያዎች ሉመርጡት የሚገባ የህግ አተረጓጓም ዘይቤን መከተል በህግ አተረጓጎም ዕዉቅና ከተሰጣቸዉ መርሆዎች አንደ ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም በሰ/መ/ ላይ በሰጠዉ የህግ ትርጉም ለዚህ መርህ ዕዉቅና ሰጥቶታል።
ከዉጭ አገር ዜጎች የቅጥር ሁኔታ ጋር በተያያዘ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 174 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ዓላማዉ ምን እንደሆነ በግልጽ የሚያመላክት ድንጋጌ ባይኖርም ከላይ ከተመለከቱት የእንቨስትመንት ህጎች ድንጋጌዎች እንዱሁም በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት መሰረት መንግስት ለእራሱ ዜጎች የስራ ዕድል ለማመቻቸት ካለበት ግዳታ አንፃር ሲታይ በአዋጁ አንቀጽ 174 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ አጠቃላይ ዓላማ የግል ድርጅቶች የዉጭ አገር ዜጎችን የሚቀጥሩት ለስራ ዕድል ፈጠራ ዓላማ ሳይሆን ለድርጅቱ ስራ አስፈላጊነታቸዉ ከታመነበት ብቻ መሆኑን ነዉ።ከዚህም በተጨማሪ የዉጭ ሀገር ዜጋ በሀገር ዉስጥ ስራ እንዱቀጠር የሚፈለገዉ በዘርፈ በቂ ባለሙያ በሀገር ዉስጥ ሳይኖር ወይም የእዉቀትና ቴክኖልጂ ሽግግር ለማድረግ ዓላማ በመያዝ ስለመሆኑ የኢንቨስትመንት አዋጅ እና አዋጁን ተከትል የወጣዉ ደንብ የሚያስገነዝቡን ጉዲይ ነዉ።ደንብ ቁጥር 474/2012 አንቀጽ 19/1/ይመለከታል።በልላ በኩል ከላይ እንደተገለጸዉ፣ የስራ ቅጥር ዉል ጊዜ ጋር በተያያዘ በአዋጁ አንቀጽ 9 እና 10 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ የዜጎችን የስራ ዋስትና የማረጋገጥ ዓላማ ያለዉ ነዉ።የስራ ዋስትና ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ የሚታይ በመሆኑም በዚህ መብት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን እድል ይፈጥራል ተብል ይታሰባል።
በመሆኑም የስራ ቅጥሩ በሚመለከተዉ አካል ይሁንታ የሚፈጸም መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ አሰሪ ከዉጭ አገር ሰራተኛ ጋር በሚያደርገዉ ዉል ዉለ ጸንቶ የሚቆይበትን ጊዜ በተመለከተ ተስማምተዉ የሚያስቀምጡት የጊዜ ገደብ ህጋዊ ዉጤት ያለዉ በመሆኑ አሰሪዉ የዉለ ጊዜ ሲያበቃ ዉለን አቋርጦ ሰራተኛዉን የማሰናበት መብት ይኖረዋል።በዚህ ረገድ በተመሳሳይ ክርክር ይህ ሰበር ችልት በመ/ቁ/194630 ላይ (ያልታተመ) የሰጠዉ ዉሳኔም ተመሳሳይ አቋም የተወሰደበት መሆኑን ያሣያል።
በመሆኑም በተያዘዉ ጉዲይ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገዉ የስራ ዉል በጊዜያዊ ቅጥር ላይ የተመሰረተ ሆኖ በየጊዜዉ እየታደሰ ተጠሪ ለአስራ አንድ ዓመታት በአመልካች ዘንድ ሲሰራ የቆየ መሆኑ ያላከራከረ ሲሆን፣ አመልካች ዉለ ከተጠሪ ጋር እንዱቀጥል ተስማምቶ ዉለ ታድሶ በመካከላቸዉ ግንኙነቱ እንዱቀጥል ለማድረግ የስራ ፈቃድ እንዱታደስ ያስፈልጋል።ዉጪ ሀገር ዜጋ የስራ ፈቃድ የሚታደሰዉ በአሰሪዉ ጥያቄ መነሻ መሆኑን አዋጁ ያሳያል።በአዋጁ አንቀጽ 174(2-4) ላይ በተመለከተዉ ድንጋጌ መሰረት የስራ እና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስቴር (በክልል ሲሆን ቢሮ) የሚሰጠዉ የስራ ፍቃድ እና አድሳት ማንኛዉም የግል ድርጅት ያለሚኒስቴሩ (ቢሮዉ) ዕዉቅና እና ይሁንታ የዉጭ አገር ዜጎችን እንዲይቀጥር ለመከላከል ታስቦ የተቀረጸ ስለመሆኑ ከድንጋጌዉ መገንዘብ ይቻላል።በመሆኑም አሰሪዉ ድርጅት ከዉጭ አገር ዜጋ ጋር በጊዜያዊነት ያደረገዉ የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት እንዱቀጥል የስራ ፈቃድ አስፈላጊ በመሆኑ ለሰራተኛዉ የስራ ፍቃድ በሚመለከተዉ አካል አለመታደሱም አመልካች የቅጥር ዉለ እንዱያራዝም የሚያስፈልግበት ምክንያት አለመኖሩን የሚያሣይ ነዉ።
በአጠቃላይ በየደረጃዉ ያለት ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን ከፍ ሲል በዝርዝር ከተመለከተዉ አንፃር በማየት ስንበቱ ህጋዊ ነዉ ማለት ሲገባቸዉ በአዋጁ አንቀጽ 9 እና 10 ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ለዉጭ አገር ዜጋ ሰራተኛም ጭምር ተፈፃሚ እንደሚሆኑ በመዉሰድ በግራ ቀኝ መካከል ለተወሰነ ጊዜ የተደረገን የስራ ዉል ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይገመታል በሚል ሃሳብ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበዉን ክርክር ዉድቅ በማድረግ ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ በማለት የሰጡት ዉሳኔ ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸዉን ድንጋጌዎቹ ዓይነተኛ ዓላማ እና ተጠሪ የዉጭ ሀገር ዜጋ ከመሆኑ አኳያ በህጉ የተፈቀደለትን መሰረት በማድረግ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ስራ ለመስራት ግራ ቀኙ ያደረጉት ስምምነት ተገዥ ሉሆኑ ይገባል የሚለዉን የዉል አጠቃላይ መርህ ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ስንበቱ ህጋዊ ነዉ ከተባለ ለተጠሪ የሚከፈል ክፍያ አለ ወይ የሚለዉንም መርመርናል።በዚህ ረገድ ከስር መዝገብ እንደሚታዉ ተጠሪ ስንበቱ ህገ ወጥ ነዉ በሚል ምክንያት የስንብት፣ካሳ፣የማስጠንቀቂያ ጊዜ እና ክፍያ የዘገየበት የሚል የጠየቃቸዉ ክፍያዎች ሲሆኑ በተጨማሪም ወደ ሀገር ቤት የሚመለስበት የትኬት ክፍያ ብር 431.053(አራት መቶ ሰላሳ አንድ ከዜሮ ሃምሳ ሶስት ሳንቲም ድላር) አመልካቹ እንድከፍል ጠይቋል።የሥር ፍርድ ቤትም ይህንኑ በመቀበል ዉሳኔ ሰጥቷል።ከላይ እንደተመለከተዉ በዚህ ሰበር ችልት ዉሳኔ መሰረት ስንበቱ ህጋዊ ነዉ ስለተባለ ህገ ወጥ ስንብት ነዉ ተብል በስር ፍርድ ቤት የተወሰኑት ክፍያዎች ተገቢነት የላቸዉም።ይሁንና ዉለ ሲቋረጥ ተጠሪ ወደ ሀገሩ የሚመለስበት የትኬት ወጪ በአመልካች እንደሚሸፈን የግራቀኙ ዉል አንቀጽ 9/d/ ላይ ተመላክቷል።አመልካችም ይህን በሚመለከት በመካድ ያቀረበዉ ክርክር የለም። ስለዚህም የሥራ ውለ ሲቋረጥ የመመለሻ ትኬት ወጪ በአመልካች የሚሸፈን ስለመሆኑ በስምምንቱ የተመለከተ በመሆኑ ይህንኑ በተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ መሰረት አመልካች ሉከፍል ይገባል ብለናል።ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
1ኛ/የሰበታ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 19/06/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት፣ የፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 29/07/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችልት እንዱሁም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.333832 በቀን 06/04/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ/ አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረገዉን የስራ ዉል ማቋረጡ በህጋዊ መንገድ በመሆኑ ለተጠሪ ሉከፍል የሚገባዉ ክፍያ ወደ ሀገሩ የመመለሻ ትኬት ወጪ ብቻ ነዉ ተብሎል።በዚሁ መሰረት 431.053(አራት መቶ ሰላሳ አንድ ከዜሮ ሃምሳ ሶስት ሳንቲም ድላር)በወቅቱ የባንክ ምንዛሪ ተለዉጦ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል ብለናል።በዚሁ ልክ የጠበቃ አበል 10% ጨምሮ ይክፈል ብለናል።የስር ፍርድ ቤትም ይህንኑ አዉቆ እንዱያስፈጽም የዉሳኔ ግልባጭ ይተላለፍለት።ይጻፍ 3ኛ/የሰበር አጣሪ ችልት በቀን 04/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ እግድ ተነስቷል።
4ኛ/በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.