No summary available.
ጥቅምት 03 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ - ነገረ ፈጅ ጌታቸው ባጫ - ቀርበዋል ተጠሪ፡- ወ/ሮ አይናበባ ተፈራ - አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በምዔራብ ሐረርጌ ጭሮ ወረዲ ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ፣ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ በቀን 15/03/2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክርክር በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከቀን 05/01/2010 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 4,558.00 እየተከፈልኝ ስሰራ ቆይቻለሁ። በዚህ ጊዜ ውስጥም ስራዬን ህግን ተከትዬ ስሰራ ብቆይም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በተደጋጋሚ የፊይንናስ ህግ በመጣስ ሀሰተኛ እና ስርዝ ድልዝ ያለበትን ሰነድ በማዘጋጀት ሂሳብ እንዱወራረድ ትዕዛዝ ሲሰጠኝ በህግ ስለሚያስጠይቀኝ ትዔዛዙን አልተቀበልኩም።
በዚህም ምክንያት ትዕዛዝ አትቀበልም በማለት ከቀን 05/02/2012 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ የተሰናበትኩ መሆኑን በሚገልጽ ደብዲቤ የስራ ዉላን በህገ-ወጥ መንገድ አቋርጦታል። ስለሆነም ወደ ስራዬ እንድመለስ ወይም ከህገ ወጥ ስንብት ጋር የተያያዙ ልዩ ልዩ ክፍያዎችን በጠቅላላው ብር 78,110.20 እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች በበኩለ በቀን 02/04/2012 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ከአመልካች ጋር የስራ ውል ግንኙነት የለኝም፤ ደመወዝ እየከፈልን አላሰራናትም፤ ቀጣሪዋ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልማትና ማህበራዊ አገልግልት ኮሚሽን ማዔከላዊ ኢትዮጵያ ሲኖድስ ድሬዲዋ ቅርንጫፍ ነው በማለት የመጀመሪያ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ነገሩ ላይ በሰጠው መልስ ደግሞ በተጠሪ ላይ የፈፀምነው ምንም አይነት በደል የለም፤ ተጠሪ በልላ መስሪያ ቤት ተቀጥራ የምትሰራ በመሆኑ በ15 ቀናት ውስጥ ከዚያ መስሪያ ቤት መልቀቂያ እንድታመጣ፣ ካላመጣች ግን ስራዋን በራሷ ፍቃድ እንደለቀቀች እንደሚቆጠር ከቀጠራት አካል ደብዲቤ ቢሰጣትም ባለማቅረቧ ከስራዋ ተሰናብታለች፤
ከዚህም ባለፈ ተጠሪዋ ህግ በመጣስ በተደጋጋሚ ጥፊት የምትፈጽምና የተሰጣትን የቃል ማስጠንቀቂያ የማታከብር በመሆኗ ከስራ የተሰናበተች በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት የወረዲዉ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካች ተጠሪን ያሰናበተዉ በህገ-ወጥ መንገድ ስለሆነ ከጥቅምት ወር 2012 ጀምሮ ያልተከፈላት ደመወዝ ተከፍሎት ወደ ስራ ትመለስ በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩበት በኋላ ተጠሪ ከስራ የተሰናበተችው በአመልካች ድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞችን በመሳደቧና አምባጓሮ በመፍጠሯ ስለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል፤ ይህም ስንብቱን ህጋዊ ያደርገዋል በማለት የወረዲ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ሽሮታል። ተጠሪ በበኩሎ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አቤቱታ ያቀረበች ሲሆን ችልቱም ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ አመልካች ተጠሪ የስነ-ምግባር ጥፊት መፈፀሟን በስነ-ምግባር ኮሚቴ ያልተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ስንብቱም የተፈጸመዉ የስነ ምግባር ጥሰት መፈጸሟን የሚሳይ ማስጠንቀቂያ በአመልካች ከተፃፈላት ከ30 ቀን በኋላ መሆኑ ስንብቱን ህገ ወጥ ያደርገዋል በማለት ከጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ የስድስት ወር ውዝፍ ደመወዝ በመክፈል አመልካች ተጠሪን ወደ ስራዋ ይመልሳት በማለት የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሽሮታል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ በአመልካች የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 08/06/2013 ዓ.ም በተፃፈ 02 ገጽ የሰበር አቤቱታ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት እና በወረዲ ፍርድ ቤቱ ተፈጽመዋል ያላቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረምለት ጠይቋል። የአቤቱታው ይዘትም የወረዲ ፍርድ ቤቱ እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪ በተመሳሳይ ሰዓት ለሁለት መስሪያ ቤት እየሰራች ምንም አይነት ጥፊት እንዲልፈፀመች በመቁጠር ስንብቱን ህገ-ወጥ ነው ማለታቸው፤ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪ የፈፀመችው ለሃላፉ ያለመታዘዝና በስራ ቦታ አምባጓሮ መፍጠር ጥፊት ያለማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያሰናብት ሆኖ እያለ ጉዲዩ በዱሲፔሉን ኮሚቴ መታየት ነበር ማለቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ ተጠሪ በቋሚነት ሁለት ቦታ እንደምትሰራ አመልካች አስረድቶ እያለ እና ተጠሪም ይህንን ባልካደችበት ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብል የመወሰኑ አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ለዚህ ሰበር ችልት ቀርቧል። በዚሁም መሰረት ተጠሪ መልስ እንድትሰጥበት ተደርጎ በቀን 24/07/2013 ዓ.ም ጽፊ ባቀረበችው መልስ በስር ፍርድ ቤቶች የተከራከርኩት አሁን የሰበር አቤቱታ ካቀረበው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን መካነ እየሱስ ዋና ጽ/ቤት ጋር ሳይሆን የጭሮ (አሰበ ተፈሪ) መካነ እየሱስ ማህበረ ምዔመናን ጋር በመሆኑ በአሁን አመልካች የቀረበው አቤቱታ ውድቅ ይደረግልኝ የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበች ሲሆን በፍሬ ነገሩ ላይ በሰጡት መልስ ደግሞ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በምሰራበት የስራ ሰዓት ውስጥ ላላ ስራ አልሰራም፤ በልላኛው መስሪያ ቤት ውስጥ የምሰራው የጽዲት ስራ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከምሰራበት የስራ ሰዓት ውጪ የምሰራው ስራ ነው፤ ለቅርብ አለቃ አትታዘም እና በስራ ቦታ አምባጓሮ ትፈጥራለች የተባለውም ሀሰት ነው በማለት ተከራክራለች። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቶ ተከራክሯል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ከተያዘው ጭብጥ፣ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ተጠሪ በልላ መስሪያ ቤት ተቀጥራ መስራቷ በአመልካች ድርጅት የተሰጣትን ኃላፉነት በአግባቡ እንዲትወጣ ምክንያት ሆኗል የሚል ክርክር አመልካች የላለዉ ሲሆን ተጠሪም የላላ መስሪያ ቤት ሰራተኛ መሆኗን ሳትክድ በልላ መስሪያ ቤት የምትሰራዉ የጽዲት ስራ በአመልካች ድርጅት ዉስጥ የምትሰራዉን የስራ ሰዓት የማይነካ መሆኑን ጠቅሳ የተከራከረች ሲሆን አመልካችም በሰጠዉ የመልስ መልስ ይህን በግልጽ ክድ አይከራከርም።
ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ስትቀጠር የላላ መስሪያ ቤት ሰራተኛ መሆን ያለመሆኑን ተጠይቃ እዉነታዉን ደብቃ በአመልካች ድርጅት መቀጠሯን የሚያሳይ ክርክር እና ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ተጠሪ በልላ ድርጅት ተቀጥራ መስራቷ ብቻዉን በአመልካች ላይ የማታለል ድርጊት ፈጽማለች ለማለት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያትም የለም። በመሆኑም ተጠሪ ላላ መስሪያ ቤት ሰራተኛ መሆኗን እንደ ጥፊት በመቁጠር ስንብቱ ህጋዊ ነዉ በማለት አመልካች የሚያቀርበዉን ክርክር ይህ ችልት አልተቀበለዉም።
ላላዉ የአመልካች ክርክር ተጠሪ ከስራ የተሰናበተችዉ ለአለቃ ባለመታዘዝ እና በስራ ቦታ አምባጓሮ በመፍጠር የስነ ምግባር ጥሰት ትፈጽማለች የሚል ነዉ። ማስረጃን መዝኖ ፍሬ ነገርን የማጣራት ስልጣን የተሰጣቸዉ የወረዲዉ እና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የስነ ምግባር ጥሰት መፈጸሟን ያረጋገጡ ሲሆን ሁለቱ በተለያየ ድምዲሜ ላይ የደረሱት የስንብት እርምጃዉ በተጠሪ ላይ የተወሰደዉ በህጉ ላይ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ መሆን ያለመሆኑ ነዉ። የወረዲዉ ፍርድ ቤት እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ በሚል ድምዲሜ ላይ የደረሱት አመልካች በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(3) ላይ የተመለከተዉ የ30 ቀን ጊዜ ካለፈ በኋላ መሆኑን በመጥቀስ ሲሆን፣ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት በበኩለ ስንብቱ ህጋዊ በማለት ለሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት ያደረገዉ አመልካች ማስጠንቀቂያ በ30 ቀናት ዉስጥ ማድረስ አለበት የሚል ግዳታ በአዋጁ አልተጣለበትም የሚል ይዘት ምክንያት በመጥቀስ ነዉ። በበኩላችን እንደተመለከትነዉ አመልካች ተጠሪ የተለያዩ ጥፊቶችን መፈጸሟን ጠቅሶ ማስጠንቀቂያ የፃፈላት ነሐሴ 28 ቀን 2011 ዓ.ም ሲሆን ከስራ ያሰናበታት ግን
No topics extracted.