No summary available.
ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም ዳኞች፡ ….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) 2. ቀነዓ ቂጣታ 3. ፈይሳ ወርቁ 4. ደጀኔ አያንሳ 5. ብርቅነሽ እሱባለዉ አመልካች፡ …….ወ/ሮ ፀሐይ አስራት- ጠበቃ ታዬ ገ/መድን - ቀርበዋል።
ተጠሪ፡ ………….አቶ አሰፊ ማሞ - ከጠበቃ ልኡል አያላው ጋር - ቀርበዋል።
ይህ መዝገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የባልና ሚስት ክርክር የተጀመረዉ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.244466 መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከተከሳሽ ጋር የነበረን ጋብቻ የፈረሰ በመሆኑ የፍቺ ውጤት የሆነዉ፣ በቀድሞ በቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 10 (አሁን ወረዲ 11) ዉስጥ የሚገኙ 1ኛ. የካርታ ቁጥር ቦላ11/16/1/6/47615/00 የሆነዉ ቤትና ከዚህ ቤት የሚገኝ የቤት ኪራይ ገቢ፣ 2ኛ. የቤት ቁጥር አዱስ ሰነድ አልባ አምስት ክፍል ቤትና ከዚህ ቤት የሚገኝ የቤት ኪራይ ገቢ፣ 3ኛ. በ500 ካ.ሜ ቦታ ላይ የተከልነው 400 እግር ባህር ዛፍ ከነይዞታው፤
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በዲሽን ባንክ በተጠሪ ስም ያለ ገንዘብ፤ የተለያዩ የቤት እቃዎችን ፤የመቃብር ፊካና እድሮችን በጋራ ያፈራን በመሆኑ ድርሻዬን እንዱያካፍለኝ በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
ተከሳሽ በዚህ ክስ ላይ ባቀረበዉ መልስ እኔና ከሳሽ በጋብቻ ስንኖር ከምግብ ያለፈ በጋራ ሰርተን ያጠራቀምነው ገንዘብ የለም፤ የካርታ ቁጥር ቦላ11/16/1/6/47615/00 የሆነውን ቤት የጋራ ያልሆነና ከእናቴ በውርስ ያገኘሁት ቤትና ቦታ መንግስት ለልማት በመዉሰደ በተሰጠ ምትክ ቦታና የካሳ ገንዘብ የተሰራ በመሆኑ የጋራ ሀብት ሳይሆን የግል ንብረቴ ነዉ፤ ላልቹም ከሳሽ የጠየቀቻቸው ንብረቶችም ከዉርስ ሀብት የተገኘና የላለ በመሆናቸው የግል ሀብት ናቸው ፤የመቃብር ፊካና እድሮቹን ትካፈል በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በማከራከር፣ የሰዉ ምስክሮችን በመስማት፣ ከሚመለከተዉ የከተማዉ አስተዲደር ጽ/ቤት ተጣርቶ እንዱቀርብ በማድረግና የሰነድ ማስረጃ በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ በተከሳሽ ስም የካርታ ቁጥር ቦላ11/16/1/6/47615/00 የተሰራለት ቤት ግራ ቀኙ ጋብቻ ፈጽመዉ እየኖሩ በነበረበት ጊዜ የተሰራ መሆኑን በግራ ቀኙ የሰዉ ምስክሮች የተረጋገጠ መሆኑና በተከሳሽም ያልተካደ ነዉ፤ በመሆኑም ይህ ቤት የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት ነዉ፤ ከዚህ ቤት የሚገኘዉን የቤት ኪራይ ገቢ (አርባ ሺህ) (ሀያ ሺህ) የከሳሽ ነዉ፤ በቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 10 የቤት ቁጥር አዱስ የሆነዉ ሰነድ አልባ ቤት 5 ክፍል መኖሩ ስላልተረጋገጠ የከሳሽ የዲኝነት ጥያቄ ዉድቅ ነዉ፤ በቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 10 ዉስጥ በ500 ካ.ሜ ባድ ቦታ ላይ የተተከለ ቁጥቋጦ በብዛት በቁጥር 17 ጉቶ በቁጥር 23 ያገኘ እና በጠቅላላዉ 40 የተቆጠረ ዛፍ ጉቶ እና ቁጥቋጦና ይዞታ የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት ነዉ፤ የቤት ቁሳቁሶች እና በባንክ አለ የተባለዉን ገንዘብ አጣርቶ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ በመስጠት፤ የጋራ ንብረት ነዉ የተባለትን ንብረቶችን የክፍፍል ሥርዓቱንም በማመልከት ወስኗል።
የሥር ተከሳሽ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በቦላ ክ/ከተማ በወረዲ 11 ዉስጥ የሚገኘዉ የካርታ ቁጥር ቦላ11/16/1/6/47615/00 የሆነዉ ያለዉና የተሰራዉ ቤት መንግስት ለልማት በወሰደዉ ቤትና ይዞታ ምትክ በተሰጠዉ ይዞታና በካሳ በተገኘ ገንዘብ የተሰራ መሆኑን ተከሳሽ ባቀረበዉ ማስረጃ በተሻለ ሁኔታ በማስረዲቱና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
(ቅጽ 17) ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም በሰጠዉ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ዉሳኔ ከባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጋር በተገናኘ በአንደኛዉ ተጋቢ በዉርስ የተገኙ ንብረቶች ለልማት በሚል በመፍረሳቸዉ የተገኘ የካሳ ክፍያ በግብይት እንደተገኘ ተቆጥሮ የግል ስለመሆኑ በፍ/ቤት አልተረጋገጠም በሚል እንደ የጋራ ሀብት ሉቆጠር የማይችል መሆኑን ዉሳኔ ያሳለፈ በመሆኑ በዚህ ጉዲይ ላይ ተፈጻሚነት ያለዉ ስለሆነ፤ ይህ ቤትና ይዞታ የተከሳሽ የግል ንብረት ነዉ፤ ከዚህ ቤት ከፍቺ በኋላ የሚገኘዉም የቤት ኪራይ ገንዘብ የተከሳሽ የግል ንብረት ነዉ በማለት የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማሻሻል ወስኗል። የሥር ከሳሽ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበች ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን በትዕዛዝ ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች በ1/7/2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ አሁን ክርክር ያስነሳው የካርታ ቁጥር ቦላ11/16/1/6/47615/00 በ500 ካ.ሜ ይዞታ ላይ የነበረዉ ጎጆ ቤት በትዲር ውስጥ በማፍረስ አመልካች ጠላ በመሸጥና ብልኬት በመሸከም የጉልበት አስተዋፀኦ በማድረግ፣ በብልኬት 7 ክፍል ቤት በጋራ መስራታችን በማስረጃ ተረጋግጦ ባለበት፤ ይህም ሰበር ሰሚ ችልት በ
ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠዉ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ለዚህ ጉዲይ አስገዲጅ ላሆን የማይችል ሆኖ ሳለ፤ ይህን ቤት በጋብቻ ዉስጥ በጋራ የሰራንና ያፈራነዉ በመሆኑ በተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 63 (1) መሰረት የጋራ ሀብት ሆኖ እያለ፤ እንዱሁም ክርክር የተነሳበት ቤት በጋብቻ ውላችን የጋራ ሀብት መሆኑን የተስማመንበትና እየተጠቀምንበት ያለን የጋራ ሀብት በመሆኑ፤ የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱሻርልኝ፣ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ እንዱጸናልኝ ወጪና ኪሳራ ከጠበቃ አበል ጋር እንዱወሰንልኝ በማለት አመልክታለች።
የሰበር አጣሪ ችልትም ጉዲዩን በማየት ፣የክርክሩ መነሻ የሆነውና በቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 11 የካርታ ቁጥር ቦላ11/16/1/6/47615/00 የሆነው ቤት ተከራካሪ ወገኖቹ በጋብቻ ውስጥ እያለ የተሰራ ስለመሆኑ በተገለፀበት ቤቱ የግል ንብረት ነው በሚል የተወሰነበት አግባብነት፣ ለማጣራት ለሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ባዘዘዉ መሰረት ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት በአጭሩ፡ ተጠሪ ከመንግስት የተረከበዉ ይዞታ ባድ ቦታና በወቅቱ የተሰራ ምንም ዓይነት ቤት አልተሰራም፤ በጋብቻ ውላችን የጋራ እንዲይሆኑ የተስማማንበትና በውርስና ስጦታ ያገኘሁት ቤትና ቦታ ለልማት በመወሰደ በተገኘ ምትክ ቦታና ካሳ ገንዘብ የተሰራ ቤት በመሆኑና ይህንንም በፍ/ቤት የግል ይባልልኝ ማቅረብ የሚያስፈልገው ባለመሆኑ፤ አመልካች ያቀረበችዉ የሰበር አቤቱታ የተዛባ በመሆኑ፣ የሥር የከፍተኛና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያስተላለፈት ውሳኔ ምንም ዓይነት መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለዉ ስለሆነ እንዱጸናልኝ፣ ወጪና ኪሳራ ዝርዝር የማቅረብ መብት እንዱጠበቅልኝ በማለት ተከራክሯል።
አመልካችም የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመርነዉ አከራካሪዉ በቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 11 የካርታ ቁጥር ቦላ11/16/1/6/47615/00 የተመዘገበዉ የመኖሪያ ቤት የአሁን አመልካች እና የተጠሪ የጋራ ሀብት ነዉ ወይስ የተጠሪ የግል ሀብት ነዉ? የሚለዉ ነጥብ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ። አመልካች ባቀረበችዉ ክርክር ይህን ቤት በጋራ ገንዘባችን በትዲር ዉስጥ የሰራንና ያፈራን ስለሆነ የጋራ ሀብታችን ነዉ በማለት የተከራከረች ሲሆን፤ ተጠሪ በበኩለ ቤቱን የሰራሁት መንግስት በዉርስ ያገኙትን ቤትና ቦታ ለልማት ወስድ በሰጠኝ ምትክ ቦታና በከፈለኝ የካሳ ገንዘብ በመሆኑ ቤቱ የግል ሀብቴ ነዉ በማለት ተከራክሯል። በዚህ መሰረት በሥር ፍ/ቤት በማስረጃ የተረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ሲታይ አመልካች እና ተጠሪ በ1999 ዓ.ም ዉስጥ ጋብቻ ፈጽመዉ ጋብቻቸዉ በፍቺ ዉሳኔ በ8/2/2011 ዓ.ም እስከፈረሰበት ድረስ በትዲር አብረዉ ሲኖሩ እንደነበሩ እና ግራ ቀኙ በትዲር አብረዉ ሲኖሩ ይህን ለክርክር መነሻ የሆነዉን የመኖሪያ ቤት በ2009 ዓ.ም ዉስጥ የሰሩትና ያፈሩት መሆናቸዉን ነዉ። ይህ ማለት አመልካች እና ተጠሪ በትዲር አብረዉ እያለ ቤቱን መስራታቸዉንና ማፍራታቸዉን የሚያስገነዝብ ነዉ።
እንደሚታወቀዉ የፋዳራለ የተሻሻለዉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 62 (1) መሰረት ባልና ሚስት በትዲር ዉስጥ በጋራ ያፈሩአቸዉ ንብረቶች የጋራ ሀብቶቻቸዉ እንደሚሆኑ እና ይህም አንደኛዉ ተገቢ የግል ሀብቱ መሆኑን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ካላስረዲ በቀር ንብረቱ በአንደኛዉ ተገቢ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቢሆንም የጋራ ሀብት እንደሆነ እንደሚቆጠር በዚህ ሕግ አንቀጽ 63 (1) ሥር ተመልክቷል። በዚህ አግባብ አሁን የተያዘዉ ጉዲይ ሲታይ ለክርክር መነሻ የሆነዉ ግራ ቀኙ በትዲር አብረዉ እየኖሩ የሰሩትና ያፈሩት መሆናቸዉን በሥር ፍ/ቤት በማስረጃ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ተጠሪ በበኩለ ግን ቤቱን ከመንግስት በተከፈለዉ የካሳ ገንዘብ እንደሰራ ገልጾ የተከራከረ ቢሆንም ተጠሪ የካሳ ገንዘብን ለቤቱ ሥራ ያዋለ መሆኑን በፋዳራላ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 58 መሰረት የካሳ ገንዘቡን ለቤቱ ሥራ አዉል ያፈራዉ መሆኑን ጠቅሶ ቤቱ የግል ሀብት እንዱባልልኝ በማለት ለፍ/ቤት አቤቱታ አቅርቦና ፍ/ቤቱ ቤቱ የተጠሪ የግል ሀብት መሆኑን ተብል ያጸደቀበት አግባብ የለም። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በ
ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም (ቅጽ 13) የሰጠዉ አስገዲጅ የህግ ትርጉም በባንክ የተቀመጠ በመንግስት የተከፈለ የካሳ ገንዘብ የሚመለከት ስለሆነ አሁን ከተያዘዉ ክርክር ጋር ተመሳሳይ የህግ ጭብጥ የላለዉ ስለሆነ በዚህ ጉዲይ ላይ ተፈጻሚነት የለዉም። በመሆኑም ተጠሪ አከራካሪዉ ቤት የግል ሀብቱ መሆኑን በሕግ አግባብ ማረጋገጡን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ የሚያመለክተዉ ነገር የለም። ስለሆነም ለክርክር መነሻ የሆነዉ በቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 11 የካርታ ቁጥር ቦላ11/16/1/6/47615/00 በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉ የመኖሪያ ቤት ግራ ቀኙ በትዲር አብረዉ እየኖሩ ያፈሩት መሆናቸዉ የተረጋገጠ በመሆኑ፤ ቤቱ የአመልካች እና የተጠሪ የጋራ ሀብት ነዉ እንጂ የተጠሪ የግል ሀብት አይደለም ብለናል። የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር በዚህ አግባብ በመረዲት አከራከሪዉ ቤት የግራ ቀኙ የጋራ ሀብት መሆኑን መወሰን ሲገባዉ የተጠሪ የግል ሀብት ነዉ በማለት መወሰኑ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህን ዉሳኔ ማረም ሲገባዉ በትዕዛዝ በማጽናት መወሰኑ የህግ ድጋፍ የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አከራከሪዉ ቤት የግራ ቀኙ የጋራ ሀብት ሆኖ ሳለ፣ የተጠሪ የግል ሀብት ነዉ በማለት መወሰናቸዉ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.244466 መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.197833 የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸባቸዉ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.73234 ሐምል 19 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት ጸንቷል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.