No summary available.
ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር) ቀነአ ቂጣታ ፈይሳ ወርቁ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው አመልካች፡- ከበደ ተፈራ - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- 1ኛ. መሬማ እሸቴ የ2ኛ ተጠሪ ወኪል ታደሰ ሁሴን እና 3ኛ ተጠሪ ቀረቡ 2ኛ. ጸጋ ተፈራ 3ኛ. የማነ ገ/ክርስቶስ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች በቀን 16/04/2013 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 08/07/2012 ዓ.ም፤ የደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ 1407 በቀን 17/02/2013 ዓ.ም እንዱሁም የአ/ብ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ በመ/1 በቀን 02/04/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ በደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር የአሁን አመልካች መልስ ሰጭ፤ የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ አመልካች ነበሩ።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው የአሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ የሟች አቶ ተፈራ መልካ ወራሽ መሆናቸውን ገልፀው ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) የእኔ የሚለው ቤተሰብ እና አሳዲጊ ስላልነበረው ከህጻንነቱ ጀምሮ ሟች አቶ ተፈራ መልካ በበጎ አድራጊነት መንፈስ ተቀብል በቤት ውስጥ ከልጆቹ ጋር ስላሳደገው ብቻ እስካሁን ድረስ በአካባቢው ሰው ከበደ ተፈራ እየተባለ የሚጠራ ቢሆንም የሟች ልጅ አይደለም፤ ከአብራኩም አይወለድም፤ የተጠሪው ትክክለኛ ስሙ ከበደ ዲምጠው ነው፤ ስለሆነም ተከሳሽ ከፍ/ቤቱ በመ/ የወሰደው የወራሽነት ሰርተፍኬት ማስረጃ እንዱሰረዝልን በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁን አመልካች በበኩላቸው በቀን 11/06/2012 ዓ.ም በሰጡት መልስ ከሟች አብራክ የተወለደ ልጅ አይደለም የሚለው አቤቱታ እውነት ነው፤ የሚካድም አይደለም፤ ይሁን እንጂ ከሟች በመወለድ የተገኘሁ ልጅ ነኝ የሚል አቤቱታ አቅርቤ የስጋ ልጅነት ማስረጃ አላወጣሁም፤በዚህ ረገድ የቀረበው ክስ ሀሰት ነው፤ ከሳሾች በክሳቸው ላይ በግልጽ እንዲመኑት ከክሱ ጋር ተያይዞ የቀረበው የህጋዊ የጉዱፈቻ ውል መሰረት ሟች ከመንግስት ጋር ባደረጉት ስምምነት ከሆስፑታል ተቀብለው በህግ ልጅነት ያሳደጉኝ የጉዱፈቻ ልጅ ነኝ። በህጋዊ መንገድ የሟች የጉዱፈቻ ልጅ መሆኔ ከታመነ በፍ/ህ/ቁ 836 ድንጋጌ መሰረት ህጋዊ ልጅ (የጉዱፈቻ) ልጅ የአሳዲጊው ህጋዊ ወራሽ እንደሆነ እና በውርስ ድርሻ ክፍፍልም ላይ ምንም አይነት ልዩነት እንደማይደረግበት የተደነገገ በመሆኑ እንደ ሟች ተወላጅ የሚቆጠር ነው እንዱባልልኝ እና የወራሽነት ምስክር ወረቀቱ ሉሻር አይገባም ተብል እንዱወሰንልኝ በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት ክርክሩንና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ውሳኔ ሰጥቷል። በሰጠው ውሳኔ በግራ ቀኙ የጋራ ማስረጃ ይሆናል የተባለው የሰነድ ማስረጃ ሲታይ ለሟች አቶ ተፈራ መልካ በቁጥር 61/58 በቀን ህዲር 7/1958 ዓ.ም በደሴ ማዘጋጃ ቤት በኩል የተጻፈ ሲሆን እናቱ የሞተችበትና ላላም የቅርብ ዘመድ አጥቶ ለጊዜው በሆስፑታል የሚገኘውን ከበደ ዲምጠው የተባለውን ልጅ ወስደው ለማሳደግ ፈቃደኛ ስለሆኑ ለላልች በጎ አድራጊዎች ተቀዲሚ ምሳላ ያሳዩ መሆኑን እና ልጁንም በማዘጋጃ ቤቱ አማካኝነት መረከባቸውን ማስረጃ ይሆን ዘንድ ይህን ደብዲቤ ከምስጋና ጋር እናቀርብልዎታለን የሚል ነው። ይህ በበጎ አድራጊነታቸው ለሟች ተፈራ መልካ የተሰጣቸው የምስጋና ደብዲቤ ከፍ/ህጉ እና ከክልለ የቤተሰብ ህግ እንዱሁም በፋደራል የቤተሰብ ህግ የጉዱፈቻ ልጅነት የህግ ድንጋጌዎች አንጻር ሲታይ የጉዱፈቻ ልጅነት ሉያስገኙ የሚችለ የህጉን ሁኔታዎች የማያሟላ ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከሳሽ በፍ/ህ/ቁ 836 መሰረት የሟች የህግ ልጅ እና ወራሽ ለመሆን የሚያስችለው በፍ/ቤት የጸደቀ የጉዱፈቻ ልጅነት የውል ስምምነት ማስረጃ በላለበት ሁኔታ ከዚሁ ፍ/ቤት ህጋዊ ልጅ ነኝ በማለት በመ//012 በቀን 21/02/2012 ዓ.ም የተሰጠው የወራሽነት ሰርተፍኬት ማስረጃ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም። ጉዲዩን በምስክር ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑም ምስክር መሰማቱ አስፈላጊ አይደለም። ስለሆነም ተከሳሽ የወሰደው የወራሽነት ሰርተፍኬት ማስረጃ አላግባብ ሆኖ ስለተገኘ በፍ/ህ/ቁ 998(1) መሰረት ተሰርዟል፤ ማስረጃውን ሉመልስ ይገባል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ቅሬታቸውን ለደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እንዱሁም ለአ/ብ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር አጣሪ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት የሰበር አቤቱታው ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው በዚህ ነው።
አመልካች በቀን 16/04/2013 ዓ/ም ባቀረቡት ማመልከቻ በስር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በግልጽ የተጠየቀው ዲኝነት አመልካች የሟች በበጎ አድራጎት መንፈስ ያሳደገው ልጅ ሆኖ ሳለ ተወላጅ ልጅ እንደሆነ አድርጎ ያወጣው የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዝልን የሚል ሲሆን በእኔ በኩል የተሰጠው መልስም እርግጥ ነው አመልካች የሟች ተወላጅ ልጅ አይደለሁም እኔም የሟች ተወላጅ ልጅ ነኝ ብዬ ማስረጃ አላወጣሁም ያወጣሁት ማስረጃ የሟች የጉዱፈቻ ልጅ ስለሆንኩ በፍ/ህ/ቁ 836 መሰረት የሟች ወራሽ ነኝ በሚል ነው፤ የጉዱፈቻ ልጅ መሆኔንም ራሳቸው ባቀረቡት ክስና የሰነድ ማስረጃ አምነው የቀረቡ በመሆኑ የጉዱፈቻ ልጅ እንደ ተወላጅ ልጅ ሉወርስ አይገባም የሚለው ክርክር የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ውድቅ ይደረግልኝ የሚል ሆኖ ፍ/ቤቱ የሰጠው ውሳኔ በተጠሪዎች ከተጠየቀው ዲኝነትና በሰበር አመልካች ከቀረበው መልስ አንጻር ከክርክሩ አውድ ውጭ በተያዘ ጭብጥ ላይ ተመስርቶ ተከራካሪዎች ባላነሱት መከራከሪያ ተመስርቶ የተሰጠ ውሳኔ ነው፣ የስር ፍ/ቤት በቁጥር 61/58 በቀን ህዲር 17/1958 ዓ.ም ተያይዞ የቀረበውን ማስረጃ በተመለከተ የጉዱፈቻ ማስረጃ ሳሆን የምስጋና ወረቀት ነው ሲል የደረሰበት ድምዲሜና ውድቅ ያደረገበት አግባብ በወቅቱ የነበረውን የመንግስት አሰራር ግምት ውስጥ ያላስገባና የማስረጃውን ይዘትም በአግባቡ ያልመረመረበት ነው፤ በመሰረቱ በህግ በልዩ ሁኔታ በተለየ ማስረጃ እንዱረጋገጥ በህግ የተደነገገ ካልሆነ በቀር አንድ ፍሬ ጉዲይ ልጅነትን ጨምሮ በማናቸውም ማስረጃ ሉረጋገጥ እንደሚችል የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በቅጽ 10 በመ/ አስገዲጅ ውሳኔ ሰጥቶበታል፤ ፍ/ቤቱ በጠቅላላው ማስረጃው በፍ/ቤት ስላልጸደቀ አመልካች የሟች የጉዱፈቻ ልጅ አይደለም ሲል የደረሰበት ድምዲሜ በ1958 ዓ.ም የነበረውን አሰራር ግምት ውስጥ ያላስገባና የማስረጃ ምዝገባንና ማጽደቅ አላማ ያላገናዘበ ነው፤ይህንን ማስረጃ የሰጠው አካል ደግሞ በወቅቱ የወሳኝ ኩነት መ/ቤት ባልነበረበት ጊዜ ይህንን ተቋም በመወከል በወቅቱ በነበረው አሰራር መሰረት የሚመለከተው አካል የሰጠው ማስረጃ ነው፤ በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ተብል እንዱሻርና አመልካች የሟች ተፈራ መልካ የጉዱፈቻ ልጅነት በተጠሪዎች ታምኖ የቀረበና በቀረበው ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካቹ በስር ፍ/ቤት ያገኘው የወራሽነት ማስረጃ ህጋዊ በመሆኑ ሉሰረዝ አይገባም ተብል እንዱወሰንልን በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የአሁን አመልካች የጉዱፈቻ ልጅ አይደለም ተብል በስር ፍ/ቤት የተወሰነበትን አግባብነት ህዲር 27/1958 ዓ.ም ከማዘጋጃ ቤት ከተጻፈው ሰነድ እና አግባብነት ካላቸው የፍትሐብሕር ሕግ ድንጋዎች ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በቀን 09/06/2013 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ አመልካች በአቤቱታው እንደጠቀሰው ሟች ተፈራ መልካ አመልካችን በ1958 ዓ.ም ከተወለደበት ሆስፑታል ወስደው አሳድገውታል። ይህ የሆነው በወቅቱ የአመልካች እናት በወሉድ ምክንያት በመሞታቸው ሟች ተፈራ መልካ ለጽድቅ (ለሞራል) ሲለ ህጻኑን በነጻ ፈቃዲቸው ወስደው አሳድገዋል። ይህን በማድረጋቸውም የደሴ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የምስጋና ወረቀት በህዲ 27/1958 ኣ.ም በስማቸው አዘጋጅቶ ሰጥቷቸዋል።
ይህ ሰነድ በፍ/ህግ ሆነ በተሻሻለው የፍደራል ቤተሰብ ህግ ሲመዘን የጉዱፈቻ ልጅነት መፈጠርን (መመስረትን) የማረጋገጥ (የማስረዲት) ብቃት የለውም። ህጉ በግልጽ በጽሁፍ የተደረገ እና በፍ/ቤት (በዳኞች) የጸደቀ የጉዱፈቻ ልጅ ውል (ስምምነት) ከላለ በቀር የጉዱፈቻ ልጅ ዝምድና አይመሰርትም በማለት ደንግጎ እያለ ከማዘጋጃ ቤት በተሰጠ ተራ የምስጋና ወረቀት የጉዱፈቻ ልጅ ዝምድና ተመስርቷል አያሰኝም። ሟች አመልካችን ከመልካም ስራ አንጻር አሳድጎ ለቁም ነገር ከማብቃት ባለፈ የጉዱፈቻ ልጅ ሉያደርጉት ባለመፈለጋቸው ስምምነቱን ሳያደርጉ አልፈዋል፤ ከመሞታቸውም በፉትም ባደረጉት የጸደቀ ኑዛዜ አመልካችን የጉዱፈቻ ልጅ ስለሆነ ካለን ንብረት ይካፈል በማለት ኑዛዜ አላደረጉለትም። ይህ የሚያስረዲው ሟች የአመልካችን የጉዱፈቻ ልጅነት እስከሞቱበት እለት ያላመኑበት (ያልተቀበለት) መሆኑን ነው። ተጠሪዎች ለስር ፍ/ቤት ባቀረቡት የተቃውሞ ክስ ወይም አቤቱታ ላይ አመልካች የሟች የጉዱፈቻ ልጅ ነው በማለት አልተከራከሩም፤ አምነው መልስ አልሰጡም። ስለሆነም የሰበር ችልቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከስር ፍ/ቤት መዝገብ ጋር በማጣራት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት እንዱያጸናልን በማለት ተከራክረዋል። 3ኛ ተጠሪ በበኩላቸው በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ህግና ማስረጃን መሰረት ያደረገ መሆኑን በመግለጽ የ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪን መልስ በማጠናከር አቅርበዋል። አመልካችም የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ነው። በበኩላችን የግራ ቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል።
እንደመረመርነው ተጠሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ ሟች አቶ ተፈራ መልካ በበጎ አድራጊነት መንፈስ ተቀብል አመልካችን ስላሳደገው ብቻ ልጅ ሳይሆን ከስር ፍ/ቤቱ የወሰደው የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰረዝልን በማለት የጠየቁ ሲሆን አመልካች በበኩላቸው ከሟች አብራክ የተወለደ ልጅ አለመሆናቸው እንደማያከራክር ገልፀው ከክሱ ጋር ተያይዞ በቀረበው የህጋዊ የጉዱፈቻ ውል መሰረት ሟች ከመንግስት ጋር ባደረጉት ስምምነት ከሆስፑታል ተቀብለው በህግ ልጅነት ያሳደጉኝ የጉዱፈቻ ልጅ ነኝ በማለት ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤት ግራቀኙ የጠቀሱትን በቁጥር 61/58 በቀን ህዲር 7/1958 ዓ.ም ከደሴ ማዘጋጃ ቤት የተፃፈውን ማስረጃ ይዘት መርምሮ ማስረጃው በበጎ አድራጊነታቸው ለሟች ተፈራ መልካ የተሰጣቸው የምስጋና ደብዲቤ መሆኑንና ከፍ/ህጉ እና ከክልለ የቤተሰብ ህግ እንዱሁም በፋደራል የቤተሰብ ህግ አንጻር የጉዱፈቻ ልጅነት ሉያስገኙ የሚችለ የህጉን ሁኔታዎች የማያሟላ መሆኑን በማረጋገጥ አመልካች ልጅ ነኝ በማለት የወሰደት ማስረጃ እንዱሰረዝ ወስኗል።
የአመልካች ዋና ቅሬታ የጉዱፈቻ ልጅ መሆኔን ተጠሪዎች ራሳቸው ባቀረቡት ክስና የሰነድ ማስረጃ አምነዋል፤ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔም በተጠሪዎች ከተጠየቀው ዲኝነትና ከክርክሩ አውድ ውጭ በተያዘ ጭብጥ ላይ የተመሰረተ ነው፤ የስር ፍ/ቤት በቁጥር 61/58 በቀን ህዲር 17/1958 ዓ.ም ተያይዞ የቀረበው ማስረጃ የጉዱፈቻ ማስረጃ ሳይሆን የምስጋና ወረቀት ነው ሲል የደረሰበት ድምዲሜም በወቅቱ (1958 ዓ.ም) የነበረውን አሰራር ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው የሚል ነው።
እንደሚታወቀው የ1952 ዓ.ም የፍትሐ ብሓር ህግ በተለይ በቁጥር 2/1952 ዓ.ም የነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከመስከረም 1 ቀን 1953 ዓ.ም ጀምሮ የጸና ሆኖ በስራ ላይ ውሎል። ይኸው የፍትሐ ብሓር ህግ በቁጥር 804(1) ስር እንደደነገገው የጉዱፈቻ ውል በፍርድ ቤት ካልተረጋገጠ (ዳኞች ካላጸኑት) በስተቀር ውጤት የላለው፤ አይጸናምም። ከዚህም ላላ አሁን ሥራ ላይ ያለት የአማራ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 79/95 እና የፋዳራለ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 194 እና 205 በተመሳሳይ ጉዱፈቻ ስምምነት ተደርጎበት ፍርድ ቤት ካላፀደቀው በስተቀር ውጤት አይኖረውም በማለት ይደነግጋለ።
ከፍ ሲል ከተጠቀሰው የህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው የጉዱፈቻ ልጅነት አለ ይባል ዘንድ የጉዱፈቻ ስምምነት መኖርና ይኸው ስምምነት ለፍርድ ቤት ቀርቦ በዳኞች መጽደቅ እንደሚኖርበት፤
ይህ ካልሆነ ግን በህጉ እይታ ውጤት ያለው የጉዱፈቻ ልጅነት አለ ለማለት እንደማይቻል ነው።
ከዚህም ላላ መሰል ጉዲይ የህግ ጉዲይ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ በራሱ አንስቶ ሉወስንበት አይችልም የሚባል አይደለም።
በተያዘው ጉዲይ ከፍሲል እንደተገለፀው የጉዱፈቻ ልጅ ነኝ በማለት ክርክር ያቀረቡት አመልካች ራሳቸው ናቸው። ይህን ክርክራቸውን ደግሞ ህጉ በሚጠይቀው አግባብ ማስረዲት ይጠበቅባቸዋል።
በማስረጃነት የጠቀሱት በቁጥር 61/58 በቀን ህዲር 17/1958 ዓ.ም ከማዘጋጃ ቤት ለሟች ተፃፈ የተባለው ሰነድ የጉዱፈቻ ስምምነት መደረጉንና ስምምነቱ ፍርድ ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ማግኘቱን እንደማያስረዲ አመልካቹም የሚክደት አይደለም። በስር ፍርድ ቤትም በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል።
ይህ ሆኖ እያለ አመልካች የጉዱፈቻ ልጅ መሆኔ በተጠሪዎች ታምኖልኛል፤ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔም ከክርክሩ አውድ ውጭ ነው፤ በፍርድ ቤት የፀደቀ የጉዱፈቻ ስምምነት እንዱኖር መጠየቁና የማዘጋጃ ቤቱ በ1958 የጻፈው ደብዲቤ ውድቅ መደረጉ በወቅቱ የነበረውን አሰራር ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው በሚል የሚያቀርቡት ክርክር ግራ ቀኙ በስር ፍርድ ቤት ያደረጉትን ክርክር፤ ጉዲዩ የሚመራበትን ስርዓት እና የፀና ጉዱፈቻ ይኖር ዘንድ ሥራ ላይ የነበረው ህግ በግልጽ የሚደነግገውን መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ መከራከሪያቸው ተቀባይነት የለውም ብለናል።
በአጠቃላይ አመልካች የሟች አቶ ተፈራ መልካ ልጅ እና ወራሽ ለመሆን የሚያስችላቸው በፍ/ቤት የጸደቀ የጉዱፈቻ ስምምነት ማስረጃ በላለበት ሁኔታ ህጋዊ ልጅ ነኝ በማለት ከፍርድ ቤት የወሰደት የወራሽነት ማስረጃ ተሰርዞ የወሰደትን ማስረጃ ሉመልሱ ይገባል ተብል በስር ፍርድ ቤት መወሰኑ እና ይኸው ውሳኔ በበላይ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ማግኘቱ ህጉን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ ባለመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 08/07/2012 ዓ.ም፤ የደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ 1407 በቀን 17/02/2013 ዓ.ም እንዱሁም የአ/ብ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ በመ/1 በቀን 02/04/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በስር ፍርድ ቤት የተጀመረው ክርክር እንዱታገድ በዚህ ፍርድ ቤት ታህሳስ 23/2013 ዓ.ም የተሰጠው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.