No summary available.
የሰበር መዝገብ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነዓ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- አቶ ሙለጌታ ዘውደ፡- ከጠበቃ ሲሳይ ወርቅነህ ጋር ቀርቧል ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ወ/ሮ ሄለን ደረሰ፡- ከጠበቃ የኋላወርቅ ተከተለው ጋር ቀርቧል 2ኛ. ወ/ሮ ፍቅርተ ደረሰ፡- ጠበቃ መስፍን ጫኔ - ቀርቧል 3ኛ. በየካ ክፍለ ከተማ ወረዲ 8 አስተዲደር ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ቅ/ጽ/ቤት 4ኛ. በየካ ክፍለ ከተማ ወረዲ 8 ቤቶች አስተዲደር ጽ/ቤት አልቀረቡም ለምርመራ ተቀጥሮ የነበረው መዝገብ ተመርምሮ ቀጣዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
አከራካሪው ሱቅ በሥጦታ የተገኘ ሳይሆን ከ4ኛ ተጠሪ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በኪራይ ያገኙት ሆኖእያለ፤ የስጦታ ውል ተብል የቀረበው ሰነድም በቤቱ ማኅደር ውስጥ የላለ ፤ ውለም በሕግ የተመለከተውን ፍርም የማያሟላ በሰነድች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ጽ/ቤት ያልተደረገ በተንኮል የተዘጋጀ የመንደር ውል በመሆኑ ዋጋ የላለው መሆኑን ፤ ዋጋ አለው ቢባል እንኳን አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በጋብቻ ውስጥ እያለ የባልና ሚስት የጋራ በሆነ ንብረት ላይ 1ኛ ተጠሪ ለብቻቸው ያደረጉት የስጦታ ውለ የማይፀና መሆኑና የስጦታ ውለም ለ1ኛ ተጠሪ በግል የተደረገላቸው መሆኑን ስለማይገልጽ በሕጉ የጋራ ንብረት እንደሆነ ይገመታል በማለት አመልካች ያቀረቡት ክርክር በጭብጥነት ሳይመረመር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔን መሻሩ የቤተሰብ ሕጉን አንቀጽ 63 እና የሕገ - መንግስቱን አንቀጽ 34(1) የሚቃረንና 1ኛ ተጠሪ ጋብቻ ከመፈፀማቸው በፉት ያወጡትን ያላገባ የምስክር ወረቀት በሀሰተኛ የቃለ - መሐላ አቤቱታ በማሳደስ የፈፀሙት ድርጊት ሕገ - ወጥነትን የሚያበረታታ መሆኑን፤ የሥጦታ ውለ በአራት ምስክሮች ፉት ባለመነበቡ፤ ውለን የፈረሙት ምስክሮችም ሁለት ብቻ በመሆናቸው እና ወ/ሮ ሃና ታደሰ የሥጦታ ውለን በፈረሙበት ጊዜ በቤቱ ላይ መብት የነበራቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ባለመቅረቡ ውለ ፈራሽ ነው በማለት አመልካች ያቀረቡት ክርክር ታልፍ ሱቁ የ1ኛ ተጠሪ የግል ንብረት ነው ተብል መወሰኑ ፤ 2ኛ ተጠሪም ጋብቻ የፈፀመችው እህታቸው የሆነችው 1ኛ ተጠሪ ጋብቻ ፈጽማም እንደማታውቅ ያላገባ የምስክር ወረቀት አውጥታ ሱቁን ስትሸጥላቸው የቅን ልቦና ገዥ ናቸው ተብለው የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው ችልት መሻሩ እና የሰበር ሰሚ ችልቱም ውሳኔውን ማጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ስህተቱ ታርሞ የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ እንዱፀናላቸው አመልካች የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ/ም ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻነት መዝገቡ ለችልት ቀርቧል።
ጉዲዩ የባልና ሚስት የጋብቻ ፍቺን ተከትል የቀረበ የንብረት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን፤ ለሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነውን የመንግስት ሱቅ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በትዲር ውስጥ እያለ በኪራይ የተገኘ ነው በማለት አመልካች ከላልች የባልና ሚስት ንብረቶች ጋር ያቀረቡትን የክፍፍል ጥያቄ የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የፍርድ ቤት አይደለም በማለቱ አመልካች በተጠሪዎች ላይ በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችልት ባቀረቡት ክስ፤ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዲ 8 ቁጥሩ 249/124 የሆነው የቀበላ ንግድ ሱቅ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ጋር የተከራዩ ቢሆንም የግራ ቀኙ ጋብቻ ታህሳስ 29 ቀን 2006 ዓ/ም በፍቺ ውሳኔ መፍረሱን ገልፀው 1ኛ ተጠሪ 3ኛ ተጠሪን በማሳሳት ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ/ም ያላገባ የምስክር ወረቀት በመውሰድ የጋራቸው የሆነውን የቀበላ ንግድ ሱቅ ለ2ኛ ተጠሪ በሰነድች እና ምዝገባ ጽ/ቤት በተደረገ የሽያጭ ውል ያስተላለፈ በመሆኑ፤ 4ኛ ተጠሪ የኪራይ ውለን እንዱሁም 3ኛ ተጠሪም ያለአግባብ የሰጠውን ያላገባ የምስክር ወረቀት እንዱሰርዝ አቤቱታ ቢያቀርቡም ባለመሰረዙ፤ በተጭበረበረ መንገድ የወጣው ያላገባ የምስክር ወረቀት እንዱሁም 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ያደረጉት ጋራ ንብረት ሽያጭ ውል ተሰርዞ 3ኛ ተጠሪ ሱቀን አካፍል ከአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ጋር የኪራይ ውል እንዱያደርግ ከወጪ እና ኪሳራ ጋር እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል።
1ኛ ተጠሪም በመልሳቸው አመልካች ያቀረቡት ክስ አስተዲደራዊ ጉዲይ በመሆኑ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን የላለው መሆኑን፤ ክሱ በይርጋ የሚታገድ መሆኑ እና ጉዲዩ ውሳኔ ያገኘ መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት አንስተው በፍሬ ነገር ክርክራቸውም የቀበላ ንግድ ቤቱ የወ/ሮ ልሚናት ወ/ፃዱቅ የነበረ ሲሆን እሳቸው የ1ኛ ተጠሪ እህት ለነበሩት ወ/ሮ ሃና ታደሰ አስተላልፈው ከወ/ሮ ሃና ታደሰ በስጦታ ያገኙት የግል ንብረት በመሆኑና 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበራቸው ትዲር ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ/ም ከፈረሰ በኋላ ያላገባ የምስክር ወረቀት አውጥተው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያደረጉት ሕጋዊ የሱቅ ሽያጭ ውል የሚፈርስበት ምክንያት ባለመኖሩ አመልካች ያቀረቡት ክስ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል። 2ኛ ተጠሪም ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው መቃወሚያን በማስቀድም በፍሬ ነገር መልሳቸው ሱቁን የገዙት 1ኛ ተጠሪ ትዲር የላላት መሆኑ ተረጋግጦ በመሆኑ ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም የተደረገው የሽያጭ ውል የሚፈርስበት ምክንያት የለም የሚል ክርክር አቅርበዋል። በአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ መካከል የነበረው ትዲር ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ/ም ከመፍረሱ በፉት 2ኛ ተጠሪ ህዲር 19 ቀን 2011 ዓ/ም ያላገባ የምሰክር ወረቀት እንዱሰጣቸው በቃለ መሃላ የተደገፈ አቤቱታ አቅርበው ትዲራቸው ከፈረሰ በኋላ ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ/ም የወሰደትን ምስክር ወረቀት እንዱመልሱ በደብዲቤ የተገለፀላቸው መሆኑ ፤ ክርክር ያስነሳው የቀበላ ንግድ ቤት የኪራይ ውለ በ1ኛ ተጠሪ ስም ብቻ በመሆኑና ያላገባ የምስክር ወረቀት በማቅረባቸው በመመሪያ ቁጥር 4/2009 አንቀጽ 24 መሰረት የተከራይነት መብቱ ለ2ኛ ተጠሪ የተላለፈ በመሆኑ 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች መመሪያው ከሚፈቅደው ውጭ የሰጡት አገልግልት ባለመኖሩ እና ሥራቸውን በአግባቡ ስለሰሩ ልንከሰስ አይገባም በማለት መልስ ሰጥተዋል።
ፍርድ ቤቱም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ ፤ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶ መዝገቡን እንደመረምረው 1ኛ ተጠሪ በትዲር ውስጥ እያለች የቀበላ ንግድ ቤት በስጦታ ውል አግኝታ በትዲር ውስጥ እያለች የኪራይ ውል የተዋዋለች መሆኑ፤ የግራ ቀኙ ትዲር ከመፍረሱ ስድስት ቀን አስቀድሞ ያላገባ የምስክር ወረቀት ለማግኘት የቃለ መሃላ አቤቱታ አቅርባ ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ/ም ያላገባ የምስክር ወረቀት የወሰደች መሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር መሆኑን ገልጾ ፤ 1ኛ ተጠሪ የፍቺ ውሳኔ ከመሰጠቱ ስድስት ቀን አስቀድሞ ያላገባ የምስክር ወረቀት ለማግኘት ማመልከቻ አቅርባ ከሕግ ውጭ የወሰደችውን ያለላባ የምስክር ወረቀት በመጠቀም ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ የሽያጭ ውል ለ2ኛ ተጠሪ ሱቁን ማስተላለፎን ከቀረበው የሰነድ ማስረጃ ግንዛቤ መወሰደን ግልፆ ፤ 3ኛ ተጠሪ ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ/ም ለ1ኛ ተጠሪ የሰጠው ያላገባ የምስክር ወረቀት ሕጉን ጠብቆ የተሰጠ ባለመሆኑ እንዱሰረዝ፤ 1ኛ ተጠሪ የኪራይ ውለን የተዋዋለችው በ2008 ዓ/ም ከአመልካች ጋር በትዲር ውስጥ እያለች ሆኖ የአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ትዲር የፈረሰው ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ/ም በመሆኑ በመመሪያ ቁጥር 5/2011 አንቀጽ 40(1) መሰረት የአመልካችና 1ኛ ተጠሪ ትዲር ከፈረሰ በኋላ ክርክር የተነሳበት ቁጥሩ 249/124 የሆነው የቀበላ ንግድ ሱቅ ለአመልካች እና ለ1ኛ ተጠሪ የሚካፈል በመሆኑ ከሕጉ ወጭ የሆነውን ያላገባ የምስክር ወረቀት መሰረት በማድረግ በ1ኛ ተጠሪ እና 2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገው ውል ህጋዊ ባለመሆኑ 4ኛ ተጠሪ ክርክር የተነሳበትን የቀበላ ንግድ ቤት ለአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ አካፍል የኪራይ ውል ሉይዝ ይገባል በማለት ወስኗል።
ይህን ውሳኔ በመቃወም 1ኛ ተጠሪ የንግድ መደብሩ የባልና ሚስቱ የጋራ ሳይሆን የግል ንብረታቸው ለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ የንግድ መደብሩ የሽያጭ ውል ሕጋዊ አይደለም መባለ፤ 2ኛ ተጠሪ ሱቁን የገዙት በአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ መፍረሱንና የሽያጭ ውለ በተፈጸመበት ጊዜ ጋብቻ የላላትና ያላገባ የምስክር ወረቀት ያወጣች መሆኑ እንዱሁም የንግድ መደብሩን 1ኛ ተጠሪ በግል ከእናቷ የተሰጣት መሆኑን በማረጋገጥ ከአንድ ጠንቃቃ እና ምክንያታዊ ገዥ የሚጠበቀውን ጥንቃቄ በማድረግ በቅን ልቦና በሰነድች ማረጋገጫ ምዝገባ ጽ/ቤት የተደረገው የመደብር ግዥ ውል እንዱፈረስ መወሰኑ አግባብ አይደለም በማለት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በተለያየ መዝገብ ያቀረቡትን የይግባኝ ቅሬታ አጣምሮ የተመለከተው የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሁለተኛ ይግባኝ ሰሚው ችልት፤ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለውሳኔ መሰረት ያደረገው አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በትዲር ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ክርክር የተነሳበት የቀበላ ንግድ ቤት በ2008 ዓ/ም 1ኛ ተጠሪ የኪራይ ውል የተዋዋለ በመሆኑ እና ትዲራቸውም የፈረሰው ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ/ም በመሆኑ በመመሪያ ቁጥር 5/2011 አንቀጽ 40(1) መሰረት ትዲር በፍቺ ውሳኔ ሲፈርስ ቤቱ እንደሚከፊፈል ስለሚደነግግ በሚል ቢሆንም፤ የንግድ መደብሩን አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በውል ከ3ኛ ተጠሪ ያገኙት ሳይሆን የ1ኛ ተጠሪ እህት የሆኑት ወ/ሮ ሃና ታደሰ ሲጠቀሙበት ቆይተው 1ኛ ተጠሪ በትዲር ውስጥ እያለ አመልካችን ሳይጨምር በግላቸው በስጦታ ያገኙ መሆኑን ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም የተደረገ የንግድ ድርጅት የስጦታ ውለ እንደሚያመለክት እና አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የነበራቸው ትዲር ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ/ም ከፈረሰ በኋላ ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም የንግድ መደብር ሽያጭ ውል በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች መካከል መደረጉን ገልፆ፤ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር የንግድ መደብሩ ያገኙ መሆኑን ባላስረደበት የአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ትዲር ከፈረሰ በኋላ የተደረገው የሽያጭ ውል ፈርሶ የንግድ ቤቱን እንዱካፈለ የሥር ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዲሜ አግባብ አለመሆኑን፤
እንዱሁም 1ኛ ተጠሪ በግል በስጦታ ያገኙት መደብር በትዲር ውስጥ ሆነውም ይሁን ከፍቺ በኋላ በግላቸው እንዲያስተላልፈ የሚከለክላቸው ሕግ ካለመኖሩም በላይ የሽጭ ውለ የሕግ ጥሰት የተፈፀመበት ነው ቢባል እንኳን 2ኛ ተጠሪ ካላቸው የዝምድና ቅርበት አኳያ በአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ መካከል የጋብቻ ፍቺ ማድረጋቸውን ተረድተው ግዥ መፈፀማቸው አንድ ጠንቃቃ ገዥ መፈፀም ያለበትን ጥንቃቄ ማድረጋቸውን ያሳያል በማለት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሽሯል።
አመልካች በውሳኔው ባለመስማማት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ አከራካሪው የንግድ መደብር ለ2ኛ ተጠሪ ከመተላለፈ በፉት የ1ኛ ተጠሪ የግል ንብረት ወይንም የአመልካች እና የ1ኛ ተጠሪ የጋራ ንብረት መሆን አለመሆኑን በጭብጥነት ይዞ የቤቱን ማህዲር በማስቀረብ የመረመረው የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት፡- ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ንግድ ቤት የቀድሞ ተከራይ ወ/ሮ ልሚናት ወ/ፃዱቅ ወ/ጊዮርጊስ መመሪያ ቁጥር 4/2009 ከመውጣቱ በፉት ቤቱን በሽያጭ ለወ/ሮ ሃና ታደሰ አስተላልፈው ከህዲር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ በወ/ሮ ሃና ታደሰ በስማቸው የኪራይ ውል ተዋውለው ቤቱን ሲጠቀሙበት ከቆዩ በኋላ ታህሳስ 1 ቀን 2008 ዓ/ም በተፃፈ የንግድ ስጦታ ውል የንግድ ቤቱ (መደብሩ) ለ1ኛ ተጠሪ ብቻ ተላልፍላቸው የኪራይ ውል ተዋውለው ቤቱን ይዘው ሲጠቀሙበት ከቆዩ በኋላ ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ የንግድ መደብር ሽያጭ ውል ለ2ኛ ተጠሪ ተላልፍ 4ኛ ተጠሪም በወቅቱ በሥራ ላይ በነበረው መመሪያ ቁጥር 4/2009 መሰረት የንግድ ቤቱን የኪራይ ውል ከ1ኛ ተጠሪ ስም ወደ 2ኛ ተጠሪ ስም አዙሮ 2ኛ ተጠሪ እየተጠቀሙበት የሚገኙ መሆኑ መረጋገጡን ጠቅሶ ፤ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የንግድ ቤት አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የተከራዩት ሳይሆን 1ኛ ተጠሪ በስጦታ ያገኙት የንግድ መደብር መሆኑን፤ አመልካች የንግድ መደብሩን ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በጋራ ያገኙ ለመሆኑ ያቀረቡት ክርክርም ሆነ ማስረጃ ባለመኖሩ የንግድ መደብሩ ወደ 2ኛ ተጠሪ ከመተላለፈ በፉት የአመልካች እና የ1ኛ ተጠሪ የጋራ ንብረት ሳይሆን የ1ኛ ተጠሪ የግል ንብረት በመሆኑ፤ 1ኛ ተጠሪ በግል በስጦታ ያገኙትን የንግድ መደብር በጋብቻ ውስጥ ሆነውም ይሁን ከፍቺ በኋላ በህጉ አግባብ በሽያጭ ማስተለላፍን የማይከለከለ በመሆኑ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም በማለት ወስኗል።
አመልካች የሥር የአዱስ አበባ ከተማ የሰበር ሰሚው እና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት ያቀረቡትን በፍርደ መግቢያ ላይ የተመለከተውን የሰበር አቤቱታ የመረመረው የሰበር አጣሪ ችልቱ ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው የንግድ ሱቅ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በጋብቻ ውስጥ እያለ 1ኛ ተጠሪ ከቀበላ መከራየታቸው ፤ 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በትዲር ውስጥ እያለ 3ኛ ተጠሪን በማሳሳት ያላገባ የምስክር ወረቀት ወስደው አከራካሪውን ሱቅ እህታቸው ለሆኑት 2ኛ ተጠሪ በሽያጭ ማስተላለፊቸውን አረጋግጦ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ እንዱከፊፈለ በማለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በበላይ ፍርድ ቤቶች የመሻሩን አግባብነት መጣራት አለበት በማለቱ የፍርድ ቤቱ መጥሪ ለተጠሪዎች ድርሶ መልስ ሰጥተዋል። 1ኛ ተጠሪ በመልሳቸው አከራካሪውን የንግድ መደብር ከመንግስት የተከራዩት ሳይሆን በስጦታ ያገኙት የግል ሀብታቸው መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ሱቁን (መደብሩን) ከቀበላ ተከራይቷል የሚለው የአመልካች ክርክር በማስረጃ አለመረጋገጡን ፤ በወ/ሮ ሃና ታደሰ እና 1ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገው የስጦታ ውል በሕጉ የተመለከተውን ፍርማሉት የሚያሟላ ባለመሆኑ አይፀናም የሚለው የአመልካች ክርክር በሥር ፍርድ ቤት ያልተነሳ በመሆኑ በሰበር ደረጃ መነሳቱ ሥነ ሥርዓታዊ አለመሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ክርከሩ የንግድ መደብር ሽያጭ ውል በመሆኑና በንግድ መደብር ላይ የሚደረገው የስጦታ ውል በጽሐፍ ከመደረጉ በቀር ላላ የተለየ ፍርማሉትን ስለማይጠይቅ እና የፍትሐ ብሓር ሕጉ ድንጋጌዎችም ለጉዲዩ አግባብነት የላላቸው መሆኑን ፤ የአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ጋብቻ ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ/ም ከፈረሰ በኋላ 1ኛ ተጠሪ ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ/ም ያላገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ወስደው ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም የሽያጭ ውል የፈፀሙ ሲሆን ፤ በቃላ መሃላ የተወሰደ ያላገባ ምስክር ወረቀት ካለመኖሩም በላይ ተወስዶል ቢባል እንኳን ማስረጃውን ከማሰረዝ ባለፈ የግል ንብረታቸው ላይ ተደረገው የሽያጭ ውል ፈርሶ በንብረቱ ላይ ምንም መብት የላለው ሰው ንብረቱን እንዱካፈል የማደረግ ውጤት የላለው መሆኑን፤ አመልካች የንግድ መደብሩ በጋራ ተሰጥቶናል የሚል ክርክር በሥር ፍርድ አለመቅረቡ እንደተጠበቀ ሆኖ መደብሩ የ1ኛ ተጠሪ የግል ንብረት መሆኑ፤ የክራይ ውለም በ1ኛ ተጠሪ ስም ብቻ በመሆኑ የንግድ መደብር ሽያጭ እና የተከራይነት መብቱ ሉተላለፍ የሚችል መሆኑ ተረጋግጦ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈፀመበት ነው በማለት ለሰበር ቅሬታው መነሻ የሆነው ውሳኔ እንዱፀናላቸው ጠይቀዋል።
2ኛ ተጠሪ ለሰበር አቤቱታው በሰጡት መልስ፡- አመልካች 2ኛ ተጠሪ የንግድ መደብሩን ሲገዙ ተገቢውን ጥንቃቄ አለማድረጋቸውን፤ የንግድ መደብሩ ከአመልካች ጋር በጋራ የተሰጣቸው መሆኑ፤ የስጦታ ውለን ህጋዊነትና ፍርማሉትን በተመለከተ እንዱሁም የስጦታ ውለ ለዚህ ክርክር ተብል በተንኮል የተዘጋጀ ነው የሚለው ክርክር በሥር ፍርድ ቤት ስላልተነሳ በፍትሐ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 329(1) መሰረት ውድቅ እንዱሆን ፤ የንግድ መደብሩ ግዥ የተፈፀሙት መደብሩን 1ኛ ተጠሪ በስጦታ ያገኙት የግል ንብረታቸው መሆኑን የስጦታ ውለን በማየት የአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ጋብቻ ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ/ም ከፈረሰ በኋላ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን ያላገባ ማስረጃ አይተው ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ/ም በሰነድችና ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት በመገኘት ተገቢውን ጥንቃቄ ያደረጉ የቅን ልቦና ገዥ መሆናቸውን አረጋግጦ የንግድ መደብሩ የሚከናወንበት ቤት ባለቤት መንግስት በመሆኑ የተከራይነት መብቱ በንግድ መደብሩ ላይ የሚካሄደውን ግብይት የሚከተል በመሆኑ የተሰጠው ውሳኔ የፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 1162(1) ፤ የንግድ ሕጉ ቁጥር 124, 151 (1) (ሀ) እና 152 ድንጋጌዎችንና በሰበር መዝገብ ላይ የተሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ ባለመሆኑ ለሰበር ቅሬታው መሰረት የሆነው ውሳኔ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች በጋራ በሰጡት መልስ ለ1ኛ ተጠሪ ያላገባ የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው በቤተሰብ ቅጽ ላይ ያላገቡ በመሆኑና እሳቸውም ያላገቡ መሆኑን በቃለ መሃላ በማረጋገጣቸው ለጉዲዩ አግባብነት ካለው መመሪያ አንፃር ሕገ ወጥ ተግባር ያልፈፀሙ መሆኑንና አመልካች ቅሬታቸውን ካቀረቡ በኋላ 1ኛ ተጠሪ የወሰደትን ያላገባ የምስክር ወረቀት እንዱመልሱ የጠየቁ ሲሆን ፤ የቤቱ የኪራይ ውለ በ1ኛ ተጠሪ ስም በመሆኑና 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት ያላገባ ምስክር ወረቀት ታይቶ በወቅቱ በሥራ ላይ ያለው መመሪያ በሚፈቅደው መሰረት 1ኛ ተጠሪ በተከራዩት የመንግስት ንግድ ቤት ውስጥ የሚገኘውን የንግድ መደብር በፋደራል ሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንስ ጽ/ቤት ለ2ኛ ተጠሪ የንግድ መደብሩን የሸጡላቸው ስለሆነ መመሪያው ከሚፈቅደው ውጭ 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ለ1ኛ ተጠሪ የሰጡት አገልግልት የላለ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚነቀፍበት አግባብ የለውም በማለት ተከራክረዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ለሰበር ቅሬታው ምክንያት የሆነው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን ከፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የተከራከሩበትን መዝገብ በትዕዛዝ በማስመጣት እንደሚከተለው መርምሮታል።
የባልና ሚሰት ንብረት ክርክር በተደረገበት የመዝገብ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ/ም በተሰጠው ውሳኔ አከራካሪው የቤት ቁጥር 249/124 የ3ኛ ወገን በመሆኑ የቀረበው የክፍፍል ጥያቄ የሕግ መሰረት የላለው ከመሆኑም በላይ ተከራይ የመሆን ጥያቄም መቅረብ ያለበት ለፍርድ ቤት ሳይሆን ጉዲዩን ለሚመለከተው የከተማ አስተዲደር ጽ/ቤት በመሆኑ አከራካሪውን ቤት አስመልክቶ ክፍፍልም ሆነ ኪራዩን በሚመለከት አስተዲደራዊ በሆነ ጉዲይ ላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱሰጥ አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ የሕግ መሰረት የለውም በማለት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ አመልካች አከራካሪውን ቤት በተመለከተ ያቀረቡትን ክስ ውድቅ ካደረገው በኋላ አመልካች አዱስ ክስ ለአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት አቅርበው ለሰበር ክርክሩ ምክንት የሆነው ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን ለመረዲት ተችሎል።
የንግድ መደብር የንግድ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያገለግለ የሚንቀሳቀሱ ንብረቾችን ሁለ የሚመለከት መሆኑን ፤ በሽያጭም ሆነ በልላ በማንኛውም ውል ሉተላለፍ እንደሚችል ፤ ሽያጩን በሚመለከት የፍትሐ ብሓር ሕጉ ቁጥር 2266 እስከ 2367 ያለት ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ያላቸው መሆኑን የቀድሞው የንግድ ሕግ ቁጥር 124 ,150 እና 151 ድንጋጌዎች መመልከት ይቻላል።
በተያዘው ጉዲይ በ1ኛ ተጠሪ እና 2ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገው የንግድ መደብር ሽያጭ መሆኑ፤
መደብሩን 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በትዲር ውስጥ እያለ በግላቸው በስጦታ አግኝተው በቀበላ ንግድ ቤቱ ላይ ከ4ኛ ተጠሪ ጋር ውል ገብተው ሲጠቀሙበት ቆይተው የአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ጋብቻ ህዲር 25 ቀን 2011 ዓ/ም ከፈረሰ በኋላ ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ የንግድ መደብር ሽያጭ ውል ለ2ኛ ተጠሪ ተላልፍ 4ኛ ተጠሪም በወቅቱ በሥራ ላይ በነበረው መመሪያ ቁጥር 4/2009 መሰረት የንግድ ቤቱን የኪራይ ውል ከ1ኛ ተጠሪ ስም ወደ 2ኛ ተጠሪ ስም አዙሮ 2ኛ ተጠሪ እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ በፍሬ ነገር ደረጃ መረጋገጡን የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ፍርድ ያመለክታል። አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩ አስተዲደራዊ በመሆኑ በፍርድ ቤት ላታይ የሚችል አይደለም በማለት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ በመሆኑ ጉዲዩ ዲግም መታየት የለበትም በማለት ያቀረበው መቃወሚያ ታልፍ ወደ ፍሬ ነገር ክርክር መገባቱ አግባብ ባይሆንም ከዚህ አንፃር ተጠሪዎች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 340 መሰረት የቀረበ አቤቱታ ባለመኖሩ በሰበር ሰሚ ችልቱ የሚታይ አይደለም። 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በትዲር ውስጥ እያለ በግላቸው በስጦታ ያገኙት የንግድ መደብር ባለሀብት የሆኑበትን ንብረት ለ2ኛ ተጠሪ ማስተላለፊቸው የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 57 ፤ የፍትሐ ብሓር ሕጉን ቁጥር 1204 ፤ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የቤቶች ልማት አስተዲደር ቢሮ የመንግስት ቤቶች አስተዲደር መመሪያ ቁጥር 4/2009 ቁጥር 24(ረ) እና የንግድ ሕጉን ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር አመልካች ካቀረቡት ቅሬታ አንፃር ሲታይ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት ስላልተቻለ ቀጣዩ ተወስኗል።
የአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚው ችልት በመዝገብ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችልት ሁለተኛ ይግባኝ ሰሚው ችልት በመዝገብ መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል ።
በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የግላቸውን ይቻለ።
የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ በመጣበት አኳን ይመለስ።
No topics extracted.