No summary available.
ሰ/መ/ቁ/ 166392 ሚያዚያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ዳኞች፡- ሰለሞን አረዲ ብርሃኑ አመነዉ ተሾመ ሽፈራዉ ሐብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ አመልካች፡- ሚ/ር ሳሚ ሳዱቅ ራቲብ ተጠሪ፡-
ለዚህ ሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 158393 በመስከረም 23 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ ነዉ። አመልካች በህዲር 11 ቀን 2011 ዓ.ም ፅፈዉ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ዉሳኔዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስላለበት ይታረምልን በማለት ያመለከቱ ሲሆን የሰበር አጣሪ ችልትም አቤቱታዉን መርምሮ ያስቀርባል በማለት መዝገቡ ለችልት ቀርቦ ግራ ቀኙ እንዱከራከሩበት ትዕዛዝ ሰጥቶ በፅሐፍ ክርክራቸዉን አቅርቦል።
የጉዲዩን አመጣጥ ስንመለከት ክርክሩ በተጀመረበት በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክስ የአቢሲኒያ ስላዉተር ሰርቪስ ኃ/ የተ/የግ/ ኩባኒያ (የአሁን ሁለተኛ ተጠሪ) ዉስጥ የ50% አክሲዮን ድርሻ የነበረኝ ሲሆን ይህን ድርሻ በብር 35,000,000 (በሰላ አምስት ሚሉዬን ብር) ለአሁን 1ኛ ተጠሪና በስር ከ/ፍ/ቤት 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ለነበሩት ለአቶ ሶሻል በየነ ወዲጆ እና አቶ ኤፋሶን ታደሰ ወላንሳ የሸጥኩ ቢሆንም ምንም ባልተገነዘብኩት ሁኔታ የአክሲዮን ሽያጭ ሂሳቡ ብር 24,000,000 (ሀያ አራት ሚሉዬን ብር) ተብል ተጽፎል። የአክሲዮን ሽያጭ ዝዉዉሩ ከመፈፀሙ በፉት ከተጠሪዎች ጋር የወጪ ቀሪ የሑሳብ መተሳሰብ ተደራርጎ ማናቸዉም ወጪዎችና ዔዲዎች ሁለ ከተቀናነሱ በኋላ ለአመልካች የሚደርሰዉ ንፁሁ የጥሬ ገንዘብ መጠን ብር 14,600,000 (አስራ አራት ሚሉዬን ስድስት መቶ ሺህ ብር) እንደሆነ ስምምነት ላይ ተደርሶ በወቅቱ ተጠሪዎች ይህን ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል ገንዘብ ስላልነበራቸዉ በተለያየ ጊዜያት የሚከፈለ በጠቅላላዉ የብር 14,600,000 (አስራ አራት ሚሉዬን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ዋጋ ያላቸዉ ሦስት ቼኮች ለአመልካች እንዱሰጣቸዉ ተደርጓል። በ1ኛ ተጠሪ ተፈርሞ የወጡና ንብረትነታቸዉ የ2ኛ ተጠሪ የሆኑት ክርክር የተነሳባቸዉ ቼኮች ሀ) ቁ. የብር 4,500,000 (አራት ሚሉዬን አምስት መቶ ሺህ ብር) ዋጋ ያለዉ በየካቲት 3 ቀን 2007 ዓ.ም የሚከፈል፣ ለ) ቁ. የብር 4,500,000 (አራት ሚሉዬን አምስት መቶ ሺህ ብር) ዋጋ ያለዉ በመጋቢት 3 ቀን 2007 ዓ.ም የሚከፈል፣ ሐ) ቁ.
የብር 5,600,000 (አምስት ሚሉዬን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ዋጋ ያለዉ በሚያዚያ 2 ቀን 2007 ዓ.ም የሚመነዘር የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲሆኑ አመልካች ቼኮቹን በእጁ ይዞ ጫና እንዲይፈጥር በማሰብ በስምምነት የአመልካችና የ1ኛ ተጠሪ የጋራ ጓደኛ በሆኑት በአቶ ጌታቸዉ ተገኔ እጅ እንዱቀመጡ ተደርጓል። ቼኮቹ የሚመነዘሩበት ጊዜ በተደጋጋሚ በማለፈና ተጠሪዎችም ቃላቸዉን በየጊዜዉ በማጠፊቸዉና የማይፈፅሙ መሆኑ ሲታወቅ ቼኮቹ ከአቶ ጌታቸዉ ተገኔ እጅ ለአመልካች ተመልሷል። ቼኮቹ ለአመልካች መመለሳቸዉን ከተረደ በኋላ 1ኛ ተጠሪ ብር 150,000 (መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)) (በቼክ ቁ. ) እና ብር 2,000,000 (ሁለት ሚሉዬን) በሁለት ቼኮች (አንድ ሚሉዬን ብር በቼክ ቁ. ፣ ላላ አንድ ሚሉዬን ብር በቼክ ቁ. 151) ክፍያ ፈፅሞ ቀሪዉን ገንዘብ ለመክፈል ጊዜ ሲጠይቁ ቆይቷል። በተጨማሪም በፍ/ቤት ትዕዛዝ መሰረት ለአመልካች የዔዲ ገንዘብ ብር 1,000,000 (አንድ ሚሉዬን ብር) ከፍሎል። ባጠቃላይ 1ኛ ተጠሪ ለአመልካች ብር 3,150,000 (ሦስት ሚሉዬን አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ስለከፈለ እነዚህን የተጠቀሱትን ክፍያዎች ለመቀናነስ በማለት ከላይ በተራ ቁ. (ሐ) ላይ የተጠቀሰዉን የቼክ ቁጥር ለ1ኛ ተጠሪ ተመልሶ ክፍያዎቹ ከተቀናነሱ በኋላ ተጠሪ ለልዩነቱ ብር 2,450,000 (ሁለት ሚሉዬን አራት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) የቼክ ቁ. ለአመልካች ሰጥቷል። በጠቅላላዉ ተጠሪዎች ለአመልካች መክፈል ከሚገባቸዉ ብር 14,600,000 (አስራ አራት ሚሉዬን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ላይ የብር 3,150,000 (ሦስት ሚሉዬን አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ክፍያ የፈፀሙ ሲሆን መክፈል ያለባቸዉ ቀሪ ገንዘብ ብር 11,450,000 (አስራ አንድ ሚሉዬን አራት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ነዉ።
አመልካችም ቀሪዉ ገንዘብ እንድከፈለዉ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ፈቃደኛ አልሆኑም። ሦስቱንም ቼኮች አመልካች ለከፊዩ ባንክ ቢያቀርብም በቼኮቹ ክፍያ እንዲይፈፀም 1ኛ ተጠሪ አሳግዶል። በመሆኑም ተጠሪዎች ባልተነጣጠለ ኃላፉነት እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል። ተጠሪዎችም ለስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት መልስ በዋናነት ለዚህ ሰበር ችልት ጽፈዉ ባቀረቡት መልስ ዉስጥ የተመለከቱትን የመከላከያ ነጥቦች (ከታች ባጭሩ እንደቀረበዉ) በመጥቀስ በሽያጭ ላስተላለፈት የአክሲዮን ድርሻቸዉ ሙለ ዋጋ የተከፈላቸዉ ስለሆነ በቼኮቹ ላይ የተመለከተዉን ገንዘብ የመክፈል ኃላፉነት ስለላለባቸዉ ክሱ ዉድቅ ተደርጎ ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብታቸዉ ተጠብቆላቸዉ በነፃ እንዱያሰናብታቸዉ ጠይቆ እንደነበር የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገብ ያሳያል። የስር ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በአንድ በኩል ቼኮቹ ክፍያ እንዲይፈፀምባቸዉ መታገዲቸዉን ያረጋገጠ ሲሆን በልላ በኩል አመልካች ከተለያየ አካላት ለነበራቸዉ ዔዲዎች የተከፈለ ብር 13,576,274.40 (አስራ ሶስት ሚሉዬን አምስት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ አራት ከ40/100፤ ከዚህ ዉስጥ ለወጋገን ባንክ ብር 8,559,274.40 (ስምንት ሚሉዬን አምስት መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሰባ አራት ብር ከ40/100 ሳንቲም) እና አቶ ሽፈሬ ለተባለ ብር 5,017,000 (አምስት ሚሉዬን አስራ ሰባት ሺህ ብር) እንዱሁም አመልካች በተለያየ ጊዜ እየመነዘረ የወሰዲቸዉን ክፍያዎች ጨምሮ በጠቅላላዉ ብር 18,526,274.40 (አስራ ስምንት ሚሉዬን አምስት መቶ ሀያ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ አራት ብር ከ40/100 ሳንቲም) ስለሆነ 1ኛ ተጠሪ ለአመልካች መክፈል ያለበት ብር 1,113,725.60 (አንድ ሚሉዬን አንድ መቶ አስራ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ አምስት ብር ከ60/100) ብቻ ነዉ፤ በቼኮቹ ላይ የተመለከተዉን ገንዘብ የመክፈል ግዳታ የለበትም፤ 2ኛ ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም በማለት ዉሳኔ ሰጥቷል። አመልካችም በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ ቅሬታ ለፋ/ጠ/ፍ/ ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱም ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ በሰጠዉ ዉሳኔ የስር ከፍተኛ ፍ/ቤትን ዉሳኔ በሁለት ነጥቦች በማሻሻል ዉሳኔ ሰጥቷል። አንደኛ የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ከተጠሪ ለአመልካች መከፈል ስለነበረበት ቀሪ ገንዘብ ያደረገዉ ስላትና የደረሰበት ድምዲሜ የተሳሳተ ነዉ በማለት ጠቅላላ የአክሲዮን ሽያጩ ዋጋ ብር 24,000,000 (ሀያ አራት ሚሉዬን ብር) ስለሆነ ተጠሪ በተለያየ ጊዜ ለአመልካች ከፍያለዉ ያላቸዉን 20,526,244.40 (ሀያ ሚሉዬን አምስት መቶ ሀያ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ አርባ አራት ብር ከ40/100 ሳንቲም) በመቀነስ ቀሪ ገንዘቡ 3,447,756 (ሶስት ሚሉዬን አራት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ስድስት ብር) እንዱከፍል በማለት ወስኗል። ሁለተኛ የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት 2ኛ ተጠሪን ምንም ሳይል በዝምታ ከክሱ ያስወጣዉ አግባብ አይደለም በማለት 2ኛ ተጠሪም ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በአንድነትና በነጠላ ተጠያቂ ነዉ በማለት ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታም ከላይ የተጠቀሱትን የስር ፍ/ቤቶችን ዉሳኔ ለማሳረም የቀረበ ማመልከቻ ነዉ። አመልካችም በሰበር አቤቱታቸዉ ላይ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞባቸዋል ያለበትን ነጥቦች በመዘርዘር ተከራክሯል። ያቀረበዉም ክርክር ባጭሩ እንደሚከተለዉ ነዉ።
1ኛ ቼኮቹ ከተጠሪዎች ለአመልካች የተሰጡት አመልካች በ2ኛ ተጠሪ ዉስጥ ለነበራቸዉ የአክሲዮን ድርሻ ለሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት በሐምል 17 ቀን 2006 ቀርቦ ለፀደቀዉ ሽያጭ ዋጋ መክፈያ መሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። ተጠሪዎች ግን ቼኮቹ ለዋስትና ነው የሚል ክርክር ቢያቀርቡም በዚህ በኩል የተደረገ ስምምነት ስለመኖሩ ያቀረቡት ማስረጃም ሆነ ዉል የለም። የዋስትና ስምምነት በሰነድ በሚደረግ ስምምነት ብቻ የሚረጋገጥ ነዉ። ቼኮቹ የተሰጡት ለዋስትና ቢሆን ኖሮ የክፍያ ጊዜያቸዉ የተለያዩ ሦስት ቼኮችን መስጠት ባላስፈለገ ነበር። ለዋስትና የድምር ሂሳብ የሚያሳይ አንድ ቼክ በቂ ነበር። ለዋስትና ተሰጥቶል ቢባልም ለምን በክሱ መሰረት ለሆኑት ቼኮች ዋጋ መጠን ስለመሰጠታቸዉ መከራከሪያ አላቀረቡም። የስር ፍ/ቤትም ምንም የሰነድ ማስረጃ ባልቀረበበት በጉዲዩ ላይ ቀጥታ ተከሳሽ የሆኑትን ግለሰቦች ቃል ላይ ብቻ ተሞርክዞ ቼኮቹ ወደፉት ሂሳብ ለመተሳሰብ በማሰብ ለአመልካች እንደተሰጠ አድርጎ የተጠቀሰዉን ዉሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ።
1ኛ ተጠሪ በመስኩ በቂ እዉቀትና ልምድ ያለዉ ሰዉ ሆኖ ሳለ ለወጋገን ባንክና ለአቶ ሽፈሬ ለተባለ ግለሰብ ተፈፀሙ የተባለትን ክፍያዎች ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ቼኮች ከመሰጠታቸዉ በፉት በማያሻማ መልኩ የሚታወቁ ሆኖ እያለ ወደፉት ለመተሳሰብ ብል ከአስራ አንድ ሚሉዬን ብር በላይ ዋጋ ያላቸዉን ቼኮች ሰጠ መባለ ተቀባይነት የለዉም። ለወጋገን ባንክ ተከፈለ የተባለዉ ክፍያም ቼኮቹ ከመሰጠታቸዉ አስቀድሞ በቀን 23/05/2006 ዓ.ም ሲሆን ክፍያዉም የተፈፀመዉ ሼባ ትራንስፕርት ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ እንጂ በ1ኛ ተጠሪ አይደለም። ለአቶ ሽፈሬ የተከፈለዉ ክፍያ በተመለከተ በተጠሪና ግለሰቡ መካከል በተደረገ ስምምነት ሲሆን አመልካች በዚህ የስምምነት ሰነድ ላይ አልተስማሙም፤
አልፈረሙም፤ ሰነደም ደግሞ የተፈረመዉ ለዚህ ክርክር ምክንያት የሆኑት ቼኮች ከመሰጠታቸዉ ከወራት በፉት ሆኖ እያለ የስር ፍ/ቤት በሰነደ ላይ የተመለከተዉን ገንዘብ ከቼኮቹ ዋጋ ላይ ተቀናሽ ሉደረጉ ይገባል ማለቱ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባል።
2ኛ የስር ፍ/ቤት አስቀድሞ የተቀናነሱትን ክፍያዎች መልሶ በድጋሚ አመልካች ከያዙት ቼክ ዋጋ ላይ መቀነሱ ስህተት ነው። 1ኛ ተጠሪ በቼክ ቁጥሮች ፣ ፤ 151 በድምሩ ብር 4,950,000 (አራት ሚሉዬን ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) ከፍያለሁ ብልም ለአመልካች የተከፈለዉ ጠቅላላ ብር 3,150,000 (ሦስት ሚሉዬን አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ዉጪ (በፍ/ቤት ትዕዛዝ መሰረት የተከፈለዉንና በቼክ ቁጥሮች ፣ ና 151 የተከፈለትን ክፍያዎች ጨምሮ) ከተጠሪ ለአመልካች የፈፀመዉ ላላ ክፍያ የለም።
3ኛ የአመልካችና የተጠሪ የጋራ ምስክር ሆኖ የቀረቡት አቶ ጌታቸዉ ተገኔ ቼኮቹ ለአመልካች የተሰጡት አሰቀድሞ የነበሩት ሂሳቦች ተቀናንሰዉ ለአመልካች ሉከፈል የሚገባ ገንዘብ መጠን የተሰሩ ስለመሆናቸዉ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ሳይቀበል የራሳቸዉ የተከሳሾችን የምስክር ቃል ክብደት በመስጠት ፍርድ መስጠቱ ስህተት ነው። በተጨማሪም የሁለት ቼኮችን ቁጥር (- ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር) ገንዘብ መጠኑም ያልተገለፀ) በመጥቀስ በእነዚህ ቼኮች የተከፈለዉ ለክርክሩ መነሻ የሆኑት ቼኮች ከመሰጠታቸዉ በፉት መሆኑን ሰነድቹ ራሳቸዉ የሚያረጋግጡ ሆኖ ሳለ ወደፉት ከተሰጠ ቼክ ላይ ታሳቢ መደረጉ ስህተት ነዉ።
ስለሆነም ለክርክሩ መነሻ በሆኑት በቼክ ቁ. ፣ እና ላይ የተመለከቱት ጠቅላላ ብር 11,450,000 (አስራ አንድ ሚሉዬን አራት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ተጠሪዎች ለአመልካች እንዱከፍለ እንዱወሰንለትና ለዚህ ክርክር የወጡትን ወጪዎችና ኪሳራዎችና ህጋዊ ወለድ ተጠሪ ለአመልካች እንዱተኩ እንዱወሰንለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተጠሪዎች በጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም በጋራ ፅፈዉ ባቀረቡት መልስ 1ኛ የአመልካች የሰበር አቤቱታም ሆነ በሰበር አጣሪ ችልት ያስቀርባል በማለት የተያዘዉ ጭብጥ የፍሬ ነገር ጉዲዮችን እንጂ የህግ ስህተቶችን የሚመለከቱ አይደለም። የሰበር ችልቱ ደግሞ የሚመለከታቸዉ ጉዲዮች ወይም አቤቱታዎች በስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔዎች ላይ የተፈፀሙትን መሰረታዊ የህግ ስህተቶችን በተመለከተ ብቻ ነዉ። በስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ የተፈፀመ ስህተት የለም እንጂ ቢኖርም እንኳን ስህተት የተባለትና የቅሬታ ነጥቦች የፍሬ ነገር ጉዲዮችን የተመለከቱ ሆነዉ ባለበት ሁኔታ ይህ የሰበር ችልት የአመልካችን ማመልከቻ ተቀብል የመወሰን ስልጣን የለዉም።
2ኛ አመልካችና 1ኛ ተጠሪ የብር 35,000,000 (ሰላሳ አምስት ሚሉዬን ብር) የአክሲዮን ሽያጭ ስምምነት አላደረጉም፤ አመልካችም ይህን ያህል የሚያወጣ ድርሻም በኩባኒያዉ ዉስጥ አልነበራቸዉም።
ለዚህም የቀረበ ማስረጃ የለም። በስር ፍ/ቤት አሻሽል ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ አመልካች በ2ኛ ተጠሪ ዉስጥ የነበራቸዉ የአክሲዮን ብዛት 2454 የአንደ የአክሲዮን ድርሻ ዋጋ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሆኖ ጠቅላላ የሽያጭ ዋጋቸዉ 24,540,000 (ሀያ አራት ሚሉዬን አምስት መቶ አርባ ሺህ) ከሆነዉ ድርሻ ዉስጥ ለ1ኛ ተጠሪ የተሸጠዉ 1964 አክሲዮን ዋጋቸዉ ብር 19,640,000 (አስራ ዘጠኝ ሚሉዬን ስድስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ ብር) ሆኖ የተቀሩት ደግሞ ለላልች ግለሰቦች መሆኑንና ይህም አመልካችን ጨምሮ ላልች የኩባንያዉ ባለድርሻዎችና አባላት በሐምል 17 ቀን 2006 ዓ.ም ባደረጉት ጉባኤና በተያዘዉ ቃለ-ጉባኤ ተረጋግጦ ለሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ቀርቦ የተመዘገበ ሲሆን ሰነደም ለስር ፍ/ቤት በማስረጃነት ቀርቧል። በተጨማሪም ተጠሪ ለአመልካች የብር 14,600,000 (አስራ አራት ሚሉዬን ስድስት መቶ ሺህ ብር) የያዘ ቼክ ለአመልካች አልሰጠም፤ ስለመሰጠቱም የቀረበ ማስረጃ የለም፤ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገ የሑሳብ መተሳሰብ የለም፤ ስለመደረጉም የቀረበዉ ማስረጃ የለም።
3ኛ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ ያስተላለፈትን የአክስዮን ሽያጭ አከፊፈልን በተመለከተ 2ኛ ተጠሪ እንደ ኩባንያ ከመመስረቱ በፉት አመልካች በግል ንግድነት ይዘዉት በነበረዉ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የንግድ የግል ግንኙነት (personal relationship) ተመስርቶ የቆየ ሲሆን በዚህን ጊዜ አመልካች የድርጅቱን ፏላንትና ማሽነሪዎች አስይዘዉ ከወጋገን ባንክ አ.ማ ለተበደሩት ብር 8,559,274.40 (ስምንት ሚሉዬን አምስት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሰባ አራት ከ40/100) ለመክፈል ባለመቻላቸዉ ባንኩም በመያዣነት የያዛቸዉን ንብረቶች በሀራጅ ለመሸጥ በሂደት ላይ ስለነበር አመልካች በ1ኛ ተጠሪና በላልች አስማሚ ግለሰቦች በጋራ ባደረጉት የማስማማት ሂደት 1ኛ ተጠሪ የአመልካችን የባንክ ዔዲ ሙለ በሙለ ከፍል ከዔዲዉ ነፃ የሆኑ ሲሆን ወደፉት 2ኛ ተጠሪ የሆነዉ ኩባንያ ሲመሰረት አመልካች ከሚያስተላልፈለት የአክሲዮን ድርሻዎች ሙለ ወይም ከፉል ዋጋ መክፈያነትም ለባንኩና ከላልች ግለሰቦች የነበሩባቸዉና የተከፈለላቸዉ የዔዲ ገንዘቦች በታሳቢነት እንዱያዝ አስማሚ ሽማግላዎች በተገኙበት ግራ ቀኙ ተስማምቶ ነበር። 1ኛ ተጠሪ ለዋስትና ዓላማ ለአመልካች የሰጡት ቼኮች ብር 11,450,000 (አስራ አንድ ሚሉዬን አራት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) ነዉ።
የተሰጡበትም አግባብ አመልካች በ2ኛ ተጠሪ ዉስጥ ከነበረዉ የአክሲዮን ድርሻዎች ዉስጥ የብር 19,640,000 (አስራ ዘጠኝ ሚሉዬን ስድስት መቶ አርባ ሺህ) ዋጋ ያላቸውን ድርሻዎችን ጁላይ 24/2014 (ሐምል 17 ቀን 2006) በተደረገ ቃለ ጉባኤ አማካኝነት ለ1ኛ ተጠሪ በማስተላለፊቸዉ ሲሆን ስምምነቱ ለሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ቀርቦ መፈረምና መረጋገጥ ስለነበረበት አመልካች ቀደም ባለዉ ጊዜያት ለነበሩባቸዉ የገንዘብ ዔዲዎች በ1ኛ ተጠሪ የተከፈለላቸዉና በቼኮች የተከፈሎቸዉ መሆኑን አምነዉ ነበር። ነገር ግን አመልካች ያስተላለፈትን ድርሻ ዋጋ የሚያሟላ በልዩነት ሉኖር የሚችልን ክፍያ ሉሸፍን የሚችልና በ2ኛ ተጠሪ ኩባንያ ስም የወጡ ቼኮች በዋስትና ወይም ለክፍያ መተማመኛነት ካልተሰጠኝ ቃለ-ጉባኤዉ እንዱፈረምና እንዱረጋገጥ አላደርግም ስላለ ላልች ሰዎች በጉዲዩ ገብተዉ እንዱያሸማግሎቸዉ ተደርጎ እነዚሁ ግለሰቦች በተገኙበት የተጠቀሰዉን የብር መጠን የያዙ ሦስት ፕስት ዳትድ ቼኮች በግራ ቀኙ መካከል የሂሳብ ሥራ እሰከሚከናወን ድረስ ለባንኩ ቀርቦ ክፍያ እዱፈፀምባቸው ሳይሆን ለክፍያ መተማመኛና ለዋስትና ዓላማ ብቻ ተሰጥቷቸዉ ቼኮቹም አቶ ጌታቸው ተገኔ በተባለ ግለሰብ እጅ በአደራ እንዱቀመጡ ተደርጓል። የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.
24435 የካቲት 4 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለዉ ችልት ቼክ ለዋስትና ያለ ምንም ፍርማሉቲ ላሰጥ እንደሚችል በሰጠዉ አስገዲጅ ትርጉም መሰረት ተጠሪ ለአመልካች ሦስቱን ቼኮች መስጠታቸዉ ህገወጥ ሉያሰኛቸዉና ቼክ በዋስትና ላሰጥ ስለማይችል አመልካች በቼኮቹ ላይ የተመለከተዉ ገንዘብ ሉከፈለኝ ይገባል ለማለት አይችልም። የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ 1ኛ ተጠሪ በሽያጭ ለተላለፈላቸዉ የብር 19,640,000 (አስራ ዘጠኝ ሚሉዬን ስድስት መቶ አርባ ሺህ ብር) አክሲዮን ድርሻ ዉስጥ ብር 18,526,274.40 (አስራ ስምንት ሚሉዬን አምስት መቶ ሀያ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ አራት ብር ከ40/100 ሳንቲም) ለአመልካች የከፈለ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ ሦስቱ ቼኮች የተሰጡበት የዋስትና ዓላማ የተሟላና ዋስትናዉ የወረደ በመሆኑ አመልካች በቼኮቹ ላይ የተመለከተዉን ብር 11,450,000 (አስራ አንድ ሚሉዬን አራት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) ይከፈለኝ በማለት በድጋሚ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም። ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ የሚነቀፍበትና የተፈፀመበት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለትና በማፅናት ያለአግባብ የቀረበዉን የአመልካች አቤቱታና የክፍያ ጥያቄ ዉድቅ በማድረግ ከበቂ የወጪና ኪሳራ ክፍያ ጋር ተጠሪዎችን በነፃ እንዱያሰናብት ጠይቋል።
አመልካች በበኩለ በየካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባቀረበዉ የመልስ መልስ ላይ በዋናነት አቤቱታቸዉን አጠናክረዉ ተከራከራክረዋል። በተለይም ተጠሪዎች ከሰበር ችልቱ ስልጣን አንፃር ላነሱት መቃወሚያ በሰጡት የመ/መልስ ላይ በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል ያለዉ አለመግባባትና ለሰበር ሰሚዉ ችልት ያደረሰን ጉዲይ ቼክ ከተሰጠ በኋላ ለክፍያ ሉከለከል የሚገባበት አግባብ፣ ቼክ ለክፍያ ከተሰጠ በኋላ ወይም ቼክ ከመሰጠቱ በፉት የተፈፀሙ ክፍያዎች ከቼኩ ዋጋ ላይ ይቀነሱ ወይም ይታሰቡ የሚለዉ መሰረታዊ የህግ ትርጉም የሚሻና የሰበር ሰሚዉ ፍ/ቤት ሥልጣን ስር የሚወድቅ ነዉ በማለት ተከራክረዋል። በተጨማሪም ቼክ ለዋስትና የሚሰጥበት አግባብ የህግ ትርጉም የሚያሻዉ ጉዲይ ነዉ። ለሰበር ችልቱ የቀረበዉ ክርክር እና በአጣሪ ቼልት የተያዘዉ ጭብጥ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ሦስት ቼኮች ለአመልካች ከመሰጠታቸዉ በፉት 1ኛ ተጠሪ ለአመልካች ከፍያለዉ ያላቸዉ ክፍያዎች ወደፉት እንዱከፍለ ከሰጡዋቸዉ ቼኮች ዋጋ ላይ ሉቀነሱ ይገባል ወይም አይገባም የሚለዉን የህግ መርህ ላይ ጭምር ስለሆነና አመልካችም ከስር ፍ/ቤት ጀምሮ እያቀረበ ያለዉ ክርክር ስለሆነ ተጠሪዎች በዚህ ዙሪያ ያነሱት ክርክር የህግ መሰረት የለዉም በማለት ተከራክሯል።
የጉዲዪ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልትም መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም የሰበር አጣሪ ችልቱ ያስቀርባል በማለት ከተያዘዉ ጭብጥ በተጨማሪ በሰበር ችልቱ ለተነሱት ክርክሮች እልባት ለመስጠት ከመሰረቱ ምላሽ ማግኘት ያለባቸዉ መሰረታዊ የህግ ክርክሮች (ጭብጦች)፡-
ቼክ ለዋስትና/ ለመያዣነት በሚሰጥበት ጊዜ መሟላት ያለበት በህግ የተቀመጠ ፍርም አለ ወይስ የለም?
በቼክ ባለዔዲ የሆነ አዉጪ ባለዔዲ የሆነበትን ቼክ ለአምጪዉ ፈርሞ ከሰጠ ወይም ካወጣ በኋላ ቼኩ ከመስጠቱ አስቀድሞ በአምጪዉ ላይ የነበረዉንና ተለይቶ የሚታወቅ ዔዲን ከቼኩ ዋጋ ላይ ሉቀንስ የሚችልበት የህግ አግባብ አለ ወይ? ሂሳብ ከተሳሰቡ በኋላ ክርክር የተነሳበትን ቼክ ፈርሞ በሚሰጥበት ጊዜ አስቀድሞ ከአምጪዉ ላይ የነበሩትን ዔዲዎች ታሰቢ አላደረገም የሚለዉ ክርክር ተቀባይነት ሉኖረዉ ይችላል ወይ? የሚለት ናቸዉ።
ይህ ችልት መዝገቡን መርምሮ እንደተረዲዉ በግራ ቀኙ መካከል የአክሲዮን ሽያጭ ስለመኖሩ፣ ለስር ፍ/ቤት የቀረበዉ የሽያጭ ዉል ሰነድ (በሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ቀርቦ የተረጋገጠዉ) የጠቅላላ የአክሲዮን ሽያጭ ዋጋ ብር 24,540,000 (ሀያ አራት ሚሉዬን አምስት መቶ አርባ ሺህ ብር) ስለመሆኑ፣ በአክሲዮን ሽያጩ ላይ የስም ዝዉዉር ከመደረጉ በፉት ከተጠሪዎች የ14,600,000 (አስራ አራት ሚሉዬን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ዋጋ ያላቸዉና የተለያዩ የመክፈያ ጊዜ ያላቸዉ ሦስት ቼኮች (ቁጥራቸዉ ከላይ የተገለፁት) ለአመልካች ስለመሰጠታቸዉና እነዚህም ቼኮች የግራ ቀኙ የጋራ ጓደኛ በሆኑት በአቶ ጌታቸዉ ተገኔ እጅ ስለመቀመጣቸዉ፣ የተባለት ቼኮች የመክፈያቸዉ ጊዜ በተደጋጋሚ ከማለፈ የተነሳ አቶ ጌታቸዉ ተገኔ ቼኮቹን ለአመልካች እንደመለሰ፣ ይህን ተከትል 1ኛ ተጠሪ በተለያየ ጊዜ የተወሰኑ ክፍያዎችን በጠቅላላዉ የብር 3,150,000 (ሶስት ሚሉዬን አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) ለአመልካች እንደከፈለ፤ በኋላ ላይ የብር 2,450,000 (ሁለት ሚሉዬን አራት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) ዋጋ ያለዉ ቼክ ቁ. 889784 ከተጠሪ ለአመልካች እንደተሰጠና ጠቅላላ ዋጋቸዉ ብር 11,450,000 (አሥራ አንድ ሚሉዬን አራት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) የሆኑ ሦስት ቼኮች በአመልካች እጅ እያለ ክፍያ እንዲይፈፀምባቸዉ በ1ኛ ተጠሪ ትዕዛዝ ስለመታገዲቸዉ ከግራ ቀኙ ክርክርና በዚህ ችልት ትዕዛዝ መሰረት ቀርቦ ከታየዉ የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገብ ለማረጋገጥ ተችሎል። በተጨማሪም ክርክር የተነሳባቸዉን እነዚህን የ2ኛ ተጠሪ ንብረት የሆኑት ሦስት ቼኮች በ1ኛ ተጠሪ ፈራሚነት ለአመልካች ከመሰጠታቸዉ ቀደም ብል አመልካችና 1ኛ ተጠሪ የግል የንግድ ግንኙነት እንደነበራቸዉና የአመልካች የተለያዩ ዔዲዎች በ1ኛ ተጠሪና በ1ኛ ተጠሪ ድርጅት በኩል እንደተፈፀመለት፤ በዚህም ምክንያት የአመልካችና የአቶ ሽፈሬ በነበረዉ 2ኛ ተጠሪ ድርጅት ዉስጥ 1ኛ ተጠሪ ድርሻ እንዱኖረዉና በስተመጨረሻም አመልካች የነበረዉን የ50% ድርሻ ሙለ በሙለ ከላይ በሰነድ በተረጋገጠዉ ጠቅላላ ዋጋ ለዚሁ 1ኛ ተጠሪ እና በሥር ፍ/ቤት 2ኛና 3ኛ ተከሳሽ ለነበሩት ከመሸጡ የተነሳ 1ኛ ተጠሪ በኩባንያዉ ዉስጥ የላቀ ድርሻ (ወደ 90%) እንዱኖረዉ ማስቻለንም ከቀረበዉ መዝገብ ለማረጋገጥ ተችሎል።
አሁን ክርክር ሆኖ የተነሳዉ መሰረታዊ ጉዲይ ሦስቱ ቼኮች ለአመልካች ከመሰጠታቸዉ በፉት በ1ኛ ተጠሪና በድርጅቱ አማካኝነት የአመልካች ዔዲዎችን ለመክፈል የተፈፀሙ ክፍያዎችና ለአመልካች የተሰጡ የሦስቱ ቼኮች ጠቅላላ ድምር ዋጋ መካከል ያለዉ ግንኙነት ነዉ። አመልካች የሚከራከረዉ ቀድሞ የነበሩት ዔዲዎችን በሙለ ከተሳሰብን በኋላ ከጠቅላላዉ የሽያጭ ዋጋ ላይ ተቀናንሰዉ ቀሪዉ ብር 14,600,000 (አስራ አራት ሚሉዬን ስድስት መቶ ሺህ) ተጠሪዎች በወቅቱ ለመክፈል አቅም ስላልነበራቸዉ በ3 ቼኮች በተለያየ ጊዜ እንዱከፈለ ተደርጎ ተሰጠኝ በማለት ነዉ። ይህ ማለት ደግሞ ሂሳብ መተሳሰብ ከተደረገ በኋላ ተጠሪዎች ለአመልካች መስጠት ከነበረበት ከጠቅላላዉ የአክሲዮን ሽያጭ ገንዘብ መጠን ላይ ወደ ብር 9,940,000 (ዘጠኝ ሚሉዬን ዘጠኝ መቶ አርባ ሺህ ብር) የሚሆን የገንዘብ መጠን ቀድሞ ለነበሩት ዔዲዎች ቅናሽ አድርጓል እንደ ማለት ነዉ።
ተጠሪዎች በበኩላቸዉ እየተከራከሩ ያለት ከአክሲዮን ሽያጩ ዉል በፉት ለአመልካች የተከፈለ የዔዲ ገንዘብ ስለነበሩ ምንም የሂሳብ መተሳሰብም ሆነ የዔዲ መቀናነስ ሳይኖር እንዱሁ የብር 14,600,000 (አስራ አራት ሚሉዬን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ዋጋ ያላቸዉ ሦስት ቼኮች ሂሳብ እስከሚሰራ ድረስ በማለት ለዋስትና ብቻ ለአመልካች ተሰጥቶታል የሚል ነው። ይህ ማለት ደግሞ ተጠሪዎች ምንም ሂሳብ ሳይሰራ (በቃልም ይሁን በምንም መልኩ) እንዱሁ (በዘፈቀደ ወይም ያለምንም መሰረት) የብር 9,940,000 (ዘጠኝ ሚሉዬን ዘጠኝ መቶ አርባ ሺህ ብር) የገንዝብ መጠን የብር 14,600,000 (አስራ አራት ሚሉዬን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ዋጋ ያላቸዉንና የተለያየ የክፍያ ቀን ያላቸዉን ሦስት ቼኮች ለአመልካች ተሰጠ እንደማለት ነዉ። ይህን ለማድረጋቸዉ እንደምክንያት የጠቀሱት ደግሞ ቀደም ብል በመካከላቸዉ የነበረዉ “የንግድ የግል ግንኙነት” ነዉ የሚል ነዉ።
አመልካች ግን ከሽያጭ ዉለ በፉት የነበሩት ዔዲዎች በሙለ የተፈፀሙት ቼኮቹ ከመዉጣታቸዉ ቢያንስ ከወራት በፉት መሆኑን በመግለፅ ቼኮቹ የተሰጡትም ቀድሞ የነበሩት ዔዲዎች በሙለ ከተቀናነሱ በኋላ ነዉ በማለት ይከራከራል።
በእርግጥም የተባለት የዔዲ ክፍያዎች ከሽያጩና ከቼኮቹ መዉጣት በፉት ስለመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔና ለዚህ ችልት የቀረበዉ የከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገብ ያመለክታል። የአክሲዮን ሽያጩን ጠቅላላ የገንዘብ መጠን፣ ከአመልካች የአክሲዮን ሽያጭ ገንዘብ ላይ የተደረገገዉን ቅናሽ፣ የቀድሞ የዔዲዎች ክፍያ ጊዜንና ለአመልካች በእጁ የተሰጡትን የሶስት ቼኮች ዋጋ በአንድ ላይ ወስደን ስንመለከት የሂሳብ መተሳሰብ በግራ ቀኙ መካከል ስለመኖሩና ቼኮቹም የሚያመለክቱት የተጣራ ንፁህ ክፍያ ስለመሆኑ አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 259/1/ መሰረት ያለበትን የማስረዲት ሸክም በበቂ ሁኔታ መወጣቱን ያሳያለ። በተጨማሪም የሁለቱ የጋራ ጓዋደኛ ስለመሆኑ በግራ ቀኙ የተገለፀዉና ክርክር የተነሳባቸዉን የብር 14,600,000 (አስራ አራት ሚሉዬን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ዋጋ የነበራቸዉን ሶስት ቼኮችን በስምምነት በአደራ በእርሱ እጅ አስቀምጠዉት የነበረዉ የአቶ ጌታቸዉ ተገኔም የምስክርነት ቃል ይህንኑን ያጠናክራል። በተለይ ይህ ችልት የስር ከፍተኛ ፍ/ቤትን አስቀርቦ ባደረገዉ ማጣራት ይህ ምስክር በሰጠዉ የምስክርነት ቃል ዉስጥ ሦስቱ ቼኮች ለአመልካች የተሰጡት ቀድሞ የነበሩት ዔዲዎች በሙለ ከተቀናነሱ በኋላ የተጣራ ክፍያ ስለመሆኑ በማያጠራጥር ሁኔታ መስክረዋል።
በተቃራኒዉ የተጠሪዎች የምስክርነት ቃል እርስ በርሱ የሚጣረስ እንደሆነ የቀረበዉ መዝገብ ያመለክታል። በማስረጃ ህግና የማስረጃ ምዘና መርሆዎች መሰረትም ቢታይ በጉዲዩ ዉስጥ በቀጥታ ጥቅም ካላቸዉ ባለጉዲዮች ምስክርነት ቃል ይልቅ የአቶ ጌታቸዉ ተገኔ ምስክር ቃል በግራ ቀኙ ዘንድ ከነበረዉ መልካም ግንኙነት፣ አሜኔታና ሁለቱን ለማግባባት ይጫወት ከነበረዉ ሚና አንፃር ሲታይ የሰጠዉ የምስክርነት ቃል ገለልተኛ፣ ተዓማኒና እዉነትነት ያለዉ ስለመሆኑ ጥርጣሬ ዉስጥ የሚገባ ጉዲይ አይደለም። ይህ ከሆነ ደግሞ የማቻቻል ጥያቄን ያነሱት ተጠሪዎች ለአመልካች ቀድሞ የተከፈለት ክፍያዎች ከሂሳብ ዉስጥ አለመግባታቸዉን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 259/2// መሰረት ግልፅና በቂ የሆነ ማስረጃ በማቅረብ ማስረዲት ይገባቸዉ ነበር።
ተጠሪዎች በ
ላይ የተሰጠዉን የሰበር ችልት ዉሳኔን በመጥቀስ ቼክ ያለ ምንም ፍርማሉቲ ለዋስትና መስጠት እንደሚቻል በተሰጠዉ አስገዲጅ የህግ ትርጉም መሰረት ከአመልካች ጋር “የንግድ የግል ግንኙነት” ስለነበረን ቼኮቹን ለዋስትና (ለመያዣ) ተሰጥቶታል በማለትም ተከራክሯል።
በተጨማሪም ተጠሪዎች በስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ባደረጉት የቃል ክርክር ለ1ኛ ተጠሪና ለላልች ሁለት የአክሲዮን ገዢዎች ለተደረገዉ የአክሲዮን ሽያጭ ዋጋ መክፈያነት 4ኛ ተጠሪ ዋስ የመሆን መብቱን ተጠቅሞ ክርክር የተነሳባቸዉን ሦሰቱን ቼኮች ለአመልካች ሰጠ እንጂ ለባንክ ቀርቦ ክፍያ እንዱፈፀምባቸዉ አይደለም በማለት ተከራክረዉ እንደነበርም ከቀረበዉ ከከፍተኛ ፍ/ቤቱ መዝገብ ማየት ተችሎል።
ነገር ግን ቼክ ያለምንም ፍርማሉት ለመያዣ ወይም ለዋስትና መስጠት ይቻላል በማለት የሰበር ችልት ዉሳኔ ሰጥቷል የሚለዉን የተጠሪዎች ክርክር በሚመለከት የተጠቀሰዉ የሰበር ዉሳኔ ዔዲ ከፊይ (ተከሳሽ) በቼክ አምጪ (ከሳሽ) ላይ ዔዲዉን ላለመክፈል ወይም ከዔዲዉ ነፃ ለመሆን ከህግ አንፃር ማቅረብ ስለሚችላቸዉ የመቃወሚያ ዓይነቶችን የሚመለከት ነዉ። በተለይ የሰበር ችልቱ የን/ህ/ቁ. 717 እና 850ን በመተርጎም ተከሳሽ ከከሳሽ ጋር ከህግ ወይም ከዉል የመነጨ ግንኙነት ከነበራቸዉ እና ይህም ግንኙነት ዔዲዉን በሙለ ወይም በከፉል ላለመክፈል ምክንያት የሚሰጠዉ ከሆነ በተጠቀሱት የን/ህጉ ቁጥሮች ድንጋጌ መሰረት መቃወሚያ ለማቅረብ ይችላል በማለት ወስኗል። በዉሳኔዉም ላይ የግል ግንኙነት የሚለዉ ሐረግ የዉል ወይም የህግ መሰረት የላለዉና ከንግድ ህጉ ዓላማ ያፈነገጠ ዓይነት ተድርጎ ትርጉም ሉሰጠዉ እንደማይገባም አስምሮበታል። አንድ ዔዲ ከፊይ (ተከሳሽ) ከተጠቀሱት የንግድ ህጉ ድንጋጌዎች አንፃር የግል ግንኙነትን መሰረት በማድረግ በአምጪዉ (በባለገንዘቡ) ላይ መቃወሚያ ለማቅረብ በመጀመሪያ የግንኙነቱ መሰረት የሆነውን ዉል ወይም ህግ አቅርቦ ማስረዲት አስፈላጊ ስለመሆኑ የሰበር ችልቱ አፅኖት የሰጠበት ነጥብ ነዉ።
ተጠሪዎች ካለት በተቃራኒ የሰበር ችልቱ በየትኛዉም የዉሳኔ ክፍለ ወይም ገፅ ላይ ቼክ ያለ ምንም ፍርማሉቲ ለዋስትና ላሰጥ ይችላል የሚልም ሆነ የግል ግንኙነትን መሰረት በማድረግ ሂሳብ መተሳሰብ ሳያስፈልግ ቼክን ለዋስትና (ለመያዣ) መስጠትና ይህንም ሂሳብ ወደፉት ከሚመነዘረዉ ከቼኩ ዋጋ ላይ ታሳቢ ማድረግ (መቀነስ) ይቻላል የሚል ዉሳኔ አልሰጠም። በመርህ ደረጃ አግባብነት ያለዉ የፍ/ብ/ህጉና የንግድ ህጉ ለቼክ የሰጡት ዋና ዓላማ ለመያዣነት እንዱያገለግል ነዉ ባይባልም እንደማንኛዉም ሉተላለፈ እንደሚችለ ሰነድች በመያዣነት ወይም በዋስትና ላሰጥ እንደሚችልና ይህ በሚሆንበት ጊዜ ግን በንግድ ህጉና በፍ/ብ/ህጉ ላይ በተቀመጡት ግልፅ ድንጋጌዎች መመራት ይኖርበታል (የን/ህ/ቁ 950 ና ፍ/ብ/ህ/ቁ. 2866)። በተለይ የመያዣ ዉል ስምምነት በሚደረግ ጊዜ ዉለ መከተል ስላለበት ፍርም በተመለከተም በግልፅ የተደነገገ ስለመሆኑ ከን/ህጉ ቁ. 952 እና የፍ/ብ/ህጉ ቁ.
2828 መመልከት ይቻላል።
የመያዣ ወይም የዋስትና ዉል ህጉ በፅሐፍ በሰነድ ካልተደረጉ በህግ ፉት ዋጋ የላቸዉም (ፈራሽ ናቸዉ) በማለት ከደነገጋቸዉ ጥቂት የዉል ዓይነቶች ዉስጥ አንደ ስለመሆኑ ግልፅ ነዉ (የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1725(ሀ)፤ 1922(1-3)፣ 2828(1-2))። ላላዉ ደግሞ የመያዣዉ ስምምነት ለምን ግዳታ እንደተደረገ፣ የግዳታዉ መጠን (ከፍተኛ የገንዘብ ወሰን) በጥንቃቄ ግልፅ መደረግ እንዲለበትና ስምምነቱ የተደረገበት ቀን በግልፅ ሉቀመጥ እንደሚገባ ህጉ የግድ ይላል (የፍ/ብ/ህ/አንቀጽ 2828 (1-2)፣ 2864- 2866ና የን/ህ/ቁ. 952)። እነዚህ የህጉ አስገዲጅ ድንጋጌዎች ካልተሟለ የመያዣ ስምምነት ዉል አለ ማለት አይቻልም። ተጠሪዎች ቼኮቹ ለአመልካች የተሰጡት ክፍያ እንዱፈፀምባቸዉ ሳይሆን ለዋስትና (ለመያዣ) ነዉ ይበለ እንጂ ይህ ስለመሆኑ እነዚህ የህግ ድንጋጌዎች በሚጠይቁት መልኩ ያቀረቡት የመያዣ ዉል ሰነድ የለም። ነገር ግን የሰበር ችልቱ በ
ላይ ቼክ ክፍያ የሚፈፀምበት ወይም የክፍያ ሰነድ እንጂ በራሱ (ብቻዉን) ዉል መኖሩን ለማረጋገጥ የሚዉል ሰነድ አይደለም በማለት አስገዲጅ ዉሳኔ ሰጥቷል። በልላ አነጋገር ቼክ በመሰጠቱ ብቻ በሁለት ወገኖች ማለትም በአዉጪዉና በአምጪዉ መካከል ዉል (የዋስትናም ይሁን የመያዣ) አለ ለማለት የሚቻልበት የህግ አግባብ የለም ማለት ነዉ (
ቅፅ 21 ገፅ 309 - 310)። ባጭሩ ቼክ ያለ ምንም ፍርማሉቲ ለዋስትና (በመያዣ) መስጠት ይቻላል የሚለዉ የተጠሪዎች ክርክር አግባብነት ያላቸዉን ግልፅ የህግ ድንጋጌዎችንና የተጠቀሰዉን የሰበር ዉሳኔን ያላገናዘበ ስለሆነ ተቀባይነት የለዉም ብለናል።
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ቼኮቹን 1ኛ ተጠሪ ለዋስትና (ለመያዣ) የሰጡት ነዉ በማለት የደረሱበት መደምደሚያ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል።
ከላይ እንደተገለፀዉ ቼክ በባህሪዉ የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ሐተታ የላለበት ትዕዛዝ የያዘ ሆኖ ለከፊዩ (payee) እንደ ቀረበ የሚከፈልበትና ሉተላለፍ የሚችል የገንዘብ መጠየቂያ ሰነድ እንደሆነ ግልፅ ነዉ (ን/ህ/ቁ. 850፣ 827፣ 732፣ 715)። ዋና ዓላማዉም አስተማማኝ፣ የተቀላጠፈና ዉጤታማ የሆነ የግብይት ሥርዓት እንዱኖር ማድረግ እንደሆነ ከቼክ መሰረታዊ ባህርያትና ቼክን መሰረት አድርጎ ለሚከሰቱ ክርክሮች በን/ህግ፣ በፍ/ሥ/ሥ/ህግና በወንጀል ህግ ዉስጥ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች መረዲት ይቻላል። ይህ ቢሆንም ግን ለቼኩ መዉጣት ወይም መሰጠት ምክንያት የሆነዉ በከሳሽና በተከሳሽ መካከል የነበረዉ ዉል የግል ግንኙነት ከሆነና በዚህ ረገድ በሁለቱ መካከል ክርክር በሚፈጠርበት ጊዜ እንደኛዉ ወገን የሚያነሳዉን መቃወሚያ ወይም ክርክር መርምሮ ተገቢዉን ዉሳኔ ለመስጠት ክርክር የተነሳበትን ቼክ ለቼኩ መሰረት ከሆነዉ ዉል ወይም ግንኙነት ጋር ማገናዘብ አስፈላጊ ላሆን ይችላል።
ይህ በዋናነት የሚረዲዉ ቼክ የተሰጠዉ ወገን ቼኩ እንዱሰጠዉ ምክንያት የሆነዉ ግንኙነት የጣለበትን ግዳታ ስለመወጣቱና በቼኩ ላይ የተቀመጠዉን መብት ለመጠቀም የሚያስችለዉ ስለመሆኑ ለማረጋገጥና ለተነሳዉም ህጋዊ ተቃዉሞ በህጉ መሰረት እልባት ለመስጠት ነዉ።
አሁን በያዝነዉ ጉዲይ ክርክር ለተነሳባቸዉ ለሦስቱ ቼኮች መዉጣት (ለአመልካች መሰጠት) መሰረቱ የአመልካች በ2ኛ ተጠሪ ዉስጥ የነበረዉን የአክሲዮን ድርሻ መሸጡና ለአክሲዮኖቹም ጠቅላላ ዋጋ መክፈያነት ስለመሆኑ ተረጋግጧል። ባጭሩ ለቼኮቹ መዉጣት መነሻዉ የአክሲዮን ሽያጭ ዉል ሲሆን 4ኛ ተጠሪ በ1ኛ ተጠሪ ፈራሚነት ቼኮቹን የሰጠ ስለመሆኑ ከመጀመሪያ ጀምሮ ካለዉ የግራ ቀኝ ክርክር፣ ከስር ፍ/ቤቶች የዉሳኔ መዝገቦችና ከቀረበዉ የከፍተኛ ፍ/ቤቱ መዝገብ መረዲት ይቻላል።
በተጨማሪም ችልቱ በመጀመሪያ ለአመልካች በቼክ የተሰጠዉ የገንዘብ መጠን ብር 14,600,000 (አሥራ አራት ሚሉዬን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ስለመሆኑ ለስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ከቀረቡት የቼክ ሰነድች ማረጋገጥ ተችሎል።
በዚህ ረገድ ከቼክ ህግ ድንጋጌዎች አፃፃፍ አንፃር ሉሰመርበት የሚገባዉ መርህ ቢኖር የአንድ ቼክ ምንጩ ምንም ይሁን ምን የሚፈጥረዉ መብትና ግዳታ የወደፉት እንጂ ወደኋላ ተመልሶ አለመሆኑን ነው። ይህ ማለት ቼክ የሚያሳየዉ በላዩ ላይ ከተገለፀዉ ቀን ጀምሮ ወደፉት ባለት የስድስት ወራት የጊዜ ገደብ ዉስጥ መፈፀም ስላለበት የክፍያ መብትና ግዳታ ነው። ከዚህ አንፃር መታየት ያለበት መሰረታዊ ነገር አዉጪዉና አምጪዉ ቼኩ ከመዉጣቱ ቀደም ብል በመካከላቸዉ የነበረ ላላ የግል ግንኙነት (other antecedent personal relations) አለ ቢባል ለቼኩ ገንዘብ ባለዔዲ የሆነዉ አዉጪ በቼኩ ላይ ባለገንዘብ ከሆነዉ አምጪ ላይ ቼኩን ከመስጠቱ በፉት የነበረዉን የዔዲ ገንዘብ ታሳቢ ሳያደርግ ወይም ሳይቀናንስ (ቼኩን ያወጣዉ እራሱ እሰከሆነ ድረስ ማለት ነዉ) ቼኩን ለአሁን ባለገንዘቡ ለቀድሞ ባለዔዲዉ ፈርሞ ይሰጣል ብል መገመት ከአንድ ምክንያታዊ ከሆነ የነጋዳ ባህሪ (reasonable business person) ወይም አስተሳሰብ ጋር በፍፁም ሉታረቅ የሚችል አይደለም።
አድርጎ ቢገኝም በራሱ ፈቃድ ወይም ቸልተኝነት እራሱን ለኪሳራ (risk) እንዲጋለጠ ይቆጠራል። በሁለቱ መካከል ያለዉ ቅርበት ይህን ሉፈጥር ይችላል እንኳን እንዲይባል በሽያጭ ገንዘቡም ጠቅላላ ዋጋም ሆነ በአክሲዮኖቹ የስም ዝዉውር ወቅት በመካከላቸዉ አለመግባባት (ጭቅጭቆች) ተፈጥሮ እንደነበርና አስታራቂ ግለሰቦች በሁለቱ መካከል መግባት አስፈላጊ ሆኖ እንደነበር ከክርክራቸዉም ሆነ ከስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔዎች ላይ በግልፅ መረዲት ይቻላል። እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ደግሞ የቼኩ ፈራሚ የሆነዉ 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ላይ የሚጠይቅ የዔዲ ገንዘብ ካለዉ ቆም ብል በጥንቃቄ እንዱያስብ ሉያደርጉት የሚችለ ሁኔታዎች ስለመሆናቸዉ አያከራክርም። ከዚህ በተጨማሪም የሽያጭ ዉለ በሚፈፀምበትና ቼኮቹ በራሱ በ1ኛ ተጠሪ በሚፈረሙበት ጊዜ ለአመልካች ከፍያለዉ ያላቸዉ የተለያዩ የገንዘብ መጠኖች በግልፅ ተለይተዉ የሚታወቁ ስለመሆናቸዉም ክርክር የለም። ወደፉት የተፈፀሙ ቢሆን እንኳን ተጠሪ ያቀረባቸዉ የማቻቻል መከራከሪያዎች ከላይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች አኳያ ሚዛን ሉደፈ ይችለ ነበር። እንዲንደ ክፍያዎች እንዱያዉም የተፈጸሙት በ1ኛ ተጠሪ ሳይሆን 1ኛ ተጠሪ ባለአክሲዮን በሆነበት ኩባንያ ነዉ። ስለሆነም ከቼኮቹ መዉጣት አስቀድሞ ለአመልካች ዔዲዎች ተፈፅሟል የተባለት ክፍያዎች ለአመልካች ከተሰጡት ቼኮች ላይ ታሳቢ ሉደረጉ/ሉቀናነሱ ይገባል መባለ ምንም የህግ መሰረት የለዉም፤ ከላይ ከተጠቀሱት የቼክ ባህሪያትና የቼክ ህግ ድንጋጌዎች አንፃርም ሲታይ መሰረታዊ ስህተት ነዉ። በህጉ አግባብ መሆን የነበረበት ከቼኮቹ መዉጣት (ከአክሲዮን ሽያጩ ስምምነት) ቀን በኋላ የነበሩትን ክፍያዎች ታሰቢ ማድረግ ብቻ ነዉ።
ከላይ የተደረሰበት ዉሳኔ እና የተሰጡት ዝርዘር ምክንያቶች እንደተጠበቁ ሆኖ ጉዲዩን ከላላ አቅጣጫም መመልከት ይቻላል። የቀረበዉ አቤቱታ እንደሚያሳየዉ የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ በአክሲዮን ሽያጭ ዉለ መሰረት ያልተከፈለዉ ቀሪ ገንዘብ መኖሩን በመጥቀስ ነዉ። ተጠሪዎች/1ኛ ተጠሪ የሽያጭ ዉለ መኖሩን ሳይክድ የተባለዉ ገንዘብ ተከፍሎል በማለት አዉንታዊ መንገድ (affirmatively) ተከራክሯል። ስለዚህ 1ኛ ተጠሪ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 259(1) በሚያዘዉ አግባብ መሰረት በክሱ ላይ የተመለከተዉን ቀሪ ገንዘብ ስለመክፈለ በቅድሚያ የማስረዲት ሸክም/ ግዳታ አለበት። 1ኛ ተጠሪ ቀሪ ገንዘቡ ተከፍሎል ብል የሚከራከረዉ ለአመልካች የተሰጠዉ ቼክ በዋስትና ሆኖ ቀሪ ገንዘቡ በልላ ዔዲ የተሰጠዉ መሆኑን በመግለጽ ቢሆንም ከላይ በተሰጠዉ ዉሳኔ ላይ ተመለከተዉ ምክንያት ክርክሩ ተቀባይነት አላገኘም። በልላ በኩል አመልካች ከክሱ ጋር አያይዞ ያቀረባቸዉ ቼኮች (ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በዋስትና አለመሰጠታቸዉ ስለተረጋገጠ) በተጠሪዎች ላይ ያልተከፈለ ዔዲ ስለመኖሩ የሚያስረደ መሆናቸዉን ያሳያለ።
በዚሁ መሰረት ቼኮቹ ከተቆረጡ (ከወጡ) ቀን አንስቶ ባለት ጊዜያት ዉስጥ ለአመልካች በተጠሪዎች ስለተከፈለት የገንዘብ መጠን በተመለከተ ችልቱ የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገብ አስቀርቦ አጣርቷል። ባደረገዉም ማጣራት በሐምል 17 ቀን 2006 ዓ.ም የአክሲዮን ሽያጭ ከተደረገ በኃላ ለአመልካች ስለተከፈለት ክፍያዎች የሚያሳዩት የቼክ ቁጥሮች ፣ 151፣ እና እና የፍ/ቤት የአፈፃፀም ትዕዛዝ ሲሆኑ ጠቅላላ ድምራቸዉ ደግሞ ብር 3.55 ሚሉዬን መሆኑን መዝገቡ ያሳያል። ቁጥሩ ሰለሆነዉና የብር 400 ሺህ ዋጋ ስላለዉና በጥቅምት 10 ቀን 2007 ስለተመነዘረዉ ቼክ በተመለከተ ግን አመልካች ክርክር የተነሳባቸዉ ሦስቱ ቼኮች ከመሰጠታቸዉ በፉት የተፃፈና የተሰጡ ናቸዉ በማለት ተከራክሯል። ሆኖም ግን ክርክር የተነሳባቸዉ ቼኮች የአክሲዮን ሽያጭና ዝዉዉር በተደረገዉ ቀን የተሰጡ ናቸዉ ከተባለና ይህ ቼክ ደግሞ የተመነዘረዉ ከዚህን ቀን በኋላ ከሆነና የተከፈለበት ላላ አሳማኝ ምክንያት ስለመኖሩ በአለመልካች በኩል የቀረበ ነገር ስለላለ በዚህ ረገድ የአመልካችን ክርክር አልተቀበልነዉም። ይህ ከሆነ ደግሞ ክርክር ከተነሳባቸዉ ቼኮች ዋጋ ላይ ለአመልካች መከፈል የነበረበት ቀሪ ገንዘብ ብር 11.05 ሚሉዬን ይሆናል ማለት ነዉ።
ባጠቃላይ ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች የተነሳ በስር ፍ/ቤቶች ክርክር ከተነሳባቸዉ ሦስቱ ቼኮች መዉጣት (ከአክሲዮን ሽያጩ ስምምነት) ቀን ቀድሞ ብል የነበሩት የዔዲ ክፍያዎች ከቼኮቹ ዋጋ ላይ ሉታሰቡ (ሉቀነሱ) ይገባል በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነዉ ብለናል። ስለሆነም የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
ሀ) የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 158393 በመስከረም 23 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔና የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 162264 በመጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ለ) ተጠሪዎች ለአመልካች ብር 11,050,000 (አስራ አንድ ሚሉዬን ሀምሳ ሺህ ብር) በአንድነትና በነጠላ ክሱ በስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ተሻሽል ከቀረበበት ቀን አንስቶ የሚታሰብ ህጋዊ ወለድ (9%) ጋር ይክፈለ።
ሐ) ተጠሪዎች የጠበቃ አበል የብር 11,050,000 (አስራ አንድ ሚሉዮን ሀምሳ ሺህ ብር) 5% (አምስት ፏርሰንት) በአንድነትና በነጠላ ለአመልካች ይክፈለ።
መ/ ላልች ወጪዎችና ኪሳራን ግራ ቀኙ ራሳቸዉን ይቻለ።
የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት መ/ቁ. 162264 ለፍ/ቤቱ ይመለስ።
መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.