No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- 1ኛ. አቶ ሐይማኖት አበራ - ቀረቡ 2ኛ. አባይ ባንክ አክስዮን ማሕበር- ነ/ፈ ለምለም ሙለታ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ፀሀይ ኢንሹራንስ ኩባንያ - ጠበቃ ምንተስኖት ታዬ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ክርክሩ የመድን ሽፊን ውልን መነሻ ያደረገ ሲሆን ጉዲዩ በተጀመረበት የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካቾች እንደየቅደም ተከተላቸው 1ኛ እና 2ኛ ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካቾች ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም በተፃፈ ክስ ተጠሪ ንብረትነቱ የ1ኛ አመልካች የሆነ የሰላዲ ቁጥሩ 3-91089-ኢት ሲኖ ትራክ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ለሚደርስበት ጉዲት ከሐምል 1 ቀን 2010 ዓ.ም እስከ ሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ.ም የሚቆይ ለብር 2,800,000 የመድን ሽፈን ሰጥቷል። ተሽከርካሪው በምእራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ ቀበላ 03 ውስጥ ከአሽከርካሪው የጥንቃቄ ጉድለት በደረሰበት አደጋ ሙለ ለሙለ የወደመ ቢሆንም ተጠሪ ካሳ ለመክፈል ፍቃደኛ አልሆነም። 1ኛ አመልካች ከ2ኛ አመልካች ጋር ሐምል 26 ቀን 2009 ዓ.ም በተደረገ የብድር ውል መነሻነት ለወሰደው ብር 875,000 ተሽከርካሪውን በዋስትና አስይዟል። በመሆኑም ተጠሪ 5% የአደጋ መነሻ ዋጋ ተቀናሽ አድርጎ 1ኛ አመልካች ለ2ኛ አመልካች ሉከፍል የሚገባውን ብር 784,738.47 ከጥር 26 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ተጠናቆ እስኪከፈል በ15.5% እና 3% ቅጣት ለ2ኛ አመልካች እንዱከፍል፤ ቀሪውን ለ1ኛ አመልካች እንዱከፍል እንዱሁም ካሳው በጊዜው ባለመከፈለ የተቋረጠ ገቢን ውሳኔ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ 1ኛ አመልካች የመጠየቅ መብቱ እንዱጠበቅለት እንዱሁም ወጪ እና ኪሳራ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪ ህዲር 3 ቀን 2011 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው መልስ አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ከተፈቀደለት የመጫን አቅም በላይ አንድ ሰው በትርፍነት ጭኖ ሲጓዝ ስለሆነ በመድን ውለ፣ በሕግ እንዱሁም በሰ/መ/ በተሰጠው ገዢ ውሳኔ መሰረት ካሳ የመክፈል ኃላፉነት የለብኝም፤
ካሳ የመክፈል ኃላፉነት አለብሕ ቢባል እንኳ በመድን ውለ መሰረት ለተቋረጠ ገቢ ኃላፉነት የለብኝም፤
ተሽከርካሪውም ሙለ ውድመት የደረሰበት ስለሆነ አመልካቾች ተሽከርካሪውን ከእዲ እና እገዲ ነፃ ሳያደርጉ ካሳ ሉጠይቁ አይችለም በማለት ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ 1ኛ አመልካች ተሽከርካሪው በሉብሬው ከተገለጸው በላይ አንድ ሰው በትርፍነት ጭኖ የነበረ መሆኑን ሳይክድ የመጫን አቅሙ ከፍተኛ ስለሆነ አንድ ሰው ትርፍ በመጫኑ ምክንያት አደጋው ሉደርስ አይችልም በሚል የሚከራከር ቢሆንም በውላቸው ክፍል 2 አጠቃላይ በውለ የተገለለ ጉዲዮች ቁጥር 2.4 ላይ በሚመለከተው ባለስልጣን በሚሰጠው የባለቤትነት ማረጋገጫ ሉብሬ ላይ ከተገለጸ ሰው በላይ ትርፍ ጭኖ ጉዲት ከደረሰ ተጠሪ ካሳ እንደማይከፍል ተገልጿል፤ ይህ ስምምነትም በፍ/ሕ/ቁጥ 1731 መሰረት በተዋዋዮቹ መካከል እንደ ሕግ የሚቆጠር በመሆኑና ግልጽ ህግን በመተላለፍ የተፈጸመ ስለሆነ ተጠሪ ካሳ ለመክፈል አይገደድም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካቾች ውሳኔውን በመቃወም ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኛቸውን ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቀጥር 348(1) መሰረት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ አፅንቶታል።
አመልካቾች መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታቸውን ያቀረቡት ይህን የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማሳረም ነው። የአቤቱታቸው ይዘት ባጭሩ በ1ኛ አመልካች እና በተጠሪ መካከል በተደረገው የመድን ሽፊን ውል ክፍል 2 አንቀፅ 2.4 ተጠሪው ካሳ የማይከፍለው አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ትርፍ በመጫኑ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ብቻ ነው። ተጠሪም አደጋው የደረሰው ትርፍ በመጫኑ ምክንያት መሆኑን ጠቅሶ ያቀረበው ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም፤ አደጋውን የመረመረው የቡሬ ከተማ አስተዲደር ፕሉስ ፅ/ቤት በቁጥር ወ/ም/2771/31/41 መጋቢት 20 ቀን 2010 ዓ.ም ለተጠሪ በፃፈው ደብዲቤም የአደጋው ምክንያት የአሽከርካሪው የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑን አረጋግጦ እያለ የግራ ቀኙን ስምምነት በሚቃረን ሁኔታ አንድ ሰው ትርፍ በመጫኑ ብቻ ካሳ ሉከፍል አይገባም ተብል የተሰጠው ውሳኔ የፍ/ሕ/ቁጥር 1731 እና የን/ሕ/ቁጥር 664(1,2) ድንጋጌን ይቃረናል።
በተጨማሪም የስር ፍ/ቤቶች ለጉዲዩ ተገቢነት የላላቸውን ለሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች የተሰጠ የመድን ሽፊን ውልን መነሻ አድርጎ በተነሳ ክርክር ላይ በሰ/መ/ የተሰጠን ውሳኔ መሰረት በማድረግ የካሳ ክፍያ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም።
No topics extracted.
አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ከተፈቀደለት 300 ኩንታል የመጫን አቅም በታች ጭኖ ሲጓጓዝ ሲሆን አሽከርካሪው ትርፍ በመጫን በፈጸመው ጥፊት ጉዲት እና ኪሳራ ቢከሰት መድን ሰጪው በሰጠው የመድን ሽፈን መሰረት ካሳ ሉከፍል የሚገባ ስለመሆኑ የሚደነግገውን የን/ሕ/ቁጥር 664(1,2) በሚቃረን መልኩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚል ነው።
አቤቱታው በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ ለክርክሩ መነሻ በሆነው ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰው አደጋ ዋና መንስኤ የአሽከርካሪው የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑ በተገለጸበት እና ተሽከርካሪው ከተፈቀደለት ሰው በላይ ትርፍ መጫኑ ለአደጋው መንስኤ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ተጠሪው ካሳ የመክፈል ኃላፉነት የለበትም ተብል የተወሰነበት አግባብ ከኢንሹራንስ ፕሉሲው ፣ አግባብነት ካላቸው ህጎች እና ከሰበር ውሳኔዎች አንፃር ለማጣራት ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልሱን እንዱያቀርብ ታዟል።
ተጠሪ በበኩለ ህዲር 9 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ መልሱን አቅርቧል። የመልሱ ይዘት ባጭሩ የመድን ውለ አጠቃላይ የማግለያ ድንጋጌዎች ትርፍ መጫንን ጨምሮ ላልች ህገወጥ ተግባራት በሚፈፀሙበት ጊዜ ተግባራዊ እንዲይሆን በማሰብ የተቀረፀ ነው። በፍ/ሕ/ቁጥር 1678(ለ) መሰረትም ውል ህጋዊ ተግባራትን ለማከናወን የሚደረግ ስለሆነና በሉብሬው 1 ሰውና 153 ኩንታል እንዱጭን ከተፈቀደው በላይ ሹፋሩን ጨምሮ 3 ሰው ጭኖ እንዱሁም በትራንስፕርት ህግ የተመለከተውን የመጫን አቅም በመተላለፍ የተፈፀመ ተግባር ሲሆን ይህም በፍ/ሕ/ቁጥር 2035 መሰረት ጥፊት በመሆኑ ህግን በመተላለፍ ለደረሰ አደጋ ተጠሪ ኃላፉነት የለብኝም። በመድን ውለ ክፍል 2 አንቀፅ 2.4 ላይም ተሽከርካሪው በሉብሬው ከተገለፀው የመጫን አቅም በላይ ጭኖ ሲሽከረከር ለሚደርስ አደጋ ተጠሪ ካሳ እንደማይከፈል ስለተገለፀ ትርፍ መጫኑ ለአደጋው መንስኤ መሆን አለመሆኑ ከግምት ውስጥ ሳይገባ ትርፍ ጭኖ ለደረሰ አደጋ ተጠሪ ካሳ ለመክፈል አይገደድም። ይህንንም በማጠናከር በሰ/መ/ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ስለተሰጠ እና ትርፍ መጫኑ ስላልተካደ ቅሬታው ተገቢነት የለውም። ተጠሪ ካሳ የመክፍል ኃላፉነት አለበት ቢባል እንኳ ለተቋረጠ ገቢ ኃላፉነት የላለበት መሆኑ በውለ ማግለያ ክፍል 1(ሀ) ተገልጿል። የብድር ውለም በአመልካቾች መካከል የተደረገ በመሆኑ በባንክ ማበደሪያ መሰረት ወለድና ቅጣት እንዱከፍል የመጠየቅ መብት የላቸውም በማለት ተከራክሯል።
አመልካቾች ህዲር 23 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልሳቸውን ያቀረቡ ሲሆን የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልቱ ያስቀርባል ሲባል የተያዘውን ጭብጥ በስር ፍ/ቤቶች ከተደረጉ ክርክሮች፣ በማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዱሁም ለጉዲዩ ተገቢነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
እንደመረመርነውም አመልካቾች በዋናነት የሚከራከሩት አደጋው በአሽከርካሪው የጥንቃቄ ጉድለት የደረሰ እንጂ ትርፍ በመጫኑ ምክንያት የደረሰ አይደለም፤ በ1ኛ አመልካች እና በተጠሪ መካከል ባለው የመድን ሽፊን ውል መሰረት ተጠሪ የ1ኛ አመልካችን የካሳ ክፍያ ጥያቄ ውድቅ ሉያደርግ የሚችለው አደጋው ተሽከርካሪው ትርፍ በመጫኑ ምክንያት የደረሰ ሲሆን ብቻ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ለጉዲዩ ተገቢነት የላላቸውን የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔዎች በመጥቀስ የአመልካቾቸን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም በማለት ነው። ተጠሪ በበኩለ በውለ መሰረት ተሽከርካሪው በሉብሬው ከተገለጸው 153 ኩንታል እና 1 ሰው የመጫን አቅም ውጪ ትርፍ ጭኖ ሲሽከረከር ለደረሰበት አደጋ ካሳ የመክፍል ኃላፉነት የለብኝም፤ አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ሹፋሩን ጨምሮ 3 ሰው በመጫን ሲሽከረከር በመሆኑና ይህም ህገ ወጥ ተግባር ስለሆነ ለአደጋው መንስኤ መሆን አለመሆኑን ማስረዲት አይጠበቅብኝም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል።
ተጠሪ የመድን ሽፊን የሰጠው ንብረትነቱ የ1ኛ አመልካች የሆነ የሰላዲ ቁጥሩ 3-91089-ኢት ተሽከርካሪ የመድን ሽፊን በተሰጠበት ጊዜ ውስጥ አደጋ የደረሰበት መሆኑ እና በተሽከርካሪው ሉብሬ ላይ የመጫን አቅሙን በሚመለከት 153 ኩንታልና አንድ ሰው ተብል የተገለፀ መሆኑ አላከራከረም።
ከክርክሩ መረዲት እንደቻለነው ተጠሪ ተሽከርካሪው በሉብሬው ከተገለፀው የመጫን አቅም በላይ አንድ ሰው በትርፍነት ጭኖ ሲጓዝ አደጋው የደረሰ ስለሆነ ካሳ ልከፍል አይገባም በማለት የሚከራከር በመሆኑ የውለ ድንጋጌ እና ውጤቱን መመልከቱ አስፈላጊ ነው። የመድን ውለ ክፍል 2 ጠቅላላ ማግለያዎች 2.4 ስር “Loss, damage or liability caused by overloading or strain or if the number of persons exceed the seating capacity of the vehicle described in the schedule as specified in the ownership booklet issued by the licensing authority.” ከዚህ የውል ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው የተሽከርካሪው ትርፍ መጫን የደረቅ ጭነትን እንዱሁም በጋቢናው የተጫነን የተሳፊሪ መጠን በሚመለከት 2 የተለያዩ ውጤቶች ያለው መሆኑን ነው። የመጀመሪያው የደረቅ ጭነትን አስመልክቶ አደጋው በሚደርስበት ጊዜ ተሽከርከራው በሉብሬው ከተገለፀው በላይ ትርፍ መጫኑ እንዱሁም አደጋው ትርፍ በመጫኑ ምክንያት የደረሰ መሆኑ ያለው የምክንያትና የውጤት ግንኙነትን ማረጋገጥ የካሳ ክፍያ ጥያቄውን ውድቅ ለማድረግ በቅድመ ሁኔታነት መታየት ያለበት መሆኑ ነው። 2ኛው የተሽከርካሪው ሰው የመጫን አቅምን የሚመለከት ሲሆን ተሽከርካሪው በሉብሬው ከተገለፀው ቁጥር በላይ ጭኖ ሲሽከረከር አደጋው የደረሰ መሆኑ ከተረጋገጠ በአደጋው እና በትርፍ መጫኑ መካከል ያለውን የምክንያት እና የውጤት ግንኙነት ማረጋገጥ ሳያስፈልግ የካሳ ክፍያው ውድቅ የሚደረግበት አግባብ ነው።
ውልች በተዋዋዮች መካከል ሉኖር የሚገባውን የቅንነት እና የመተማመን ግንኙነት እንዱሁም በጉዲዩ ውስጥ ያለውን ልማዲዊ አሰራር መሰረት በማድረግ በቅን ልቦና ሉተረጎሙ የሚገባ ስለመሆኑ በፍ/ሕ/ቁጥ 1732 ላይ ተመላክቷል። በመሆኑም በተያዘው ጉዲይ የስር ፍርድ ቤቶች ተሽከርካሪው በሉብሬው ከተገለፀው በላይ አንድ ሰው በትርፍነት ጭኗል በሚል የአመልካቾችን የካሳ ክፍያ የዲኝት ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው የውለን ይዘት በዘርፈ ያለውን ልማዲዊ አሰራር ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለመሆኑ ሉመረመር የሚገባው ነው። በሀገራችን ለጭነት ተሽከርካሪዎች የሚሰጠው የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር (ሉብሬ) ላይ በገቢና እንዱጭኑ የተፈቀደላቸውን የሰው ብዛት በሚመለከት አሽከርካሪውን የሚጨምር እንዲልሆነ ይታወቃል። ተጠሪም አሽከርካሪውን ይጨምራል በማለት የሚያቀርበው መከራከሪያ የለም። በዘርፈ በዲበረው አሰራርም የጭነት ተሽከርካሪዎች በአብዛኛው ያለረዲት ሹፋር የማይንቀሳቀሱ መሆኑ ይታወቃል። በሉብሬውም አንድ ሰው ተብል የተገለፀው በዘርፈ ከዲበረው ልማድ ጋር ተገናዝቦ ሲተረጎም ሹፋሩን እና ረዲት ሹፋሩን የማይጨምር መሆኑን ያስገነዝባል። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች በዘርፈ ያለውን ልማዲዊ አሰራር በፍ/ሕ/ቁጥር 1732 መሰረት ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ ለጉዲዩ ተገቢነት የላለውን የሕዝብ ጭነት ተሽከርካሪን በሚመለከት የተሰጡ የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔዎችን በመጥቀስ ተጠሪ ለአመልካቾች የካሳ ክፍያ ጥያቄ ኃላፉነተ የለበትም በማለት የደረሱበት ድምዲሜ ተገቢነት የለውም።
በመሆኑም ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት ተጠሪ በ1ኛ አመልካች ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት ካሳ የመክፈል ኃላፉነት ያለበት በመሆኑ የካሳ መጠንን በተመለከተ እንዱሁም 2ኛ አመልካች የጠየቀውን ዲኝነት በተመለከተ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 20/05/2011 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በይ/መ/ የካቲት 2 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተዘጋውን መዝገብ አንቀሳቅሶ ተጠሪ ለአንደኛ አመልካች ተሽከርካሪ ሉከፍል የሚገባው የካሳ መጠን ምን ያክል ነው? 2ኛ አመልካች በጠየቀው ዲኝነት መሰረት ለ1ኛ አመልካች ከሚከፈለው የካሳ ገንዘብ ላይ ምን ያክል የብድር ገንዘብ ሉከፈለው ይገባል። 2ኛ አመልካች ከካሳው ገንዘብ ላይ የብድር ገንዘቡ ከተከፈለው በኋላ ለ1ኛ አመልካች የሚከፈል ተራፉ ገንዘብ አለ የለም? የሚለትን ነጥቦች በግራ ቀኙ ማስረጃ እንዱሁም አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ ማስረጃ በማስቀረብ ተገቢውን እንዱወስን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 143/1 መሰረት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ።