No summary available.
ሐምል 27 ቀን 2010 ዓ.ም ዳኞች፡
ይህ ጉዲይ የተጀመረዉ በሰሜን ጎንደር መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ.149867 በ05/04/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልን በማለት አመልካች ያቀረበዉን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ዉሳኔ ለመስጠት ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ ባቀረበዉ ክስ ከሳሽ እና ተከሳሽ ባንክ መካከል በተደረገዉ የብድር ዉል መነሻነት በጎንደር ከተማ አዘዞ ድማዛ ክ/ከተማ ኤም.ቲ.ማይ አቢሲኒያ ቲችንግ ኮላጅ የሚገኘዉን ንብረትነቱ የከሳሽ የሆነዉን በመያዣነት የያዘዉን ተከሳሽ በሕጉ አግባብ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ በጨረታ ሽጦ፣ በመያዣነት ያልያዘዉን ሆስፑታል አስረክብ እያለ ስለሆነ፣ ጨረታዉን ሲያወጣዉ ሕጉ የጣለበትን ስርዓት ስላልተከተለ ጨረታዉ ፈርሶ ሆስፑታለን ከበቂ ኪሳራ ጋር ይከፈለን በማለት ከሷል።
በዚህ ክስ ላይ ተከሳሽ ባቀረበዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና አማራጭ መልስ፡ ፍ/ቤቱ ይህን ክርክር ለማየት ስልጣን የለዉም፣ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት ፍ/ቤት በመያዣነት የተሸጠዉን ንብረት የሚመለከት የማየት ስልጣን የለዉም፣ ከሳሽ በብድር ዉለ መሰረት ዔዲዉን በጊዜ ሳይከፍል በመቅረቱ ተከሳሽ ለከሳሽ ጨረታዉ ከመዉጣቱ በፉት የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት በአዱስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ አዉጥቶ ጨረታዉ የፍትሒ ብሓር ስነ ስርዓት ሕጉን ተክትል የሸጠ በመሆኑ፣ ሆስፑታለም የመያዣዉ አካል በመሆኑ በሕጉ አግባብ የተሸጠ ስለሆነ በከሳሽ የደረሰዉ ምንም ጥፊት የለም በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የሰዉ ምስክሮች በመስማት እና የሰነድ ማስረጃ በመመዘን በሰጠዉ ዉሳኔ በከሳሽ እና በተከሳሽ መካከል በተደረገዉ የመያዣ ዉል በመያዣነት የተያዘዉ ኮላጁ ቢሆንም ሆስፑታለ በመያዣነት የተያዛ ባይሆንም በመያዣ በተያዘዉ ንብረት ይዞታ ላይ የተሰራ መሆኑን በሰዉ ምስክሮች እና በክፍለ ክ/ከተማ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ ሆስፑታለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.3066 መሰረት የመያዣ አካል ስለሆነ ተከሳሽ ይህን ሆስፑታል መሸጡ በመያዣነት ያልተያዘ ንብረት ሸጧል የሚያስብል አይደለም፣ ሆስፑታለ በመያዣዉ ስለሚጠቃለል ይህን ንብረት መሸጥ ሕግን የተከተለ ነዉ፤ የጨረታ ሂደቱን በተመለከተ ተከሳሽ ለከሳሽ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠዉ ንብረቱ በጨረታ የተሸጠ ስለሆነ የጨረታዉ ሂደት የስነ ስርዓት ሕጉን እና አዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 6 መሰረት ያላደረገ ነዉ፤ ነገር ግን ጨረታዉ ስርዓትን አልተከተለም በሚል ምክንያት እንዱሰረዝ የሚቀርብ ዲኝነት ፍ/ቤት የማየት ስልጣን የለዉም፣ ጨረታዉ በሥርዓት ባለመካሄደ የንብረቱ ባለቤት ጉዲት የደረሰበት እንደሆነ ግን ካሳ መጠየቅ እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 97/90 ሥር ተመልክቷል፤ ከሳሽ በዚህ ምክንያት ጉዲት ደርሶብኛል የሚል ከሆነ ኪሳራ (ካሳ) በልላ መዝገብ ዲኝነት ከፍል መጠየቅ ይችላል በማለት ወስኗል።
የሥር ከሳሽ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤት ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ መልስ ሰጪዉ ጨረታዉን የፍትሒ ብሓር ሥነሥርዓት ሕጉ እና በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 3 እና 6 መሰረት ያልተደረገ በመሆኑ፣ ጨረታዉ በሕጉ አግባብ ያልተፈጸመ በመሆኑ፣ መልስ ሰጪን ጨረታ ሰረዘነዋል ቀሪ አደርገነዋል፤
መልስ ሰጪዉ በመያዣነት የያዘዉን የይግባኝ ባይ ንብረት በሕጉ አግባብ በግለጽ ሁኔታ ጨረታ አዉጥቶ የመሸጥ መብት አለዉ በማለት የሥር ዉሳኔ በመሻር ወስኗል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የቀረበለትን ይግባኝ ማመልከቻ ዉድቅ በማድረግ የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች የካቲት 12 ቀን 2010 ዓ.ም በተጻፈ ስድስት ገጽ የሰበር አቤቱታ፡ የአሁን ተጠሪ ባቀረበዉ ክስ አመልካች በመያዣነት የያዘዉን ንብረት ሲሸጥ ጨረታዉ ሕጉን ያልተከተለ በመሆኑ ሐራጁ እንዱሰረዝልኝ/እንዱፈርስልኝ በማለት የጠየቀዉን ዲኝነት መደበኛዉ ፍ/ቤት የማየት ስልጣን የላለዉ ሆኖ ሳለ፣ የሐራጅ ሽያጭ የተደረገዉ በፍትሒ ብሓር ሕጉ እና በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት የተፈጸመ ስለሆነ፣ የሥር ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱታረምልን በማለት በዝርዝር አመልክቷል።
ይህ ችልት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ባዘዘዉ መሰረት ግንቦት 3 ቀን 2010 ዓ.ም የተጻፈ አራት ገጽ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት በአጭሩ፡ በዚህ ጉዲይ የሥረ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ በአግባቡ ስለሆነ አመልካች ያቀረበዉ ቅሬታ የሕግ ምክንያት የላለዉ ስለሆነ ዉድቅ እንዱደረግልኝ በማለት በዝርዝር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም የአሁን አመልካች በመያዣነት የያዘዉን ንብረት በጨረታ የሸጠዉ ሕጉን ባልተከተለ ስርዓት በመሆኑ ጨረታዉ እንዱሰረዝልኝ በማለት የአሁን ተጠሪ የጠየቀዉን ዲኝነት መደበኛዉ ፍ/ቤት የማየት ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? የሚለዉን ነጥብ እንደጭብጥ በመያዝ እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በነበረዉ የመያዣ ዉል መነሻነት የአሁን ተጠሪ ኤም.ቲ.ማይ አቢሲኒያ ቲችንግ ኮላጅ በመያዣነት አመልካች እንዱይዝ በማድረግ ገንዘብ ከአመልካች ተበድሮ የነበረ መሆኑን የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ያሳያል። ላላዉ የአሁን ተጠሪ በመያዣነት በያዘዉ ኮልጅ ባረፈዉ ይዞታ ላይ ሆስፑታል የሰራ መሆኑን የሰዉ ምስክሮች እና በአዘዞ ድማዞ ክ/ከተማ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ሆስፑታለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.3066 መሰረት የመያዣ አካል እንደሆነ በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጠዉ ጉዲይ ነዉ። ስለሆነም ይህ ሆስፑታል የመያዣዉ አካል እንደሆነ ስለተረጋገጠ በዚህ ረገድ ይህ ችልት በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር የሚቀበለዉ ይሆናል።
በልላ በኩል መታየት ያለበት ጉዲይ አመልካች ያካሄደዉ የጨረታ ሂደትን የሚመለከት ነዉ። በዚህ ረገድ የሥር ፍ/ቤቶች ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን በተሰጣቸዉ ስልጣን የአሁን አመልካች በመያዣነት የያዘዉን የተጠሪን ንብረት በጨረታ ሲሸጥ የፍትሒ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕጉን እና በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 3 እና 6 ሥር የተመለከተዉን ሂደት ያልተከተለ እንደነበር በማረጋገጥ ዉሳኔ ሰጥቷል። የአሁን አመልካች ይህን ነጥብ በተመለከተ የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ መሆኑን የሚያመለክት ነገር ስለላለ፣ በዚህ አግባብ ይግባኝ ባላቀረበበት ጉዲይ አመልካች ለዚህ ችልት የሚያቀረበዉ ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም።
በመሆኑም የአሁን አመልካች በመያዣ የያዘዉን ንብረት የሸጠበት ሂደት የሕጉን ሂደት ያልተከተለ ነዉ ተብል በሥር ፍ/ቤት የተደረሰበት ድምዲሜ ይህ ችልት ከሚቀበለዉ በስተቀር የሚያርምበት አግባብ የለም ብለናል።
በመቀጠል መታየት ያለበት ጉዲይ የአመልካች ባንክ በመያዣ የያዛቸዉን ንብረት ለመሸጥ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት ለሚፈጽመዉ የሐራጅ ሽያጭ እንዱፈርስልኝ በማለት የሚቀርበዉን የዲኝነት ጥያቄ መደበኛዉ ፍ/ቤት የማየት ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? የሚለዉን ነጥብ ነዉ። ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ ይህ ጉዲይ የአሁን አመልካች በመያዣያነት የያዘዉን የተጠሪን የማይንቀሳቀስ ንብረት በሐራጅ ከመሸጥ ጋር የሚያያዝ መሆኑ ግልጽ ነዉ። በመሆኑም ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያለዉ ሕግ ‹‹በባንክ በመያዣ ስለተያዘ ንብረት የወጣ አዋጅ ቁጥር 97/90›› እንደሆነ የሚያከራከር ጉዲይ አይደለም። በዚህ አዋጅ መሰረት ባንክ በመያዣነት የያዘዉን ንብረት ለመሸጥ ያለዉ ስልጣን፣ ከዚህ ሽያጭ ጋር በተያያዘ መደበኛ ፍ/ቤት ያለዉ ስልጣን፣ በዚህ አዋጅ አግባብ ለተፈጸመ የሐራጅ ሽያጭ ጋር በተያያዘ በምን አግባብ ለመደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩ ላቀርብ እንደሚችል ሁኔታ መታየት ያለባቸዉ ነጥቦች ናቸዉ።
የዚህ አዋጅ ዓላማ ከአዋጁ መግቢያ /preamble/ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን፣ በመግቢያዉ እንደተመለከተዉ ባንኮች በመያዣ የያዙትን ንብረቶች ለመሸጥ መደበኛ ሥነ ሥርዓት ተክትል ለመደበኛ ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ለማስወሰንና ዉሳኔዉን ለማስፈጸም ረጅም ጊዜ በመዉሰደ፤ ባንኮች ገንዘብ አበድረዉ ወለድ በመሰብሰብ ገቢ የማግኘት ሥራቸዉ ላይ ከፍተኛ ተጽዔኖ በማሳደሩ፣ ባንኮች የሚሰጡትን ብድሮች በተቀላጠፈ መንገድ መሰብሰብ እንዱችለ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር አዋጁ ማስፈለጉን ያስገነዝባል። ከዚህም በላይ በአዋጁ አንቀጽ 3 እና 4 እንደተመለከተዉ ባንኮች በመያዣነት የያዙአቸዉን ንብረቶች ተፈላጊዉ ዔዲ ያልተከፈለ እንደሆነ በድንጋጌዎቹ የተመለከተዉን ሥርዓት ተከትል ንብረቶቹን በሐራጅ የመሸጥ እና ለገዢዉ ባለቤትነቱን የማዛወር እና ሁለት ጊዜ ሐራጅ ወጥቶ ያልተሸጠ እንደሆነ ንብረቱን በመያዣ ስምምነቱ ላይ በተመለከተዉ ግምት መዉሰድ እንደሚችለ እና ወደ ስሙ ለማዛወር ስልጣኑ የባንኮች እንደሆነ ማየት ይቻላል። ባንክ ይህን የሐራጅ ሽያጭ ሲያካሄድ እንደአግባብነቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.394--449 ተፈጻሚ ማድረግ እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 6 ሥር ተመልክቷል። ከዚህ ሁለ መገንዘብ እንደሚቻለዉ ባንክ ለዔዲ በመያዣ የያዘዉን ንብረት በሐራጅ በመሸጥ ዋናዉን ገንዘብ እና ወለድ ለመሰብሰብ ለሚያካሄደዉ የሐራጅ ሽያጭ ሂደት ጋር በተያያዘ ስልጣኑ የባንኩ መሆኑን እና መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ማየት እንደማይችል ነዉ። መደበኛ ፍ/ቤት ባንክ ያካሄደዉ የሐራጅ ሽያጭ በአግባብ ነዉ ወይስ አይደለም? የሐራጅ ሽያጩ ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለትን ነጥቦች አይቶ ለመወሰን ስልጣን እንደላለዉ የሚያስገነዝብ ነዉ። መደበኛ ፍ/ቤቶች እነዚህን ነጥቦች በማየት የሐራጅ ሽያጩ የተካሄደዉ በአግባብ ነዉ ወይስ አይደለም? በዚህ ምክንያት ሽያጩ ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለትን በመመርመር የሚወስኑ ከሆኑ ከላይ የተመለከተዉን የአዋጁን ዓላማ ሙለ በሙለ ዋጋ ሚያሳጣ እና የአዋጁንም ተፈጻሚነት የሚገድብ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። በመሆኑም ሕግ አዉጭዉ ባንክ በመያዣ የያዘዉን ንብረት በሐራጅ በመሸጥ ያበደረዉን ገንዘብ መሰብሰብ እንዱችል በአዋጁ የተዘረጋዉን ሥርዓት መደበኛ ፍ/ቤቶች በማክበር ተፈጻሚ ማድረግ ይገባቸዋል እንጂ አዋጁ ለባንክ የሰጠዉን ስልጣን በመንጠቅ ጉዲዩን የማየት ስልጣን አለን በማለት የአዋጁን ዓላማ ዋጋ ማሳጣት የለባቸዉም። ስለሆነም መደበኛ ፍ/ቤት አንድ ባለዔዲ የሐራጅ ሽያጭ ያለ አግባብ የተደረገ ስለሆነ እንዱፈርስልኝ ወይም እንዱሰረዝልኝ በማለት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.445 በመጥቀስ ያቀረበዉን ክስ በመቀበል ክርክር በማካሄድ ዉሳኔ በመስጠት አዋጁ የወጣበትን ዓላማ ዋጋ ማሳጣት የለበትም።
በልላ በኩል ባለዔዲዉ የሐራጅ ሽያጭ በአግባቡ አልተደረገም የሚል ከሆነ በዚህ ምክንያት የደረሰበትን ጉዲት ለይቶ ክስ ማቅረብ እንዲለበት አዋጁ ያሳያል። የአዋጁ አንቀጽ 7 ስለባንክ ተጠያቂነት ሲደነግግ ‹‹ባንክ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 6 የተጠቀሱትን አግባብ ያላቸዉን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ሽያጩን በመፈጸሙ በባለዔዲዉ ላይ ለሚደርሰዉ ጉዲት በኃላፉነት ተጠያቂ ይሆናል›› በማለት ይደነግጋል።
የእንግሉዝኛዉ ቅጅ Liability of of the Bank በማለት <<The Bank shall be liable for any damage it causes to the debtor in the process of selling by auction in violation of the relevant provisions of the civil procedure code specified under Article 6 of this Proclamation>> በማለት ይደነግጋል። ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለዉ አንድ ባለዔዲ ከሐራጅ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ጉዲዩን ለመደበኛ ፍ/ቤት ማቅረብ የሚችለዉ የሐራጅ ሽያጩ ያለ አግባብ ከሕግ ዉጭ የተደረገ ነዉ የሚል ከሆነ፣ በዚህ ምክንያት የደረሰበት ጉዲት ካለ አግባብነት ባለዉ ማስረጃ በማስደገፍ ክስ አቅርቦ ካሳ እንዱከፈለዉ ዲኝነት ከመጠየቅ ዉጭ የሐራጅ ሽያጩ እንዱፈርስ ወይም እንዱሰረዝለት የሚጠይቅበት የሕግ አግባብ የለም። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ደረሰብኝ የሚለዉን ካሳ አግባብነት ባለዉ ማስረጃ በማስደገፍ ስልጣን ላለዉ መደበኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ከመጠየቅ በስተቀር ሐራጁ እንዱፈርስ ክስ ማቅረብ አይችልም።
በመሆኑም መደበኛ ፍ/ቤት በዚህ አዋጅ አግባብ የሚቀርብ ክስ የካሳን ጥያቄ የሚመለከት ካልሆነ በስተቀር ጨረታ እንዱፈርስ በማለት የሚቀርበዉን ክስ ተቀብል ግራ ቀኛቸዉን አከራክሮ ተገቢ የሆነ ዉሳኔ ለመስጠት ስልጣን የለዉም።
ይህን አዋጅ መሰረት በማድረግ ባንክ ያካሄደዉ ሐራጅ እንዱፈርስ የሚል ክስ የቀረበ እንደሆነ፣ ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.9 /1/ እና 231 መሰረት ክሱን ተቀባይነት የለዉም በማለት ለባለጉዲዩ መመለስ ይጠበቅበታል። ነገር ግን ፍ/ቤቱ ክሱን ተቀብልም ቢሆን ጉዲዩን ለማየት የሥረ ነገር ስልጣን የላለዉ በመሆኑ፣ በልላ ተከራከሪ ወገን መቃወሚያ ቢቀርብም ባይቀርብም፣ ፍ/ቤቱ ይህን ጉዲይ ለማየት ስልጣን እንደላለዉ በተገነዘበ ጊዜ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.244 /2/ /ሀ/ እና 245 /2/ መሰረት ክሱን ዉድቅ በማድረግ መዝገቡን መዝጋት አለበት።
በዚህ መሰረት አሁን የተያዘዉ ጉዲይ ሲታይ የአሁን ተጠሪ አመልካች ያካሄደዉ ጨረታ ሂደቱን ያልተከተለ ስለሆነ ጨረታዉ እንዱፈርስልኝ በማለት በመደበኛ ፍ/ቤት ዲኝነት የማቅረብ መብት የለዉም፣ ተጠሪ ክስ ቢያቀርብም አመልካች ባቀረበዉ መቃወሚያ መሰረት ይህን ነጥብ በተመለከተ ግራ ቀኛቸዉን አከራክሮ ለመወሰን የሥረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት በዚህ ረገድ የተጠሪን የዲኝነት ጥያቄ ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህን ዉሳኔ ሳያርመዉ በትዕዛዝ በማጽናት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ።
ሲጠቃለል የሥር የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች በመያዣ የያዘዉን ንብረት በተመለከተ ያካሄዉ ጨረታ የሕጉን ሂደት ያልተከተለ ነዉ በማለት ጨረታዉ እንዱፈርስልኝ በማለት ተጠሪ ያቀረበዉን የዲኝነት ጥያቄ ተቀብል አይቶ ለመወሰን የሥረ ነገር ስልጣን ሳይኖራቸዉ፣ በዚህ ነጥብ ላይ ጉዲዩን በማየት ጨረታዉ ሉሰረዝ ይገባል፣ አመልካች በሕግ አግባብ ጨረታዉን በግልጽ እንዱያካሄድ መብት ተጠብቋል በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ የሚከተለዉ ተወስኗል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ.01-00929 ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህን ዉሳኔ በማጽናት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.149867 በ5/4/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.01-29474 በ2/5/2009 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለዉ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ጸንቷል።
የአሁን ተጠሪ የአመልካች ባንክ ለዔዲ ምክንያት በመያዣነት የያዘዉን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት በሐራጅ ከመሸጥ ጋር በተያያዘ የሐራጅ ሽያጩ የሕጉን ሂደት ያልተከተለ ስለሆነ እንዱፈርስልኝ በማለት የጠየቀዉን ዲኝነት መደበኛ ፍ/ቤት ተቀብል አይቶ ለመወሰን ስልጣን የለዉም። የአሁን ተጠሪ በአመልካች በተደረገዉ የጨረታ ሂደት ምክንያት የደረሰባቸዉ ጉዲት ያለ እንደሆነ የአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 7 በሚደነግገዉ እና በሕጉ አግባብ በመደበኛ ፍ/ቤት ክስ በማቅረብ ካሳ ከመጠየቅ ይህ ዉሳኔ የሚከለክላቸዉ አይሆንም ብለናል።
ግራ ቀኛቸዉ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ሰኔ 18 ቀን 2010 ዓ.ም የተሰጠዉ እግድ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
No topics extracted.