በህግ ጥበቃ በሚደረግለት ግኑኝነት ውስጥ ያልተወለደ ልጅ አባት ነው የተባለ ግለሰብ የአባትነት ጉዲይ በህግ ግምት የሚወሰድበት ባለመሆኑ የልጁን መወለድ ለመቃወም የሚቀርብ ክስ አባትነትን ስለመካድ በሚቀርበው አኳኋን ላሆን ይገባል የሚባልበት የህግ መሰረት የላለ ስለመሆኑ አባትነትን ፈቅድ የተቀበለ እና በፍርድ ቤት ውሳኔ “አባት ነህ” የተባለው ሰው ወይም ከዚሁ ሰው መብቱ የተላለፈለት ሰው የመካድ ወ/ሪት አብነት ሐብታሙ ካሴ እና ህፃን ናፍቆት ሐብታሙ ካሴ 219 ለማቅረብ ህግ የማይፈቅድለት ስለመሆኑ የተሻሻለዉ የፋዳራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ /92 አንቀፅ 168፣ 170 እና 174 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ
No summary available.
የመ.ቁ.238021 ሐምል 25/2015 ዓ.ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) እንዲሻው አዲነ ተሾመ ሽፈራው መላኩ ካሳዬ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ወ/ሪት አብነት ሐብታሙ ካሴ - ጠ አቶ ውቤ አለነ - ቀረቡ ተጠሪ፡
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ልጅን ለመካድ በሚል የቀረበ ክስን መነሻ አድርጎ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ነው። ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልቱ የቀረበውም የአሁን ተጠሪ በህግ እውቅና ከሚሰጠው ግኑኝነት ውጭ የተወለደች ስለመሆኑ ተመልክቶ እያለ አመልካች ያቀረቡት ክስ እንደመካድ ክስ ተቆጥሮ ክሱን ለማቅረብ የፍርድ ቤት ፈቃድ ያስፈልጋል በሚል ውድቅ የተደረገበትን አግባብ መርምሮ ለመወሰን ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች ጥር 30/2014 ዓ.ም ፅፈው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአሁን ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። የክሱም ጭብጥ የአሁን ተጠሪ ሞግዚትና አሳዲጊ(እናት) የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት ጣሰው ከአመልካች ወላጅ አባታቸው አቶ ሀብታሙ ካሴ ጋር በጋብቻም ሆነ ከጋብቻ ውጭ እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግኑኝነት ሳይኖራቸው ሟች አባታቸው ከሞቱ 6 ውር በኋላ የተወለደትን የአሁን ተጠሪን ከሟቹ የወለደ መሆኑን ጠቅሰው ከፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የወራሽነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ወስደው የሟች ውርስ እንዱጣራላችው ለፍርድ ቤት አቤቱታ በማቅረባቸው ስለጉዲዩ ያወቁ መሆኑን፤ ይህንኑ ተከትል የወራሽነት ማስረጃውን ለሰጠው ፍርድ ቤት የመቃወም አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ተገቢ የመካድ ክስ ቀርቦ ተጠሪ የሟቹ ልጅ አለመሆናቸው ባልተወሰነበት የመቃወም አቤቱታው ላቀርብ እንደማይችል በመጥቀስ ይኸው እስኪረጋገጥ ድረስ በሚል መዝገቡ የተዘጋ መሆኑን፤ የተጠሪ ሞግዚትና አሳዲጊ(እናት) ከሟች ጋር በህግ የታወቀ ግኑኝነት ሳይኖራቸው እንዱሁም ሟች የአሁን ተጠሪ ልጄ ናቸው በሚል አባትነታቸውን አምነው ባልተቀበለበት ተወልጃለሁ መባለ አግባብ አለመሆኑን እና አመልካችም የሚክደት መሆኑን በመጥቀስ የDNA ምርመራ ተደርጎ ተጠሪ የሟች ልጅ አይደለችም ተብል እንዱወሰን ዲኝነት የሚጠይቅ ነው።
በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥ በታዘዘው መሰረት የአሁን ተጠሪ ሞግዚትና አሳዲጊ(እናት) በሰጡት መልስ ከሟች አቶ ሀብታሙ ካሴ ጋር በጋብቻ አልያም ከጋብቻ ውጭ እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግኑኝነት ያልነበራቸው ቢሆንም ከ3 ዓመት በላይ የቆየ የፍርቅ ግኑኝነት የነበራቸው እና ተጠሪም በዚሁ ግኑኝነት ውስጥ የተወለደች መሆኑን፤ ይኸው ለመሆኑም የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርበው በማረጋገጥ የወራሽነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቱ የተሰጣቸው መሆኑን፤
የቀረበው ማስረጃ በቂ አይደለም የሚባል ከሆነ ከሟቹ አስከሬን ላይ ናሙና ተወስድ የተጠየቀው ምርመራ ቢከናወን የማይቃወሙ መሆኑን በመግለፅ ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር ከመረመረ በኋላ በሰጠው ውሳኔ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ የመካድ ክስ ማቅረብ የሚችለው በህግ ግምት “አባት ነህ” የተባለው ሰው ብቻ መሆኑን፤ የአሁን ተጠሪ ከጋብቻ እና ጋብቻ ሳይኖር እንደ ባልና ሚስት አብሮ ከመኖር ግኑኝነት ውጭ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የተወለደች ስለመሆኑ ክርክሩ የሚያሳይ በመሆኑ የአመልካች አባት(ሟች) በህግ ግምት የተጠሪ አባት ነው የሚባል ሰው ባለመሆኑ የመካድ ክስ ለማቅረብ የሚቻልበት የህግ መሰረት የላለ መሆኑን፤ የመካድ ክሱ ላቀርብ ይችላል የሚባል ቢሆን እንኳን ክሱን ለማቅረብ የፍርድ ቤት ፈቃድ የሚያስፈልግ በመሆኑ አመልካች ፈቃድ ሳያገኙ የመካድ ክስ ማቅረባቸው ከህግ አግባብ ውጭ ነው በማለት ክሱ ውድቅ አድርጓል። አመልካች ይህንኑ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት ይግባኙን ዘግቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው። አመልካች ህዲር 29/2015 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እና ትዕዛዝ ላይ ተፈፅሟል ያለትን መሰረታዊ የህግ ስሀተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ከላይ በዚህ ፍርድ መግቢያ ላይ የተመለከለተውን ነጥብ ተጠሪ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል ተብል ግራ ቀኙ በጽሁፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና መሰረታዊ የክርክሩ ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በመሰረቱ አባትነትን ከማረጋገጥ ጋር በተያያዘ “የአንድ ህፃን አባት ማነው?” ለሚለው ጥያቄ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ሶሰት አበይት ማረጋገጫ መንገድችን ዘርግቷል። እነዚህም አንደኛው “የልጁ አባት እገላ ነው” በሚል ህጉ በራሱ የሚወስደው ግምት ነው። ሁለተኛው “የልጁ አባት እኔ ነኝ” በሚል በገዛ ፈቃድ ልጅነትን በመቀበል በሚደረግ መተማማኛ ሲሆን ሶስተኛ እና የመጨረሻው ደግሞ “የልጁ አባት እገላ ነው” በሚል ፍርድ ቤት በሚሰጠው ውሳኔ ስለመሆኑ ከአንቀፅ 126 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
የቤተሰብ ህጉ አባትነትን አስምልክቶ የዚህ ዓይነት የህግ ግምት የሚወስደው ልጁ በሚፀነስበት ወይም በሚወለድበት ጊዜ በልጁ እናት እና በአንድ ወንድ መካከል በህግ የታወቀ ግኑኝነት መኖሩ ሲረጋገጥ እንደሆነ፤ በዚህ መልኩ በህግ እውቅና የተሰጠው ግኑኝነትም ጋብቻ እና ጋብቻ ሳይኖር እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግኑኝነት ብቻ ስለመሆኑ የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 126 እና 130 ድንጋጌዎች ይዘት ያስገነዝባለ። ከእነዚህ ሁለቱ ግኑኝነቶች ውጭ በሆነ ሁኔታ በእናቲቱ እና በአንድ ወንድ መካከል በተደረገ የግብረ ስጋ ግኑኝነት የተወለደ ልጅን ጉዲይ አስመልክቶ አባትነቱ ሉረጋገጥ የሚችለው በተቀሩት ሁለቱ ማረጋገጫ መንገድች ይሆናል ማለት ነው።
በእርግጥ በአባት በኩል ያለውን መወለድ ለማረጋገጥ የቤተሰብ ህጉ እነዚህን ሶስት አማራጭ መንገድችን ያስቀመጠ ቢሆንም በቀጥታም ሆነ በፍርድ ቤት ፈቃድ የመካድ ክስ ለማቅረብ የተፈቀደው በህግ ግምት “አባት ነህ” ለተባለው ሰው ብቻ ስለመሆኑ ከቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 168፣ 170 እና 174 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል። በልላ አነጋገር አባትነትን ፈቅድ የተቀበለ እና በፍርድ ቤት ውሳኔ “አባት ነህ” የተባለው ሰው ወይም ከዚሁ ሰው መብቱ የተላለፈለት ሰው የመካድ ክስ ለማቅረብ ህግ አይፈቅድለትም ማለት ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ አመልካች ለአሁኑ ክርክር ምክንያት የሆነውን ክስ ያቀረቡት የተጠሪን የወራሽነት ማስረጃ በመቃወም ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ የመካድ ክስ እንዱቀርብ ማስረጃውን በሰጠው ፍርድ ቤት በመታዘዙ ምክንያት መሆኑን በክሰ አቤቱታቸው ገልፀዋል። ክሱ ልጅን ለመካድ እንደቀረበ የተመለከተ ቢሆንም ዝርዝር ይዘቱ የአሁን ተጠሪ በህግ በታወቀ ግኑኝነት ውስጥ ያልተወለደች እንዱሁም ሟች ልጅነትዋን አምኖ ያልተቀበለ በመሆኑ የሟቹ ልጅ ናት ልትባል አይገባም የሚል መሆኑን ያስገነዝባል። ተጠሪ በህግ ጥበቃ በሚደረግለት ግኑኝነት ውስጥ ያልተወለደች ስለመሆኑ የተጠሪ ሞግዚትና አሳዲጊ(እናት) በራሳቸው የተቀበለት ጉዲይ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ የተጠሪ አባት ናቸው የተባለት ግለሰብ የአባትነት ጉዲይ በህግ ግምት የሚወሰድበት ባለመሆኑ የተጠሪን መወለድ ለመቃወም የሚቀርብ ክስ አባትነትን ስለመካድ በሚቀርበው አኳኋን ላሆን ይገባል የሚባልበት የህግ መሰረት የለም።
የተጠሪን ተወላጅነት ለመቃወም የመካድ ክስ ማቅረብ የማያስፈልግ ከሆነ ደግሞ የፍርድ ቤት ፈቃድ የሚጠየቅበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም። ከላይ እንደተመለከተው አመልካች ያቀረቡት ክስ አርእስቱ ልጅን ከመካድ ክስ ጋር የተያያዘ መሆኑን የሚጠቁም ቢሆንም ዝርዝር ይዘቱ በመካደ ክስ የማይስተናገድ መሆኑን ያረጋግጣል። በፍትሓ ብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉም ቢሆን ከባለጉዲዮች የሚጠበቀው ለዲኝነት ጥያቄያቸው መሰረት የሆነው ፍሬ ነገር በግልፅ መጥቀስ ብቻ ሲሆን ከተጠቀሰው ፍሬ ነገር አኳያ ዲኝነቱ በየትኛው የህግ ማዕቀፍ እንደሚዲኝ የመለየት እና የቀረበውን ክርክር ከዚሁ አኳያ አቃንቶ ሙግቱን የመምራት ኃላፉነቱ የፍርድ ቤቱ ይሆናል።
ከዚህ አኳያ የአሁን ተጠሪ የተወለደችው አባትነት በህግ ግምት ከሚረጋገጥበት እና በህግም እውቅና ከሚሰጠው ግኑኝነት ውጭ በመሆኑ የተነሳ አመልካች ያቀረቡት ክሰ በመካድ ክስ የሚስተናገድ እንዲልሆነ ክሱ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በራሱ የተቀበለው ስለመሆኑ በውሳኔው ገልጿል። ፍርድ ቤቱ ይህንን ከተቀበለ ከቀረበው ክርክር አኳያ ዲኝነቱን በማቃናት፤
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ክሱ ተሻሽል እንዱቀርብ በማድረግ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን መርምሮ መወሰን ሲገባው ክሱን ለማቅረብ በህግ ያልተመለከተን ቅድመ ሁኔታ ጠቅሶ ውድቅ ማድረጉ፤ እንዱሁም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ከዚሁ አኳያ ማረም ሲገባው በትዕዛዝ ማፅናቱ የክርክሩን ይዘት እና ከዚሁ በተጓዲኝ ያለውን የህግ ማዕቀፍ መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/138158 ላይ ግንቦት 05/2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና ይህንኑ በማፅናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/294567 ላይ ጥቅምት 21/2015 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
የአሁን ተጠሪ ከሟች አቶ ሐብታሙ ካሴ ተወልዲለች የተባለው በቤተሰብ ህጉ አባትነትን በህግ ግምት ለማረጋገጥ እውቅና ከተሰጠው የወንድ እና ሴት ግኑኝነት ውጭ በሆነ ፆታዊ ግኑኝነት ውስጥ ስለመሆኑ የተገለፀ በመሆኑ ጉዲዩ ልጅን በመካድ ክስ የሚስተናገድ አይደለም፤ ተወላጅነቷንም ለመቃወም የፍርድ ቤት ፈቃድ አያስፈልገውም።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በውሳኔ የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ ከሟች አቶ ሐብታሙ ካሴ አስከሬን ላይ ናሙና ተወስድ ከተጠሪ ደም ጋር በማመሳከር የዘር ባህሪ ወሳኝ ቅንጣት (DNA) ምርመራ እንዱደረግ በማዘዝ የሚገኘውን ውጤት በግራ ቀኙ ከቀረቡት ማስረጃዎች ጋር አገናዝቦ በመመርመር ሟች አቶ ሐብታሙ ካሴ የተጠሪ አባት ነው? ወይስ አይደለም? በሚለው ነጥብ ላይ እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 341(1) መሰረት ጉዲዩ ይመለስለት።
የዚህን ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
በዚህ መዝገብ ላይ የተሰጠ የእግድ ትዕዛዝ ካለ ተነስቷል። ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.