No summary available.
ጥቅምት 03 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- ወ/ሮ መሰረት ኃይለ - ጠበቃ ሰለሞን ረዲ ተጠሪ- ወ/ሮ ቢቂልቱ በየነ - ቀርበዋል **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በቡራዩ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ተጠሪ የፍርድ ባለመብት በመሆን የፍርድ ባለዔዲ በሆኑት በአመልካች እና ላልች ሁለት ግለሰቦች ላይ ባቀረቡት አቤቱታ የቡራዩ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ ላይ በቀን 10/08/2009 ዓ.ም በዋለዉ ችልት በሰጠዉ ውሳኔ መሰረት እንዱፈፀምላቸው የጠየቁትን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ።
የአፈፃፀም አቤቱታዉ የቀረበለት ፍርድ ቤት አከራካሪው ይዞታ በገፈርሳ ቡራዩ ቀበላ አስተዲደር አማካኝነት ተለክቶ እንዱቀርብለት ካደረገ በኋላ ስፊቱ 842.8 ካ.ሜ እንደሆነ፤ ተጠሪ ደግሞ በክሳቸው ላይ የጠቀሱት የይዞታ መጠን 660 ካ.ሜ ስለመሆኑ መገንዘቡን ጠቅሶ የፍርድ ባለእዲዎች በዚሁ መጠን ለአመልካች እንዱያስረክቡ፣ ከዚህ ውጪ የሚተርፍ ይዞታ ካለና ባለመብት ካልተገኘ የከተማው አስተዲደር ወደ መሬት ባንክ እንዱያስገባ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ግራ ቀኙ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን የይግባኝ አቤቱታ በማጣመር ከመረመረ በኋላ ትርፍ ነው የተባለውን መሬት የቡራዩ ከተማ አስተዲደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ይዉሰድ መባለ ስህተት ነው፤ ተጠሪ በአራቱም አቅጣጫ አዋሳኝ ጠቅሰው ያቀረቡትን ክስ መጠኑ በባለሞያ እንዱጣራ ከማዘዝ ውጪ ትክክለኛውን መጠን አልጠቀሱም ልባል አይገባም በማለት የወረዲ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ ሽሮታል። አመልካች በበኩላቸው በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ እና የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እና ሰበር ሰሚ ችልቶች በቅደም ተከተል ቢያቀርቡም ተቀባይት አላገኘም። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች በቀን 12/05/2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት 03 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈጽመዋል ያሎቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙላቸው ጠይቀዋል።
የአቤቱታቸው ይዘትም በአጭሩ ክርክር ያስነሳውና ተጠሪ እንዱረከቡት የተወሰነላቸው ይዞታ መጠን 660 ካ.ሜ ሆኖ እያለ ከዚህ መጠን በላይ አመልካች በውርስ ያገኘሁትን ይዞታ በማጠቃለል በአፈፃፀም እንዱረከቡ መወሰኑ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ከዚህ በፉት በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ያላገናዘበ እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የአከራካሪው ይዞታ አፈፃፀም ፍርደን የተከተለ ነው?
ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ ከፍትሐብሕር ስነ-ስርዓት ህግ አንፃር መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ለዚህ ሰበር ችልት ቀርቧል። በዚሁም መሰረት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ በቀን 22/06/2013 ዓ.ም በተፃፈ መልሳቸው የቡራዩ ከተማ ወረዲ ፍርድ ለአፈፃፀሙ ምክንያት የሆነውን ውሳኔ ሲሰጥ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን መሬት ስፊት ያላጣራ ሲሆን በደፈናው የተጠሪ ይዞታ ላይ የተፈጠረው ሁከት ተወግድ የፍርድ ባለእዲዎች የሰሩትን አጥር አፍርሰው ይዞታውን እንዱለቁ ወሰነ እንጂ የይዞታውን መጠን አልገለፀም፤ በስር ፍርድ ቤት ክስ ያቀረብቡኩበት ይዞታ መጠኑ 1300 ካ.ሜ የነበረ ሲሆን መንግስት በይዞታው ላይ መንገድ በማውጣቱ መጠኑ ቀንሷል፤ አመልካች በዚህ አካባቢ ምንም አይነት መሬት የላቸውም፤ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዋሳኙ የተጠቀሰውን መሬት በአፈፃፀም እንድረከብ ትዕዛዝ መስጠቱ ስህተት ስለላለው ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክራለች። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተው ተከራክረዋል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ከተያዘው ጭብጥ፣ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረዉም ለአፈፃፀሙ ምክንያት ለሆነዉ ዉሳኔ መነሻ የሆነዉን ክስ ተጠሪ ሲያቀርቡ አዋሳኛቹንም በአራት አቅጣጫ በመጥቀስ ሲሆን ለአፈፃፀሙ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ ይዘትም አዋሳኙ ከተጠቀሰዉ ይዞታ ዉስጥ የሚገኘዉ ይዞታ የተጠሪ በመሆኑ አመልካችን ጨምሮ ላልች ተከሳሾች ሁከት አስወግድ በቦታዉ ላይ ያጠሩትን አጥር ያፍርሱ የሚል ስለመሆኑ በፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሰጠዉ የፍርድ ሃተታ መገንዘብ ይቻላል። አመልካች ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ ወይም ለአፈፃፀሙ መነሻ የሆነዉ ፍርድ ካረፈበት ይዞታ አጠገብ አዋሳኝ ይዞታ ያላቸዉ ስለመሆኑ የቀረበ ክርክር የለም። ለፍርድ አፈፃፀም ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔም ይሄዉ ነዉ።
No topics extracted.
ፍርድ እንዱያስፈጽም አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት እንደ ፍርደ፣ ማለትም በፍርደ ላይ በተመለከተዉ ላይ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ፣ የማስፈጸም ኃላፉነት አለበት። በፍርድ ቤት የሚሰጥ ዲኝነት ያላግባብ የተወሰደ ንብረት ወይም ሀብት እንዱመለስ ወይም ገንዘብ እንዱከፈል ላሆን ይችላል።
በዚህ መልኩ በሚሰጥ ዉሳኔ የፍርድ ባለመብት ተጠቃሚ ላሆን የሚችለዉ በተሰጠ ፍርድ መሰረት የተፈጸመለት እንደሆነ ነዉ። እያንዲንደ ጉዲይ የሚፈጀዉ ጊዜ እንደ የጉዲዩ ዓይነትና ባህርይ ሉለያይ የሚችል ቢሆንም፣ ክስ ከቀረበበት ጀምሮ እስከ ዉሳኔ ድረስ ያለዉ ሂደት የተወሰነ ጊዜ መዉሰደ አይቀሬ ነዉ። በዚህም ሂደት የፍርድ ቤት ብልም የተከራካሪ ወገኖች ጊዜ ይባክናል፤ ወጪና ድካም ይኖራል። ስለሆነም ፍርድን እንደ ፍርደ ማስፈጸም ይህን ሂደት በማለፍ የተሰጠ ፍርድ ፍሬ አልባ እንዲይሆን የማድረግ ዉጤት ሉያስከትል የሚችል ከመሆኑም በላይ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት ፍርድ ተፈፃሚነቱ ተገማች እንዱሆን ያስችላል። የፍት/ብ/ሥነ ሥርዓት ህጋችን ሰባተኛ መጽሐፍ ከአንቀጽ 371 ጀምሮ ባለት ድንጋጌዎቹ የፍርድ አፈፃፀም የሚመራበትን ሥነ-ሥርዓት ይደነግጋል። የፍርድ አፈፃፀም የቀረበለት ፍርድ ቤትም በዚህ የመጽሐፈ ክፍል የተዘረጋዉን ስርዓት በመከተል ድንጋጌዎቹን እንደየአግባብነታቸዉ ተግባራዊ በማድረግ አፈፃፀሙን በመምራት እንደ ፍርደ የማስፈጸም ግዳታ አለበት።
ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት ለአፈፃፀሙ መነሻ ለሆነዉ ዉሳኔ ምክንያት በሆነዉ ክስ ተጠሪ የጠቀሱት የይዞታ መጠን 660 ካ/ሜትር የሚል ቢሆንም የተሰጠዉ ዉሳኔ በክሱ ላይ አዋሳኞቹ የተጠቀሰዉ ይዞታ የተጠሪ መሆኑን የሚያሳይ ከሆነ በአዋሳኙ የተመለከተዉ የይዞታ መጠን ከ660 ካ/ሜትር በላይ 842.8 ካ/ሜትር መሆኑ ቀሪዉ ይዞታ ማለትም 182 ካ/ሜትር ፍርድ ያላላረፈበት ነዉ ለማለት የሚያስችል አይደለም። በመሆኑም የወረዲዉ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ከዚህ አንፃር ማየት ሲገባዉ ይዞታዉ ተለክቶ በታወቀዉ መጠን እና በተጠሪ ክስ ላይ በተጠቀሰዉ መጠን መካከል ልዩነት በመፈጠሩ ብቻ 182 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ፍርድ አላረፈም በማለት መቀነሱ የፍርደን ትክክለኛ ይዘት ያላገናዘበ ሲሆን፣ በአንፃሩ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንኑ በማረም በፍርደ ላይ አዋሳኙ የተጠቀሰዉ ይዞታ ለተጠሪ እንዱፈጸም በማለት ዉሳኔ መስጠቱ እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችልቶች ይህንኑ ዉሳኔ በማጽናት የሰጡት ትዕዛዝ የፍርድ አፈፃፀም ሥርዓት መሰረታዊ መርህን ለአፈፃፀሙ ምክንያት ከሆነዉ ዉሳኔ ጋር በማገናዘብ የተሰጠ እና በአግባቡ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
በፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 16/04/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ፣ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 27/04/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት እንዱሁም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 03/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንተዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት በመ/ በቀን 25/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ እግድ ተነስቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ሄ/መ