የፍርድ ቤት ብሓራዊ የመዲኘት ሥልጣን ከሀገሮች ለዓላዊነት፣ የሚሰጠው ፍርድ በላልች ሀገሮች ዔውቅና ሉሰጠውና ሉፈጸም የሚችል መሆን አለመሆኑ እና ከተከሳሽ መብት ጋር የተያያዘ መሰረቱ ዓለም አቀፍ ሕግና የታወቁ የሕግ መርሆዎች ሆኖ የአንድ ሀገር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመመልከት ከተከሳሹ ወይም የክርክሩ ምክንያት የሆነው ተግባር ከተፈጸመበት ወይም አከራካሪ የሆነው ንብረት ከሚገኝበት ቦታ ጋር በቂ የሆነ ግንኙነት ያለው ሆኖ ሲገኝ ወይም ተከሳሽ የሆነው ወገን በሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች ለመዲኘት ያለው ፈቃድ ላይ መሰረት በማድረግ የሚወሰን ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 25
No summary available.
ቀን፡- ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡-
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከሥር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት ተከሳሾችና የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅራቢዎች ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ። ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በአዱስ አበባ ከተማ ንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዲ 09 የቤት ቁጥር 202 የሆነ ቤት አመልካቾች እንዱያስረክቡ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካቾች ለክሱ መልስ ካቀረቡ በኋላ በዚህ ችልት ደረጃ አከራካሪ ሆኖ የቀረበው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርበዋል። የክሱ ይዘትም የአመልካቾች ወላጆች የጋራ ንብረት በሆነው በኤርትራ ሀገር አሰብ ከተማ የሚገኘው የቤት ቁጥሩ ሲ/385 እና ተጠሪ ክስ ያቀረበቡት ቤት ጋር መስከረም 02 ቀን 1991 ዓ/ም የቤት ልውውጥ ውል የተደረገ በመሆኑ ውለ እንዱፈርስ እንዱወሰን፣ ኤርትራ አሰብ ከተማ የሚገኘውን ቤት ተጠሪ እንዱያስረክቡ እና ተጠሪ ክስ ያቀረቡበትን ቤት ከተረከብን በኋላ ለዔድሳት ያወጣነውን ብር 50,000.00 ተጠሪ እንዱተኩልን እንዱወሰንልን የሚል ነው። ተጠሪ ለቀረበው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ባቀረቡት መልስ ኤርትራ ሀገር የሚገኝ ቤት በዚህ ሀገር ፍርድ ቤት ላታይ አይችልም የሚለና ላልች ክርክሮችን አቅርበዋል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾች ባቀረቡት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላይ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን በመመርመር ክሱ በኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገ ውል ይፍረስልኝ የሚል ነው።
የውለ መሰረት ኤርትራ አገር የሚገኝ ቤትን የሚመለከት ሲሆን ተጠሪም ኤርትራዊ እንደመሆናቸው ጉዲዩ የግለሰብ ዓለምአቀፍ ሕግ ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ ፍርድ ቤት ሉመለከተው ይችላል። ነገር ግን የውለ መነሻ የሆነው ቤት ኤርትራ አገር የሚገኝ በመሆኑ ክሱ ላቀርብ የሚገባው ንብረቱ ባለበት አገር ላሆን ይገባል። በልላ በኩል አመልካቾች ክሱ በቀረበበት ጉዲይ መብትና ጥቅም ያላቸው መሆኑን አራጋግጠው ክሱን አላቀረቡም። እንዱሁም የውል ይፍረስልኝ ክሱ በ10 ዓመት ጊዜ ስላልቀረበ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ወስኗል። አመልካቾች ይግባኙን ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱ ግራቀኙን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 25 መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት ክርክር የሚቀርበው ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ሥልጣን የለኝም ማለቱ ተገቢ ነው።
ነገር ግን ጉዲዩን ለመመልከት ሥልጣን የለኝም ካለ በኋላ አመልካቾች መብትና ጥቅም የላቸውም፤ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ማለቱ ተገቢ ባለመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ውሳኔው አሻሽል ወስኗል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ክስ ያቀረብነው አዱስ አበባ የተደረገ ውል እንዱፈርስ ነው፣ ውለ ሲፈርስ ወደነበርንበት ስለምንመለስ በውለ የተገኘው አዱስ አበባ የሚገኘውን ቤት ልናስረክብና አሰብ ከተማ የሚገኘው ቤት ተጠሪ ሉያስረክቡን እንጂ በቀጥታ አሰብ ከተማ ያለው ቤት ላይ ክስ አላቀረብንም። ውል ይፍረስልኝ ክስ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 24 መሰረት የሚታይ ነው። የግለሰብ ዓለምቀአፍ ሕግን የሚመለከት አይደለም፤ ይመለከታል ቢባል እንኳን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመመልከት ሥልጣን አለው የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ ኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገው የቤት ልውውጥ ውል እንዱፈርስ የቀረበው ክስ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለመመልከት ሥልጣን የለኝም ማለቱ ሕጋዊነቱን ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርቡ አዟል። ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ለክሱ መሰረት ያረጉት ውል ሰበር ችልት በመዝብ ውሳኔ የሰጠበት ነው። የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን ያለው መሆኑን ተቀብል መብትና ጥቅም ያላቸው መሆን አለመሆኑን እና የይርጋ ክርክሩን መርምሮ ውሳኔ ሰጥቶበታል። በሀሰት የተዘጋጀ ውል ነው። ክሱ ላይ መብትና ጥቅም የላቸውም፤ የሰበር አቤቱታው ተቀባይነት የለውም ተብል ውደቅ ላደረግ ይገባል ብለዋል። አመልካቾች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም አመልካቾች ያቀረቡት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስን የሥር ፍርድ ቤቶች የመመልከት ሥልጣን የለንም በማለት መወሰናቸው ሕጋዊ መሆን አለመሆኑን?
በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካቾች በተጠሪ ላይ ያቀረቡት ተከሳሽነት ከሳሽነት ክስ የአመልካቾች ወላጆች የጋራ ንብረት በሆነው በኤርትራ ሀገር አሰብ ከተማ የሚገኘው የቤት ቁጥሩ ሲ/385 እና ተጠሪ ክስ ያቀረበቡት ቤት ጋር መስከረም 02 ቀን 1991 ዓ/ም የቤት ልውውጥ ውል የተደረገ በመሆኑ ውለ እንዱፈርስ እንዱወሰን፣ ኤርትራ አሰብ ከተማ የሚገኘውን ቤት ተጠሪ እንዱያስረክቡ እና ተጠሪ ክስ ያቀረቡበትን ቤት ከተረከብን በኋላ ለዔድሳት ያወጣነውን ብር 50,000.00 ተጠሪ እንዱተኩልን እንዱወሰንልን የሚል ነው። አሁን አከራካሪ ሆነው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ክሱን የማየት ብሓራዊ የዲኝነት ሥልጣን አለው ወይስ የለውም የሚለውን የሚመለከት ነው።
ክርክሩን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፉነት ሲሆን በዚህ ሂደት ከሚመረምራቸው ጉዲዮች መካከል ጉዲዩ ላይ ለመወሰን ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑ ዋነኛው ነው። የፍርድ ቤት ሥልጣን ብሓራዊ የመዲኘት ሥልጣን (judicial jurisdiction)፣ የሥረ-ነገር ሥልጣን እና የግዛት ሥልጣን በሚል የተከፊፈለ ነው። ብሓራዊ የመዲኘት ሥልጣን ከሀገሮች ለዓላዊነት፣ የሚሰጠው ፍርድ በላልች ሀገሮች ዔውቅና ሉሰጠውና ሉፈጸም የሚችል መሆን አለመሆኑ እና ከተከሳሽ መብት ጋር የተያያዘ መሰረቱ ዓለምአቀፍ ሕግና የታወቁ የሕግ መርሆዎች ሆኖ የአንድ ሀገር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለመመልከት ከተከሳሹ ወይም የክርክሩ ምክንያት የሆነው ተግባር ከተፈጸመበት ወይም አከራካሪ የሆነው ንብረት ከሚገኝበት ቦታ ጋር በቂ የሆነ ግንኙነት ያለው ሆኖ ሲገኝ ወይም ተከሳሽ የሆነው ወገን በሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች ለመዲኘት ያለው ፈቃድ ላይ መሰረት በማድረግ የሚወሰን ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካቾች ኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገ ውል እንዱፈርስ ዲኝነት መጠየቃቸው የክርክሩ ምክንያት የሆነው ተግባር ከተፈጸመበት ቦታ ጋር በቂ ግንኙነት መኖሩን ስለሚያሳይ ኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን ያገኛለ። አመልካቾች ውል ይፍረስ የሚል ዲኝነት ያቀረቡ በመሆኑ ኤርትራ አሰብ ከተማ የሚገኘው ቤት ላይ በቀጥታ የመፊለም ክስ እንዲቀረበቡት ሉቆጠር የሚገባው አይደለም። ነገር ግን ውለ ከፈረሰ ወደነበሩበት መመለስ ስለሚኖራባቸው በተከራካሪዎች መካከል የሚመላለሱት ንብረት ውስጥ አንደኛው በአዱስ አበባ ከተማ የሚገኘውን ቤት በመሆኑ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን ለማየት ተጨማሪ ሕጋዊ ምክንያት ያገኛለ። ተጠሪ በዜግነት ኤርትራዊ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን በሥር ፍርድ ቤት የብሓራዊ ዲኝነት ሥልጣን የለውም በማለት የተቃወሙ ስለመሆኑ ከውሳኔው ይዘት የተረዲን ሲሆን በዚህ ችልት ደረጃ ፍርድ ቤት ሥልጣን ያለው መሆኑን ተረድቶ በላልች መቃወሚያዎች ተመስርቶ ነው ክሱን ውደቅ ያደረገው በማለት በክሱ ሥረ-ነገር ላይ ክርክር ማቅረባቸው በፍርድ ቤቱ ለመዲኘት ፈቃድ እንደሰጡ ሉወሰድ ይችላል። ስለሆነም በአመልካቾች የቀረበው ክስ ክሱ ከቀረበበት ሀገር ጋር በቂ ግንኙነት ያለው በመሆኑ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን ለማየት የብሓራዊ ዲኝነት ሥልጣን አላቸው ብለናል። የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደን ዲኝነት ነጥል በማየት ኤርትራ ሀገር በሚገኝ ቤት ላይ ለቀረበ ዲኝነት ሥልጣን የለኝም ማለቱ ዋናው የክሱ መሰረት በኢትዮጵያ የተደረገ ውል ይፍረስልኝ መሆኑን ያላገናዘበ እና ተገቢነት የላለው ነው። ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱም ኤርትራ ሀገር የሚገኘው ቤት ላይ የመፊለም ክስ እንደቀረበበት አድርጎ በመውሰድ ለግዛት ክልል ተፈጻሚነት ያለውን የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 25 ድንጋጌ መሰረት ፍርድ ቤቱ ሥልጣን የለውም ማለቱ ሕጋዊነት የለውም ብለናል፤ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሐምል 20 ቀን 2012 ዓ/ም፤ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ/ም አመልካቾች ያቀረቡትን የተከሳሽነት ከሳሽነት ክስ አስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለውም በማለት የሰጠው ውሳኔ ክፍል ተሽሯል። ቀሪው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ ፀንቷል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ መመልከቱን በመቀጠል ተጠሪ ያቀረቧቸውን ላልች መቃወሚያዎች በመመርመርና ክሱ በመቃወሚያው መሰረት ውድቅ የማይደረግ ከሆነ በሥረ-ነገሩ ተመልክቶ እንዱወሰን ጉዲዩን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341(1) መሰረት መልሰናል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔው መሰረት እንዱፈጽም አዘናል። ይጻፍ ክርክሩ እንዱታገድ የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ሄ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.