No summary available.
መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በዔውቀት በላይ ቀነዓ ቂጣታ ብርሃኑ መንግስቱ ማርታ ተካ አመልካች፡- የጦሳ ነጋዳዎች አጠቃላይ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማኅበር ተጠሪ፡- የኢፋዱሪ ፍትህ ሚኒስቴር - ዐቃቤ ሕግ ጉዲዩ በሰባት ዳኞች የተለየ የህግ ትርጉም ስለማያስፈልገው አመልካች ካቀረቡት ሰበር አቤቱታ አንጻር የግራቀኙን ክርክር መሰረት በማድረግ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት በተመራው መሰረት ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ሲታይ፡- ክርክሩ የተጀመረዉ በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆኖ የአሁን ተጠሪ ተወካይ የነበረዉ የአማራ ብሓራዊ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአሁን አመልካችና የአመልካች ሥራ አስኪያጅ እና ሰራተኛ በሆኑት ላይ ሁለት ክሶችን መስርቷል።
አንደኛው ክስ በአመልካች ድርጅት ሥራ አስኪያጅ እና የጥበቃ ሰራተኛ ላይ ሲሆን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1/ሀ) እና በፋዳራል ታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ላይ የተደነገገዉን በመተላለፍ ያለደረሰኝ ግብይት በማከናወናቸው ያለደረሰኝ ግብይት በመፈጸም ወንጀል ተከሰዋል የሚል ሲሆን ሁለተኛው ክስ ደግሞ አመልካች በሆነው ድርጅት ላይ ሲሆን የክሱ ይዘትም አመልካች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 34/1 እና በፋዳራል ታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ ደረሰኝ የመስጠት ግዳታ እንዲለበት እያወቀ በቀን 10/03/2013 ዓ/ም ከምሽቱ በግምት 1፡00 ሰዓት በደሴ ከተማ ሆጤ ክፍለ ከተማ መናኸሪያ አካባቢ በሚገኘዉ ጦሳ ቁጥር 1 መኝታ ቤት ደንበኛ የሆኑት ግለሰብ ለተከራዩት አልጋ ደረሰኝ ባለመስጠቱ በፈጸመዉ ያለደረሰኝ ግብይት መፈጸም ወንጀል ተከሷል የሚለ ናቸው።
ለአመልካችና ለስር ተከሳሾች የክስ ማመልከቻዉ በጠበቃቸዉ በተወከለበት እንዱደርሳቸዉ ተደርጎ ተነብቦላቸዉ አመልካች በጠበቃዉ አማካኝነት ባቀረበዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ይህ የወንጀል ክስ ከመቅረቡ በፉት የገቢዎች ሚኒስቴር ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዚሁ ጉዲይ በአመልካች ላይ አስተዲደራዊ ክስ ስለወሰነብኝ በድጋሚ ልከሰስ አይገባም በማለት ቢቃወምም ፍርድ ቤቱም አመልካች አስተዲደራዊ ቅጣት መቀጣቱ የወንጀል ክስ እንዲይቀርብበት አያደርግም በማለት መቃወሚያዉን ዉድቅ ካደረገ በኋላ ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸዉን እንዱሰጡ ጠይቋቸዉ ጥፊተኛ አይደለንም በማለት ክደዉ በመከራከራቸዉ ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ሰምቶ ምስክሮች የሰጡት ቃል እና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ አመልካች የተጨማሪ እሴት ታክስ(ተ.እ.ታ) ተመዝጋቢ መሆኑን የሰነድ ማስረጃ የሚያሳይ መሆኑን፤ የአመልካች የጥበቃ ሰራተኛ የመኝታ አገልግልት ፈልጎ ለመጣዉ ለአመልካች ደንበኛ አልጋ በማስያዝ ብር 120.00 ተቀብል ደረሰኝ ሳይሰጥ ግብይት መፈጸሙ ተመስክሯል፣ደንበኛዉም አልጋ መያዛቸዉን የሚያሳይ የእንግድች መመዝገቢያ ፍርም የቀረበ መሆኑን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ እንደ ክስ አቀራረቡ ያስረዲ በመሆኑ አመልካችን ጨምሮ የስር ተከሳሾች እያንዲንዲቸው ክሱን እንዱከላከለ ብይን ሰጥቷል።
የስር ፍርድ ቤት የተከሳሾችን መከላከያ ምስክሮች ከሰማ በኋላ የግራ ቀኙን ምስክሮች ቃልና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ በመ/ ላይ በቀን 24/06/2014ዓ/ም በሰጠዉ ፍርድ፡- የአመልካች ሥራ አስኪያጅ የነበሩት የስር 1ኛ ተከሳሽ ወንጀለ በተፈጸመበት ጊዜ በህመም ምክንያት እረፍት ላይ መሆናቸዉን በማስረዲት ክሱን መከላከላቸዉን በመግለጽ በነጻ እንዱሰናበቱ ሲወስን፤ የስር 2ኛ ተከሳሽ የነበሩት ምንም እንኳን በድርጅቱ የሥራ ድርሻቸዉ ጥበቃ ቢሆንም አልጋ በማስያዝ ገንዘብ ለመቀበል ፈቅደዉ ለሰሩት ሥራ ደረሰኝ የመስጠት ሕጋዊ ግዳታ ያልተወጡ መሆኑን በዐቃቤ ህግ የተመሰከረባቸዉን በማስተባበል ስላልተከላከለ ጥፊተኛ ናቸዉ በማለት የጥፊተኝነት ፍርድ ሰጥቷል እንዱሁም የአሁን አመልካችን በሚመለከትም ታክስ ከፊይ የሆነ ሕጋዊ ሰዉነት ያለዉ ድርጅት በመሆን የአገልግልት ግብይት ሲፈጽም ደረሰኝ የመስጠት ሕጋዊ ኃላፉነት እያለበት ደረሰኝ ሳይሰጥ ግብይት መፈጸሙ በማስረጃ የተረጋገጠበትን በማስተባበል ስላልተከላከለ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 34/1 እና በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ስር ጥፊተኛ ነዉ በማለት ፍርድ በመስጠት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመመርመር አመልካች በብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ ወስኗል።
አመልካች ይህንኑ ዉሳኔ በመቃወም ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ አቀርቦ በመ/5 ላይ በቀን 15/07/2014ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ ይግባኙን በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 195/1 መሰረት ሰርዞበታል። በመቀጠል የሰበር አቤቱታዉን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ጉዲዩ የፋዳራል ጉዲይ በመሆኑ አቤቱታ የቀረበበትን የመጨረሻ ዉሳኔ በሰበር ለመመርመር ሥልጣን የለኝም በማለት በመ/4 በቀን 16/02/2015ዓ/ም ወስኗል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ነው።
አመልካች በጠበቃዉ አማካኝነት በቀን 19/03/2015 ዓ/ም የተዘጋጀ ለዚሁ ሰበር ችልት ያቀረቡት ሰበር አቤቱታ ይዘቱ አጠር ባለ መልኩ ሲታይ፡- አመልካች ከዚህ ቀደም በዚሁ ጉዲይ አስተዲደራዊ ዉሳኔ ተላልፍበት በብር 15,000.00 ተቀጥቶ እያለ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 23 እና በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 2/5 ስር የተደነገገዉን በሚቃረን አኳኋን በዚያዉ ድርጊት ለሁለተኛ ጊዜ ተከሶ መቀጣቱ ተገቢ አለመሆኑን፤ አመልካች ድርጅት ሕጋዊ ሰዉነት ያለዉ ግኡዝ በመሆኑ ሥራዉን የሚመራዉ፣ የሚያንቀሳቀስዉና የሚያስተዲድረዉ በቀጠራቸዉ ሰራተኞች አማካኝነት ሲሆን የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የሆነው ስር 1ኛ ተከሳሽ ድርጊቱ በተፈጸመበት ጊዜ በቦታዉ አልነበረም ተብል ከወንጀለ በነጻ ሲሰናበት አመልካች የሆነው ድርጅት ግን በማያዉቀዉና ባልፈጸመዉ ድርጊት ያለደረሰኝ ግብይት ፈጽመሃል ተብል ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ ተገቢ አለመሆኑ፤ አመልካች ወደ ድርጅቱ የሚመጡ እንግድች ደረሰኝ ሳይቀበለ ክፍያ እንዲይፈጽሙ ማስታወቂያ ግልጽ ቦታ በለጠፈበት ሁኔታ በወንጀል ተጠያቂ ላሆን ስለማይገባ ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ እንዱሻር በመጠየቅ ተከራክሯል።
የሰበር አጣሪ ችልቱም የአመልካችን ሰበር አቤቱታ መርምሮ፡- አመልካች ድርጅት ያለደረሰኝ ግብይት ፈጽሟል ተብል በአስተዲደር ብር 15,000.00 እንዱከፍል በተደረገበት ሁኔታ በወንጀል ተከሶ ጥፊተኛ ተብል በብር 30,000.00 የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ የተወሰነበትን አግባብነት ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 2/5 እና ጥፊተኛ ከተባለበት አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ጋር ተገናዝቦ ተጠሪ ባለበት ለመመርመር ሲባል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን 05/07/2015 ዓ/ም ጽፍ የሰጠው መልስ ይዘቱ፡- አስተዲደራዊ ቅጣትና የወንጀል ቅጣት ራሳቸዉን ችለዉ የሚቆሙ ስለሆኑ በአመልካች ላይ የወንጀል ቅጣት መወሰኑ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 23 እና የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 2/5ን የወንጀል ክስንና ጥፊተኝነትን የሚመለከት እንጂ አስተዲደራዊ ቅጣትን የሚመለከት ባለመሆኑ ዉሳኔዉ እነዚህን ድንጋጌዎች የሚቃረን ስላልሆነ የሰበር አቤቱታዉ ዉድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ በመስጠት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከተጠናቀቀ በኋላ ጉዲዩን በሚመረመርበት ጊዜ ተጨማሪ ጭብጥ መመስረት “አመልካች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 34/1 እና በፋዳራል ታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ ያለደረሰኝ ግብይት ፈጽሟል በሚል የተከሰሰዉና ጥፊተኛ ተብል የተቀጣዉ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 34/1 አነጋገር መሰረት ሕጋዊ ሰዉነት የተሰጠዉ ድርጅት ያለደረሰኝ ግብይት ከፈጸመ በወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆን በፋዳራል ታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 በግልጽ መደንገጉ ተረጋግጦ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉን ከዚህ ቀደም በሰ/መ/፣58008 ፣69899፣74237፣፣94913 እና በላልችም መዛግብት ላይ ከተሰጡ የሕግ ትርጉሞች ጋር በማገናዘብ መመርመር ይቻል ዘንድ ለተጠሪ ደርሶት ተጨማሪ በተያዘው ጭብጥ ላይ ግራቀኙ በጽሁፍ ክርክራቸውን እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ በሰበር አጣሪው ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
አመልካች በጉዲዩ ላይ በድጋሚ ሉቀጣ አይገባም በሚል የሚከራከሩበት ምክንያት ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በዚሁ ጉዲይ በአስተዲደራዊ ዉሳኔ በብር 15,000.00 ተቀጥቶ እያለ ለሁለተኛ ጊዜ በወንጀል ተከሶ (ሀምሳ ሺህ ብር) እንዱቀጣ መወሰኑ ተገቢነት የለውም በሚል ነው። አመልካች ከሆነው ድርጅት ክርክር መገንዘብ የሚቻለው አመልካች በአንድ ጉዲይ ሁለት ጊዜ ልቀጣ አይገባም በማለት በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የሚከለክለውን የኢ.ፋ.ድ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 23 ድንጋጌንና በዚህ ረገድ ተቀባይነት ያለውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 2(5) ድንጋጌ ፅንሰ ሀሳብ መሰረት በማድረግ የሚከራከሩ መሆኑን ነው። ይህ ሰበር ችልትም የተጠቀሰው የህገ መንግስት ድንጋጌ እና ወንጀል ሕግ ጽንስ ሀሳብ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያለው መሆን አለመሆኑን ተመልክቷል። በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰው በወንጀል ሕግና ሥነ ሥርዓት መሰረት ተከሶ የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ጥፊተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና የማይከሰስ ወይም የማይቀጣ መሆኑን ከወንጀል ህጉ ጽንሰ ሃሳብ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን በኢ.ፋ.ድ.ሪ ሕገ መንግስትም ይህንኑ በግልጽ ተመልክቶ ይገኛል። ከዚህም መረዲት እንደሚቻለው በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የተከለከለው የመጨረሻ ውሳኔ በሆነ ጥፊተኝነቱ በተረጋጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።
እንደሚታወቀው በወንጀል ሕጉ ምዔራፍ አንድ አንቀጽ 3 ይህ የወንጀል ሕግ ቢኖርም ቅጣት የሚደነግጉ ደንቦችና ልዩ ሕጎች የተጠበቁ ናቸው፤ በእነዚህ ደንቦችና ሕጎች ላይ በተለየ አኳሃን ካልተደነገገ በቀር የዚህ ሕግ መርሆዎች ለእነርሱም ተፈጻሚ ይሆናለ በማለት ይደነግጋል።
አመልካች በተከሰሱበት የታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 በዚሁ አዋጅ ክፍል አስራ አምስት ምእራፍ አንድ ስር ስለ አስተዲደራዊ ቅጣቶችንና የወንጀል ሀላፉነቶችን የሚመለከቱ ጠቅላላ ድንጋጌዎች በተመለከተ አንድን ድርጊት መፈጸም ወይም አለመፈጸም አስተዲደራዊ ቅጣት እና የወንጀል ሀላፉነትን የሚያስከትል በሚሆንበት ጊዜ ጥፊቱን የፈጸመው ሰው አስተዲደራዊ ቅጣት መቀጣቱ የወንጀል ተጠያቂነቱን እንደማያስቀር በዚሁ አንቀጽ 100 ንኡስ አንቀጽ 1 ስር በግልጽ ተደንግጓል።
በዚሁ አዋጅ ክፍል አስራ አምስት ምእራፍ ሁለት ስር ባለት ድንጋጌዎች ስለ አስተዲደራዊ ቅጣቶችን የሚደነግጉ ሲሆን በምእራፍ ሦስት ስር ደግሞ ስለ ታክስ ወንጀልች እና የሚስቀጡት ቅጣት መጠን በግልጽ ተለይተው ተደንግገው ይገኛለ። አመልካች የሆነው ድርጅት የተከሰሰው ያለደረሰኝ ግብይት መፈፀም ወንጀል ተላልፎል በሚል ሲሆን በታክስ አስተዲደር አዋጁ አንቀጽ 108 ስር የታክስ ደረሰኝ አለመስጠት በአስተዲደራዊ የገንዘብ ቅጣት እንደሚያስቀጣ የሚያስቀምጥ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በአዋጁ አንቀጽ 120(1) ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዳታ ያለበት ታክስ ከፊይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25,000 እስከ ብር 50,000 የገንዘብ መቀጫ እና ከሶስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት እንደሚያስቀጣ ተደንግጓል።
ከዚህም መረዲት እንደሚቻለው ደረሰኝ የመስጠት ግዳታ ያለበት ታክስ ከፊይ የሆነ ድርጅት ያለደረሰኝ ግብይት ፈጽሞ በተገኘ ጊዜ በአዋጁ መሰረት በአስተዲደራዊ ውሳኔ ከሚያስከትለው ቅጣት በተጨማሪ የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ስለመሆኑ በግልጽ በህጉ በተደነገገ ጊዜ በአስተዲደራዊ ውሳኔ መቀጣት የወንጀል ተጠያቂነት ሉያስቀር የሚችል ካለመሆኑም በላይ በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የመከልከልን ጥያቄ የሚያስነሳ ላሆንም አይችልም። በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የመከልከል ጥያቄ ሉነሳ የሚችለው በፍርድ ቤት ጉዲዩ ታይቶ ተገቢ ነው የተባለው ውሳኔ በተሰጠበት ጉዲይ በድጋሚ በዚሁ ጉዲይ በወንጀል የተከሰሰ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው። በመሆኑም ድርጅቱ በአስተዲደራዊ ውሳኔ ተቀጥቶ እያለ በድጋሚ በወንጀል ሉቀጣ አይገባም በሚል አመልካች ያነሱት የሕግ ክርክር ስለድጋሚ ቅጣት ክልከላ መርህ (principle of double jeopardy) የተቀመጡትን መመዘኛዎች የሚያሟላ ባለመሆኑ ተቀባይነት ያለው ሁኖ አላገኘነውም።
ላላው አመልካች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 34/1 እና በፋዳራል ታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ ያለደረሰኝ ግብይት ፈጽሟል በሚል የተከሰሰዉና ጥፊተኛ ተብል የተቀጣዉ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 34/1 አነጋገር መሰረት ሕጋዊ ሰዉነት የተሰጠዉ ድርጅት ያለደረሰኝ ግብይት ከፈጸመ በወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆን በፋዳራል ታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 በግልጽ መደንገጉ ተረጋግጦ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉን ከዚህ በፉት በሰ/መ/፣58008 ፣69899፣74237፣94913 እና በላልች መዝገቦች ከተሰጡት ውሳኔዎች አንጻር በሰባት ዲኛ እንዱታይ የተመራ ቢሆንም ተጨማሪ ተደርጎ በተያዘው ጭብጥ ላይ የተለየ ትርጉም መስጠት ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም በሚለው ላይ በሰባት ዲኛ ታይቶ አመልካች የተከሰሱበት አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ያለደረሰኝ ግብይት መፈጸም ወንጀል ሕጋዊ ሰዉነት የተሰጠዉ ድርጅት ያለደረሰኝ ግብይት ፈጽሞ በተገኘ ጊዜ ድርጅቱ በወንጀል ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑን የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 132/1 ድንጋጌ የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት የወንጀል ተጠያቂነት ለማስቀረት የተደነገገ ድንጋጌ አለመሆኑን ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ያለደረሰኝ ግብይት ፈጽሞ በተገኘ ጊዜ አዋጁን መሰረት በማድረግ በወንጀል ተጠያቂ ላሆን እንደሚችል ተጠቅሶ ከዚህ በፉት በዚህ አግባብ የተሰጡ የሕግ ትርጉሞች ለመለወጥም ሆነ ለማሻሻል የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት ባለመኖሩ የተለየ የሕግ ትርጉም አያስፈልገውም በማለት በዚሁ መዝገብ በሰባት ዲኛ በ29/6/2016ዓ.ም አብላጫ ድምጽ ፍርድ የተሰጠበት በመሆኑ ተጨማሪ ተደርጎ የተያዘው ጭብጥ በድጋሚ ማየቱ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘነውም።
ሲጠቃለል አመልካች የሆነው ድርጅት ያለደረሰኝ ግብይት የፈፀመ መሆኑ በሰውና ሰነድ ማስረጃ ተረጋግጦ በስር ፍርድ ቤቶች ጥፊተኛ ተብል በገንዘብ እንዱቀጣ መወሰኑ በፋደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/4) እና አንቀጽ 10 (1) መሰረት መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙን የሚያሳይ ሆኖ ስላላገኘነው ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/፤ የካቲት 24 ቀን 2014ዓ.ም የሰጠው ፍርድ፤ ይህንኑ ፍርድ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/5፤ መጋቢት 15 ቀን 2014ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ስነ- ስርኣት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አንቀጽ 9/1 መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ፍ/ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
ብ/ም የመስማሚያ ሀሳብ በተራ ቁጥር 2 እና 4 ላይ የተሰየምን ዳኞች በአብላጫ ድምጽ በቀን 26/07/2016ዓ/ም በዋለዉ ችልት በተሰጠዉ የፍርድ ዉሳኔ ላይ የሚከተለዉን የመስማሚያ ሀሳብ አስፍረናል።
አመልካች በታክስ አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1ን ተላለፎል ተብል በዚህኛዉ የወንጀል ክስ ተከሶ ጥፊተኛ ተብል ከመቀጣቱ በፉት በዚህ ክስ በተከሰሰበት ድርጊት ከዚህ ቀደም በልላ የወንጀል ክስ ተከሶ ጥፊተኛ ተብል ስለመቀጣቱ ወይም በነጻ ስለመሰናበቱ በመግለጽ ያቀረበዉ ክርክር የለም።የአመልካች ክርክር የወንጀል ክስ በቀረበብኝ ድርጊት አስተዲደራዊ ቅጣት ተቀጥቻለሁ የሚል ነዉ።በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 100/1 ስር አስተዲደራዊ ቅጣት መቀጣት የወንጀል ተጠያቂነትን አያስቀርም በሚል ተደንግጓል።በኢፋዱሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 23 ስር የተደነገገዉ መብት በአንድ የወንጀል ድርጊት ለሁለተኛ ጊዜ በወንጀል መከሰስንና ድጋሚ ቅጣትን የሚከለክል መብት የሚሰጥ እንጂ አስተዲደራዊ ቅጣት የተቀጣ ሰዉ በወንጀል ተጠያቂ አይሆንም የሚል አይደለም።
በመሆኑም ከዚህ ጭብጥ አኳያ አመልካች ያቀረበዉ ክርክር ዉድቅ ተደርጎ በአብላጫ ድምጽ በቀን 26/07/2016ዓ/ም በዋለዉ ችልት በተሰጠ ድምዲሜ እንስማማለን።ሆኖም በቀን 29/06/2016 ዓ/ም በዋለዉ ችልት ባሰፈርነዉ የልዩነት ሀሳብ ላይ አመልካች የተከሰሰበት የአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 የሕግ ሰዉነት የተሰጠዉ ድርጅት በወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆን የተደነገገበት ባለመሆኑ አመልካች በዚህ ድንጋጌ ተከሶ ጥፊተኛ ተብል በገንዘብ እንዱቀጣ መወሰኑ ሉታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ ተሽሮ አመልካች በተከሰሰበት ድርጊት የወንጀል ተጠያቂነት የለበትም ተብል ሉወሰን ይገባል በማለት በሀሳብ ስለተለየን ይህንኑ ከግምት በማስገባት የመስማሚያ ሀሳባችንን አስፍረናል።
No topics extracted.