No summary available.
የሰበር መዝገብ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ሰናይት አድነው ደጀኔ አያንሳ አመልካች፡- ሚ/ር ይቬዝን አውግስቲን አላክስ ፋሬዝ ተጠሪ፡- ሚስ ማርካዳት ዣክሉን ሱዛን ግራሲያ ለምርመራ ተቀጥሮ የነበረው መዝገብ ተመርምሮ ቀጣዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
የግራ ቀኙ ጋብቻ የፈረሰው ፈረንሳይ ሀገር ባለ ፍርድ ቤት የሀገርቱን ሕግ መሰረት አድርጎ በተላለፈ ውሳኔ መሆኑ ያላከራከረ በመሆኑ የፍቺ ውጤት የሆነው የንብረት ክርክርም መታየት ያለበት በዚያው ሀገር ፍርድ ቤት ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩ የማየት የሥረ ነገር ሥልጣን ሳይኖረው አከራካሪው የብድር ገንዘብ የጋራ መሆኑን አመልካች ያልተቀበለትን እንደታመነ ወስድ፤ የፈረንሳይ ሕግ ከኢትዮጵያ ሕግ ጋር እንደማይቃረን በጥናት ድርሸበታለሁኝ በማለት ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኝ አበዲሪ ድርጅት የሰጠውን ብድር መጠየቅ የሚቻለው ድርጅቱ በሚኖርበት ሀገር ባለ ፍርድ ቤት ሆኖ ሳለ፤
ለአመልካች ሳይሆን አበዲሪ ለሆነው ድርጅት እንድከፈል የተወሰነውንና የብድር ዔዲው መከፈለ እርግጠኛ ያልሆነውን ገንዘብ ብድሩን ለማስመለስ ለግልግል ዲኝነት የተከፈለ፤ የጠበቃ አበል እና ላልች ወጪዎች ተቀናሽ ሳይደረግ የብድር ገንዘቡን እኩላታ ተጠሪ እንዱካፈለ መወሰኑ አግባብ ባለመሆኑ ተጠሪ የጋራ ሃብት አላቸው የሚባል ከሆነም ሉጋሩ የሚገባው ዔዲዎቹን ለማስመለስ የተከፈለ ወጪዎች ተቀንሶ ተራፉውን ገንዘብ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሻር አለበት በማለት አመልካች የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ/ም የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ መዝገቡ ለሰበር ሰሚ ችልቱ ቀርቧል።
ጉዲዩ የጋብቻ በፍርድ ቤት ውሳኔ መፍረስን ተከትል የቀረበ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር ሲሆን ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን በተመለከተው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ በከሳሽነት ፤
አመልካች ደግሞ በተከሳሽነት ተከራክረዋል። ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ይዘት፡- ግራ ቀኙ ፈረንሳያዊያን በመሆናቸው በዚያው ሀገር በ1969 ዓ/ም ጋብቻቸውን መስርተው ሲኖሩ መስማማት ባለመቻላቸው ትዲራቸው በፈረንሳይ ሀገር በፍርድ ቤት በተሰጠ የፍቺ ውሳኔ መፍረሱን ተከትል ግራ ቀኙ በትዲር ውስጥ እያለ አመልካች ብቸኛ ባለድርሻ በመሆን ባቋቋሙት ቲኢ.ኤፍ.ዜድ.ኢ የሚባል ድርጅት ከተጠሪ እውቅና ውጪ ለዋይ. ጅ.ኤፍ ሰርቪስስ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ/ም እ.አ.አ ብር 6,300,000.00 (ስድስት ሚልዮን ሶስት መቶ ሺ) እና የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ/ም እ.አ.አ 265,000.00(ሁለት መቶ ስልሳ አምስት ሺ) ብር ፤ እንዱሁም ለሰመር ቱር ኤንድ ትራቭል ኃ/የተ//የግ/ ማህበር 2,700,000.00 (ሁለት ሚልዮን ሰባት መቶ ሺ) ማበደራቸውን የፍቺ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ እንዲወቁ ገልፀው፤ ከላይ የተጠቀሱት ተበዲሪ ተቋማት የወሰደትን የብድር ገንዘብ እንዱከፍለ ጠይቆ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አመልካች የብድር ገንዘቡን ለማስመለስ በተቋማቱ ላይ ያቀረቡት ክስ ውሳኔ አግኝቶ የአፈፃፀም ፊይል በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከፍቶ ጉዲዩ በመታየት ላይ ስለሚገኝ ይህ ግራ ቀኙ በትዲር ውስጥ እያለ በብድር የተሰጠው ገንዘብ ከነወለደ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 መሰረት የጋራ የባልና ሚስት ሀብት ነው ተብል እንዱወሰን ጠይቀዋል።
አመልካችም በተጠሪ ለቀረበው ከስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን በማስቀደም በፍሬ ነገሩ ላይ በሰጡት መልስ ግራ ቀኙ የነበራቸው ትዲር በፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ መፍረሱን፤ አመልካች የአበዲሪው ድርጅት ብቸኛ ባለድርሻ መሆናቸው እና አበዲሪው ድርጅትም ለዋይ. ጅ.ኤፍ ሰርቪስስ ኃ/የተ//የግ/ ማሕበር እና ለሰመር ቱር ኤንድ ትራቭል ኃ/የተ//የግ/ ማህበር ብደር መስጠቱን አምነው በብድር የተሰጠውን ገንዘብ በአበዲሪ ድርጅቱ ላይ ያፈሰሰው ችልድረን ኦፍ ዘ ሰን የሚባል በጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ ብድሩ የሚመለስበት ዝርዘርም የፍቺ ውሳኔውን በሰጠው ፈረንሳይ ፍርድ ቤት መዝገብ ተያይዞ የሚገኝ እና ክርክሩ ታይቶ የተወሰነ ሆኖ ሳለ እንደ አዱስ መቅረቡ ተገቢ አለመሆኑን፤ አፈፃፀም ላይ በደረሰው ክርክር ተጠሪ በምስክርነት ቀርበው እያለ ጉዲዩን እንደማያውቁት እና ፍቺውን በሰጠው ፍርድ ቤትም ጉዲዩ እንደማይታወቅ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም። ተጠሪ የጠየቁት ገንዘብ እሳቸውን የማይመከለት፤ አበዲሪው ድርጅት እና አመልካች ባላቸው የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለ3ኛ ወገን መመለስ ያለበት፤ ፈረንሳይ ሀገር በሚገኘው የንብረት ክፍፍለን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት መግለጫ ቀርቦ በዚያው ፍርድ ቤት ውሳኔ ማግኘት ያለበት በመሆኑ ተጠሪ ገንዘቡን የመጠየቅ መብት የላቸውም ተብል እንዱወሰን ጠይቀዋል። ክሱ በተሰማበት ወቅት አመልካች ጉዲዩ መዲኘት ያለበት በፈረንሳይ ሀገር ሕግ መሆን እንዲለበት የተከራከሩ ሲሆን፤ ተጠሪ በበኩላቸው ተበዲሪዎቹ ተቋማት ኢትዮያዊያን ሆኖእያለ አበዲሪው የፈረንሳይ ሀገር ዜጋ በመሆኑ ብቻ በፈረንሳይ ህግ ሉዲኙ እንደማይገባ ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን የተመለከተው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩ መዲኘት ያለበት በኢትዮጵያ ወይንስ በፈረንሳይ ሕግ ?፤ አመልካች ለተበዲሪዎቹ ተቋማት ያበደሩትን ገንዘብ ግራ ቀኙ መካፈል አለባቸው ወይስ የለባቸውም? የሚለ ጭብጦችን ይዞ ጉዲዩ እንደሚከተለው መርምሮታል።
አመልካች ብቸኛ ባለድርሻ በመሆን ያቋቋሙት ቲኢ.ኤፍ.ዜድ.ኢ የተሰኘ ድርጅት ለዋይ. ጅ.ኤፍ ሰርቪስስ ኃ/የተ//የግ/ማህበር እዱሁም ለሰመር ቱር ኤንድ ትራቭል ኃ/የተ//የግ/ ማኅበር በክሱ ላይ የተመለከተውን ገንዘብ ማበደሩ በማስረጃ ተረጋግጧል። የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ በግራ ቀኙ ጋብቻ ውስጥ የተፈራና አመልካች በክሱ ውስጥ ለተመለከቱት ድርጅቶች ያበደሩት ገንዘብ የጋራ እንዱባልላቸው የጋብቻ ፍቺ ውጤትን የሚመለከት ሆኖ የተከራካሪዎቹ ጋብቻ የተመሰረተው በፈረንሳይ ሀገር መሆኑ፤ የፍቺ ውሳኔውም የፈረንሳይ ሕግን መሰረት አድርጎ በዚያው ሀገር ስለተሰጠ የፍቺ ውጤት የሆነው የንብረት ክርክርም መታየት የሚገባው በፈረንሳይ ሕግ መሆኑ ግልጽ ቢሆንም በፈረንሳይ ሀገር ሕግ እና በኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ መካከል ግጭት አለመኖሩን ፍርድ ቤቱ ባደረገው ጥናት ተረጋግጧል።
በፈረንሳይ ሀገር ሕግም በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የባልና ሚስት ንብረት እኩል እንደሚካፈል በሕጉ የተመላከተ ሲሆን አመልካች ገንዘቡ በጋብቻ ውስጥ እንዲልተፈራ፤ የግላቸው እንደሆነ ወይንም ከፍቺ በኋላ የተፈራ ነው የሚል ክርክር ስላላቀረቡ እና ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ገንዘብ አበዲሪ ችልድረን ኦ ዘ ሰን ሳይሆን አመልካች ብቸኛ ባለድርሻ በመሆን ያቋቋሙት ድርጅት መሆኑን በብድር ውለ ላይ በግልጽ የተመለከተውንና ለአመልካች እንዱከፈል የግልግል ዲኝነት ውሳኔ አርፍበት በአፈፃፀም ክርክር ላይ የሚገኘው 9,265,000.00 (ዘጠኝ ሚልዮን ሁለት መቶ ስልሳ አምስት ሺ) ግማሽ ብር 4,632,500.00 (አራት ሚልዮን ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺ አምስት መቶ) አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍለ ወስኗል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ጉድለት አልተገኘበትም በማለት የይግባኝ አቤቱታውን በመሰረዙ አመልካች ያቀረቡትን በፍርደ መግቢያ ላይ የተመለከተውን የሰበር አቤቱታ የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልቱ፡- ግራ ቀኙ የፈረንሳይ ሀገር ዜግነት ያላቸው እና የፍቺ ውሳኔውም የተሰጠው በዚያው ሀገር ከመሆኑ አንፃር የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት የሥረ ነገር ሥልጣን ያለው መሆን / አለመሆኑን ፤ ሥልጣን ነበረው ቢባል እንኳን በፍሬ ነገሩ ላይ የሰጠው ውሳኔ አግባብነት ተጠሪ ባለበት መጣራት አለበት በማለቱ ተጠሪ በሰጡት መልስ፡የውጭ ሀገር ዜግነት ባላቸው ተከራካሪዎች መካክል የሚነሱ ክርክሮችን የማየት ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 25/88 ሆነ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሆኑ ከሥልን አንፃር የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም። የአመልካች አድራሻ አዱስ አበባ በመሆኑና ክሱ በአድራሻቸው መቅረቡ አግባብ መሆኑን፤ ዋይ. ጅ.ኤፍ ሰርቪስስ ኃ/የተ//የግ/ ማህበር እና ለሰመር ቱር ኤንድ ትራቭል ኃ/የተ//የግ/ ማኅበር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ የተቋቋሙ ኢትዮጵያዊያን ተቋማት አመልካች ከተጠሪ ደብቀው በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ከሰው በማስፈረድ ባለመበት ሆነው ጉዲዩ በአፈፃፀም ላይ እያለ ንብረቱ በሚገኝበት ሀገር ክስ መቅረቡ የሚነቀፍ አለመሆኑን፤ አመልካች ጉዲዩ በፈረንሳይ ሕግ ይታይልኝ ከማለት ውጪ የፈረንሳይ ሕግ የባልና ሚስት ንብረትን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ እንደሚቃረን ያቀረቡት አቤቱታ ካለመኖሩም በላይ የሥር ፍርድ ቤት የሁለቱ ሀገራት ሕጎች እንደማይቃረኑ አረጋግጦ የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም። የአመልካች አበዲሪው ድርጅት የግል ድርጅት መሆኑን አውቀው በራሳቸው ስም ከሳሽ ሆኖ ጉዲዩ ውሳኔ አግኝቶ እያለ ተጠሪ ከሳሽ ሲሆኑ ጉዲዩ መልኩን ቀይሮ ክሱ በአረብ ኢምሬት መቅረብ አለበት በማለት ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት የላለው በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ሆኖ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ፀንቶ፤ የጠበቃ እና ላልች ወጪዎችን አመልካች እንዱተኩላቸው ጠይቀዋል። አመልካችም ነሃሴ 2 ቀን 2014 ዓ/ም በተፃፈ የመልስ መልስ ክርክራቸው የብሓራዊ የዲኝነት ሥልጣንን የሚመለከት እንጂ በፋደራል ፍርድ ቤቶች መካከል ስላለው ሥልጣን ባለመሆኑ ተጠሪ የጠቀሱት ሕግ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው መሆኑን ፤የአመልካች አድራሻ አዱስ አበባ ላሆን የቻለው በየአመቱ በሚታደስ ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ክርክሩን ሉቀይር አለመቻለን ፤ ድርጅቱ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ሆኖ የአንድ ሰው ኩባኒያ እንጅ የግል (ሶል ፔሮፔራይተር) አለመሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የግል ድርጅት ነው ቢባል እንኳን ድርጅቱ ፈርሶ የሂሳብ ማጣራት ሳይደረግ ለድርጅቱ የተከፈለውን ገንዘብ ባልና ሚስት ሉከፊፈለ የሚችለበት የሕግ አግባብ የለም በማለት የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናክር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ለሰበር ቅሬታው ምክንያት የሆነው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን የሰበር አቤቱታው ያስቀርባ ሲባል የተያዘውን ጭብጥ ለጉዲዩ አግባነት ካለው ሕግ አንፃር እንደሚከተለው ተመርምሯል።
የፍርድ ቤቶች ሥልጣን ከሶስት መሰረታዊ ጉዲዮች አንፃር የሚታይ መሆኑ ይታወቃል። ይኸውም ብሓራዊ የዲኝነት ስልጣን (judicial jurisdiction)፤ የስረ ነገር የዲኝነት ስልጣን (material jurisdiction) እና የግዛት ክልል ሥልጣን (local jurisdiction) ናቸው። የስረ ነገር እና የግዛት ክልል የዲኝነት ስልጣን የሚወሰነው በሀገራዊ (ብሓራዊ) ሕጎች (domestic or national laws) ሲሆን በዋናነት በስነ ስርዓት ሕጎች አልያም በመሰረታዊ ሕጎች (substantive laws) ተደንግጎ ይገኛል። ብሓራዊ የዲኝነት ስልጣን (judicial jurisdiction) የሥልጣን ምንጭ ዓለም ዓቀፍ የግለሰብ ሕግ (private International law) ፣ በሀገሮች መካከል በሚደረግ ሁለትዮሽ ወይንም ሶስትዮሽ ስምምነቶች ፤ ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነትን ያገኙ ሕጉች ወይንም ልማድች ላሆን ይችላል። በኢትዮጵያም ዓለም ዓቀፍ የግለሰብ ሕግ (private International law) የዲበሩ ልምድች እና ተቀባይነት ያላቸው መርሆዎች መሰረት ተደርጎ ለጉዲዮች እልባት ሲሰጥ ቆይቷል። ከእነዚህ የዲበሩ ልምድችና በዘርፈ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የአንድ ሀገር ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ ብሓራዊ የዲኝነት ሥልጣን አለው ወይስ የለውም ለማለት መሰረት ተደርጎ የሚወሰደው ከተከሳሽ ጋር ያለው ግንኙነት መለኪያ አንደ ሲሆን፤ ይኸውም ከተከሳሽ ሰው ወይንም (action impersonal) የሕግ ይሁን የተፈጥሮ ሰው ዘግነቱ ወይንም መደበኛ መኖሪያው ከፍርድ ቤቱ ጋር ያለው ቁርኝት፤ ለክሱ ምክንያት የሆነው ድርጊት (Act) ውል፤ ከውል ውጪ የተፈፀመበት ከሀገር ጋር ያለው ቁርኝት፤ ለክሱ ምክንያት የሆነው ንብረት (property) ተንቀሳቃሽ ይሁን የማይንቀሳቀስ የሚገኝበት አልያም የተከሳሽ ፈቃድ (consent) መኖር ወይንም አለመኖር መለኪያዎች ተደርጎ ይወሰዲለ። ከዚህ ባለፈም በጉዲዩ ላይ ያለው ብሓራዊ ጥቅምና ፕሉስ (National interest or public policy) መኖሩ ሲረጋገጥ ክሱ የቀረበበት ሀገር ብሓራዊ የዲኝነት ሥልጣን አለው ልባል ይችላል።
ከዚህ አንፃር ወደተያዘው ጉዲይ ስንመልስ የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ ዜግነታቸውም ሆነ መደበኛ ነዋሪነታቸው ፈረንሳይ ሀገር በሆኑት በግራ ቀኙ ጋብቻ ውስጥ በፈረንሳይ ሀገር የተፈሩ ኢትዮጵያዊያን ለሆኑ የንግድ ድርጅቶች በብድር ተሰጥቶ ብድሩን ለማስመለስ አመልካች በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ የብድሩ ገንዘቡ ለአመልካች እንዱከፈል ውሳኔ ተሰጥቶ፤ አመልካች የብድር ገንዘቡ እንዱመለስላቸው በፍርድ ባለመብት የሆኑበትን ፍርድ ለማስፈፀም የአፈፃፀም አቤቱታ የቀረበበት ገንዘብ የጋራ እንዱባልላቸው የጋብቻ ፍቺ ውጤትን የሚመለከት የባልና ሚስት ንብረት ክርክር መሆኑን ከመዝገቡ ለመረዲት ተችሎል። ከላይ በማብራሪያው ውስጥ እንደተመለከተው ለክሱ ምክንያት የሆነው ንብረት መገኛ መሆን ለብሓራዊ የዲኝነት ሥልጣን መኖር አንደ ምክንያት ሲሆን፤ የብድር ገንዘቡ ተመላሽ እንዱሆን ውሳኔ የተሰጠው ወይንም አመልካች በገንዘቡ ላይ መብት ያላቸው መሆኑ የተረጋገጠው በኢትዮጵያ ውስጥ ከመሆኑም ባሻገር አመልካች በፍርድ ያገኙት መብት እውን የሚሆነው የፍርድ አፈፃፀሙ የፍርድ ባለዔዲ የሆኑት ኢትዮጵያዊያን የንግድ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ባፈሩት ንብረቶች ላይ በመሆኑ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቾች ጉዲዩን የማየት ብሓራዊ የዲኝነት ሥልጣን አላቸው።
በፋደራል ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 ቁጥር 5(1) (በ) መሰረት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጠየቀውን ዲኝነት አይቶ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችለው የስረ - ነገር ስልጣን (material jurisdiction) ያለው በመሆኑ ውሳኔው ስህተት ነው ለማለት ስላልተቻለ ከዚህ አንፃር የቀረበው የሰበር ቅሬታ የሕግ ድጋፍ ያለው ሆኖ ስላተገኘ ተቀባይነት አላገኘም። አመልካች በፈረንሳይ እና በኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ መካከል የሕግ ግጭት ስላለ በተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ሕግ መዲኝት የለብኝም የሚል ክርክር በሥር ፍርድ ቤት ሳያነሱ በሰበር ደረጃ አዱስ ክርክር መቅረቡ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 329 ድንጋጌ መሰረት ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ሲጠቃለል የገንዘቡ አበዲሪ አመልካች ብቸኛ ባለድርሻ በመሆን ያቋቋሙት ድርጅት መሆኑን፤
አመልካችም ገንዘቡ በጋብቻ ውስጥ ያልተፈራ የግላቸው መሆኑን ወይንም ከፍቺ በኋላ የተፈራ ነው የሚል ክርክር ስላላቀረቡ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ገንዘብ የግራ ቀኙ የጋራ በመሆኑ እኩል ሉካፈለ ይገባል በማለት የስር ፍርድ ቤት የደረሰበት የፍሬ ነገር መደምደሚያን አይቶ የመቀየር ሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 ቁጥር 10(1) ለፋደራል ጠይቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የተሰጠ ሥልጣን ባለመሆኑና የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት ስላልተቻለ ቀጣዩ ተወስኗል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት በመዝገብ ህዲር 17 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ ፤ እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው የሰጠው ፍርድ ፤ ውሳኔ እና ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል ።
በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የግላቸውን ይቻለ።
ውሳኔው ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ/ም በችልት ተነቧል።
No topics extracted.