No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ብርሀን ኢንሹራንስ ኩባንያ አክሲዮን ማህበር - ነገረ ፈጅ ዲንኤል ደፊር - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዝናቡ ጌታነህ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ክርክሩ የመድን ውልን መሰረት ያደረገ ሲሆን ጉዲዩ በመጀመሪያ በታየበት የግልግል ጉባኤ ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ ነሐሴ 29 ቀን 2011 ዓ.ም ባቀረበው ክስ የሰላዲ ቁጥሩ 03-78476-ኢት ዋና መኪና እና የሰላዲ ቁጥሩ 3-23823-ኢት ተሳቢ ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነ ተሽከርካሪ ለሚደርስበትም ሆነ ለሚያደርሰው ጉዲት አመልካች ከነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም - ነሐሴ 14 ቀን 2011 ዓ.ም የሚቆይ የመድን ሽፊን ሰጥቷል። ተሽከርካሪዎቹ በአዊ አስተዲደር ዞን ባንጃ ወረዲ ልዩ ስሙ ጎመርታ በሚባል ቦታ ተገልብጠው ከፍተኛ ጉዲት የደረሰባቸው ሲሆን አመልካች ጉዲቱ የደረሰው ተሽከርካሪዎቹ ከአቅም በላይ በመጫናቸው ነው በሚል የካሳ ክፍያ ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል። ተሽከርካሪዎቹ 420 ኩንታል የጫኑት የትራንስፕርት ባለስልጣን ባቀረበው ሀገራዊ ግዲጅ ሲሆን ከአቅም በላይ አልጫኑም።
በመሆኑም አመልካች ተሽከርካሪዎቹን ጠግኖ እንዱያስረክበኝ ወይም የዋናውን መኪና ግምት ብር 3,400,000 እና የተሳቢውን ብር 1,100,000 በድምሩ ብር 4,500,000 ከወጪና ኪሳራ ጭምር እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
አመልካች መስከረም 9 ቀን 2012 ዓ.ም ባቀረበው መልስ ሽፊን የተሰጠው ዋና ተሽከርካሪ የመጫን አቅም 155 እንዱሁም ተሳቢው 255 ኩንታል በድምሩ 380 ኩንታል ሲሆን አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪዎቹ 40 ኩንታል ትርፍ ጭነው ሲጓዙ ስለሆነ በንግድ ህጉ ቁጥር 663(1)፣ 665(1) እና በመድን ውለ ቁጥር መ(መ) መሰረት ኃላፉነት የለብኝም። የተሽከርካሪው የመጫን አቅም ተሽከርካሪውን በሰራው ኢንጂነር ወይም አምራች ድርጅት የሚወሰን በመሆኑ የማዲበሪያ እጥረት በማጋጠሙ ወይም ባለስልጣን በሚፅፈው ደብዲቤ አይሻሻልም። በተጨማሪም በንግድ ህጉ ቁጥር 675(1)፣ 678፣ በፍ/ሕ/ቁጥር 2090 እና 2091 መሰረት ተጠሪ የጉዲቱን መጠን ገምቶ ባላቀረበበት ሁኔታ የካሳውን ጣሪያ ሉጠይቅ አይችልም፤ የጉዲት መነሻም 7.5% ተቀናሽ ላደረግ ይገባል፤ ለተቋረጠ ጥቅም ኃላፉነት የለብኝም በማለት ተከራክሯል።
የግልግል ጉባኤውም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶ ግራ ቀኙ የድርጅቱ አምራች የሆነው አምቼ በወሰነው የመጫን አቅም እንጂ በተሽከርካሪው ሉብሬ በተገለጸው የመጫን አቅም ላይ አልተካካደም። የትራንስፕርት ባለስልጣኑ በውስጥ የተፃፃፈባቸውን ሰነድች ጨምሮ አምራቹ ድርጅት የላካቸውን ሰነድች በፕስታ አሽጎ ልኳል። ከአምቼ የቀረበው ማስረጃ ዋናው ተሽከርካሪ ሲመረት 245 ኩንታል እንዱሁም ተሳቢው 280 ኩንታል ለመጫን እንዱችል ተደርጎ መሰራቱን የሚገልፅ ሲሆን የፍደራል ትራንስፕርት ባለስልጣንም በቁጥር ኮ/70/1/ማጉባ/717/001/06/11 የካቲት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በፃፈው ደብዲቤ ማዲበሪያ የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች የመጫን አቅማቸውን አሟጦ መጠቀም እንዱቻል ተጨማሪ 50 ኩንታል እንዱጭኑ መደረጉን ገልጿል። ይህም የተሽከርካሪው የመጫን አቅም በሉብሬው ላይ ከተገለፀው በላይ መሆኑን የሚያመላክት በመሆኑ ተሽከርካሪው ከመጫን አቅሙ በላይ ጭኗል ለማለት አይቻልም። በመድን ውለ ክፍል 2 መ ላይም ስልጣን ባለው ፈቃድ ሰጪ አካል በመኪናው ባለቤትነት ደብተር ላይ እንደተጠቀሰው በውለ ሰንጠረዥ የተገለፀውን የመጫን አቅም አልፍ መጫን በሚል የተገለፀው የሰው ቁጥርን እንጂ ትርፍ ጭነትን የሚመለከት አይደለም። በመድን ውለ ላይ የተገለፀው ከመጠን በላይ መጫን (Over Loading) በሉብሬው ላይ የተገለፀውን የሚመለከት ቢሆን በሉብሬው ላይ ከተገለፀው በላይ ሰው መጫን ካሳ እንደማያስከፍል በተገለፀው አግባብ ይገለፅ ነበር። የውለ ድንጋጌ ትርፍ መጫንን በሚመለከት በሉብሬው የተገለፀውን ወይም በአምራቹ የተወሰነውን የመጫን አቅም የሚያመላክት መሆኑ አሻሚ ነው። በተጨማሪም ተሽከርካሪው ከሉብሬው በላይ 40 ኩንታል መጫኑ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አደጋውን ያደረሰ ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ የለም። ስለሆነም አመልካች በተሽከርካሪው ላይ ለደረሰው ጉዲት ካሳ የመክፈል ኃላፉነት ስላለበት ተሽከርካሪቹን ጠግኖ ያስረክብ ወይም በውለ የተገለፀውን ብር 4,500,000 ይክፈል። ግራ ቀኙ ጉዲያቸው በግልግል ጉባኤው እንዱታይ ሲስማሙ ክርክሩ የሚወስደውን ጊዜ በመቀበል ስለሆነ ተጠሪ የተቋረጠ ገቢ በወር ብር 100,000 ታስቦ እንዱከፈለው ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም። የአደጋ መነሻ በውለ መሰረት ከካሳው ላይ 7.5% ተቀናሽ ይደረግ በማለት በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።
No topics extracted.
አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ይግባኙን ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት በመሰረዙ የካቲት 2 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታውን አቅርቧል።
የአቤቱታው ይዘት ባጭሩ በግራ ቀኛችን መካከል በተደረገው የመድን ውል ጠቅላላ ማግለያዎች ፉደል መ ላይ ትርፍ መጫን የካሳ ክፍያ የማያስከፍል መሆኑን እና ይህም በሉብሬ ከተገለፀው የመጫን አቅም ጋር የሚገናዘብ መሆኑ ተገልጿል። የግልግል ጉባኤው አብላጫ ድምፅ ከተዋዋዮች ግልፅ ስምምነት ውጪ እንዱሁም የማግለያ ድንጋጌውን አተረጓጎም በተመለከተ በብሓራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ሱፏርቪዥን ዲይሬክቶሬትን አስተያየት ወደ ጎን በመተው የሰጡት ውሳኔ የፍ/ሕ/ቁጥር 1733፣ 1735፣ 1737 ድንጋጌዎችን እንዱሁም ሰበር ሰሚ ችልቱ በቅፅ 4 በመ/ የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነው። የማግለያ ውለ ሉብሬን አያጣቅስም፤ ከብሓራዊ ባንክ የመጣው ማብራሪያም ተገቢነት የለውም ቢባል እንኳ የተሽከርካሪ መለያ፣ መመርመሪያ እና መመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 681/2002 አንቀፅ 4 እና 7(1)(መ) መሰረት ማንኛውም የተሽከርካሪ ባለንብረት የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር(ሉብሬ) ሉኖረው እንደሚገባ እና ሉብሬው ከሚይዛቸው ጉዲዮች መካከል አንደ የመጫን አቅምን በመሆኑ የውለን ክፍተት ከዚህ የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ ሉሞላ ሲገባ ከዚህ በተቃራኒ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
ጉዲዩ በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ መኪናው በሉብሬው ላይ ከተመለከተው የመጫን አቅም በላይ መጫኑ ከመረጋገጡ አንፃር የሰበር አመልካች ለጉዲዩ ኃላፉነት አለብህ ተብል የተሰጠው ውሳኔ ውለን መሰረት ያደረገ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልሳቸውን እንዱያቀርቡ ታዟል።
ተጠሪም መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። የመልሱ ይዘት ባጭሩ በግልግል ጉባኤው በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ክርክር ተሽከርካሪው ከአቅም በላይ ጭኖ ነበር ወይ? የሚለው ነበር፤ አመልካችም ትክክለኛውን የመጫን አቅም የሚወስነው አምራቹ ነው በሚል ተከራክሯል።
የግልግል ጉባኤውም ከአምራቹ ኩባንያና ከፈቃድ ሰጪው ትራንስፕርት ባለስልጣን ማስረጃ ሰብስቦ አደጋ በደረሰበት ጊዜ ተሽከርካሪው ከጫነው ጭነት በላይ መጫን እንደሚችል አረጋግጦ የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው። በመድን ውለ ክፍል 2 መ ድንጋጌ መሰረት በጭነት መጠን ምክንያት የኢንሹራንስ ሽፊንን ማግለል የሚቻለው ተሽከርካሪው ከአቅም በላይ ወይም ተወጥሮ የተጫነ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው። በዚህ ድንጋጌ ሉብሬ የተጠቀሰው ተሽከርካሪው መጫን ካለበት የሰው መጠን አንፃር ብቻ ነው።
የተሽከርካሪዎችን የመጫን አቅም መወሰን ስልጣን ያለው የትራንስፕርት ባለስልጣን ሚያዝያ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ለአመልካች በፃፈው ደብዲቤ በሉብሬ ከተገለፀው በላይ 50 ኩንታል ጨምሮ እንዱጭን የተፈቀደለት እና ይህም የትራንስፕርት አቅምን አሟጦ ለመጠቀም እንዱቻል መሆኑን ስለገለፀ የትራንስፕርት ህጉን በመጥቀስ አመልካች የሚያነሳው መከራከሪያ ተገቢነት የለውም። የብሓራዊ ባንክም የካሳ ክፍያ መከልከለ ከቅን ልቦና ውጪ የተፈፀመ መሆኑን የገለፀ በመሆኑ አመልካች አንድን ሀረግ ብቻ መዞ ያቀረበው መከራከሪያ ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች በበኩለ ሰኔ 9 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልሱን ያቀረበ ሲሆን የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልቱ ያስቀርባል ሲባል የተያዘውን ጭብጥ በስር ከተደረጉ ክርክሮች፣ በማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዱሁም ለጉዲዩ ተገቢነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
እንደመረመርነውም አመልካች ንብረትነታቸው የተጠሪ ለሆነ የሰላዲ ቁጥሩ 03-78476-ኢት ዋና መኪና እና የሰላዲ ቁጥሩ 3-23823-ኢት ተሳቢ ተሽከርካሪ ለሚደርስባቸው አደጋም ሆነ በልላ 3ኛ ወገን ንብረት ላይ ለሚያደርሱት ጉዲት ከነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም - ነሐሴ 14 ቀን 2011 ዓ.ም የሚቆይ የመድን ሽፊን መስጠቱ፤ በዚህም ጊዜ ውስጥ ዋናው እና ተሳቢ ተሽከርካሪው በድምሩ 420 ኩንታል ማዲበሪያ ጭነው ሲጓጓዙ በደረሰባቸው አደጋ ከፍተኛ ጉዲት ማጋጠሙን፣ ተሽከርካሪው ትርፍ ጭኖ ሲጓጓዝ ለሚደርስበት አደጋ አመልካች ካሳ ለመክፍል የማይገደድ መሆኑ እንዱሁም በሉብሬው ላይ የተገለፀው የተሽከርካሪዎቹ የመጫን አቅም በድምሩ 380 ኩንታል መሆኑ ግራ ቀኙን አላከራከረም።
ግራ ቀኙን የሚያራክረው የተሽከርካሪው ትርፍ መጫን የሚወሰንበት አግባብ ነው። አመልካች የተሽከርካሪው ትርፍ መጫን በሉብሬው የሚወሰን መሆኑን ገልጾ የሚከራከር ሲሆን በአንፃሩ ተጠሪ የመጫን አቅም በሉብሬ የሚወሰን መሆኑ በውለ የተገለፀው የሰው የመጫን አቅምን በሚመለከት ስለሆነ በተያዘው ጉዲይ ትርፍ ጭኗል ወይስ አልጫነም የሚለውን ለመወሰን ከግምት ውስጥ መግባት ያለበት የተሽከርካሪው አምራች የወሰነው የመጫን አቅም መሆን አለበት በማለት ነው። በመሆኑም የውለን ይዘት መመልከቱ ተገቢ ነው። የመድን ውለ ክፍል 2 መ ላይ “The company shall not be liable to make payment in respect of; loss, damage or liability happen while the vehicle is overloaded or strained or if the number of persons exceeding the seating capacity of the vehicle described in the schedule as specified in the ownership booklet issued by the licensing authority”. በሚል ተገልጿል። ድንጋጌው መድን ሰጪው ካሳ ለመክፈል የማይገደድበትን ሁኔታዎች በሚመለከት ተሽከርካሪው ትርፍ ጭኖ ወይም በመወጠር ወይም ከተፈቀደለት ሰው በላይ ጭኖ ሲያሽከረክር አደጋው የደረሰ እንደሆነ መሆኑን ያመላክታል። የውለ ድንጋጌ እነኚህን ካሳ የማያስከፍለ አማራጮች “ወይም” በሚል ሐረግ በማገናኘት አንደን ከአንደ አስከትል የሚስቀምጣቸው በመሆኑ ትርፍ መጫን ወይም አለመጫን በውለ ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው ስልጣን ባለው አካል በተሰጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ሉብሬ ይወሰናል የሚለው አገላለፅ ይህን ሐረግ ቀድመው በአማራጭ ለተጠቀሱት የጭነት መጠንን ወይም የሰው ቁጥርን የሚመለከቱ ናቸው።በተዋዋዮች መካከል ያለው የውል ቃል ግልጽ በሆነበት ጊዜ ፍርድ ቤቶች ውለን በመተርጎም ከተዋዋዮቹ ሀሳብ መራቅ የላለባቸው መሆኑ በፍ/ሕ/ቁጥር 1733 ላይ ተመላክቷል። በመሆኑም ይህ የውል ድንጋጌ በፍ/ሕ/ቁጥር 1731 መሰረት በተዋዋዮች መካከል ሕግ ሁኖ የሚያገለግል፤ የድንጋጌው ይዘትም ግልፅ ሁኖ እያለ ከውለ ይዘት ውጪ በመውጣት የግልግል ጉባኤው አምራቹ የወሰነውን የጭነት መጠን መሰረት አድርጎ የሰጠው ትርጓሜ የፍ/ሕ/ቁ 1733 ድንጋጌን፣ የንግድ ሕግ ቁጥር 663 እንዱሁም በሀገራችን የተሽከርካሪ የጭነት መጠን የአየር ፀባይን፣ የመንገድችን የጥራት ደረጃና የመልከዓ ምድር አቀማመጥን መሰረት አድርጎ በሉብሬ ወይም በባለቤትነት ማረጋገጫ የሚወሰንበትን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው።
በተጨማሪም የግልግል ጉባኤው በአንድ በኩል በውለ ላይ ትርፍ መጫን በሉብሬው በተገለፀው አግባብ እንዱወሰን የተገለፀው ከተሽከርካሪው የሰው ቁጥር የመጫን አቅም ጋር የሚገናኝ እንጂ ጭነትን የሚመለከት አይደለም በማለት ያሰፈረ ሲሆን በልላ በኩል ውለ በዚህ ረገድ የትኛውን ለማመላከት እንደሆነ ግልጽ አይደለም፤ አሻሚ ነው በሚል የደረሰበት መደምደሚያ እርስ በእርሱ የሚቃረንና የውል ስምምነቱን ያላገናዘበ ነው። የተሽከርካሪው ትርፍ መጫንም ለአደጋው መንስኤ ሁኗል ወይስ አልሆነም የሚለው በማስረጃ ሉረጋገጥ የሚገባው በውላቸው ላይ በግልጽ አደጋው ትርፍ በመጫኑ ምክንያት የደረሰ እንደሆነ (loss caused by overloading) ካሳ የማያስከፍል መሆኑ የምክንያት እና የውጤት ግንኙነትን በሚያመላክት ሁኔታ በውለ በግልፅ የተቀመጠ ሲሆን ነው። ከዚህ በተቃራኒ ተሽከርካሪው በሉብሬው ከተገለፀው በላይ 40 ኩንታል ትርፍ ጭኖ እንደነበር ተረጋግጦ እያለ የግልግል ጉባኤው አደጋው ትርፍ በመጫኑ ምክንያት የደረሰ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በሚል በፍርደ ማስፈሩ የውለን ይዘት ያላገናዘበ ነው። ይግባኝ ሰሚው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የግልግል ጉባኤው የፈፀመውን ስህተት አለማረሙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የተነሳውን ክርክር ለመዲኘት የተቋቋመው የግልግል ጉባኤ ጥር 16 ቀን 2012 ዓ.ም በአብላጫ ድምፅ የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በፍ/ይ/መ/ ህዲር 4 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችልት የግልግል ጉባኤውን ውሳኔ በማጽናት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ንብረትነቱ የተጠሪ የሆነው የሰላዲ ቁጥሩ 03-78476-ኢት ዋና መኪና እና የሰላዲ ቁጥሩ 3- 23823-ኢት ተሳቢ ተሽከርካሪ በሉብሬው ከተጠቀሰው 380 ኩንታል የመመጫን አቅም በላይ 40 ኩንታል በትርፍነት ጭኖ ሲጓዝ አደጋው የደረሰ በመሆኑ እና በሉብሬው ከተገለፀው የመጫን አቅም በላይ ጭኖ ሲጓጓዝ ለሚደርስበት አደጋ መድን ሰጪው ኃላፉነት የላለበት መሆኑ በመድን ውለ የማግለያ ድንጋጌ ክፍል 2 መ ላይ የተገለጸ በመሆኑ ለተጠሪ ካሳ ሉከፍል አይገባም በማለት ወስነናል።
በዚህ ችልት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ።