No summary available.
ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ታግሮ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተጠሪዎች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነዉ ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለእዲ፣ ከ 2ኛ - 4ኛ ተጠሪዎች የፍርድ ባለመብት በመሆን በሚከራከሩበት መዝገብ ላይ አመልካች ያቀረበዉን አቤቱታ ባለመቀበል የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚል አቤቱታ በመቅረቡ ነዉ። አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረበዉ አቤቱታ ይዘትም በአጭሩ ለፍርድ አፈፃፀም እንዱከበሩ ትዕዛዝ የተሰጠባቸው 154 ባለ 3 እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ንብረትነታቸው የፍርድ ባለዔዲ (የ1ኛ ተጠሪ) አለመሆኑንና የእግድ ትዔዛዙ ከመሰጠቱ በፉት ለ3ኛ ወገን በሽያጭ የተላለፈ ስለሆነ በይዞታዉ ስር የላለ ሆነዉ እያለ በግል የባንክ ሂሳቡ ላይ የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ያላግባብ በመሆኑ ይነሳልኝ የሚል ነዉ።
አመልካች ባቀረበው አቤቱታ ላይ 2ኛ ተጠሪ በሰጡት አስተያየት የአሁን አመልካች ተመሳሳይ አቤቱታ በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ ላይ አቅርበው በቀን 14/02/2010 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ ውድቅ መደረጉን በዚህም እስከ ፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ የባጃጆቹ ባለንብረት ማነው? የሚል ጭብጥ ተይዞ ባለንብረቱ የአሁን 1ኛ ተጠሪ መሆናቸው ተረጋግጦ ፍርድ የተሰጠ በመሆኑ አቤቱታው ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር መርምሮ አመልካች 1ኛ ተጠሪን ተክቶ የተጠሪዋን እዲ እንዱፈፅም የተሰጠ ትዕዛዝ የለም። አመልካች በእጁ ያለትን 154 ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ለፋደራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዲይሬክቶሬት እንዱያስረክብ እና በሀራጅ ተሽጠው ለፍርድ ባለመብቶቹ እንዱከፈል ፍ/ቤቱ መጋቢት 13 እና ሚያዝያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም ትእዛዝ የሰጠ ሲሆን ትዔዛዙ በፍርድ ቤቱም ሆነ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አልተቀየረም። የባጃጅ ተሽከርካሪዎቹ የ1ኛ ተጠሪ ንብረት እንጂ የአመልካች እንዲልሆኑ እንዱሁም አመልካች ያቀረቡት የእግድ ይነሳልኝ ክርክር ንብረት ለማሸሽ መሆኑ ተረጋግጦ ውሳኔ ተሰጥቷል። ውሳኔው እስከ ፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ክርክር ተደርጎበት ጸንቷል። ፍርድ ቤቱም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ፍርደን አመቺ በሆነ መንገድ እንዱፈፀም ማድረግ ይችላል። አመልካች ባጃጆቹን መሸጡን ገልፆ የሚከራከር በመሆኑ የእግድ ትዕዛዝ ከተሰጠበት የባጃጅ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ በተገኘው ገንዘብ ላይ አፈፃፀሙ እንዱቀጥል መደረጉ ተገቢ ነው በማለት አቤቱታውን ውድቅ አድርጎ በአመልካች ስም በባንክ የተቀመጠው የሽያጭ ገንዘብ ተጠሪዎች ያስፈረደትን ገንዘብ የማይሸፍን በመሆኑ በፍ/ስ/ሥ/ሕ/ቁጥር 403 በድርሻቸው መጠን ይከፊፈለ በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ከ1ኛ ተጠሪ ወደ አመልካች በሽያጭ ተዘዋውረዋል ከመባለ በፉት የ1ኛ ተጠሪ ንብረት የነበሩ መሆኑ በአመልካችም ጭምር የታመነ ፍሬ ጉዲይ ነው። አመልካች ባጃጆቹን የእግድ ትዔዛዙ ከመሰጠቱ በፉት ለ3ኛ ወገን በሽያጭ ያስተላለፈ እና በይዞታው ስር የማይገኙ መሆኑን ጠቅሶ በባጃጆቹ ላይ የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ እንዱነሳ ባቀረበው አቤቱታ መነሻነት ከፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እስከ ፋደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ በተደረገው ክርክር ንብረቶቹ የ1ኛ ተጠሪ እንጂ የአመልካች አለመሆናቸው ይልቁኑም የአመልካች ክርክር ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር ንብረቶቹን ለማሸሽ የቀረበ መሆኑ ተረጋግጦ የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጥቷል። አመልካች ባጃጆቹን እንዱያስረክብ ተጠይቆ ማስረከብ ስላልቻለ አፈፃፀሙ በሽያጭ ገንዘቡ ላይ እንዱቀጥል መወሰኑ በአግባቡ ነው በማለት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔን አፅንቷል።
ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ለማስለወጥ ነው። አመልካች በጠበቃው አማካኝነት ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም በተፃፈ 03 ገፅ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈፅመዋል ያላቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ሰበር ችልት እዱንታረሙለት ጠይቋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም በአጭሩ በግራ ቀኙ መካከል እስከ ፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ክርክር የተደረገው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 154 መሰረት የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ እንዱነሳ ብቻ ሁኖ እያለ የክርክሩ መነሻ የሆኑት 154 ባጃጆች የ1ኛ ተጠሪ ንብረት ናቸው ተብል ውሳኔ ተሰጥቷል በሚል ምክንያት በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም። በተጨማሪም አመልካች የእግድ ይነሳልኝ አቤቱታው ተቀባይነት ባለማግኘቱ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 421 በመዝገብ በባጃጆቹ ላይ ያለው መብት እንዱታወቅለት ክርክር አቅርቦ ጉዲዩ በመታየት ላይ እያለና ይህም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በመዝገብ የያዘውን ጭብጥ ለመወሰን የግድ አስፈላጊ በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 197 መሰረት መዝገቡ በቀጠሮ ማቆየት ሲገባው በዝምታ አልፍ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚል ነው።
ጉዲዩ በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪዎች መልሳቸውን እንዱያቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። 1ኛ ተጠሪ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው መልስ የማቅረብ መብታቸው የታለፈ ሲሆን ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች በተናጠል መልሳቸውን አቅርበዋል። የመልሳቸዉ የተጠቃለለ ይዘትም አመልካች በባጃጆቹ ላይ የተሰጠው እግድ እንዱነሳ ያቀረበው አቤቱታ የባጃጆቹ ባለንብረት ማነው? የሚል ጭብጥ ተይዞ ንብረቶቹ የ1ኛ ተጠሪ መሆናቸው ተረጋግጦ የእግድ ትዔዛዙ እንዱነሳ በአመልካች የቀረበው አቤቱታው ንብረት ለማሸሽ ነው በሚል እስከ ሰበር ሰሚ ችለቱ በተደረገ ክርክር ውደቅ ተደርጓል። የስር ፍ/ቤቶች አመልካች የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 መሰረት አመልካች ያቀረበውን አቤቱታ መርምረው አመልካች ንብረትነታቸው የ1ኛ ተጠሪ የሆኑ ባጃጅ ተሽከርካሪዎች በመሸጥ ያገኘው ገንዘብ ላይ አፈፃፀም እንዱቀጥል የተሰጠው ውሳኔ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ በመሆኑ በውሳኔዎቹ የተፈፀመ ሕግ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታው በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቶ ክርክሩ ተጠናቋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ባጃጆቹን አስመልክቶ የአሁን አመልካች የመፊለም ክስ አቅርቦ ጉዲዩ በልላ መዝገብ በመታየት ላይ እያለ ባጃጆቹ የ1ኛ ተጠሪ (የፍርድ ባለ ዔዲ) መሆናቸዉ ተረጋግጧል የሚል ይዘት ያለዉ ምክንያት በመጥቀስ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠዉ ዉሳኔ በአግባቡ መሆን አለመሆኑ የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሻዉ ጭብጥ ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በ1ኛ ተጠሪ እና ከ2ኛ-4ኛ ተጠሪዎች መካከል በነበረው የአፈፃፀም ክርክር ንብረትነታቸው የፍርድ ባለ እዲ (የ1ኛ ተጠሪ) ናቸው የተባለት 154 ባለ ሶስት እግር ባጃጅ ተሸከርካሪዎች በአመልካች እጅ ስለሚገኙ ለፍርድ ማስፈፀሚያነት እንዱውለ በስር ፍርድ ቤት ታግደዋል። አመልካች ትዔዛዙን በመቃወም እንዱነሳለት በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 418 መሰረት አፈፃጸሙን ሲመለከት ለነበረዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የመቃወም አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም። ይህ ዉሳኔ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ እንዱሁም በሰበር ሰሚ ችልት በመ/ የጸና ስለመሆኑ አላከራከረም።
አመልካች በእነዚህ መዛግብት ላይ ለተሰጡት ዉሳኔዎች ምክንያት የሆነዉን አቤቱታ ያቀረበዉ በባጃጆቹ ላይ የቅድሚያ መብት አለኝ በሚል ሃሳብ ነዉ። የአመልካች የመቃወም አቤቱታ ዉድቅ የተደረገዉም ክርክሩን ከዚሁ አንፃር በመመርመር ነዉ። በየደረጃዉ ባለት ፍርድ ቤቶች የተሰጠዉ ዉሳኔም አመልካች በባጃጆቹ ላይ የቅድሚያ መብት የለዉም በሚል ምክንያት አቤቱታዉ ዉድቅ መደረጉን እንጂ ባጃጆቹ የፍርድ ባለዔዲዋ (የአሁን 1ኛ ተጠሪ) መሆናቸዉን የሚያሳዩ እንዲልሆኑ ከዉሳኔዎቹ ይዘት የምንገነዘበዉ ነዉ። በፍ/ብሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 418 መሰረት የሚቀርብ አቤቱታ በባህርዉ እንደላልች መደበኛ ክርክሮች የተሟላ ክርክር የማይደረግበት ከመሆኑ እና የክርክሩም አድማስ የመቃወም አመልካች ለአፈፃጸም እንዱዉል አግድ በተላለፈበት ንብረት ላይ የቅድሚያ መብት ያለዉ መሆን አለመሆኑ ላይ የተገደበ ከመሆኑ አንፃር ሲታይ፣ አመልካች በባጃጆቹ ላይ የቅድሚያ መብት የለዉም በሚል ቀደም ሲል በተሰጡት ዉሳኔዎች የተደረሰበት ድምዲሜ በምንም መልኩ ባጃጆቹ የፍርድ ባለ ዔዲ ናቸዉ በሚል እንደተወሰነ ሉተረጎም የሚገባዉ አይደለም። ስለሆነም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከላይ በተጠቀሱት መዝገቦች ላይ ቀደም ሲል የተሰጡት ዉሳኔዎች ባጃጆቹ የፍርድ ባለዔዲ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ ነዉ በሚል የደረሰበት ድምዲሜ እና ይግባኝ ሰሚዉ ችልትም ይህንኑ በመቀበል የሰጠዉ ዉሳኔ ለዉሳኔዉ ምክንያት የሆነዉን ክርክር ባህርይ ከዉሳኔዉ ትክክለኛ ይዘት ጋር ካለማገናዘብ የመነጨ ስህተት በመሆኑ ሉታረም የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል አመልካች በባጃጆቹ ላይ ያለዉን የባለቤትነት መብት ለማስከበር ሲባል በኮ/መ/ ላይ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ጉዲይ በመታየት ላይ የሚገኝ ስለመሆኑ አላከራከረም። በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 418 መሰረት ያቀረበዉ አቤቱታ ዉድቅ የተደረገበት ሰዉ በንብረቱ ላይ ያለዉን መብት ለማረጋገጥ አዱስ ክስ ማቅረብ እንደሚችል የህጉ አንቀጽ 421 ድንጋጌ ያስገነዝባል። አመልካች በባጃጆቹ ላይ የቅድሚያ መብት አለኝ በሚል ያቀረበዉ መቃወሚያ ዉድቅ በመደረጉ ምክንያት በባጃጆቹ ላይ ያለዉን መብት በፍርድ ለማረጋገጥ ክስ ያቀረበዉም በዚህ ድንጋጌ መሰረት ነዉ። ስለሆነም ባጃጆቹ በእርግጥ የፍርድ ባለ ዔዲ (1ኛ ተጠሪ) ናቸዉ? ወይስ የአመልካች?
የሚለዉ ጉዲይ ክሱ በቀረበበት መዝገብ ላይ ታይቶ እልባት ላሰጥበት የሚገባ ጉዲይ ነዉ። ለፍርድ አፈፃጸም የሚዉል የፍርድ ባለዔዲዉ እንጂ የሦስተኛ ወገን ንብረት ካለመሆኑ አንፃር ሲታይ፣ ባጃጆቹ የፍርድ ባለዔዲዋ ስለመሆናቸዉ እራሱ ገና በፍርድ ሂደት ተጣርቶ ዉሳኔ የሚያገኝ እንጂ አሁን ላይ ባልታወቀበት ሁኔታ ከባጃጆቹ ጋር በተያያዘ ምክንያት በአመልካች ስም በባንክ በተቀመጠዉ ገንዘብ ላይ አፃፀሙ እንዱቀጥል ማድረግ በኮ/መ/ ላይ በመካሄድ ላይ ያለዉን ክርክር ዉጤት አልባ የሚያደርግ ነዉ። በመሰማት ላይ ያለዉን ክርክር መወሰን የሚቻለዉ በልላ መዝገብ ላይ በመታየት ላይ ያለ ጉዲይ ዉሳኔ ሲያገኝ መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የያዘዉን መዝገብ በቀጠሮ ማቆየት እንደሚችል በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓ ህጉ አንቀጽ 197(2) ላይ ተመልክቷል። የዚህ ድንጋጌ ዓይነተኛ ዓላማ በአንድ ጉዲይ ላይ የተለያዩ ምናልባትም የሚጋጩ ዉሳኔዎች እንዲይሰጡ ወይም በአንድ መዝገብ ላይ የሚሰጥ ትዕዛዝ/ዉሳኔ በልላ መዝገብ ላይ በመታየት ላይ ያለዉ ክርክር ዉጤት አልባ እንዲይሆን በማድረግ የሥነ ሥርዓታዊ ፍትሕ፣ የወጥነት እና የተገማችነት መርሆዎች እዉን እንዱሆኑ ለማስቻል እንደሆነ ይታመናል። ይህ ድንጋጌ እላዩ ላዩን ሲታይ አፈፃጸምን ሳይሆን በዋና ጉዲይ ላይ የሚታይ ክርክርን የሚመለከት ቢመስልም፣ በአፈፃጸም መዝገብ ላይ የሚሰጥ ትዕዛዝ/ዉሳኔ በልላ መዝገብ ላይ እየታየ ያለዉን ክርክር ዋጋ የሚያሳጣዉ መሆኑ ከተረጋገጠ ይህ ድንጋጌ በአፈፃጸም ጉዲይ ላይ ተፈፃሚ ላሆን የማይችልበት ምክንያት የለም። በመሆኑም ምንም እንኳ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 421 መሰረት በቀረበ ክስ መነሻነት የሚሰጥ ዉሳኔ እስከሚታወቅ ድረስ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 418 መሰረት የሚቀርብ የመቃወም አቤቱታን ዉድቅ በማድረግ የሚሰጥ ዉሳኔ እንደጸና የሚቆይ ስለመሆኑ በድንጋጌዉ የተመለከተ ቢሆንም፣ ለመቃወም አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ንብረት በተመለከተ የቀረበ ክስ ታይቶ ዉሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በአፈፃፀም መዝገብ ላይ ንብረቱን አስመልክቶ የሚሰጥ ዉሳኔ/ትዕዛዝ በሂደት ላይ ያለዉን ክርክር ዉጤት የሚጎዲ መሆኑ ከተረጋገጠ ንብረቱን አስመልክቶ የቀረበ ክስ እልባት እስኪሰጠዉ ድረስ ንብረቱን በተመለከተ የሚሰጥ/የተሰጠ የአፈፃፀም ትዕዛዝ ለጊዜዉ ታግድ እንዱቆይ የማይደረግበት ምክንያት የለም።
ስለሆነም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ከዚህ አንፃር በማየት በኮ/መ/ ላይ በመታየት ላይ ያለዉ ክርክር ዉጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ከአመልካች የግል የባንክ ሂሳብ ላይ ገንዘብ ወጪ ተደርጎ እንዲይከፈል በፍት/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 197(2) መሰረት ማቆየት ሲገባዉ ይህን ባለማድረግ ይባስ ብልም ባጃጆቹ የ1ኛ ተጠሪ መሆን አለመሆናቸዉ ገና በአመልካች በቀረበዉ ክስ መሰረት ታይቶ እና ተጣርቶ ዉሳኔ የሚሰጥበት ሆኖ እያለ ባጃጆቹ የፍርድ ባለዔዲዋ ናቸዉ በሚል ድምዲሜ ላይ በመድረስ የሰጠዉ ዉሳኔ ገና በልላ መዝገብ ላይ በክርክር ላይ ባለዉ ጉዲይ ከወዱሁ ዉሳኔ በመስጠት የፍርድ ሂደቱን ዉጤት አልባ የማድረግ ዉጤት ያለዉ ሲሆን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይህን ማረም ሲገባዉ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ዉሳኔ በማጽናት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የክርክር አመራር ግድፈት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 167153 በቀን 28/03/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በይ/መ/ቁ. 166908 በቀን 30/01/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ለዚህ ክርክር መነሻ የሆኑት 154 ባለ ሦስት እግር ባጃጆች የፍርድ የፍርድ ባለዔዲዋ (1ኛ ተጠሪ) መሆን አለመሆናቸዉ የሚወሰነዉ በኮ/መ/ ላይ በመታየት ላይ ባለዉ መዝገብ ላይ ነዉ ብለናል።
በኮ/መ/ ላይ በመታየት ላይ ያለ ክርክር ዉሳኔ እስከሚያገኝ ድረስ በአመልካች ስም የተቀመጠዉ እና የታገደዉ ገንዘብ ለ2-4ኛ ተጠሪዎች ባስፈረደት የገንዘብ መጠን መቶኛ ስላት መሰረት እንዱያከፊፍለ ለወጋገን ባንክ፣ ለዘመን ባንክ፣ ለህብረት ባንክ፣ ለቡና ባንክ፣ ለንብ ባንክ፣ ለዲሽን ባንክ፣ ለአዋሽ ባንክ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ለብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ እና ለአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የተላለፈ ትዕዛዝ ሳይፈጸም እንዱቆይ ተወስኗል።
በዚህ ችልት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
በዚህ ችልት ትዕዛዝ መሰረት ከፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበዉ መ/ በመጣበት አኳኋን ለፍርድ ቤቱ ይመለስ በዉሳኔዉ መሰረት እንዱፈጽም የዚህ ፍርድ እና ዉሳኔ ግልባጭ ለስር ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይድረስ።
No topics extracted.