No summary available.
የሰበር መዝገብ ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም ዳኞች፡- …
መዝገቡ ለሰበር ሰሚ ችልቱ ላቀርብ የቻለው የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችልት በአዋጅ ቁጥር 1161/2011 ቁጥር 19 እና 20 መሰረት ለአቤቱታ ሰሚ እና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ያልቀረበውን የካሳ ይከፈለን እና ምትክ መሬት ይሰጠን ጥያቄን ተቀብል የማስተናገድ የሥረ ነገር ሥልጣን የላለው በመሆኑና ክሱም በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት የሰጠው ብይን፤ እንዱሁም ይህን ብይን በመቃወም የቀረበውን የይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ በተመለከቱት የሥር ፍርድ ቤቶች አቤቱታው ተቀባይነት ማጣቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው በማለት በሰበር ታይቶ እንዱታረምላቸው አመልካቾች መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ/ም ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻነት ነው።
ጉዲዩ የካሳ ክፍያ እና በተወሰደ መሬት ምትክ መሬት መጠየቅን የሚመለከት ሆኖ ክሱ በቀረበበት በሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችልት አመልካች በከሳሽነት ተጠሪ ደግሞ በተከሳሽነት የተከራከሩ ሲሆን፤ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ በአጭሩ፡- አዋሳኞቹ በክሱ ላይ የተመለከቱት በሁለት አከባቢዎች የሚገኝ አጠቃላይ ስፊቱ 2,500.00( ሁለት ሺህ አምት መቶ) የሆነ ቦታ ላይ የሚገኘውን 5,000.00 (አምስት ሺህ) እግር ቡና ተገቢውን ከሳ ሳይከፍል እና ምትክ ቦታ ሳይሰጥ ተጠሪ አትክልቱን ነቃቅል በማንሳት መሬቱን ለባለሥልጣናት እና ለላልች ግለሰቦች ስለሰጠ የንብረት ግምቱን 800,000.00 (ስምንት መቶ ሽህ) ብር ከፍል ምትክ ቦታ እንዱሰጣቸው እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል። ተጠሪም ለክሱ በሰጠው መልስ አመልካቾች ይዞታቸው ያለአግባብ ከተወሰደባቸው በአዋጅ ቁጥር 1161/2011 መሰረት ቅሬታቸውን ለይግባኝ ሰሚው አካል ማቅረብ ሲገባቸው ያቀረቡት ሂደቱን ያልጠበቀውን ክስ ፍርድ ቤት ተቀብል የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን ያለውም። አመልካቾች ይዞታቸው ተወሰደብን የሚለት ከ24 – 26/01/2002 ባለው ጊዜ ውስጥ ሆኖ ከ10 ዓመት በኋላ የቀረበው ክስ በይርጋ ይታገዲል። ይዞታው የራሳቸው ለመሆኑ አመልካቾች ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ ስለላለ በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 33(2) መሰረት ክስ ለማቅረብ መብት እና ጥቅም የላላቸው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ከክሱ እንዱያሰናብታቸው በመጠየቅ በፍሬ ነገር ክርክሩ ላይም ዝርዘር ምላሽ አቅርበዋል። አመልካቾች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያው ላይ ባቀረቡት ክርክር ቅሬታውን ተቀብል የሚያስተናግድ ኮሚቴ አለመኖሩን ፤
ከ10/07/2001 እስከ 2005 ዓ/ም ድረስ የከተማ ቦታዎች እንዲይሸነሸኑ የክልለ መንግስት ዕግድ ሰጥቶ ባለበት ይዞታቸው ተሸንሽኖ ለግለሰቦች ስለተሰጠ የይርጋ ጊዜው መቆጠር ያለበት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ በመሆኑ ያቀረቡት ክስ በይርጋ የማይታገድ መሆኑን፤ የይዞታው ባለቤት ለመሆናቸው ግብር የከፈለበት ደረሰኝ ስላላቸው ክስ ለማቅረብ መብትና ጥቅም አለን በማለት ተከራክረዋል።
የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችልትም ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑንና ክሱ በይርጋ መታገድ አለመታገደን በጭብጥነት ይዞ እንደመረመረው፡- ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 1161/2011 ቁጥር 19 እና 20 ድንጋጌ መሰረት ለቅሬታ እና ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሳይቀርብ ፍርድ ቤት በቀጥታ ጉዲዩን ተቀብል የማስተናገድ የሥረ ነገር ሥልጣን የላለው በመሆኑና አመልካቾች ለተወሰደባቸው መሬት ካሳ እና ምትክ መሬት እንዱሰጣቸው ያቀረቡት ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት መዝገቡን በብይን የዘጋ ሲሆን ፤
ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካቾች ያቀረቡትን የይግባኝ አቤቱታ በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 337 መሰረት በመሰረዙ እና የሰበር አጣሪ ችልቱም የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይንና ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በማለት አመልካቾች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ ሳይቀበል ቀርቷል።
አመልካቾች በየደረጃ ያለት ጉዲዩን የተመለከቱት ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይንና ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ በአጭሩ ተጠሪ ይዞታቸውን የተሸነሸነው በክልለ መንግስት የተጣለ ዕገዲ እያለ መሆኑን፤ አዋጅ ቁጥር 1161/2011 የወጣው በ2011 ሆኖ አመልካቾች ይዞታቸውን የተነጠቁት ከዚያ በፉት በመሆኑና ቅሬታ ለመስማት የተቋቋመ አካል በላለበት አዋጅ ቁጥር 1161/2011ን መሰረት አድርጎ የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ማግኘቱ አግባብነት የለውም። ይዞታው የተወሰደው አዋጅ ቁጥር 1161/2011 ከመውጣቱ በፉት ስለሆነ ጉዲዩ በመደበኛ የፍትሐ ብሕር ሕግ የሚታይ ሆኖ ሳለ የሥር ፍርድ ቤቶች ሥልጣን የለንም ማለታቸው ተገቢ አይደለም። የይርጋ ጊዜው መቆጠር ያለበት የዕግድ ትዕዛዙ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ በመሆኑና በከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በ2006 ዓ.ም በክርክር ላይ መቆየታቸው ይርጋውን የሚያቋርጥ ምክንያት ሆኖ እያለ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው መባለ ስህተት በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሸሮ ጉዲዩ ወደ ሥር ፍርድ ቤት ተመልሶ የፍሬ ነገር ክርክሩ ታይቶ ውሳኔ እንዱያገኝ ጠይቀዋል።
የሰበር አቤቱታውን የመረመረው የሰበር ሰሚ ችልቱ የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የለኝም ካለ በኋላ የቀረበው ክስ በይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጠው ውሳኔ የሕግ መሰረት ያለው መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ተጠሪ በጽሐፍ መልስ እንዱሰጥ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተጠሪ የፍርድ ቤት መጥሪያ የደረሰው ለመሆኑ ማረጋገጫ ስለቀረበ እና ቀርቦ መልስ ስላልሰጠ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተው ሲሆን ችልቱም ለሰበር አቤቱታው መሰረት የሆነው ውሳኔ መሰረታዊ ሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ አግባብነት ካለው የሕግ ድንጋጌ አንፃር እንደሚከተለው መርምሮታል።
ማንኛውም ሰው በፍርድ ሉቋጭ በሚችል ጉዲይ ለፍርድ ቤት ወይንም ላላ በሕግ ለተቋቋመ የዲኝነት አካል በማቅረብ ፍትሕ የማግኘት መሰረታዊ መብት እንዲለው የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37 ይደነግጋል። በዋነኛነት የዲኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች መሆኑን እና ለላልች ተቋማትም በሕግ የዲኝነት ሥልጣን ላሰጥ እንደሚችል ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 37 እና 79(1) ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል። በሕግ በግልጽ የዲኝነት ሥልጣን ለላላ አካል እስካልተሰጠ ድረስ በፍርድ እልባት ሉያገኙ የሚችለ ጉዲዮችን ተቀብል የመዲኘት ሥልጣን የፍርድ ቤት ነው።
ለማንኛውም ኢትዩጵያዊ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት የመሆን መብት በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40(1) ተከብሯል። ኢትዩጵያዊ ዜጋ በጉልበቱ ወይንም በገንዘቡ በመሬት ላይ ለሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይንም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል ሙለ መብት ያለው መሆኑን፤ ይህ መብትም የመሸጥ፤ የመለወጥ፤ የማውረስ ፤ የመሬት ተጠቃሚነቱ ሲቋረጥ ንብረቱን የማንሳት፤ ባለቤትነቱን የማዛወር ወይንም የካሳ ክፍያ የመጠየቅ መብትንም እንደሚያካትት እና አፈፃፀሙ በሕግ እንደሚወሰን አንቀጽ 40(7) ያመለክታል። በንዐስ አንቀጽ 8 ድንጋጌ መሰረት የግል ንብረት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ መንግስት ለሕዝብ ጥቅም ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ በመክፈል የግል ንብረትን ሉወስድ ይችላል። ሕግ መንግስቱን መሰረት አድርጎ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፤ ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሶ የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመሰወን የወጣው አዋጅ ቁጥር 1161/2011 ቁጥር 11 ድንጋጌ መሰረት ለህዝብ ጥቅም ሲባል ወይንም የተሻለ ልማት ሉካሄድበት ይገባል ተብል ሲታመን አግባብ ባለው የመንግስት አካል ውሳኔ ሲተላለፍ በአዋጁ መሰረት ቅድሚያ ለተነሽ ባለው የንብረትና ይዞታ መብት መሰረት የንብረት እና የልማት ተነሽ ካሳ ከፍል መሬቱን የማስለቀቅ ሥልጣንን ለከተማ አስተዲደር ወይንም ለወረዲ አስተዲደር ይሰጣል። የሚከፈለው ካሣም በመሬቱ ላይ ለሚገኘው ንብረት እና በመሬቱ ላይ ለተደረገው ቋሚ መሻሻል እንደሆነ ከአዋጁ ቁጥር 12 ድንጋጌ መረዲት ይቻላል። በቋሚነት ለሚነሳ የከተማ መሬት ባለይዞታ ልማት ተነሽ ካሰ እና ምትክ ቦታ የሚሰጥበት አግባብ በቁጥር 13(4) ሥር ተመላክቷል። አዋጁን መሰረት አድርጎ በሚሰጥ ውሳኔ ላይ የሚቀርብ አቤቱታን እና ይግባኝ የሚመለከት አካል መቋቋም ያለበት መሆኑን ከቁጥር 18 ድንጋጌ መረዲት ይቻላል።
አዋጁ አቤቱታ እና ይግባኝ የሚቀርብበትን ሥርዓት መዘርጋቱንም የቁጥር 19 እና 20 ድንጋጌ ያመለክታል።
በተያዘው ጉዲይ የአመልካቾች የዲኝነት ጥያቄ ለተወሰደባቸው ይዞታ ምትክ መሬት እንዱሰጣቸው እና በይዞታቸው ላይ ላፈሩት ንብረት ካሳ እንዱከፈላቸው ሲሆን ፤ ጉዲዩ መታየት ያለበት የመሬት ይዞታቸው በተወሰደባቸው ወቅት በሥራ ላይ በነበረው ሕግ ወይስ ክሱ በቀረበበት ጊዜ ያለውን ሕግ መሰረት አድርጎ መሆኑ ፤ ለጉዲዩ አግባብነት ባለው ሕግ መሰረት የአመልካቾችን የዲኝነት ጥያቄ ተቀብል ሉያስተናግድ የሚችል በህግ ሥልጣን የተሰጠው አካል መኖር አለመኖሩ ፤ ጉዲዩን አይቶ ውሳኔ ላሰጥ የሚችል በሕግ አግባብ የተቋቋመ አካል የላለ ከሆነ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አይቶ መወሰን መቻል አለመቻለ እና ላልች ተያያዥነት ያላቸው ጭብጦች በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 246 ፤ 247 እና 248 ድንጋጌዎች መሰረት ሳይመረመሩ የተሰጠው ውሳኔ የአመልካቾችን ፍትሕ የማግኘት መብት የሚገድብ ነው።
በልላ በኩል የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን የለኝም ካለ በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥዓት ሕጉ ቁጥር 9(1) እና 231 (1) (ለ) መሰረት የክስ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት መዝገቡን ዘግቶ ተከራካሪዎቹን ማሰናበት ሲገባው ተጠሪ በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 244(2) (መ) መሰረት ያቀረበውን መቃወሚያ ተቀብል በቁጥር 245 መሰረት መርምሮ ክሱ በይርጋ ይታገዲል ማለቱ የሥነ ሥርዓት ጉድለት ነው።
ሲጠቃለል ከላይ በዝርዘር በተጠቀሰው ምክንያት ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ብይን እና ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ተከታዩ ተወስኗል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር አጣሪው ችልት በሰበር በመዝገብ ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችልት በፍርድ ሀተታው ውስጥ በተመለከተው መሰረት ጉዲዩን አይቶ ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ እንዱሰጥ መዝገቡ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341(1) መሰረት ተመልሶለታል።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኛቸው የሰበር ክርክሩ ያስከተለው ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.