No summary available.
ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በእውቀት በላይ ቀነዓ ቂጣታ ላሉሴ ደሳለኝ ኑረዱን ከድር አመልካች፡ ካንትሪ ክለብ ዳቬልፔርስ ሪል ስቴት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር - ታማኝ በየነ - ቀረቡ ተጠሪ፡ ወ/ሮ እናኑ ዘለቀ - ጠበቃ በላይ መሸሻ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
መዝገቡ ለዚህ ችልት የቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 06/04/2013 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 29/10/2013 ዓ.ም ይግባኙን በመሰረዝ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ በማጽናቱ ዉሳኔዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረም በማለት አመልካች ባቀረበው አቤቱታ መነሻ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ሲታይ በስር ፍ/ቤት ከሳሽ ተጠሪ ሲሆኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።ተጠሪ ባቀረቡት ክስ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ጥቅምት 02 ቀን 2001ዓ.ም በተደረገ ቤትን ገንብቶ የማስረከብ ውል አመልካች ከመንግስት በሉዝ ከተረከበው ቦታ በቦታ ቁጥር A-936 የቤት አይነት 1/ በመነሻ/1001.7 ካ.ሜ በሆነ የግቢ ስፊት የስምምነቱ አካል በሆኑት የቦታ ፔላን፣ የቤት ፔላን፣ የስራ ዝርዝር እና የግንባታ እቃዎች ዝርዝር የኤላክትሪክ፣ውሃና የስልክ መስመር እንዱሁም ዋና ዋና የውስጥ ለውስጥ አስፊልት መንገድችን ጨምሮ ቤት ገንብቶ በ18 ወራት ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ ተጠሪ ለቤቱ እና ተጓዲኝ አገልግልቶች ግንባታ ቫትን ጨምሮ የሚስፈልገውን ብር 2‚894‚285.50 (ሁለት ሚሉዮን ስምንት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ አምስት ከ50/100) ለመክፈል ተዋውለዋል።አመልካች ግንባታውን ለማጠናቀቅና ለማስረከብ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የኮንስትራክሽን ግብዓት ላይ የዋጋ ንረት የገጠማቸው እና የዋጋ ጭማሪ ማስተካከያ እንዱደረግላቸው እና ቤቶቹ ከሚያዚያ 2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 2004 ዓ.ም ለማስረከብ በተደረገ ስምምነት መሰረት የዋናው ክፍያ እና የጭማሪ ዋጋ ማስተካከያ እንዱሁም ከ2000 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ላለው ስምንት አመት ጊዜ ውስጥ የሚከፈል የሉዝ ክፍያን ጨምሮ ተጠሪ አጠቃላይ ብር 3‚426‚248.47 (ሶስት ሚሉዮን አራት መቶ ሃያ ስድስት ሺ ሁለት መቶ አርባ ስምንት ከ47/100) የከፈለ ሲሆን በውለ መሰረት አመልካች ቤቱን ገንብቶ እንዱያስረክባቸው፣በወቅቱ ግንባታውን ገንብቶ ባለማጠናቀቁ የውለ 10% ብር 342‚624.85 (ሶስት መቶ አርባ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ አራት ከ85/100) መቀጮ እንዱከፍላቸው፣ቤቱን በወቅቱ ገንብቶ ባለማጠናቀቁ ከቤቱ በኪራይ ያገኙ የነበረውን በወር ብር 10‚000 (አስር ሺህ) ከታህሳስ 2004 ዓ.ም ጀምሮ ክሱ እስከ ቀረበበት ቀን ድረስ 87 ወራት ብር 870‚000 (ስምንት መቶ ሰባ ሺህ ብር) እና ወጪና ኪሳራ እንዱከፈላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች በጽሁፍ በሰጠው መልስ ተጠሪ ክስ ያቀረቡበት ጅምር ቤት የሚገኘው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለገጣፍ ለገዲዱ ከተማ አስተዲደር ውስጥ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 25 መሰረት ፍ/ቤቱ ስልጣን የለውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድ በሰጠው መልስ በውለ አንቀጽ 14.4 እና 14.5 መሰረት አመልካች በውለ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ቤቱን ገንብቶ ማስረከብ ያልቻለ እንደሆነ ለተጠሪው የተቀመጠው መፍትሓ (remedy) አመልካች ውለን ተገድ እንዱፈጽምለት መጠየቅ ሳይሆን የከፈለው ገንዘብ እንዱመለስለት እና ለደረሰበት ጉዲት ኪሳራ መጠየቅ ብቻ በመሆኑ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ውለን ሳይረደት ነው።ተጠሪ የሪል ስቴት ቤት ላላ ቦታ እንደማይገኝ አድርገው ውለ በግድ ይፈጸምልኝ በማለት ያቀረቡት ክርክር አግባብ አይደለም።በፍ/ብ/ህ/ቁ 2876 የአንድ ተዋዋይ ግዳታ የላለን ቤት ገንብቶ የማስረከብ በሆነ ጊዜ ውለ ህንፃ ስራ ውል እንጂ የሽያጭ ውል ልባል እንደማይቻል በግልጽ ተደንግጓል።አመልካችና ተጠሪ የቤት ግንባታ ውልን በተፈራረምንበት ወቅት ምንም የተገነባ ነገር የላለበት ቦታ አዱስ ቤትን ገንብቶ የማስረከብ ውል ነው።ስለዚህ እየተገነባ ያለው ቤት ውል በምንዋዋልበት ወቅት ያልነበረ እና ውላችንም ግንባታ እንጂ የሽያጭ ውል ስላልሆነ ከሳሽ የፍ/ብሓር ህጉ አንቀጽ 2892(1/2) ድንጋጌ ያለቦታው በመጥቀስ ያቀረቡት ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል።አመልካች ውለን ተገድ ቢፈጽም የውል ፈፃሚውን ነፃነት ስለሚጎዲ በተጠሪ ላይ ጉዲት የደረሰ እንደሆነ ይህንኑ ከመጠየቅ በቀር ውለን አመልካች ተገድ የሚፈጽምበት ምክንያት የለም።የተጠሪ የውል ይፈፀምልኝ ክስ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1776 ላይ ከሰጠው አስገዲጅ ህግ ትርጉም አንፃር አንደንም መስፈርት ስለማያሟላ ክሱ ውድቅ ይደረግ፤አመልካች የቤቱን ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ እንዲላጠናቀቀ ሁለ ተጠሪም በበኩላቸው የሚፈለጉባቸውን ክፍያ በውለ መሰረት አልከፈለም የከፈለትም ቢሆን በውለ አንቀጽ 7 በተቀመጠው ሁኔታ ሳይሆን ቆራርጠው በመክፈላቸው የተጠሪ ቤት ግንባታ በተደጋጋሚ ተቋርጧል።ተጠሪ የሚፈለግባቸውን ክፍያ ሳይፈጽሙ እና ግዳታቸውን በወቅቱ ሳይወጡ ወይም ለመወጣት ዝግጁ የነበሩ መሆኑን ሳያስረደ አመልካች ውለን ተገድ እንዱፈጽም ያቀረቡት ክስ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1757 የሚቃረን ስለሆነ 10% ኪሳራ ይከፈለኝ ሲለ ያቀረቡት መከራከሪያ የህግ መሰረት የለውም።ተጠሪ ቤቱ የዘገየበት ኪሳራ ይከፈለኝ ማለታቸው ተቀባይነት የለውም ኪሳራ መጠየቅ ይችላለ እንኳን ቢባል የኪሳራውን መጠን በተመለከተ ተጠሪ በክሳቸው ላይ የጠቀሱትን ቤቱ ቢከራይ ኖሮ ያስገኝ የነበረውን ገቢ ለመጠየቅ አይችለም።በፍ/ብ/ህ/ቁ 1889 እና 2090 በተደነገገው መሰረት ተዋዋይ ወገኖች ስለሚከፈለው ኪሳራ አስቀድመው በውላቸው መወሰን እንደሚችለ በተደነገገው መሰረት የቤቱ ግንባታ ከውለ የጊዜ ገደብ በላይ ለዘገየበት ጊዜ ለቤት አሰሪው መከፈል የሚገባው ኪሳራ 0.1% በየቀኑ ተሰልቶ 10% እስኪደርስ መሆኑ በግንባታ ውለ አንቀጽ 14.5 ተመላክቶ ይገኛል።ስለሆነም ተጠሪ ከውለ ላይ ከተቀመጠው ጣሪያ በላይ ኪሳራ ሉጠይቁ አይችለም።ተጠሪ በወር ብር 10,000 (አስር ሺህ) ሂሳብ ተሰልቶ እንዱከፈላቸው የጠየቁት የቤት ኪራይ መጠን ቤቱ የሚገኘው አካባቢ ገና በመልማት ላይ ያለና ከመሀል ከተማ የራቀ በመሆኑ የተጋነነ እና የአካባቢውን ሁኔታ ያላገናዘበ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ቤቱ ቢከራይ ከብር 5000 (አምስት ሺህ) በላይ ሉከራይ የማይችል በመሆኑ ተጠሪ የጠየቁትን ዲኝነት ውድቅ በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በብይን ዉድቅ በማድረግ በፍሬ ነገሩ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ አመልካች የግንባታ ስራውን በውለ መሰረት ማጠናቀቅ በነበረበት ጊዜ ውስጥ ባለማጠናቀቁ እና የግንባታ ጊዜው ተራዝሞ ባለበት ሁኔታ በውለ ተገድጄ የግንባታ ስራን የምፈጽምበት ግዳታ ቀሪ አድርጌያለሁ ሲል አመልካቹ ያቀረበዉን መከራከሪያን ውድቅ በማድረግ፣በፍ/ብ/ህ/ቁ 1776(1) እና በሰበር መ/ ላይ የህግ ትርጉም መሰረት አመልካች በህግ የሰውነት መብትና ግዳታ ያገኘ በመሆኑ ነፃነቴን ስለሚነካ ተገድጄ አልፈጽምም ያለውን በተመለከተ ነፃነቱን የሚነካ የህግ ምክንያት የለም፤ቀሪ የቤቱ ስራ የአመልካችን ልዩ ሙያና ችልታ የሚጠይቅ ቴክኒካል የሆኑ ስራዎች ስለሆኑ በውል መሰረት ተገደው ሉፈጽም ይገባል።ተጠሪ የጠየቁት መቀጮ 10% ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1790 መሰረት በአንድ በኩል ተገድ ውል ይፈፀምልኝ በልላ በኩል የውለን መቀጮ ይክፈለኝ በማለት መጠየቅ አይችለም።አመልካች በውለ መሰረት ባለመፈፀሙ ተጠሪ ከቤቱ ማግኘት የነበረባቸውን ጥቅም ያጡ ስለሆነ የቤቱን ኪራይ በወር ብር 5000 (አምስት ሺህ) ሂሳብ ከታህሳስ 2004 ዓ.ም ጀምሮ የ87 ወራት በድምሩ ብር 435,000 (አራት መቶ ሰሰላሳ አምስት ሺህ) ከመጋቢት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እዲው ተከፍል እስኪያልቅ ድረስ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዱከፍለ በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ በመ/ ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ በቀን 29/10/2013 ዓ.ም ይግባኙን በመሰረዝ መዝገቡን ዘግቶታል። ይህ አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ በሰበር ለማሳረም ነው።
የአመልካች ጠበቃ በቀን 06/12/2013 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት አቤቱታ አጭር ይዘቱ፡ የስር ፍ/ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 22 እና 24 በመጥቀስ ውለ የተደረገው በአዱስ አበባ በመሆኑ እና የአመልካች ዋና መስሪያ ቤት አዱስ አበባ በመሆኑ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ጉዲዩን በውክልና ማየት የሚችል ቢሆንም ከፍተኛው ፍ/ቤት አዱስ አበባ ውስጥ ስለሚገኝ ሁለቱም ተደራሽ ስለሆኑ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር በመ/ ጉዲዩን የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ማየት አይችልም ብል ቢወስንም ውሳኔው ያልታተመ በመሆኑና ከዚህ በፉት በተቃራኒው የተሰጠ ውሳኔ ጠቅሶ ስላልሻረ አስገዲጅነት የለውም በማለት የሰጠው ውሳኔ ከአዋጁ ድንጋጌ ውጪ ራሱን ቅድመ ሁኔታ በመፍጠር በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም ውድቅ ያደረገበት ሁኔታ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት።በህገ መንግስቱ አንቀጽ 80(2) መሰረት ክልልች በግዛታቸው ውስጥ የሚነሱ የፋዳራል ጉዲዮችን የማየት ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፤እንዱሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 25 መሰረት የግዛት ስልጣን ያለው የኦሮሚያ ክልል ፍ/ቤት እንጂ ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አይደለም፣አመልካችና ተጠሪ ባደረግነው ውል አንቀጽ 14.4 እና 14.5 መረዲት የሚቻለው ቤት ሰሪ በውለ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ቤቱን ገንብቶ ማስረከብ ካልቻለ ለቤት አሰሪው የተቀመጠው መፍትሓ ቤት ሰሪው ውለን ተገድ እንዱፈጽም መጠየቅ ሳይሆን የከፈለው ገንዘብ እንዱመለስለት እና እስከ 10 በመቶ ድረስ ኪሳራ እንዱከፈለው ለመጠየቅ መሆኑን ስምምነት ተደርጓል። የውለን ተገድ መፈፀም አማራጭ በውል ቀሪ አድርገናል የሚለውን ክርክራችን በማለፍ አመልካች ተገድ ውለን መፈፀም አለበት በማለት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። በፍ/ብ/ህ/ቁ 1771 እና 1779 መሰረት ተጠሪ ግዳታቸውን ሳይወጡ ክፍያዎችን አቆራርጠው በመክፈላቸውና በማዘግየታቸው ቤቱ ግንባታ የዘገየ ሆኖ ሳለ እንዱሁም አመልካችና ተጠሪ የተስማማንበት የኪሳራ መጠን በውላችን ላይ ተመልክቶ እያለ የስር ፍ/ቤት ከህግ ውጪ የቤት ኪራይ እንድከፍል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ ህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ዉሳኔዉ እንዱታረም በማለት አመልክተዋል።
የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤት የክርክር መነሻ የሆነውና በተከራካሪ ወገኖች መካከል በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ልዩ ስሙ ለገጣፍ ተብል በሚታወቅ ቦታ የቤት ግንባታና ማስረከብ ውል በሚመለከት የቀረበውን አቤቱታ ተቀብል ለማየት የግዛት ዲኝነት ሥልጣን ያላቸው መሆን አለመሆን፣ ውለንም ተገደው ስለመፈፀም አማራጭ ቀሪ ያደረጉ ስለመሆናቸው በውላቸው ተገልፆ እያለ አመልካች ተገድ እንዱፈጽም፣ ኪሳራ ጭምር እንዱከፍል የተወሰነበት አግባብ ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 80(2)፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 25፣ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1776 እና ተከታይ ድንጋጌዎች እንደዚሁም ጥቅምት 2 ቀን 2001 ዓ.ም ከተደረገው የቤት ግንባታና ማስረከብ ውል አንቀጽ 14.4 እና 14.5 አንፃር ለማጣራት መዝገቡ ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዟል።
ተጠሪ በቀን ጽፍ ባቀረቡት መልስ የስር ፍ/ቤት ግዛት ስልጣን የለውም በማለት በቀረበው መቃወሚያ ላይ ፍ/ቤቱ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 10(2) እና በሰ/መ/ ቅጽ 19 ከተሰጠው ሰበር ውሳኔ አንፃር ፍትህን የሚያጓድል ባልሆነበት ይግባኝ ላቀርብ አይገባም፤ አመልካች ከዚህ ቀደም የሰበር አመልካች ሆኖ በሰበር መ/ ህዲር 28 ቀን 2011 ዓ.ም ከፍ/ቤቶች የግዛት ክልል ስልጣን አንፃር ያስወሰነውን ፍርድ የህገ-መንግስት አጣሪ ጉባዓ መጋቢት 25 ቀን 2011 ዓ.ም በመ/ቁ 1937/09 በዋለው ችልት ሽሮታል፣የፋዳሬሽን ምክር ቤት ህገ-መንግስቱን ለመተርጎም ባለው ስልጣን ተጠቅሞ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ሆኖ መፈፀም እንደሚገባው በሰበር መ/ ቅጽ 11 ላይ አስገዲጅና ገዢ ትርጉም ሰጥቶበታል፤ክስ የቀረበበት ቤት ገንብቶ የማስረከብ ውል የተያዘው አዱስ አበባ በመሆኑና የአመልካች ዋና መስሪያ ቤት አዱስ አበባ በመሆኑ፣የተጠሪ መኖሪያ አድራሻ ካናዲ ቶሮንቶ በመሆኑ በፋዳራል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ 1234/13 አንቀጽ 5(1)(ሸ) እንዱሁም የሰበር መ/ ቅጽ 8 እና ሰበር መ/ ቅጽ 23 መሰረት የፋዳራል ፍ/ቤቶች የስረ ነገርና ግዛት ክልል ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ አስገዲጅ ውሳኔ ተሰጥቶበታል፤ውለ የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት ነው ቢባል እንኳን ክሱ ግንባታው በሚገኝበት ላስቻለው ባለስልጣን ፍ/ቤት ወይም የአመልካች ዋና መስሪያ ቤት በሚገኘበት አዱስ አበባ በሚያስችለው ስልጣን ባለው ፍ/ቤት በአማራጭ ለማቅረብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 25(2) መሰረት እንዱሟለ የሚጠበቁበት ሁለት መስፈርቶች የተሟለ በመሆናቸው ተጠሪ ክሱን ለፋዳራል ፍ/ቤት ማቅረቡ ህጋዊ መሰረት ያለው ነው፤በተመሳሳይ ሁኔታ ቤት ገንብቶ የማስረከብ ውል በፋዳራል ፍርድ ቤቶች በአመልካች ላይ ክስ ቀርቦበት እንደ ውሳኔው ሲፈጸም ለመቆየቱ ማሳያ ይሆን ዘንድ ሰበር መ/ ዉሳኔ ይገኛል፤በልላ በኩል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 22(1) ላይ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ወይም ቅርንጫፍ መ/ቤት ባለበት ክስ ማቅረብ እንደሚቻል በግልጽ ደንግጓል፤አመልካች በገባው የመጀመሪያ ውል መሰረት ቤቱን አጠናቆ ለማስረከብ በዋጋ ንረት ምክንያት አለመቻለን ቤቱን አጠናቆ የቤት ማስረከቢያ ጊዜ ማራዘሚያ ስምምነት በመደረጉ ምክንያት አመልካቹ ጠቅሶ እየተከራከረበት ያለው የውለ አንቀጽ 14.4 ተፈፃሚነት የለውም።አንቀጹ ተፈፃሚነት ሉያገኝ የሚችለው ብቸኛ ሁኔታ ተዋዋዮች የግንባታ ጊዜውን በስምምነት ማራዘም ሳይችለ ቀርተው ቢሆን ኖሮ ብቻ ነው፤
የቤት ማስረከቢያ ጊዜው መራዘሙን ተከትል አመልካች ለተጠሪ ቤት ሰርቶ ሉያስረክብ በገባው ግዳታ መሰረት ቤቱን ገንብቶ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ በካርታ ቁጥር L/X/L/D/7459/07 በቀን 15/08/07 ዓ.ም አሰርቶ መስጠቱ፣የሉዝ ክፍያ መጠናቀቁ በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።አመልካቹ በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ ቤቱን አጠናቆ ለማስረከብ ባለመቻለ ይህን ክስ በስር ፍ/ቤት ስናቀርብና ሲፈረድበት የቤቱ አብዛኛው ስራ የተጠናቀቀ በመሆኑና የቀሩትን ማጠቃለያ ስራዎች በጋራ ለመለየት እንዱቻል የግራ ቀኙን ባለሙያዎች ይዘው ያልተጠናቀቁና እንደውለ ሉሟለ የሚገባቸው 16 የሚሆኑ በዓይነትና በስም ዝርዝር ግራ ቀኙ ተማምነውበት ተፈርሞ አመልካቹ በቀን 20/12/2013 ዓ.ም በቁጥር ሲሲዱ/693/13 በተፃፈ ደብዲቤ በጋራ ተለይቶ የተፈረመውን ቀሪ ስራ አባሪ በማድረግ እነዚህ ጉድለቶችን እስከ የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ አስተካክል ሉያስረክብ ማረጋገጫ መስጠቱ እንደውለ ተገዲጅ መሆኑን ራሱ አምኖ የተቀበለ እና ቤት ሰርቶ የማስረከብ ውለ ቀሪ ያልተደረገም መሆኑን ነው። አመልካች የውለን አንቀጽ 14.4 እና 14.5 በመጥቀስ የጉዲት ኪሳራው ውሳኔ ተገቢነት የለውም በማለት ያቀረበው ክርክር አንቀጾችን ሙለ በሙለ በእጅጉ የሚጣረስ ነው።እነዚህ አንቀፆች ግንባታ ውለ በስምምነት ተራዝሞ ውለ ቀሪ ባልተደረገበት ሁኔታ ከግንባታ መዘግየት ጋር ለሚደርስ ጉዲት ተፈፃሚነት የማይኖራቸው በመሆኑ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም በማለት ተከራክረዋል።አመልካች አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና ክርክሩ በአጭሩ ከላይ የተገለፀውን የሚመስል ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር እና አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል።
የመጀመሪያዉ ጭብጥ የዲኝነት ስልጣን የሚመለከት ነዉ በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘዉ የመጀመሪያ ጭብጥ የክርክር መነሻ የሆነውና በተከራካሪ ወገኖች መካከል የተደረገዉ ዉል በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ልዩ ስሙ ለገጣፍ ተብል በሚታወቅ ቦታ ቤት ገንብቶ ማስረከብ ውል በሚመለከት የቀረበውን ክስ የፋዳራል ፍርድ ቤት ተቀብል ለማየት የግዛት ዲኝነት ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነዉ።
በመሰረቱ የፍርድ ቤቶች የዲኝነት ስልጣን በሶስት መሰረታዊ ጉዲዮች ተከፍል የሚታይ መሆኑ ይታወቃል።ይኸዉም ብሓራዊ የዲኝነት ስልጣን (judicial jurisdiction)፣ የስረ ነገር የዲኝነት ስልጣን (material jurisdiction) እና የግዛት ክልል የዲኝነት ስልጣን(local jurisdiction) ተብል የሚከፈል ሲሆን የመጀመሪያዉ የዲኝነት ስልጣን ምንጭ ዓለም አቀፍ የግለሰብ ህግ ወይም ስምምነቶች ወይም ተቀባይነት ያገኙ መርሆዎችን በመከተል ሉወሰን ይችላል።የአንድ ፍርድ ቤት የስረ ነገር እና/ወይም የግዛት ክልል ስልጣን ምንጩ ብሓራዊ ህጎች ሲሆኑ በዋናነት የስነ ስርዓት እና እንደ አግባብነቱ በመሰረታዊ ህጎችም ተደንግጎ እናገኛለን።በተለይም የፋዳራል ስርዓት በሚከተለ ሀገሮች የዲኝነት አካል አወቃቀር እና የስልጣን ክፍፍል በዋናነት በህገ መንግስት የሚወሰን ስለመሆኑ የበርካታ ሀገሮች ልምድ ያሣያል።
የሀገራችን የፍርድ ቤቶች አወቃቀር ስንመለከት የፋዳራል መንግስት አወቃቀር ስርዓት በ1987 ዓ.ም በወጣዉ ህገ መንግስት መሰረት ስርዓቱ ፋዳራላዊ መሆኑን ተከትል ፍርድ ቤቶችም የፋዳራል እና የክልል ፍርድ ቤቶች ተብለዉ ትይዩ የሆኑ ሁለት ፍርድ ቤቶች የተዋቀሩ ስለመሆኑና የፋዳራል ፍርድ ቤቶች በፋደራል ጉዲይ ላይ እንዱሁም የክልል ፍርድ ቤቶች በክልል ጉዲይ የዲኝነት ስልጣን የተሰጣቸዉ መሆኑን ከህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 78 እና 80(1/2) ይመለከቷል።ከዚህ የስልጣን ክፍፍል መርህ መገንዘብ የሚቻለዉ ክልልች በክልላዊ ጉዲይ ላይ ለዓላዊ ስልጣን ያላቸዉ መሆኑን ነዉ።ከዚህም በተጨማሪ የፋዳራል ጉዲዮችን የሚመለከት የፋዳራል ፍርድ ቤት ባልተቋቋመባቸዉ ክልልች ዉስጥ የክልል ፍርድ ቤቶች በህገ መንግስቱ በተሰጠ ዉክልና መሰረት የፋዳራል ጉዲዮችን የመዲኘት ስልጣን በጣምራነት እንደተሰጣቸዉ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 80(2/4) ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል።በመሆኑም በክልል የሚነሱ የፍደራል ፍርድ ቤት ስልጣን የሆኑ ጉዲዮች በልላ ህግ በግልጽ ካልተመለከተ በስተቀር በክልል ፍርድ ቤት ዲኝነት የሚታዩ መሆናቸዉን እንገነዘባለን።ስለሆነም የክልል ፍርድ ቤቶች በጣምራ ስልጣናቸዉ በክልል ግዛት ወሰን የተነሱ የፋዳራል ጉዲዮችን የማየት ስልጣን ስላላቸዉ ጉዲዩ ወደ ፋዳራል ፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሚወድቅ አይደለም ማለት ነዉ።በልላ አገላለጽ ጉዲይ በህጉ ፣በተከራካሪዎቹ ወይም በንብረቱ ምክንያት የፋዳራል ጉዲይ ቢሆንም በክልል ግዛት ስር የሚገኝ ከሆነ የክልል ፍርድ ቤቶች እንዱያዪት በህገ መንግስት ዉክልና ተሰጥቷቸዋል።ከዚህም የተነሳ የክልል ፍርድ ቤቶች በግዛታቸዉ ባለ ሰዎች ወይም ንብረቶች ጋር በተያያዘ የሚነሳ የፋዳራል ጉዲይን ዉክልናቸዉ እስካልተነሳ ድረስ የመመልከት ስልጣን አላቸዉ።ከዚህም በተጨማሪ በህገ መንግስት ለፋዳራል እና ለክልል ፍርድ ቤቶች ጣምራ ስልጣን መሰጠቱ ተከራካሪ ወገኖች ወደ ፈለጉት ፍርድ ቤት እንዱወስደ (forum shopping) የሚፈቅድ እንዲይሆን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
በተያዘዉ ጉዲይ ተከራካሪ ወገኖች በተለያየ ክልል ነዋሪ መሆናቸዉን እና አመልካቹ በፋዳራል መንግስት የተመዘገበ ድርጅት መሆኑን ተከትል ጉዲዩ የፋዳራል ጉዲይ ስለመሆኑ ክርክር አልቀረበበትም።ይሁንና የከሳሽ የዲኝነት ጥያቄ በዉለ መሰረት እንዱፈጽም የሚል በመሆኑ የግዛት ስልጣን የሚወሰነዉ በፍ/ብ/ስ/ስህግ ቁጥር 24 መሰረት ነዉ በሚል የሥር ፍርድ ቤት የዲኝነት ስልጣን ላይ የቀረበዉን መቃወሚያ ዉድቅ ያደረገ ሲሆን አመልካች በበኩለ ጉዲዩ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመረከብ የቀረበ ነዉ በሚል በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 25 መሰረት ንብረቱ ያለበት ፍርድ ቤት የግዛት ስልጣን አለዉ በሚል ተከራክሯል።በክርክሩ እንደተገለጸዉ ክሱ ዉልን መሰረት ያደረገ ሲሆን የተጠየቀዉ ዲኝነት የቤቱን ግንባታ አጠናቆ እንዱያስረክብ የሚል ነዉ።የዉል ግንኙነት መብትና ግዳታ የሚፈጥረዉ አንድም በተዋዋዩ ሰዉ(right in personum) ላይ ወይም በሆነ ንብረት (right in rem)ላይ ላሆን ይችላል።በዉለ የተፈጠረዉ መብት በሰዉ ላይ ግዳታን የሚፈጥር ሲሆን ክሱ የሚቀርብበትን ፍርድ ቤት በመምረጥ ረገድ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህጉ አንቀጽ 24(1) ለከሳሽ ወገን የተተወ መሆኑ አከራካሪ አይደለም።ነገር ግን ጉዲዩ መነሻ ዉል ቢሆንም በተለይም የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚመለከት ሲሆን የግዛት ዲኝነት ስልጣኑ የሚለየዉ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 25 ስር በተደነገገዉ አግባብ እንደሆነ ከድንጋጌዉ ይዘት ማየት ይቻላል። በዚህም ጉዲይ ክሱ ቤቱን ለመረከብ የቀረበ እንደመሆኑ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 25(1/ሐ) እንደተመለከተዉ ጉዲዩ በንብረቱ ላይ ያለዉን መብት ለማስወሰን የቀረበ መሆኑን ያሣያል።ይህ ከሆነ ደግሞ ክሱ መቅረብ የሚገባዉ ንብረቱ የሚገኝበት ግዛት ክልል ባለዉ ፍርድ ቤት ነዉ።በዚህ ረገድ በተመሳሳይ ሁኔታ አመልካቹ ተከራካሪ በሆነበት ጉዲይ ላይ ክርክሩ የግዛት ስልጣንና የስረ ነገር ልጣን አጣምሮ የያዘ መሆኑን፤ጉዲዩ ለተከራካሪ ወገኖች አመቺነት በሚል ምክንያት ለተከራካሪ ወገኖች ምርጫ የሚተዉ አለመሆኑን በመግለጽ ክሱ ንብረቱ በሚገኝበት ግዛት ክልል ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት በሚል አስገዲጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።ሰበር መ/ቁ/ 159041 ይመለከታል።ሰበር ችልቱ የሰጠዉ የህግ ትርጉም በተመሳሳይ ጉዲዮች ላይ አስገዲጅነት እንዲለዉ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26(3) ስር ተደንግጓል።ስለዚህም የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ የሰጠዉ ብይን የሰበር ችልቱን ዉሳኔ ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም ይገባል።
በልላ በኩል ተጠሪ በበኩለ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ክርክር (ጉዲዩ) በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወስኖ አመልካቹም አቤቱታ እስከ ህገ መንገስት አጣሪ ጉባኤ አቅርቦ የሰበር ችልቱ ዉሳኔ ተሸሯል በማለት የጠቀሳቸዉን ዉሳኔዎች ይዘት መርምረናል።በተለይም የተጠቀሰዉ የህገ መንገስት አጣሪ ጉባኤ መ/ቁ 1937/09 የሰጠዉ ዉሳኔ ሲሆን በይዘቱ ሲታይ በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መታየቱ የህገ መንግስት ትርጉም የሚያስፈልገዉ አይደለም ተብል የአመልካቹ አቤቱታ ዉድቅ መደረጉን የሚያሳይ እንጂ ሰበር ችልቱ በመ/ቁ/159041 ላይ እና በላልችም ተመሳሳይ ክርክሮች ላይ የሰጠዉን አስገዲጅ ዉሳኔ በግልጽ የሻረዉ መሆኑን አያሣይም።እንደሚታወቀዉ የህገ መንግስት ትርጉም አስገዲጅ ዉሳኔ ተብል የሚወሰደዉ ጉዲዩ ለፋዳሬሽን ም/ቤት ቀርቦ ህገ መንግስታዊ ትርጉም የተሰጠበት ሲሆን ነዉ።(አዋጅ ቁጥር 251/1993 አንቀጽ 11 እንዱሁም አዋጅ ቁጥር 1261/2013 አንቀጽ 22(1)ይመለከታል)።በዚህ ጉዲይ የተሰጠ ህገመንግስታዊ ትርጉም ስለመኖሩ የቀረበ አስረጂ ባለመኖሩ በተጠሪ በኩል የቀረበዉን ክርክር አልተቀበልንም። ከዚህም ባሻገር ሰበር ችልቱ በመ/ቁ/100541 ላይ የሰጠዉ ዉሳኔ ይዘት ሲታይ የፍሬ ነገር ክርክሩን በሚመለከት እንጂ የዲኝነት ስልጣን በሚመለከት ጭብጥ ተይዞ አቋም የተወሰደበት ባለመሆኑ ለተያዘዉ ክርክር ነጥብ አግባብነት የለዉም።በዚህ ሁለ ምክንያት የስር ፍርድ ቤት በአመልካች የቀረበዉን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ዉድቅ ማድረጉ ስህተት ነዉ ብለናል።ጉዲዩ በዚህ ጭብጥ የተቋጨ ስለሆነ ተከታዮቹን የፍሬ ነገር ጭብጦችን መመርመር አላስፈለገም።
ሲጠቃለል ጉዲዩ ከተከራካሪ ወገኖች ማንነት እና አድራሻ አኳያ ሲታይ የስረ ነገር የዲኝነት ስልጣን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች መሆኑ አከራካሪ ባይሆንም የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመረከብ የቀረበ ክስ በመሆኑና ንብረቱ የሚገኘዉ ኦሮሚያ ክልል ስለመሆኑ ክርክር ያልቀረበበት በመሆኑ በህገ መንግስቱ የተሰጠ ዉክልና ስልጣንና ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ አንጻር በተመሳሳይ ጉዲይ የግዛትም ሆነ የስረ ነገር ስልጣን በተመለከተ ሰበር ችልቱ ቀደም ሲል በመ/ቁ/ 159041 በሰጠዉ አስገዲጅ ዉሳኔ መሰረት መታየት ሲገባዉ የዉል ጉዲይ ነዉ በሚል ምክንያት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቀብል በስረ ነገሩ ላይ አከራክሮ የሰጠዉ ዉሳኔም ሆነ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሳያርመዉ ማለፈ የሰበር ችልቱን አስገዲጅ ዉሳኔ የሚቃረን ስለሆነ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች 1234/2013 አንቀጽ 2(4/ሸ) እና 10(1/ለ) መሰረት ሉታረም የሚገባዉ ሆኖ አግንተኛል።በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ/የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 228731 ላይ በቀን 06/04/2013 ዓ.ም የሰጠዉን ፍርድ በማጽናት የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 201266 ላይ በቀን 29/10/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ ተሽሯል።
2ኛ/ይህ ፍርድ ተጠሪ ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት ክስ የማቅረብ መብቱን የሚከለክል አይደለም።
3ኛ/ በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
ፍርደ በአዲሪ ሲሰራ ቆይቶ በቀን13/06/2015 ዓ.ም ግራ ቀኙ በተገኙበት ተነበበ።
No topics extracted.