No summary available.
የሰ.መ.
ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ተካልኝ ጫላ ገቢሳ - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች በቀን 2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 285529 በጥር 03 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት፤ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 261287 በግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው።
ጉዲዩ የሁከት ይወገድ ክስ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል። የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በአዱስ አበባ ከተማ ኮልፋ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዲ 8 የቤት ቁጥር 660 የግል ቤት ሲሆን በካርታ ቁጥር መ8/ወ1101/400/10919/01 በሴሪ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ስፊት 605 ካ.ሜ የሆነውን ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የብድር ውል አማካኝነት ገንዘብ ተበድሬ ካርታውን ያስያዝኩ ሲሆን አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በነበረን የብድር ውል አማካኝነት በኪሳራ ምክንያት ገንዘቡን በወቅቱ ባለመክፈላ 1ኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ ጨረታ እንደሚያወጣ አሳውቆኛል፤ 1ኛ ተጠሪ ከሚመራበት የጨረታ መመሪያ ውጪ የመጀመሪያ ዙር እና ሁለተኛ ዙር ጨረታ ማስታወቂያ ሳያወጣ የ3ኛ ዙር በማውጣት እና ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር ቤቱ ሉያወጣ የሚገባውን ዋጋ እንዲያገኝ እና ተጫራቾች በስፊት መጥተው እንዲይጫረቱ በማድረግ መብቴ እና ጥቅሜን የሚጎዲ ተግባር ፈጽሟል፤ 1ኛ ተጠሪ በሪፕርተር ጋዜጣ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም ለ2ኛ ግዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ በማለት የተጭበረበረ ጨረታ በማውጣት እና አመልካችን በማስለቀቅ ቤቴን ለ2ኛ ተጠሪ ለማስተላለፍ ጥረት ማድረጉን ስለደረስኩበት ይህንንም ጉዲይ ለ1ኛ ተጠሪም ሆነ የበላይ ኃላፉ ለሆነው የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ለዋናው መስሪያ ቤት አሳውቄ ጉዲዩ እንዱስተካከልልኝ በመጠየቅ ላይ እያለሁ 2ኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ ብል ቤቱን ለ2ኛ ተጠሪ እና ዘመደ ለሆነ ሰውን በድምሩ ሁለት ሰዎችን ብቻ በማጫረት ሉጫረቱ የመጡትን አቶ ቶላ ገዲ የተባለትን ግለሰብ እንዲይጫረቱ በማድረግ ቤቱ ሉያወጣ የሚችለውን ዋጋ ያሳጡኝ መሆኑን ለ1ኛ ተጠሪም ሆነ ለበላይ ኃላፉው አሳውቄ መፍትሄ እንደሚሰጠኝ በተነገረኝ መሰረት እየተከታተልኩ እገኛለሁ፤ ከሳሽ የጨረታው ሂደት አግባብነት የላለው መሆኑን በቃለ ጉባኤ ላይ ሀሳቤን የገለፅኩ ሲሆን የጨረታው ሂደት ቤቱ ከሚያወጣው ዋጋ በታች መሆኑን ገልጬ ገንዘቡን መልሼ ቤቱን ልረከብ ብልም ከሳሽ ላቀረብኩት ቅሬታና አቤቱታ 1ኛ ተጠሪ ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጠኝ ከዛሬ ነገ አይተንልህ መፍትሄ እንሰጣለን እያለ ጉዲዩ ከሶስት ወር በላይ ከቆየ በኋላ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር ቤት መልቀቅ አለብህ ብለው ከህግ ውጪ ቤቴን በኃይል ሉያስለቅቁኝ የሁከት ተግባር እየፈጸሙ መሆናቸውን በመግለጽ በይዞታዬ ላይ እየተፈጸመ ያለው የሁከት ተግባር ሉወገድ ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ በሰጠው መልስ፡- አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ላይ የወሰደትን ብድር በውለ መሰረት ያልመለሱ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት አመልካች በዋስትና ያስያዙት ቤት በጨረታ ተሽጦ እዲውን እንደሚሰበስብ ጨረታ ከማውጣቱ በፉት ለአመልካች አሳውቋል፤ ይህንንም አመልካች አልካደም፤ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት 1ኛ ተጠሪ ወደ ፍርድ ቤት መሄድ ሳያስፈልገው ንብረቱን በጨረታ ሽጦ ስመሀብቱን ወደ ገዢው እንዱያዛውር ስልጣን ተሰጥቶታል፤ ይህም በፍርድ ቤት ሉፈርስ እንደማይችል በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቅጽ 13 መ.ቁ. 68708 እና በቅጽ 14 መ.ቁ. 84353 አስገዲጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል፤ 1ኛ ተጠሪ የጨረታ ማስታወቂያ በየካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም ሲያስነግር 1ኛ እና 2ኛ የጨረታ ማስታወቂያ ሳያወጣ በስህተት ለ3ኛ ግዜ ተብል የወጣ ቢሆንም ወድያውኑ እንዱታረም በማድረግ አመልካች በተገኘበት ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ ለማድረግ የተገኘን ቢሆንም በጨረታው ለመሳተፍ የቀረበ ተጫራች ባለመኖሩ ጨረታው ሳይካሄድ ቀርቷል፤ በዚህ መሰረት ጨረታው ለ2ኛ ግዜ በቀን 09/07/2012 ዓ.ም በሪፕርተር ጋዜጣ እንዱወጣ ተደርጎ በ2ኛ ጨረታ ሁለት ተጫራቾች ቀርበው አመልካች በታዛቢነት በተገኘንበት ጨረታው ተካሂድ 2ኛ ተጠሪ ባቀረቡት ዋጋ አሸናፉ ሆነዋል፤ በጨረታው መመሪያ መሰረት ጨረታው በሚካሄድበት ሰዓት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፑኦ አሟልተው የቀረቡት ሁለት ተጫራቾች ብቻ ናቸው፤ መመሪያውን አሟልቶ የቀረበ ተጫራች በጨረታው እንዲይሳተፍ አልተደረገም፤ የቀረቡት ሁለቱ ተጫራቾች በመካከላቸው ዝምድና ስለመኖሩ 1ኛ ተጠሪ አያውቅም፤ የማወቅም ግዳታ የለበትም፤ አመልካችም 1ኛ ተጠሪ ዝምድና ያላቸው መሆኑን ያውቃል የሚል መቃወሚያም ሆነ ክርክር አልቀረበም፤ ከጨረታውም በፉትም ሆነ በኋላ 1ኛ ተጠሪ አመልካች እዲውን እንዱከፍል በተደጋጋሚ ቢያሳውቀውም ሉከፍል ባለመቻለ የንብረቱ ስመሀብት ገዢ ወደ ሆኑት 2ኛ ተጠሪ ዞሯል፤ አመልካች በንብረቱ ላይ ከገዢው የተሻለ መብት ካለመኖሩም በተጨማሪ ምንም ዓይነት ህጋዊ መብት የለውም፤ 1ኛ ተጠሪ አመልካች ከመኖሪያ ቤቱ ለቆ ለ2ኛ ተጠሪ እንዱያስረክብ መጠየቁ የሁከት ተግባር አያስብለውም፤ ይልቁንም አመልካች ቤቱን እንዱያስረክቡ በቃል እና በጽሁፍ በተደጋጋሚ የተነገራቸው ቢሆንም ከነገ ዛሬ አስረክባለሁ እያለ ሳያስረክቡ በኃይል ይዘውት ይገኛለ፤ 1ኛ ተጠሪ ለ2ኛ ጊዜ የተጭበረበረ ጨረታ በማውጣት ሆን ብል አመልካችን በሚጎዲ መልኩ ለ2ኛ ተጠሪ ቤቴን ለማስተላለፍ እየጣረ ነው ብል ያቀረበው ክስ ከቅን ልቦና ውጪ የቀረበ ሀሰተኛ ክስ ነው፤ በስህተት የወጣውን የጨረታ ማስታወቂያ መስተካከለን አመልካች እያወቁ 1ኛ ተጠሪ እንዱስተካከል በጋዜጣ ማስነገሩ የጨረታውን አወጣጥ ሂደት መሰረት አድርገው ያቀረቧቸው ዝርዝር ጉዲዮች ከእውነት የራቀ መሆኑን በመግለጽ የአመልካች የሁከት ይወገድልኝ ክስ ወድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የአሁን 2ኛ ተጠሪ በሰጡት መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት ግምት ተገምቶ ክስ ያላቀረበ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል ወይም ትክክለኛውን የዲኝነት ግምት ቀርቦ ሉከፍለ ይገባል፤ በፍርክልዠር ህግ መሰረት የሚከናወን የሀራጅ ጨረታ በፍርድ ቤት የሚሰረዝበት አግባብ የላለ በመሆኑ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም፤ ከሁለት ወራት በኋላ ጨረታው እንዱሰረዝ የቀረበ ክስ በመሆኑ በይርጋ ይታገዲል፤ በፍሬ ነገር ላይ ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ በሚል የወጣው ጨረታ ማስታወቂያ በስህተት በመሆኑ ይህም በጋዜጣ እርማት ተደርጎ በመጀመሪያው የጨረታ ሂደት ላይ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታ አልተደረገም፤ አመልካች ቤቱ በሚሸጥበት ወቅት 1ኛ ተጠሪ 1ኛ እና 2ኛ ጨረታ ሳያወጣ 3ኛ ጨረታ በማውጣት እና ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር የፈጠረው ህገ ወጥ ተግባር የለም፤ አመልካች በየጨረታ ሂደቱ በህጉ አግባብ ባለመፈጸሙ ጉዲት ደረሰብኝ የሚል ከሆነ በሻጭ ላይ የጉዲት ካሳ ብቻ መጠየቅ እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 7 እና በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አስገዲጅ የህግ ትርጉም የተሰጠበት መሆኑን በመግለጽ የአመልካች ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን በብይን ውድቅ አድርጓል።
በመቀጠልም ፍርድ ቤቱ 1ኛ ተጠሪ ያካሄደውን የጨረታ ሂደት የሚገልጽ ቃለ ጉባዓ እንዱቀርብ ካደረገ በኋላ አመልካች ይዞታውን በዋስትና አስይዘው ከ1ኛ ተጠሪ ገንዘብ የተበደሩ እና 2ኛ ተጠሪም በጨረታ አሸንፈው ይዞታውን የገዙ ስለመሆኑ ተረጋግጧል፤ የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የተያዘ በኪሳራ የፈረሰ ማህበር ንብረት በሀራጁ ጨረታ የተሸጠ በመሆኑ ሽያጭ ሉፈርስ ይገባል በሚልም ሆነ በመያዣ የተያዘውን ንብረት በባንኩ በሀራጅ የተሸጠ በመሆኑ በባለእዲው በኩል ቢሸጥ የተሸለ ዋጋ ያስገኝ ስለነበር ሽያጭ ሉፈርስ ይገባል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የላለው መሆኑን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት መ.ቁ. 84353 አና መ.ቁ. 38708 መሰረት አስገዲጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል፤ 1ኛ ተጠሪ በአሻሻጡ ሂደት ባንኩ ህግን ባለመከተል የፈጸመው ስህተት ቢኖር እና በባለእዲው ላይ ጉዲት ቢደርስ ግን ለዚህ ጉዲት ለባለ እዲው ካሳ የመክፈል ኃላፉነት ከሚኖርበት ውጪ ፍርድ ቤቶችም ሀራጁን ለማስቆም ስልጣን እንደላለው በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 የተደነገገ በመሆኑ ተጠሪዎች በአመልካች ላይ የፈጸሙት የሁከት ተግባር የለም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል። ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤትም የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን ይዘቱም፡- አመልካች በስር ፍርድ ቤቶች ያነሳው የጨረታው ሂደት ህጋዊ አይደለም በሚል እንጂ በአዋጅ ቁጥር 97/90 የተሰጠውን ስልጣን በመቃወም አይደለም፤ አንደኛ ተጠሪ በየካቲት 1 ቀን 2012 ዓ/ም በስህተት ያወጣው የሀራጅ ማስታወቂያ ላይ እርማት ሲያወጣ ማስታወቂያው ዝርዝር ላይ የሚታረሙ ብቻ ተስተካክለው የቀደመው ሀራጅ በዚህ ቀን፣ወር እና ዓ/ም በማስታወስ የሚከናወን ሆኖ ሳለ 1ኛ ተጠሪ ይህንን ሳያደርግ በደፈናው ላላ አይነት የሀራጅ ማስታወቂያ በሚመስል መልኩ ለ ሁለተኛ ጊዜ የወጣ በሚል መቀመጡ ቀድሞ በስህተት ከወጣው የጨረታ ማስታወቂያ ጋር የተለያየ የሚመስል እና የአመልካችን ንብረቱን ከፍል የማስቀረት መብቱን ወይም የኢ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40 እንዲይጠቀም አድርጎታል፤ በሁለተኛ ጨረታ ከአሁን አመልካች ውጭ ቀደም ሲል በተበዲሪዎች ዝርዝር ውስጥ ያልነበሩ ተካተውበታል፤ የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪዎች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 ላይ አበዲሪው ባንክ በዋስትና የያዘውን ንብረት ወደ ፍርድ ቤት መሄድ ሳያስፈልገው ንብረቱን በጨረታ ሻጩ ስመሀብቱን ወደ ገዢ የማዛወር ስልጣን ተሰቶኛል በሚል ያቀረቡትን ክርክር ያለመንቀፊቸው የአመልካችን በኢ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 ፍትህ የማግኘት መብቴን የሚቃረን ነው፤ አመልካች ስለ ህገወጥ የጨረታ ሂደት እያነሳ ባለበት የስር ፍርድ ቤቶች የጨረታውን ህግ እና ደንብ አስቀርቦ መመርመር ሲገባቸው የጨረታውን ቃለ ጉባኤ ብቻ መሰረት በማድረግ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የአሁን አመልካች የፍትህ ጥያቄ ባንክ ሀራጅ ማውጣት ስልጣን የለውም የሚል ሳይሆን በህግ አግባብ 1ኛ እና 2ኛ ጨረታ ሳይወጣ 3ኛ ጨረታ አውጥቶ ከህግ ውጪ ንብረቴን በአነስተኛ ዋጋ እየሸጠ ስለሆነ ሁከት ይወገድ የሚል ሆኖ ሳለ የስር ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 ለባንክ የተሰጠውን ስልጣን ብቻ መሰረት በማድረግ ከህግ ውጪ የተደረገ ጨረታ አይፈርስም በማለት የወሰነበትን አግባብ ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 37 እና 40፣ ከአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 136092 ከተሰጠው የህግ ትርጉም ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዚህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የ1ኛ ተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡-አመልካች ጨረታው ህጉን ተከትል ያልተፈጸመ በመሆኑ ጨረታው እንዱሰረዝ እና የሁከት ተግባር እንዱቆም በሚል ክስ ያቀረቡ ሲሆን 1ኛ ተጠሪም ጨረታው የማይፈርስበትም ምክንያቶች በመጥቀስ ተከራክሯል፤ አመልካች በጨረታው ምክንያት ጉዲት ደርሶብኛል በማለት የጉዲት መጠኑን ጠቅሰው ያቀረቡት የካሳ ጥያቄ በላለበት የስር ፍ/ቤት የጨረታው ሂደት ውስጥ በመግባት ጨረታው በህጉ አግባብ ስለመካሄደ አለመካሄደ የሚመረምርበት እና ውሳኔ የሚሰጥበት የህግ መሰረት የለም፤ አመልካች ጉዲት ደርሶብኛል የሚለ ከሆነ የጉዲት መጠኑን ጠቅሰው ክስ ከመመስረት ውጪ ጨረታው በፍ/ቤት የሚሰረዝበት የህግ መሰረት የለም፤ አመልካች በሰበር አቤቱታቸው የጠቀሱት የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በቅጽ 22 በመ/ቁ. 136092 የሰጠው አስገዲጅ ውሳኔ አሁን ክርክር ካስነሳው ጉዲይ ጋር የሚያያዝ አይደለም። በሁለተኛ ጨረታ ከአሁን አመልካች ውጭ ቀደም ሲል በተበዲሪዎች ዝርዝር ውስጥ ያልነበሩ ተካተውበታል በማለት ያቀረቡት ክርክር በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳ እና ህጋዊ መሰረት የላለው በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
የ2ኛ ተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችልት የተያዘው ጭብጥ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡትን የክርክር ይዘት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ይዘት እንዱሁም ጨረታው ክሱ በቀረበበት ጊዜ የነበረበትን ሂደት በተሳሳተ ሁኔታ በመገንዘብ ነው፤ 1ኛ ተጠሪ በስህተት የወጣውን የጨረታ ጥሪ በጋዜጣ ላይ እርማት በማድረግ በዚሁ ጨረታ ላይ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት የቤቱ ሽያጭ ያልተከናወነ በመሆኑም በእርማት በመደረጉ ምክንያት የደረሰ ጉዲት የለም፤ በጨረታ ሂደቱ ላይ የተፈጠረ ስህተት ወይም የማጭበርበር ድርጊት አልነበረም፤ አመልካች በጨረታው ሂደት፣ እርማቱ ተገቢ አይደለም እንዱሁም እዲውን ከፍዬ ቤቱን ላስቀር በሚል አቤቱታ አቅርቤ አልተፈቀደልኝም የሚል ክርክር በስር ፍርድ ቤት በአመልካች አልተነሳም፤ በጨረታ የተሸጠው ቤት አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ለተበደሩት ብድር በመያዣነት የተያዘ ሆኖ ብድሩ ባለመክፈለ ለጨረታ የቀረበ ስለመሆኑ አመልካች አልካደም በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርከሩ ሑደት መገንዘብ የቻልነው አመልካች በስር ፍ/ቤት ሂደት የሚጎዲኝ ሆኖ የጨረታን ህግ እና ደንብ አስቀርቦ መመርመር ሲገባቸው የጨረታውን ቃለ ጉባኤ ብቻ መሰረት በማድረግ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በሚል የሚከራከሩ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የመጀመሪያ ደረጃ የዲኝነት ሥልጣን የለውም የሚል መቃወሚያን በማንሳት መከራከሩን እና የስር ፍ/ቤቶችም መቃወሚያውን መሰረት በማድረግ ሥልጣን የለንም ሲለ መወሰናቸውን ነው።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በጭብጥነት ተይዞ ሉመረመር የሚገባው አጣሪው ከያዘው ጭብጥ በተጨማሪ አመልካች አጥብቀው እየተከራከሩ ያለት አስቀድሞ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ውሣኔ ያገኘ በመ/ቁ/ 136092 በሆነው መዝገበ የተወሰነ ውሣኔ እያለ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ተገቢ አይደለም በሚል የተከራከሩ በመሆኑ የውሣኔውን አግባብነት አስቀድሞ በተመሳሳይ ጉዲይ ይኸው ሰበር ሰሚ ችልት ከሰጣቸው የህግ ትርጉሞች አንፃር፣ እንዱሁም የቀረበው የሁከት ክስ ከመሆኑ አኳያ ተመርምሮ ስለመወሰን አለመወሰኑ ነው።
አመልካች በስር ፍ/ቤት አቅርበውት የነበረው ክስ የሚመለክተው 1ኛ እና 2ኛ ዙር ጨረታ በጋዜጣ ሳያወጣ 3ኛ ዙር ጨረታ ብል በጋዜጣ ማውጣቱ ባንኩ ከሚመራበት የጨረታ መመሪያ ውጪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር በጨረታ የሚሸጠው ቤት ሉያወጣ የሚገባውን እንዲያገኝ እና ተጫራቾች በስፊት እንዲይቀርቡ በሪፕርተር ጋዜጣ ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ በሚል ጥቅሜን የሚጎዲ ተግባር በመፈፀም፣ እንዱሁም ከሳሽ የጨረታው ሂደት አግባብነት የላለው መሆኑን በቃለ ጉባኤ ላይ ሀሳቤን የገለፅኩ ሲሆን የጨረታው ሂደት ቤቱ ከሚያወጣው ዋጋ በታች መሆኑን ገልጬ ገንዘቡን መልሼ ቤቱን ልረከብ ብልም ከሳሽ ላቀረብኩት ቅሬታና አቤቱታ 1ኛ ተጠሪ ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጠኝ ከዛሬ ነገ አይተንልህ መፍትሄ እንሰጣለን እያለ ጉዲዩ ከሶስት ወር በላይ ከቆየ በኋላ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር ቤት መልቀቅ አለብህ ብለው ከህግ ውጪ ቤቴን በኃይል ሉያስለቅቁኝ የሁከት ተግባር እየፈጸሙ በመሆኑ የሁከት ተግባር ሉወገድ ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
በመሰረቱ በሰበር ሰሚ ችልት የተሰጡ የህግ ትርጉም ተፈፃሚ ላሆን የሚገባው በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ የቀረበ ጉዲይን ለማስተናገድ ሲሆን፣ በአጣሪ በተያዘው ጭብጥ ላይ የተጠቀሰው የሰበር ውሣኔ በተጫራቾች መካከል በተደረገ የጨረታ አካሄድ ላይ የተሰጠ ውሣኔ እንጂ በባንክ በተያዘ እና በተከበረ ንብረት ላይ ባለዔዲው ዔዲውን መክፈል ባልቻለ ጊዜ በሚወጣ የጨረታ አካሄድ ላይ የቀረበ ቅሬታን አስመልክቶ የተሰጠ የህግ ትርጉም ባለመሆኑ በሰ/መ/ቁ/ 136092 ላይ የተሰጠው ትርጉም ከቀረበው ጉዲይ ጋር ተመሳሳይነት የላለው በመሆኑ ተቀባይነት ሉያገኝ የሚገባው አይደለም።
አዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92ን አስመልክቶ ለቀረቡ መዛግብት ከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጡ ትርጉሞችን ስንመለከት፡- በሀራጁ ጨረታ የተሸጠ በመሆኑ ሽያጭ ሉፈርስ ይገባል በሚልም ሆነ በመያዣ የተያዘውን ንብረት በባንኩ በሀራጅ የተሸጠ በመሆኑ በባለእዲው በኩል ቢሸጥ የተሻለ ዋጋ ያስገኝ ስለነበር ሽያጭ ሉፈርስ ይገባል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የላለው መሆኑን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት መ.ቁ. 84353 እና መ.ቁ. 38708 እንዱሁም በላልች መዛግብት አስገዲጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ ከላይ እንደተመለከተው የአመልካች የሁከት ይወገድልኝ ክስ መሰረት ያደረገው ባንኩ የጨረታ ህግን ሳይከተል ጨረታ በአግባቡ ሳያወጣ ንብረቴን ሉሸጥና ከንብረቱ ላገኝ የሚገባኝን ጥቅም ሉያሳጣኝ ነው የሚል በመሆኑ እንዱሁም በተያዘው ጉዲይ ጨረታው ወጥቶ ቤቱ ተሽጦ ለ2ኛ ተጠሪ ለማስተላለፍ አመልካች ቤቱን እንዱለቁ የተጠየቁ በመሆኑ በቤቱ ላይ የወጣውን ጨረታ የማሳገድ ሳይሆን በጨረታ የተሸጠውን ንብረት ወደገዢ እንዲይተላለፍ እና በውጤት ደረጃም እንዱታገድ የማድረግ ውጤት ያለው መሆኑን እንረዲለን። በመሆኑም አንድ በባንክ ዔዲ ምክንያት በጨረታ የተሸጠን ንብረት እንዱለቅ የሚጠየቅ ባለዔዲ በጨረታ ሂደቱ ላይ ጉድለት ያለበት የሚል ከሆነ ጉዲት መድረሱን አረጋግጦ ክስ ከሚያቀርብ በስተቀር ቤት እንድለቅ መጠየቄ የሁከት ተግባር ነው በሚል የሁከት ክስ ለማቅረብ የሚችልበት የህግም አግባብ የላለ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ሁከት የለም ብለው መወሰናቸው ተገቢ እንጂ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ባለመገኘቱ አቤቱታው ውድቅ ሆኖ ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ.261287 ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 285529 ጥር 03 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርከር የወጣውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
በ26/09/2013 ዓ.ም. በዋለው ችልት ጨረታው ለጊዜው ታግድ እንዱቆይ የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ
የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
No topics extracted.