No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- መዓዛ አሸናፉ ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ወ/ሮ ሰርካለም አበበ -- ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አፈወርቅ ቅጣው -- አልቀረቡም መዝገቡን ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች በቀን 12/02/2013 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 18/10/2011 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 24/11/2012 ዓ.ም የሰጡት ብይንና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው በስር የፋ/መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ ከተጠሪ ጋር ጋብቻ ፈጽመን በነበረበት ወቅት ጥር 5/2004 ዓ.ም ከጋራ ገንዘባችን በተጠሪ ስም ብር 160,000.00 (አንድ መቶ ስልሳ ሺህ) ወጪ በማድረግ በ250 አክስዮኖች የተከፊፈለ ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ) ካፑታል ያለውን ተጠሪና ወንድማቸው አቶ ቃለአብ ቅጣው መስራች አባላት የሆኑበትን ኮንሶለሹን አስመጪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በኋላ ስሙ ኮንሾሱሽን ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሆነ ማህበር አቋቁመናል፤ የማህበሩ ካፑታል ወዱያውኑ ባልና ሚስት ሆነን በጋራ ካፈራነው ሀብት በጥሬ ገንዘብ የተከፈለ ሲሆን መዋጮው ሙለ በሙለ የተከፈለ ስለመሆኑ በኮንሶለሽን ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መመስረቻ ጽሁፍ ተረጋግጧል፤ በተጠሪ ስም የተመዘገበው አክስዮን ብዛቱም እያንዲንዲቸው ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) ዋጋ ያላቸው 11,350 (አስራ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሀምሳ) አክስዮኖች ሆነዋል፤ በመካከላችን የነበረው ጋብቻ በመፍረሱ ምክንያት ይህ በጋራ ገንዘብ መዋጮ የተቋቋመው ኮንሶለሽን ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አክስዮኖች የሚያስገኘው መብትና ጥቅም እንዱሁም ገንዘብና ንብረት የጋራ በመሆናቸው አክስዮኖቹና አክስዮኖቹ የሚያስገኙት እና ያስገኙት ትርፍ ለአመልካች እና ለተጠሪ እኩል ሉካፈል ይገባል በማለት ጠይቀዋል።
ተጠሪ በሰጡት መልስ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በመካከላችን የነበረው ትዲር በፍ/ቤት የፈረሰው ሐምል 9/2004 ዓ.ም ሲሆን አመልካች የጋራ ሀብት ክፍፍል ጥያቄ በታህሳስ 7/2006 ዓ.ም አቅርበው በዚህ መነሻነት የጋራ ሀብት ክፍፍል ውሳኔ ተሰጥቷል፤ አመልካች የክፍፍል ጥያቄውን ሲያቀርቡ የአሁኑንም አብረው ማቅረብ ነበረባቸው፤ አሁን ክፍፍል የጠየቁበትን ማህበር ከምስረታው ጀምሮ ያውቁታል ይህንም ባቀረቡት ክስ ላይ ስሙ ኮንሶለሽን ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አቋቋምን በማለት አረጋግጠዋል፤ ስለሆነም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216 መሰረት ቀንሰው ያስቀሩትን መብት እንደገና ሉከሱበት አይችለም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት የመቃወሚያ ክርክሩን ከሰማ በኋላ አመልካች የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ተጠሪ ያካፍለኝ ብለው ታህሳስ 7/2006 ዓ.ም አቤቱታ ሲያቀርቡ ኮንሶለሽን ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሆነውን ንብረት አብረው ማቅረብ እየቻለ ሆን ብለው ቀንሰው ካስቀሩ በኋላ አሁን ይህን ንብረት ተጠሪ ግማሽ ድርሻዬን ያካፍለኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ የህግ ድጋፍ የለውም በማለት ብይን ሰጥቷል።
በዚህ ብይን ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ጉድለት የለበትም ተብል ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዟል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው።
አመልካች በቀን 12/02/2013 ዓ/ም ባቀረቡት የሰበር ማመልከቻ በስር ፍ/ቤት በአሁን አመልካች የቀረበው አቤቱታ የፍቺ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የሚቀርብ የፍቺ ውጤት የሆነው የባልና ሚስት ሀብት እንዱጣራ እና ንብረት ክፍፍል እንዱደረግ ነው እንጂ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216 እንደተመለከተው የቀረበ አይደለም፤ ንብረቱ በተጠሪ ቁጥጥር ሆነ እንጂ የአመልካችም ንብረት ነው። በዚህም ግዜ የጋራ ንብረቱ በእጁ ያለ ሰው (ባል ወይም ሚስት) ንብረቱ መኖሩንና የማጣራቱ አካል እንዱሆን ማሳወቅ አለበት፣ ይህ ካልሆነ ንብረት መሸሸግና አላግባብ መበልጸግን ያስከትላል። ከተጋቢዎች አንደኛው የጋራ ንብረት እንድንካፈል በማለት አቤቱታ ሲያቀርብ ፍርድ ቤቱ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 85 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት የባልና ሚስት ሀብት እንዱጣራ ከማድረግ በስተቀር እንደ ክስ ተቆጥሮ መሰል መቃወሚያ የሚቀርብበት አይደለም።የፍቺ ወጤት የሆነ ንብረት ክፍፍልን በመቃወሚያ ማስቆም ህጉ አይፈቅድም። ሀብት የሚጣራው ከተጋቢዎች አንደኛው በሚያቀርበው የንብረት ዝርዝር ተመስርቶ ሲሆን ይህ ሂደትም የሀብት ማጣራት ሂደት እንጂ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ አራተኛው መጽሀፍ ምዔራፍ 1 (ከ215-240) የተመለከተው ክስ አይደለም። ንብረት የሚጣራውም በየቦታው ያለና በየግዜው የሚገኙ ንብረቶች ማሰባሰብ እና ለባለቤቶቹ ማለትም ለባልና ሚስት ለማካፈል ነው። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ እንዱሻርና የጋራ ንብረት የሆኑ በተጠሪ ስም የተመዘገቡ አክስዮኖች ካስገኙት ትርፍና ወደ ካፑታል ማሳደጊያ ያልዋለው ትርፍ የግራ ቀኛችን የጋራ ሀብት በመሆናቸው በቤተሰብ ህጉ መሰረት እኩል እንድንካፈል ይወሰንልኝ በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልቱ ተመርምሮ በአመልካችና ተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ መፍረሱን ተከትል በመካሄድ ላይ በሚገኘው የንብረት ክፍፍል አመልካች በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የሶለሽን ንግድ አክስዮኖችና አክስዮኖቹ ያስገኟቸው ጥቅሞች የጋራ ሀብት መሆናቸውን በመጥቀስ የድርሻቸው ተካፍል እንዱሰጣቸው ያቀረቡት አቤቱታ ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ ቀንሰው ያስቀሩት መብትና ጥያቄ ነው በሚል ውድቅ የተደረገበት አግባብነት ከፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216 አንጻር ለማጣራት በሚል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
ተጠሪ በቀን 08/08/2013 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ የአመልካች የሰበር አቤቱታ የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠ በ90 ቀናት ውስጥ ያልቀረበ በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባል። የአመልካች ተጨማሪ ሀብት ክፍፍል ጥያቄ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216 መሰረት የሚገዛ ነው፤ የሥነ ሥርአት ህጉ በስራ ላይ እንዱውል ከታወጀበት ጀምሮ ለሚቀርቡ ክሶችና በክርክር ላይ ላለትም ክሶች ተፈጻሚነት እንዲለው የህጉን የአፈጻጸም ወሰን በወሰነው አንቀጽ 1 ላይ ተደንግጓል። አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ደግሞ ይግባኝ ወይም የሰበር ወይም የአፈጻጸም አቤቱታ ሳይሆን ለመጀመሪያ ግዜ የቀረበ የክፍፍል ክስ በመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216 ተፈጻሚነት አለው። በልላ በኩል በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 108 ላይ በግልጽ እንደተመለከተው በቤተሰብ ህጉ የተመለከቱ የሥነ ሥርአት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዚህ ህግ ውስጥ በተመለከቱት ጉዲዮች ላይ ለሚነሱ ክርክሮች የፍ/ሥ/ሥ/ህጎች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል በማለት ይደነግጋል፤ በቤተሰብ ህጉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216 ተፈጻሚነትን የሚያስቀር የሥነ ሥርአት ድንጋጌም የለም። ስለዚህ የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216 ለቤተሰብ ጉዲዮች ክርክርም ተፈጻሚነት አለው። አመልካች ክፍፍል ሲጠይቁ አብረው መጠየቅ የሚችለትን ነገር ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ ቀንሰው ያስቀሩትን የመብት ጥያቄ አሁን ነጥለው አቤቱታ ሉያቀርቡበት ስለማይችለ አቤቱታቸው በስር ፍ/ቤቶች በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216 መሰረት ውድቅ መደረጉ ተገቢ ነው። ከዚህም ላላ አመልካች እና ተጠሪ በትዲር እያለ የነበረው የአክስዮን መጠን 160 ስለሆነ የአመልካች አቤቱታ በፍ/ብሥ/ሥ/ህ/ቁ 216 መሰረት ተቀባይነት የለውም እንጂ አለው የሚባል ከሆነ የድርሻ መጠናቸው የ160 አክስዮኖች ግማሽ 80 አክስዮኖች ብቻ ናቸው። ከትዲር መፍረስ በኋላ ተጠሪ የግል ገንዘባቸውን በመጨመር ያሳደጉት አክስዮን አመልካችን አይመለከትም፤ አመልካች ይገባቸዋል ከተባለ በማህበሩ ውስጥ የሚገባቸው አክስዮን 80 አክስዮን ስለሆነ የእነዚህን አክስዮኖች ዋጋ ተጠሪ ሉከፍሎቸው ይችላለ፤ በቤተሰብ በተያዘ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ውስጥ ግን አመልካች የማህበሩ አባል የሚሆኑበት ምክንያት የለም፤ የንግድ ህግ ቁጥር 523 እና የማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 9.2 አይፈቅድም። ስለሆነም 80 አክስዮኖች ያስገኙት ትርፍም ሆነ ወደፉት ትርፍ ካስገኘ ከማህበሩ ተጣርቶ በሚቀርበው መጠን መሰረት ሉከፈላቸው ይችላል። አመልካች በትዲር ዘመን ያላፈሩትን እና የላለውን 11,350 አክስዮኖች ልካፈል፣ ትርፍም በዚሁ መጠን ይከፈለኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግና የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱጸናልኝ በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም በመልስ መልሳቸው የስር ክርክራቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
ከፍ ሲል ባጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን በበኩላችን ለሰበር ችልቱ የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኙ ክርክር እንዱሁም ከተገቢው የህጉ ድንጋጌ በማያያዝ ቅሬታ በቀረበበት ውሳኔ የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል። ለውሳኔ አሰጣጥ እንዱረዲንም የፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የኮ/መ/ የሆነውን መዝገብ አስቀርበን ተመልክተናል።
እንደመረመርነው ተጠሪ ባቀረቡት መልስ የአመልካች የሰበር አቤቱታ የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠ በ90 ቀናት ውስጥ ያልቀረበ በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባል በሚል ቀዲሚ መከራከሪያ ያቀረቡ ቢሆንም ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን መርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ (ትዕዛዝ) የሰጠው ሀምላ 23/2012 ዓ.ም ሲሆን የሰበር አቤቱታው የቀረበውና የዲኝነቱ ተከፍል የሰበር ፊይል የተከፈተው ጥቅምት 12/2013 ዓ.ም ነው። ስለሆነም የሰበር አቤቱታው በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠ በ90 ቀናት ውስጥ የቀረበ በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበው መከራከሪያ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ለሰበር ችልቱ ወደተያዘው ጭብጥ ስንመለስ ከሳሽ ሉከስበት ሲችል ሆነ ብል በመቀነስ ባስቀረው ሀብት ምክንያት እንደገና ላላ ክስ ማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ እና ከሳሽ ያቀረበው ክስ በአንድ ጉዲይ ላይ የተመሰረተ ሆኖ የሚጠይቀው ዲኝነት ግን ከአንድ በላይ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ሳይፈቅድለት ሉጠይቅ ይገባው ከነበረው ዲኝነት ውስጥ በከፉል ራሱ ቀንሶ ባስቀረው መብት እንደገና ሉከስበት የማይችል ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216 (3) (4) መረዲት ይቻላል። ይኸው የስነ ስርዓት ህጉ ድንጋጌ እንደአግባብነቱ በቤተሰብ ክርክሮችም ተፈፃሚነት አይኖረውም የሚባልበት የህግ ምክንያት የለም። ይሁን እንጂ ጉዲዩን በቤተሰብ ህጉ ስለጋብቻ ንብረት ማጣራት ከተደነገጉት ድንጋጌዎች እና በተለይም ከግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አንፃር መመልከቱ ተገቢ ይሆናል።
በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ከአንቀጽ 85 ጀምሮ ያለ ድንጋጌዎች የባልና ሚስትን ሀብት ስለማጣራት ይደነግጋለ። የባልና ሚስትን ሀብት የማጣራቱም ሆነ የክፍፍለ ተግባር የሚመራበት የህጉ መሰረታዊ መርህ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ለሁለቱም እኩል የሚከፊፈል በመሆኑ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ከድንጋጌዎቹ መገንዘብ ይቻላል። ግራ ቀኙ በሚያደርጉት ስምምነትና በህጉ አግባብ የግል ሀብት መልሶ የሚወሰድ መሆኑ እንዱሁም የካሳና የእዲ ጉዲዮች የባልና ሚስት ሀብት ከመከፈለ በፉት ተቀንሶ የሚከፈል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ በመለስ ግን የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ለሁለቱም እኩል እንዱከፈል የሚደረግ መሆኑ የህጉ መሰረታዊ መርህ ነው።
ከዚህም ላላ ከቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 108 እና 109 ግልጽ ድንጋጌዎች መገንዘብ እንደሚቻለውም የፍትሐብሄር ሥነ ሥርዓት ህጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት የሚኖራቸው በቤተሰብ ህጉ ባልተመለከቱ የሥነ ሥርዓት ጉዲዮች ላይ ብቻ ነው። በባልና ሚስት የጋብቻ ንብረት ክርክር ብቻም ሳይሆን ጋብቻው የፈረሰው በሞት ቢሆን እንኳ በህይወት ባለው ተጋቢ እና በሟች ወራሾች መካከል የንብረት ክፍፍልን በተመለከተ ክርክር የተነሳ እንደሆነ የባልና ሚስትን ሀብት ስለማጣራት በቤተሰብ ህጉ በምዔራፍ 5 የተደነገጉት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ተመልክቷል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለውም የጋብቻ ንብረት ማጣራትና ክፍፍል ጉዲይ የቤተሰብ ህጉን ድንጋጌዎች በጥብቅ ተከትል ሉፈፀም የሚገባ ስለመሆኑ ነው።
በተያዘው ጉዲይ በግራቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ቀሪ ሆኖ የፍች ውጤት በሆነው የጋብቻ ንብረት ክፍፍል ጉዲይ ረዥም ጊዜ የወሰደና የተለያየ መልክ የያዘ ክርክር በመካሓድ ላይ የሚገኝ መሆኑ ግራ ቀኙን የሚያከራክር አይደለም። አስቀርበን የተመለከትነው የፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የኮ/መ/ የጋብቻ ንብረት ክርክሩ በሂደት ላይ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
የአመልካች ቀዲሚ የዲኝነት ጥያቄም የጋብቻ ንብረት ተጣርቶ ድርሻቸው እንዱከፈል ሲሆን በተለይም የማህበር ድርሻ የመብት ጥያቄን በተመለከተ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች የዔግድ ትዕዛዝ ሲሰጥበት የቆየና የማጣራቱ አካል ሆኖ መኖሩን ከመዝገቡ መረዲት ይቻላል።
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ኮንሶለሽን ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሆነውን ንብረት ጉዲይ አብረው ማቅረብ እየቻለ ቀንሰው አስቀርተዋል ስለሆነም አቤቱታቸው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 216 አንፃር ተቀባይነት የለውም በማለት የደረሱበት መደምደሚያ እና ያሳለፈት ብይንና ትዕዛዝ ግራ ቀኙ እያደረጉት ያለውን የንብረት ክርክር እና የጋብቻ ንብረትን ስለማጣራት በቤተሰብ ህጉ የተዘረጋው ስርዓት ስርዓት የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል ተጠሪ ባቀረቡት መልስ የአመልካች የድርሻ መጠን የ160 አክስዮኖች ግማሽ 80 አክስዮኖች ብቻ መሆኑን፤ ከትዲር መፍረስ በኋላ ተጠሪ የግል ገንዘባቸውን በመጨመር ያሳደጉት አክስዮን መኖሩን፤ በቤተሰብ አባላት በተያዘ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ውስጥ አመልካች አባል ሉሆኑ እንደማይገባ፤ እንዱሁም አመልካች በትዲር ዘመን ያላፈሩትን እና የላለውን 11,350 አክስዮኖች ልካፈል፣ ትርፍም በዚሁ መጠን ይከፈለኝ በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ሉኖረው እንደማይገባ ተከራክረዋል። ነገር ግን በተጠሪ የተጠቀሱት እነዚህ መከራከሪያዎች ከመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በኋላ የሚታዩ ፍሬ ጉዲዩን የተመለከቱ በመሆናቸውና በዚህ ረገድ በስር ፍርድ ቤቶች ተሰጠ ውሳኔ ባለመኖሩ ከወዱሁ የምንመለከተው አይሆንም ።
በአጠቃላይ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ብይንና ትዕዛዝ ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ህጎች እና የግራ ቀኙን ክርክር ሂደት ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም በማለት ተከታዩን ወስነናል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 18/10/2011 ዓ.ም እንዱሁም የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 24/11/2012 ዓ.ም የሰጡት ብይንና ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የፍሬ ነገር ክርክር ተመልክቶ ተገቢውን እንዱወስን ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 341(1) መሰረት መልሰናል። ይጻፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
እግድ ተነስቷል ይጻፍ። የሥር ፍ/ቤት መዝገብ ይመለስ።
አ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.