No summary available.
ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው በእውቀት በላይ ቀነአ ቂጣታ ብርሃኑ መንግሥቱ ማርታ ተካ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የዲኝነት ሥልጣን የሚመለከት ነዉ። ክርክሩ የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካቾች በተጠሪ ላይ የመሰረቱት ክስ በአዱስ አበባ ከተማ በቀድሞው ወረዲ 5 ቀበላ 6 በአሁኑ አዱስ ከተማ ወረዲ 08 በብልክ ቁጥር 4 በፒርሴል ቁጥር 34 በቤት ቁጥር 108 የሚታወቅ የድርጅት ቤት አመልካቾች አለን።ይህ ቤት ሴት አያታችን የቤቱ ባለቤት የነበሩት አቶ ማኮ ጮረና ሀምላ 12 ቀን 1944 ዓ.ም በአደረጉት ኑዛዜ መሰረት አስተላልፈዉልናል። ኑዛዜውም በቀድሞ የአዱስ አበባ 8ኛ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 486/45 በ21/12/1945 ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ ፀድቆ ተመዝግቧል።ይህን ቤት አያታችን አዋጅ ቁጥር 47/1967 እስከታወጀበት ጊዜ ድረስ ለ22 ዓመታት የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት በመሆን ከእጃቸው ሳይወጣ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል።አዋጅ ቁጥር 47/67 ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜም አያታችን ለክሱ መነሻ የሆነውን ቤት በመምረጣቸው ለዚሁ ቤታቸው የከተማ ልማት እና ቤት ሚኒስቴር በቁጥር 5/07886 መስከረም 11 ቀን 1974 ዓ.ም የከተማ ባለቤትነት ደብተር ሰቷቸዋል።አዋጅ ቁጥር 47/1967 በሥራ ላይ ከዋለበት ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2008 ዓ.ም ለ40 ዓመታት በቤት ቁጥር 108 ለመንግስት የቤት ግብር እና የአፈር ግብር ሲከፈልበት ቆይቷል።ከሴት አያታችን ሞት በኋላም ለአባታችን በውርስ ተላልፍለት እስከለተ ሞቱ ድረስ ሲያስተዲድረው ቆይቷል።አባታችን ከሞተ በኋላም አመልካቾች ወራሽነታችንን አረጋግጠን የአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ የይዞታ አስተዲደር የሽግግር ጊዜ መስተንግድ ማስተባበሪያ ፔሮጀክት በእነ ዮሀንስ ተስፊዬ (አራት ሰዎች) የሚል ተነፃፃሪ የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ሰጥቶናል።አባታችን ለክሱ መነሻ የሆነውን ቤት በመከፊፈል ለእነ ሀሚድ መሀመድ(6 ሰዎች) አከራይተው ሲጠቀሙበት ነበር።ይሁንና አዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር መንግስት ከሚያስተዲድራቸው ቤቶች ጋር በተያያዘ ያወጣውን መመሪያ ቁጥር 4/2004 ተከትል እነ ሀሚድ ከቀበላው መስተዲድር ጋር የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር ቤቱ የመንግስት ስለሆነ ኪራይ አንከፍልም ብለው አባታችንም በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቤት ኪራይ ከፍለው ቤቱን ለቀው ይውጡ የሚል ክስ አቅርበዉ ክሱ ውድቅ የተደረገበት ሲሆን ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ደግሞ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር እያንዲንዲቸው ተከራዮች ያለባቸውን ውዝፍ ቤት ኪራይ ከፍለው ቤቱንም ያስረክቡ ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።ተጠሪም ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 መሰረት መቃወሚያ አቅርቦ ለክሱ መነሻ የሆነው ቤት ቁጥር 108 የሚባል የለም ቤቱ በቤት ቁጥር 101 የሚታወቅ የመንግስት ቤት ነው በማለት ለአባታችን የተወሰነውን ውሳኔ አሽሯል።ይሁንና በግራ ቀናችን መካከል የፍትሐ ብሄር ሕግ ቁጥር 1206 ድንጋጌን መሰረት አድርጎ የቀረበ የመፊለም ክስ ስለላለ አሁን ያቀረብነው ክስ አዱስ ነው።ለክሱ መነሻ የሆነው ቤት ቁጥር 108 የአመልካቾች የግል ንብረት ሆኖ ሳለ ተጠሪ ይህንን ቤት ሳይወርስ ወይም በመንግስት በጀት ሳይሰራ መንግስታዊ ስልጣኑን በመጠቀም የፈጠራ መረጃ አደራጅቶ ቤቱ የመንግስት ነው በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም፤ ቤቱ የአመልካቾች የግል ሀብት ተብል ተጠሪ ለክሱ ምክንያት የሆነው ቤት ቁጥር 108 ተከራዮችን በማስወጣት እንዱያስረክበን ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን በማስቀደም ባቀረበዉ መልስ አመልካቾች ከዚህ በፉት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ አቅርበው ይህ ቤት የአመልካቾች እንዲልሆነ እና ካርታውንም ያገኙት የቤት ቁጥር 101/2 የተባለውን የመንግስት ቤት ወደ ግል ቤትነት ቀይረው መሆኑ ተረጋግጦ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የመንግስት ነው በሚል ውሳኔ ተሰጥቶ ይህም ውሳኔ እስከ ፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ ፀንቷል።አመልካቾች በድጋሚ ድጋሚ ዲኝነት አቅርበው ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደረገባቸው ሲሆን በድጋሚ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አላግባብ ካርታችን መክኗል በሚል ክስ መስርተው ውድቅ ተደርጎባቸዋል።ስለሆነም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5 እና 244(2/ለ) መሰረት ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ ክሱ ዉድቅ ላሆን ይገባል።በአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዲ 08 የቤት ቁጥሩ 101/2 የሆነው ቤት ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 64/2011 እና በመመሪያ ቁጥር 5/2011 ዓ.ም የሚያስተዲድረው የመንግስት ቤት ነው። የከተማ አስተዲደሩ ከሚያስተዲድረው ቤት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮችን በተመለከተ በቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 41(1/ረ) እና በፋደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5(1/ደ) መሰረት ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን የለዉም በማለት ተቃዉሟል።እንዱሁም ላልች መከራከሪያዎችንም በማቅረብ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም በመ/ ላይ በቀን 04/05/2015 ዓ/ም በሰጠዉ ብይን ክስ የቀረበዉ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይዞ እያስተዲደረ ባለው ቤት ላይ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5(1/ደ) ስር በተደነገገዉ መሰረት ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች ነዉ በማለት የክሱን መዝገብ በመዝጋት አመልካቾች ሥልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት ክሳቸዉን ማቅረብ ይችላለ ሲል ወስኗል። አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ተጠሪን ሳያስቀርብ ይግባኙን ሰርዞባቸዋል።
አመልካቾች መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም አቤቱታቸውን ያቀረቡት ከላይ በተጠቀሰው መንገድ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል በማለት ሲሆን የአቤቱታቸውም አጭር ይዘት፡-የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በያዘው ቤት ባለቤትነትን የመፊለም ክስ እንዱሁም በቤቱ ባለቤትነት ላይ ክርክር እስከቀረበበት ድረስ የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን የለውም ሲል የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።በዚህ መሰረት የፈደራል ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን የማየት የሥረ ነገር ስልጣን እያላቸው ሥልጣኑ የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ናቸው በማለት የስር ፍርድ ቤቶች ሥልጣን የለንም በማለት የሰጡት ብይን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ተሽሮ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፍሬ ነገሩ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩ ሉመለስለት ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታዉን መርምሮ አመልካቾች በተጠሪ ላይ የመሰረቱት ክስ የቤት ባለቤትነት መብት መፊለምን የሚመለከት ሆኖ እያለ የስር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የመዲኘት ስልጣን የለኝም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎ መወሰኑ እና ይህንን ውሳኔ በመቃወም ያቀረቡትን ይግባኝ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሰረዙ አግባብ መሆን አለመሆኑን በሰ/መ/ ከተሰጠው የሕግ ትርጉም እና በፋደራል ፍ/ቤች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 5(1/ደ) አኳያ እንዱመረመር ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ አዝዟል።
ተጠሪ ሐምል 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበዉ መልስ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5(1/ደ) ስር ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን ለአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ስልተሰጠ ይህ አዋጅ ከጸና በኋላ በተጠቀሰዉ የሰበር መዝገብ ላይ የተሰጠዉ የሕግ ትርጉም ተፈጻሚነት አይኖረዉም።ስለሆነም በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል። አመልካቾችም የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ተከራክረዋል።
ከላይ አጠር ባለ መልኩ የተገለጸዉ የግራ ቀኙን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠ ዉሳኔ ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈጸም አለመፈጸሙን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነዉም በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ላይ በዋናነት የፋዳራል ፍርድ ቤቶች የዲኝነት ሥልጣን በጠቅላላዉ የተደነገገ ሲሆን በአንቀጽ 5(1/ደ) ስር ደግሞ ለአዱስ አበባ እና ድሬዲዋ ከተሞች ፍርድ ቤቶች በቻርተር አዋጆቻቸዉ የተሰጣቸዉ የዲኝነት ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ የከተሞቹ አስተዲደሮች ከሚያስተዲድሩት ቤት ጋር በተያያዘ በሚነሳ የይዞታ ወይም የባለቤትነት ወይም ላላ ማንኛዉም ክርክር የመዲኘት ሥልጣን የከተሞቹ አስተዲደሮች ፍርድ ቤቶች እንደሆነ ተደንግጓል።
ይህም በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ላይ በልዩ ሁኔታ ስለአዱስ አበባ እና ድሬዲዋ ከተሞች ፍርድ ቤቶች የሥረ ነገር ዲኝነት ሥልጣን መደንገጉን የሚያሳይ ነዉ።በዚህ መልኩ የተደነገገዉ አስቀድሞ በተሻሻለዉ የአዱስ አበባ ከተማ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1/ረ) እና በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33(1/ረ) ስር እንደ ቅደም ተከተላቸዉ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ከሚያስተዲድራቸዉ የመንግሥት ቤቶች እና የድሬዲዋ ከተማ አስተዲደር የሚያስተዲድራቸዉ ሆኖ ለንግድ፣ለመኖሪያ ወይም ለላላ አገልግልት በመስጠት ላይ ካለ የመንግሥት ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዲዮችን(ክሶችን) የመዲኘት ሥልጣን የከተሞቹ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ነዉ በሚል ደንግገዋል።በእነዚህ አዋጆች የተደነገገዉን ግልጽ በሚያደርግ አኳኋን ከቤቶቹ ጋር በተያያዘ የሚነሳ የይዞታ እና የባለቤትነት መብቶች የመፊለም ክሶች (The petitory action and the possessory action) ወይም ላላ ማንኛዉም ክርክር በሚል ሰፊ ባለ አኳኋን መደንገጉን የሚያሳይ ነዉ።
እንዱሁም የአዋጁን አንቀጽ 5(1/ደ)ን ከአዋጁ አንቀጽ 5(1/ሰ) እና በአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1/ረ) እና በአዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33(1/ረ) ስር ከተደነገገዉ ጋር አገናዝበን የተመለከትን እንደሆነ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ዲኝነት ሥልጣን የሚሆነዉ የአዱስ አበባ እና የድሬዲዋ ከተሞች አስተዲደሮች የሚያስተዲድሯቸዉንና ለንግድ፣ለመኖሪያ ወይም ለላላ አገልግልት በመስጠት ላይ ካለ የመንግሥት ቤቶች ዉጭ በሆኑት የፋዳራል መንግሥቱን ንብረቶች በተመለከተ የሚነሱ ጉዲዮች ማለትም ከፋዳራል ሦስቱም የመንግሥት አካላት እና ከፋዳራል የልማት ድርጅቶች ንብረቶች ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ማናቸዉም ክሶች በተመለከተ እንደሆነ ነዉ።ከዚህ ጋር በተያያዘም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በቀን 28/09/2016ዓ/ም(ያልታተመ) አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
በልላ በኩል የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1/ረ) ስር የተደነገገዉን በሰ/መ/ (ቅጽ 5) ላይ በሰጠዉ ዉሳኔ በመተርጎም የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በሚያስተዲድራቸዉ ቤቶች ላይ ባለቤትነት በማፊለም የሚቀርብ ክስ ለመዲኘት ሥልጣን የላቸዉም የሚል አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።ይህ የሕግ ትርጉም የተሰጠዉ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ከመጽናቱ በፉት መሆኑ ግልጽ ነዉ።ሆኖም ከላይ እንደተገለጸዉ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 ከጸናበት ከጥር 13 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 5(1/ደ) ስር በተደነገገዉ መሰረት የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በሚያስተዲድራቸዉ ቤቶች ላይ የባለቤትነት መብት በማፊለም የሚቀርብ ክስ የመዲኘት ሥልጣን የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች በመሆኑ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ከጸናበት ቀን ጀምሮ በሰ/መ/ ላይ የተሰጠዉ የሕግ ትርጉም ተፈጻሚነቱ ቀሪ ሆኗል።
በተያዘዉ ጉዲይ አመልካቾች ክስ የመሰረቱት በክሱ ላይ የተጠቀሰዉ ቤት የሥራና ቤት ሚኒስቴር ለአያታቸዉ (ለአዉራሻቸዉ) የፈቀደላቸዉ እና በስማቸዉ የተመዘገበ በኋላም በዉርስ ወደአባታቸዉ ተላልፍ ሲተዲደር የቆየዉን ተጠሪ ከሕግ አግባብ ዉጭ በመያዝ እያስተዲደር እንደሚገኝ በመግለጽ መብት ሳይኖረዉ ይዞ እያከራየ ያለዉ ተጠሪ ተከራዮችን አስለቅቆ እንዱያስረክባቸዉ ዲኝነት በመጠየቅ ያቀረቡት ክስ ነዉ።ይህም ክሱ የከተማ አስተዲደሩ እያስተዲደረ የሚገኘዉን ቤት ባለቤትነት መብት በመፊለም እንደቀረበ የሚያሳይ ነዉ። በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5(1/ደ) መሰረት ክሱን ተቀብል የመዲኘት ሥልጣን ያላቸዉ የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ናቸዉ።ስለሆነም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠሪን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በመቀበል ጉዲዩን የመዲኘት ሥልጣን የለኝም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔም ሆነ ይህንን ዉሳኔ በመቃወም አመልካቾች ያቀረቡትን ይግባኝ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረዝ የሰጠዉ ብይን በሕግ የተደነገገዉን የዲኝነት ሥልጣን ክፍፍል መሰረት ያደረገ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችልት ደረጃ ሉታረም የሚችል ስህተት የተፈጸመበት ባለመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 04/05/2015 ዓ/ም የሰጠዉ ብይን እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ በቀን 16/06/2015ዓ/ም የሰጠዉ ብይን በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አንቀጽ 9/1 መሰረት ጸንተዋል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በሚያስተዲድራቸዉ ቤቶች ላይ የባለቤትነት መብት በማፊለም የሚቀርብ ክስ የመዲኘት ሥልጣን የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ነዉ።
ግራ ቀኝ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዱችለ ተወስኗል።
ት እ ዛ ዝ
የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ።
ዉሳኔዉ በቀን 11/11/2016 ዓ/ም ተነበበ።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.