No summary available.
መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) እንዲሻው አዲነ ተሾመ ሽፈራው ዋዚሞ ዋሲራ ሰናይት አድነው አመልካች፡- ወ/ሮ ምህረት መኮንን - የቀረበ የለም ተጠሪ፡-
መዝገቡ የተቀጠረው ለሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም የነበረ ቢሆንም 2ኛ ተጠሪ ቀጠሮ ተሰብሮ ይታይልኝ በማለት መጋቢት 3 ቀን 2016 ዓ.ም በመጠየቃቸው ቀጠሮ ተሰብሮ ለዛሬ እንዱታይ ችልቱ በማዘዙ ነው።
ይህ የአፈጻጸም ክርክር የተጀመረው በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁን 1ኛ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት የአሁን አመልካች የፍርድ ባለእዲ በመሆን በተሰጠ ውሳኔ መነሻነት ለእዲው መክፈያ በሀራጅ እንዱሸጥ የተወሰነበትን ቤት የአሁን 2ኛ ተጠሪ በጨረታ ከመግዛታቸው ጋር ተያይዞ የአሁን 2ኛ ተጠሪ ጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ለመክፈል በሀራጅ ማስታወቂያ ላይ ከተገለጸው 15 ቀን ላላ ተጨማሪ 15 ቀን ይፈቀድልኝ በማለት ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት ግራ ቀኙ ተከራክረዋል።
ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለው የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ አመልካች ቅር ተሰኝተው ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ ያቀረቡት ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በመ/ በቀን 25/10/2015 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትእዛዝ በማጽናት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች ሀምላ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ከወላጆቻቸው በውርስ ያገኙትን ቤት በፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት በሀራጅ ተሽጦ እንዱካፈለ በተሰጠ የአፈጻጸም ትእዛዝ መነሻነት ቤቱ በሃራጅ እንዱሸጥ በጋዜጣ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት የአሁን 2ኛ ተጠሪ ጨረታውን ተወዲድረው እና አሸንፈው እያለ መጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም በወጣው የጨረታ ማስታወቂያ መሰረት ጨረታውን በአሸነፈ በ15 ቀን ውስጥ ጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ መክፈል እንዲለባቸው የተገለጸ ቢሆንም 2ኛ ተጠሪ 15 ቀን ሉያበቃ 1 ቀን ሲቀረው ሚያዝያ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ጨረታውን ያሸነፈ ሰው በ15 ቀን ውስጥ ጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ መክፈል እንዲለበት የተገለጸ ቢሆንም ባለቤቴ ለውሉድ ሆስፑታል ገብታ የነበረ በመሆኑ ገንዘቡ በተባለው ጊዜ መክፈል ስላልቻልኩ ተጨማሪ 15 ቀን ይፈቀድልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም 2ኛ ተጠሪ ባለቤታቸው ሚያዝያ 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለወሉድ ሆስፑታል የነበሩ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ያቀረቡ ስለሆነ ይህ ምክንያት የሽያጩን ገንዘብ በተባለው 15 ቀን ውስጥ ገቢ ለማድረግ የሚከለክል በቂ ምክንያት ነው በማለት ደምድሞ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችልት ከዚህ ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ተጨማሪ 15 ቀን ለመፍቀድ ትእዛዝ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኙት የአሁን አመልካች ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታቸውን ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማጽናቴ ውሳኔ ሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘት በአጭሩ በጨረታው ላይ የተገለጸው ለመክፈያ ጊዜ 15 ቀን ከመሆኑ በስተቀር ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የዐመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘት በአጭሩ በጨረታው ላይ የተገለጸው የመክፈያ ጊዜ 15 ቀን ከመሆኑ በስተቀር ይህ ጊዜ ሉራዘም የሚችልበት አግባብ ስለመሆኑ ባልተገለጸበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤቶች 2ኛ ተጠሪ በህጉ በተፈቀደው 15 ቀን ጊዜ ውስጥ ክፍያውን ጨርሰው ባለመክፈላቸው ድጋሚ ጨረታ እንዱወጣ ማዘዝ ሲገባቸው ተጨማሪ 15 ቀን ጊዜ መፍቀዲቸው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉን የሚያሻሽል ከመሆኑም በተጨማሪ የኔን መብት የሚነካ ስለሆነ የስር ፍርድ ቡቶች የሰጡት ውሳኔ ተሽሮ ድጋሚ ጨረታ እንዱወጣ ተብል ይወሰንልኝ የሚል ነው።
የአመልካችም አቤቱታ በሰበር አጣሪው ችልት ተመርምሮ ክፍያው ለ15 ቀን እንዱራዘም የተወሰነበትን አግባብነት ተጠሪዎች ባለበት ለመመርመር ሲባል መዘዝገቡ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ታዟል።
1ኛ ተጠሪ ህዲር 20 ቀን 2016 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል ይዘቱም በአጭሩ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ የሚነቀፍ ባለመሆኑ ሉጸና ይገባል ሲለ 2ኛ ተጠሪ ህዲር 20 ቀን 2016 ዓ.ም በተጻፈ የሰጡት መልስ የመክፈያ ተጨማሪ ጊዜ በራሴ ጊዜ ያላራዘምኩኝ ይልቁኑስ በወቅቱ ያጋጠመኝን ምክንያት ከግምት በማስገባት በፍርድ ቤቶች የተፈቀደልኝ ከመሆኑም በተጨማሪ በተፈቀደልኝ 15 ቀን ጊዜው ውስጥ ሙለ ክፍያ ከፍዬ የጨረስኩኝ ስለሆነ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ የሚነቀፍ እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም፤ ስለሆነም ሉጸና ይገባል በማለት ክርክራቸውን ሲያቀርብ አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
No topics extracted.
የጉዲዩ አመጣጥና የክርከሩ ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን ያለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ እና ከተገቢው ህግ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደመረመርነው በመሰረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 441 ላይ ለፍርድ አፈጻጸም ሲባል ንብረት በሀራጅ እንዱሸጥ ሲታዘዝ በሀራጅ የተሸጠው ንብረት ዋጋ በሙለ የሚከፈለው ገዢው ንብረቱን መግዛቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ እንደሆነ ተደንግጎ ይገኛል። በተጨማሪም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 442 ላይ እንደተመለከተው ከላይ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ የንብረቱ ዋጋ ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ ገዢው አስይዞት ከነበረው ገንዘብ ውስጥ ለሽያጩ ስርአት እና ለማናቸውም ጉዲይ ውጭ የተደረገው ገንዘብ ተቀንሶ የቀረው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ፍርድ ቤቱ ለማዘዝ ይችላል ንብረቱም እንደገና እንዱሸጥ ትዕዛዝ ይሰጣል እንዱህ በሆነ ጊዜ ግዳታውን ሳይፈጽም የቀረው ገዢ በሽያጭ ገንዘቡ ወይም በተሸጠው ንብረት ላይ ምንም መብት አይኖረውም በማለት ደንግጎ ይገኛል።
የጨረታ ማስታወቂያውም ክፍያው በ15 ቀን ውስጥ እንደሚከፈል የሚገልጽ መሆኑን ግራ ቀኙን አላከራከረም። አከራካሪው ጉዲይ በሥ/ሥ/ህጉ የተደነገገው እና በሃራጅ ማስታወቂያ ላይ የተገለጸው የ15 ቀን መክፈያ ጊዜ በዳኞች ትእዛዛ ሉሻሻል ይገባል አይገባም የሚለው ነው።
ይህንን አከራካሪ ጭብጥ ለመወሰን የድንጋጌዎቹ ይዘት ህጉ ለወጣበት አላማ አንጻር ማየቱ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የድንጋጌዎቹን ይዘት ስንመለከት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 441 ላይ ለፍርድ አፈጻጸም ሲባል ንብረት በሀራጅ እንዱሸጥ ሲታዘዝ በሀራጅ የተሸጠው ንብረት ዋጋ በሙለ የሚከፈለው ገዢው ንብረቱን መግዛቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ በ 15 ቀን ውስጥ ነው በማለት ሲደነገግ፡ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 442 ላይ እንደተመለከተው ከላይ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ የንብረቱ ዋጋ ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ ገዢው አስይዞት ከነበረው ገንዘብ ውስጥ ለሽያጩ ስርዓት እና ለማናቸውም ጉዲይ ወጭ የተደረገው ገንዘብ ተቀንሶ የቀረው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ፍርድ ቤቱ ለማዘዝ ይችላል ንብረቱም አንደገና እንዱሸጥ ትእዛዝ ይሰጣል፤ እንዱህ በሆነ ጊዜ ግጌታውን ሳፈጽም የቀረው ገዢ በሽያጭ ገንዘቡ ወይም በተሸጠው ንብረት ላይ ምንም መብት አይኖረውም በማለት ደንግጎ ይገኛል።
የድንጋጌዎቹ አገላለጽ በመጀመሪያ ደረጀ በ15 ቀን ውስጥ የሽያጩ ገንዘብ መከፈል እንዲለበት በአስገዲጅ ሁኔታ ሲደነግግ ቀጥል ያለው ድንጋጌ በ15 ቀን ውስጥ ክፍያው ያለመፈጸሙ ገዢው አስይዞት ከነበረው ገንዘብ ላይ ለሽያጩ ስርአት እና ለማናቸውም ጉዲይ ወጪ የተደረገ ገንዘብ ሉቀነስበት እንደሚገባ በአስገዲጅ ሁኔታ ደንግጎ የቀረው ገንዘብም ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ፍርድ ቤቶች ለማዘዝ እንደሚችለ ከደነገገ በኋላ ንብረቱም እንደገና እንዱሸጥ ትእዛዝ ይሰጣል በማለት በአስገዲጅነት በመግለጽ የተቀመጠው የህጉ ድንጋጌ ገዢ ጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ በህጉ በተመለከተው ጊዜ ካልከፈለ ላላ ሃላፉነት የሚጥልበት መሆኑን በአስገዲጅ ሁኔታ እና በጥብቅ የደነገገ መሆኑን ከድንጋጌው አገላለጽ መረዲት የሚቻል ጉዲይ ነው።
ህጉ በዚህ አግባብ መደንገጉም አላማው ንብረት በጨረታ ለመግዛት የሚመጣ ሰው ጨረታውን ቢያሸንፍ ክፍያውን ወዱያው ከፍል ንብረቱን መረከብ የሚችል ሰው መሆኑን በመገመት እና ወይም ጨረታውን ቢያሸነፍም ያሸነፈበትን ገንዘብ ለመክፈል የሚችል ሰው ጨረታውን አስቀድሞም አይወዲደርም ብል በማሰብ እና የተባለው ንብረት በተባለው ጊዜ ካልተሸጠ የሚያስከትለውን የገበያ ውጣ ውረድ ሃላፉነት ለመቀነስ በማሰብ የ 15 ቀን ጊዜውን በጥብቅ አገላለጽ የደነገገው።
ከዚህ የድንጋጌ አላማ ስንነሳ ጨረታ አሸናፉው በ15 ቀን ውስጥ ክፍያውን ካልከፈለ ንብረቱ እንዱሸጥ እና ገዢው ላይ ተጨማሪ ሃላፉነት በሚጥልበት ሁኔታ በጥብቅ ድንጋጌ የተቀመጠን ሥነ-ሰርአት ዳኞች እንደፈለጉ ሉለውጡት የሚችለበት የህግ ምክንያት የለም።
ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች የአሁን 2ኛ ተጠሪ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ በ15 ቀን ውስጥ ያለመክፈላቸውን ካረጋገጡ በህጉ አግባብ በድጋሚ ጨረታ ንብረቱ እንዱሸጥ ማዘዝ ሲገባቸው ይህንን ካለማድረጋቸው በተጨማሪ 2ኛ ተጠሪ ንብረቱን በሀራጅ የገዙበትን ዋጋ ለመክፈል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 441 ላይ ከተመለከተው በተጨማሪ የ15 ቀን ጊዜ እንዱጨመርላቸው ያቀረቡት ጥያቄ የስነ ስርዓት ህጉን ያልተከተለና ሕጋዊ ዔውቅና እና ውጤት ሉሰጠው የሚገባው ባልሆነበት ሁኔታ 2ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን የ15 ቀን ተጨማሪ ጊዜ በመፍቀድ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ በማጽናት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 441፣ እና 442 ድንጋጌዎች ያላገናዘበና መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችልት የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ በማጽናት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ንብረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 442 መሰረት በድጋሚ ጨረታ ሉሸጥ ይገባል ብለናል።
የፍደራል መጀመሪያ ደራጅ ፍርድ ቤት መዝገቡን በማንቀሳቀስ ገዢው (2ኛ) ተጠሪ አስይዘውት ከነበረው ገንዘብ ውስጥ ለሽያጩ ስርአት እና ለማናቸውም ጉዲይ ውጪ የተደረገው ገንዘብ የሚቀነስበትን ሁኔታ እና ስለቀሪው ገንዘብ ተገቢውን ትዕዛዝ እንዱሰጥ እንዱሁም ንብረቱ እንደገና በ2ኛ ሀራጅ ሽያጭ እንዱሰጥ ተገቢውን ትዕዛዝ እንዱሰጥ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት ነሀሴ 5 ቀን 2015 ዓ.ም የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ።