No summary available.
ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) እንዲሻዉ አዲነ ተሾመ ሽፈራው መላኩ ካሳዬ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች:- 1ኛ ወ/ሮ ሙለ ጥበቡ 2ኛ ወ/ሮ ኤልሳ ጥበቡ ጠበቃ መድን መሀሪ - ቀርበዋል 3ኛ አቶ ኪሮስ ጥበቡ 4ኛ አቶ ፀጋዬ ጥበቡ ተጠሪዎች:- 1ኛ ወ/ሮ አዜብ አሰፊ አበራ 2ኛ አቶ አብርሃም ጥበቡ ጠበቃ ግርማ ወልደአረጋን - ቀርበዋል **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ይህ ጉዲይ የተጀመረዉ በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ አመልካቾች በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ 1ኛ ተጠሪ የ2ኛ ተጠሪ እናት ሲሆኑ 2ኛ ተጠሪ የተሰጣቸውን ውክልና በመጠቀም 1ኛ ተጠሪ የአቶ ጥበቡ ገ/ማርያም ልጅ በማስመሰል እንዱሁም እራሳቸውንም የአቶ ጥበቡ ገ/ማርያም እና የወ/ሮ ምህረት አለማየሁ ልጅ ሳይሆኑ ልጅ በመምሰል የውርስ ሰርትፍኬት መዉሰዲቸዉን ጠቅሰዉ ተጠሪዎች ልጅ አይደለም ተብል እንዱወሰንላቸዉ የጠየቁትን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ። ተጠሪዎች በሰጡት መልስ ከአቶ ጥበቡ ገ/ማርያም እና ከወ/ሮ ምህረት አለማየሁ በፀና ጋብቻ ውስጥ የተወለደ መሆኑን ጠቅሰዉ አመልካቾች በቀጥታ የመካድ ክስ ማቅረብ እንደማይችለ እና የመካድ ክስ ማቅረብ የሚቻለዉ ፍርድ ቤት ሲፈቅድ ሆኖ ልጁ በተወለደ በ180 ቀናት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ እንደሚታገድ ጠቅሰዉ ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኝ በዚህ መልኩ የቀረበዉን ክርክር ከሰማ በኋላ ግራ ቀኝ ሚያዝያ 27 ቀን 2007 ዓ.ም የቤተሰብ ሽምግልና በማድረግ አመልካቾች እና ተጠሪዎች የመቶ አለቃ ገ/ማርያም ልጆች መሆናቸው እና ከወ/ሮ ምህረት አለማየሁ መወለዲቸዉን አረጋግጠዋል፤ በተጨማሪም አመልካቾች 2ኛ ተጠሪን ወንድማችን ነዉ በማለት ለስጋ ዘመድ ብቻ የሚሰጠዉን ዉክልና መስጠታቸዉ ተጠሪዎች በጋብቻ ዉስጥ መወለዲቸዉን ያመላክታል ካለ በኋላ የተጠሪዎች የመካድ ክስ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 178(1)፤176(1) እና በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244 (2)መ መሰረት በይርጋ ይታገዲል በማለት ውድቅ አድርጎታል። አመልካቾች በዚህ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ይግባኝ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍድ ቤት የሰጠውን ብይን በማጽናት ወስኗል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካቾች መስከረም 09 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈጽመዋል ያሎቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአቤቱታቸው ይዘትም በአጭሩ የስር ፍርድ ቤት ክርክር ሳይደረግበት አመልካቾች የማያውቁትንና ስለሰነደ ሁኔታ ባላመኑበት ሁኔታ ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን ሰነድ ከክስ መስማት በፉት ተቀብል ሚያዝያ 27 ቀን 2007 እና ሚያዝያ 29 ቀን 2007 የተሰጠ ውክልና ሰነድ በመቀበል በተለይ 1ኛ ተጠሪ እስከ ዛሬ ድረስ ወ/ሮ አዜብ አሰፊ አበራ እየተባለ የሚታወቁ እንጂ የአቶ ጥበቡ ገ/ማርያም ጋር ግንኙነት ያላቸው ስለመሆኑ ምንም አይነት ባልቀረበበት ተጠሪዎች ልጆች ናቸዉ ማለቱ ስህተት ነዉ።
የመካድ ክስ ለማቅረብ የፍርድ ቤት ፈቃድ የሚያስፈልገው በሕግ አባት የተባለን ሰው የሚመለከት እንጂ ለኛ ጉዲይ ተገቢነት የለውም። እስከ ዛሬ ድረስ 1ኛ ተጠሪ ወ/ሮ አዜብ አሰፊ አበራ እየተባለ የሚጠሩ እንጂ የአቶ ጥበቡ ገ/ማርያም ልጅ መሆናቸውን የሚገልጽ እና አመልካቾች የምናውቀው ሁኔታ ስለላለ በይርጋ ሉቋረጥ የሚችልበት ምክንያት የለም። ተጠሪዎች በጋብቻ የተወለድን ነን በማለት ያነሱት ክርክር የህግ ግምት ሉወሰድ የሚገባው በቅድሚያ በጋብቻ ውስጥ ስለመወለዲቸው በፍሬ ነገር አልተረጋገጠም። 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች እናት እና ልጅ ሲሆኑ ከአባታችን ጋር ምንም አይነት የስጋ ዝምድና የላቸዉም፤ በማስረጃ ተጣርቶ መወሰን ሲገባው የስር ፍ/ቤቶች አግባብነት የላለውን አንቀጽ በተሳሳተ ሁኔታ በመተርጎም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ የሚል ነዉ።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮም የስር ፍርድ ቤቶች የጠቀሱት የቤተሰብ ህግ አንቀጾች ለዚህ ጉዲይ ተገቢ አንቀጾች መሆን አለመሆናቸዉን ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል ተብሎል። በዚሁም መሰረት ተጠሪዎች ታህሳስ 07 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ ተጠሪዎች እና አመልካቾች የአንድ እናት አባት ልጆች እህትና ወንድማማቾች ነን፤ አመልካቾች እና ተጠሪዎች ወላጆታችን በፀና ጋብቻ ውስጥ እያለ ተወልደናል፤ አብረን አንድ ቤት በወላጆቻችን እቅፍ ውስጥ አድገናል፤ አመልካቾች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ሆነው ለ2ኛ ተጠሪ ወንድማቸው ለሆንኩት አቶ አብርሃም ጥበቡ በሰነድች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት መታወቂያቸውን ይዘው በአካል ቀርበው 2ተኛ ተጠሪ ወንድማችን ነው ጉዲያችንም አንድ ዓይነት ነው የውርስ ሃብታችን አንዱጣራ እንዱያደርግል ንብረታችን ተረክቦ እንዱያስተዲድርልን ወራሽነታችን እንዱያረጋግጥልን የሚል ውክልና ሚያዝያ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ሲሰጡኝ እህት እና ወንድም መሆናችንን ያውቁ ነበር፤ አመልካቾች እና ተጠሪዎች አውራሾቻችን ካረፈ በኃላ በንብረት ላይ ፀብ እንዲይነሳ ሁላችንም ተወላጆች በተገኘንበት የቤተ ዘመድ ጉባኤ ሰብስቦን ንብረቱን 2ተኛ ተጠሪ ወንድማቸው እንዲስተዲደር ሚያዚያ 27 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈው ቃለ-ጉባኤ ከተፈራረምንበት ግዜ አንስቶ ልጆች መሆናችንን ያውቁ ነበር፤ በፀና ጋብቻ ውስጥ የተወለደ ልጆችን ለመካድ የሚቻለው የልጆቹን መወለድ ካወቀበት ወይም ማወቅ ከነበረበት ግዜ አንስቶ በ180 ቀናት ውስጥ የፍ/ቤቱን ፈቃድ አግኝተው መሆን እንዲለበት በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 171(1) በግልጽ ተደንግጓል። በመሆኑም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሸሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 176(1) እና የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244 2(መ) ጠቅሶ ዉሳኔ መስጠቱ እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ይህንኑ በማጽናት የሰጠው ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ የተፈፀመበት አይደለም በማለት ተከራክረዋል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታዉን ለማስቀረብ በሰበር አጣሪ የተያዘውን ጭብጥ፣ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረዉም አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ለጠየቁት ዲኝነት መነሻ ያደረጉት ተጠሪዎች የአቶ ጥበቡ ገ/ማርያም እና የወ/ሮ ምህረት አለማየሁ ልጆች ሳይሆኑ ልጆች ነን በማለት የውርስ ሰርተፍኬት መዉሰዲቸዉን በመጥቅስ ሲሆን፣ ተጠሪዎች በበኩላቸዉ ክሱ በይርጋ ይታገዲል የሚል ክርክር በማስቀደም የሟቾች ልጆች መሆናቸዉን ጠቅሰዉ የፍሬ ነገር ክርክር ማቅረባቸዉን ለመገንዘብ ተችሎል። የስር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ሆነ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት ሲወስኑ መሰረት ያደረጉት ክሱ የመካድ ክስን የሚመለከት ነዉ በሚል ሃሳብ ስለመሆኑ ከየዉሳኔዎቹ ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም ፍርድ ቤቶች ክሱ በይርጋ ይታገዲል ሲለ የደረሱበት ድምዲሜ የአመልካቾችን የክስ ምክንያት መሰረት ያደረገ መሆን ያለመሆኑ ጉዲይ የዚህን ችልት ምላሽ የሚያሻዉ ሆኖ ተገኝቷል።
የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ የመጀመሪያ መቃወሚያዎች ሁለ ተጠቃለዉ መቅረብ እንዲለባቸዉ ይደነግጋል (የህጉ አንቀጽ 244/3/ ይመለከቷል)። እንዱሁም ፍርድ ቤቱ ክስ ከሰማ በኋላ ግራ ቀኝ የተለያዩበትን የህግ እና/ወይም የፍሬ ነገር ነጥብ መሰረት በማድረግ ጭብጥ መስርቶ ወደሚቀጥለዉ የክርክር ሂደት ከመግባቱ በፉት በመጀመሪያ መቃወሚያ ላይ ብይን መስጠት እንዲለበት በህጉ አንቀጽ 245 (2) እና 246 (1) ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። የሥነ ሥርዓት ህጉ በዚህ ሁኔታ ሲደነግግ ማሳካት የፈለጋቸዉ የተለያዩ ዓላማዎች እንዲለት የሚታወቅ ሲሆን ከዚህም ዉስጥ አንደ እና መሰረታዊዉ የቀረበዉ ክስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ዉድቅ የሚደረግ ከሆነ ከፍሬ ነገር ጋር በተያያዘ የግራ ቀኝን ክርክር እንዱሁም ማስረጃዎችን ለመስማት የሚባክነዉን የፍርድ ቤቱ እና የተከራካሪ ወገኖችን ወጪ፣ ጊዜ እና ድካም ለማስቀረት፣ ጉዲዩም በአጭር ጊዜ ዉስጥ መቋጫ እንዱያገኝ በሚል ዓላማ እንደሆነ ይታመናል። በልላ በኩል እንደነገሩ ሁኔታ በመጀመሪያ መቃወሚያ ላይ ዉሳኔ ለመስጠት ማስረጃን መስማት እና መመርመር አስፈላጊ ላሆን የሚችልበት ሁኔታ መኖሩ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዋናዉ ጉዲይ ላይ ክርክር እና ማስረጃ ቀርቦበት እልባት ላሰጥበት የሚገባዉ የክርክር ጭብጥ የመጀመሪያ መቃወሚያን ለመወሰን የክርክር ነጥብ ላሆን የሚችልበት ሁኔታ የለም።
ይልቁንም የፍሬ ነገር ክርክር የሚመረመረዉ ክሱ በመጀመሪያ መቃወሚያ ዉድቅ የማይደረግ ከሆነ ብቻ ስለመሆኑ እሙን ነዉ።
በመጀመሪያ መቃወሚያነት የሚነሱ እና ፍርድ ቤቱ የፍሬ ነገር ክርክርን አስመልክቶ ጭብጥ መስርቶ ወደሚቀጥለዉ የክርክር ሂደት ከመግባቱ በፉት መርምሮ ዉሳኔ እንዱሰጥበት ምክንያት ከሚሆኑት ዉስጥ አንደ ይርጋ ስለመሆኑ የሚታወቅ ነዉ። ይርጋ መብትን ለማስከበር የሚቀርብ ክስን (limitation of action) ቀሪ የሚያደርግ ሲሆን፣ የሚነሳዉም ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ ንብረት ወይም ጉዲይ ላይ ካለዉ መብት አኳያ ሳይሆን ከሳሽ የሆነዉ ወገን መብቱን ለማስከበር በምን ያህል ጊዜ ክሱን ማቅረብ እንዲለበት የሚመለከትና በህግ ተለይቶ የተመለከተዉ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ ክስ የማቅረብ መብትን ቀሪ የማድረግ ዉጤት ያለዉ ነዉ። ይህም ከሳሽ የሆነዉ ወገን ክስ የሚያቀርብበት ጉዲይ ላይ መብት ቢኖረዉም በጊዜዉ ክሱን ባለማቅረቡ ብቻ ለክሱ መሰረት ካደረገዉ ጉዲይ ጋር በተያያዘ ያለዉን መብት ሉያጣ የሚችልበት ሁኔታ መኖሩን ታሳቢ ያደረገ ነዉ። ሕግ አዉጪዉ ለተለያዩ የመብት ዓይነቶች የተለያየ የይርጋ ደንብ የሚያስቀምጥ በመሆኑ አንድ ክስ በይርጋ የሚታገድ መሆን አለመሆኑን በመወሰን ረገድ ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ከሳሽ በክሱ የጠቀሰዉን የክስ ምክንያት ለጉዲዩ አግባብነት ካለዉ የይርጋ ደንብ አንፃር የመመርመር ኃላፉነት እንዲለበት መገንዘቡም ተገቢ ነዉ።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ፣ ከላይ እንደተገለጸዉ፣ የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካቾችን ክስ ዉድቅ ያደረጉት ጉዲዩ የመካድ ክስን የሚመለከት ነዉ በሚል ሃሳብ ነዉ። በመሰረቱ የመካድ ክስ የሚቀርበዉ የልጅ አባት ነዉ ተብል በህግ ግምት የሚወሰድበት ሰዉ የልጁ አባት አለመሆኑን ፍርድ ቤት እንዱወስንለት የሚቀርብ ዲኝነት ስለመሆኑ በተሻሻለዉ የፋዳራል የቤተሰብ ህጉ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 126 እና 167 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች የምንገነዘበዉ ነዉ። ከመካድ ክስ ጋር በተያያዘ በቤተሰብ ህጉ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች (አንቀጽ 167 እስከ 178 ይመለከቷል) በአጠቃላይ የምንገነዘበዉ፣ ልጁ የተጸነሰዉ ወይም የተወለደዉ የልጁ አባት በተባለዉ ሰዉ እና በልጁ እናት መካከል በህግ በታወቀ ግንኙነት (ማለትም ባልና ሚስት ወይም እንደባልና ሚስት) አብረዉ የመኖር ግንኙነት በነበረበት ወቅት ከሆነ እና በዚህም ምክንያት በህግ የልጁ አባት ነዉ ተብል ግምት የሚወሰድበት ሰዉ ወይም በህጉ መብት የተሰጠዉ ላላ ሰዉ፣ የልጁ አባት ላሆን የማይችልበትን ምክንያት አስመልክቶ በቤተሰብ ህጉ ተለይቶ ከተቀመጡት ምክንያቶች ዉስጥ አንደን በመጥቀስ በህጉ በተመለከተዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ (አንቀጽ 176 ይመለከቷል) ክስ አቅርቦ ካላስወሰነ በስተቀር የአባትነት ግምቱ በማንኛዉም ጊዜ እና ሁኔታ በዘፈቀደ ሉስተባበል የማይችል መሆኑን ነዉ። ስለሆነም የመካድ ክስ የሚያቀርብ ሰዉ በህግ የልጁ አባት እንደሆነ ግምት የሚወሰድበት ሰዉ ወይም በህግ ይህን ክስ የማቅረብ መብት የተሰጣቸዉ ሆኖ፣ ክሱ የመካድ ክስ ነዉ ለማለት የሚቻለዉም ከሳሹ የመካድ ክስ የቀረበበት ልጅ የተወለደዉ አባት ነዉ ተብል የህግ ግምት የተወሰደበት ሰዉ እናቱ በጋብቻ ወይም እንደባልና ሚስት አብረዉ ሲኖሩ በነበረበት ወቅት መሆኑን ተቀብል ነገር ግን በልላ ምክንያት ልጁ በህግ አባቱ ነዉ የተባለዉ ሰዉ ልጅ አለመሆኑን በመጥቀስ የቀረበ ክስ ሲሆን ነዉ።
ይሁንና በተያዘዉ ጉዲይ አመልካቾች ክስ ሲያቀርቡ ተጠሪዎች በጋብቻ ዉስጥ የተወለደ መሆኑን አልጠቀሱም። ክሳቸዉ ተጠሪዎች የሟች ወላጆቻቸዉ የአቶ ጥበቡ ገብረማርያም እና የወ/ሮ ምህረት አለማየሁ ነን በማለት የወራሽነት ማረጋገጫ ማስረጃ መያዛቸዉን በመጥቀስ ነዉ። ምንም እንኳ በክሳቸዉ የጠየቁት ዲኝነት ተጠሪዎች የሟች ወላጆቻቸዉ አቶ ጥበቡ ገብረማርያም እና የወ/ሮ ምህረት አለማየሁ ልጆች አይደለም ተብል ይወሰንልን የሚል ቢሆንም፣ ክሱ ተጠሪዎች በጋብቻ ዉስጥ የተወለደ ስለመሆኑ ዔዉቅና ባልሰጠበት ሁኔታ የአመልካቾች ክስ የመካድ ክስ ነዉ ለማለት አይቻልም።
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪዎች በጋብቻ ዉስጥ የተወለደ መሆን አለመሆኑ እና በጋብቻ ዉስጥ ተወልደዋል ከተባለ ህጋዊ ዉጤቱ ምንድን ነዉ የሚለዉ ነጥብ ይርጋን አስመልክቶ የቀረበዉ ክርክር ዉድቅ ከተደረገ በኋላ ግራ ቀኝ በሚያቀርቧቸዉ ክርክሮች እና ማስረጃዎች መሰረት ተጣርቶ ዉሳኔ ላሰጥበት የሚገባ የስረ ነገር ጭብጥ ነዉ። ከዚህ ዉጪ፣ የአመልካቾች የክስ ይዘት ሲታይ የመካድ ክስ ባልሆነበት ሁኔታ፣ ተጠሪዎች በጋብቻ ዉስጥ የተወለደ መሆናቸዉን የሚሳይ ማስረጃ መቅረቡ (በእርግጥ ቀርቧል ወይስ አልቀረበም የሚለዉ ነጥብ እንደተጠበቀ ሆኖ) የቀረበዉ ክስ ልጅነትን እንደ መካድ ክስ ተወስድ ክሱ በይርጋ ቀሪ ለማድረግ ምክንያት ላሆን አይችልም።
ከዚህ ሁለ አንፃር ሲታይ የአመልካቾች ክስ በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 176 መሰረት በይርጋ ይታገዲል በማለት በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸናዉ ዉሳኔ፣ የአመልካቾችን ክስ መሰረታዊ ባህርይ እና ይዘቱን ያገናዘበ ባለመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ብይን እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
የአመልካቾች ክስ በይርጋ አልታገደም ተብል ተወስኗል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተዘግቶ የነበረዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ፣ ተጠሪዎች ከሟች አቶ ጥበቡ ገብረማርያም እና ከሟች ወ/ሮ ምህረት አለማየሁ የተወለደ መሆን አለመሆናቸዉን አስመልክቶ ግራ ቀኝ በሚያቀርቡት ክርክር እና ማስረጃ ላይ በመንተራስ መርምሮ አግባብ ነዉ የሚለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 341(1) መሰረት ተመልሶለታል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.