በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የባልና ሚስት ወይም የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት ሆኖ በጋብቻ ወቅት የተፈራ መሆኑ ከመረጋገጡ በተጨማሪ ሁለም ተሳትፍ የነበራቸው ከሆነ በዚህ ሁኔታ የተፈራ ንብረት እኩል መብት እያላቸው የአንደኛው ድርሻ ከላላው ወገን ድርሻ በተለየ ሁኔታ የተረጋገጠ ሳይኖር የሚያንስበት ህጋዊ የሆነ ምክንያት የላለ ስለመሆኑ የአ.ብ.ክ.መ ቤተሰብ ህግ አንቀጽ 73/1/ እና 74/1/
No summary available.
ታህሳስ 24 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- ወ/ሮ አንሻ ሰይድ ተጠሪዎች፡-
ጉዲይ የቀረበው አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በኮምቦልቻ ከተማ አስተዲደር ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በወረዲ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ 1ኛ ተጠሪ ተከሳሽ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በ1991 ዓ.ም ጋብቻ መስርተን ስንኖር 2 ልጆች የወልደን እና የጋራ ሀብት በኮምቦልቻ ከተማ ቀበላ 01 ክልል ውስጥ የሚገኝ በ175 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት አፍርተናል። ስለሆነም ጋብቻው እንዱፈርስ፤ የልጅ ቀለብ እንዱቆረጥ የጋራ ሀብት የሆነውን ቤት የድርሻዬን እንዱያካፍለኝ እንዱሁም የልጅ ቀለብ እንዱሰጠኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። 1ኛ ተጠሪ ለክሱ የሰጡት መልስ ከአመልካች ጋር ጋብቻ የፈፀመን ቢሆንም ለ3 ወር ያክል አንድ ላይ አብረን አልኖርንም በ1996 ዓ.ም በሀገር ባህል ተለያይተናል። በ1993 ዓ.ም ፊጡማ ሰይድ የምትባል አግብቼ ሶስት ልጆች ወልጄ እገኛለሁ። ቤቱም የሰራሁትም ከአመልካች ጋር ተለያይቼ 2ኛ ተጠሪን ከአገባሁ በኋላ ነው። ልጆችን በተመለከተ መሀመድ ሁሴን ልጄ ሲሆን ሱመያ ሁሴን ግን ልጄ አይደለችም በማለት ተከራክረዋል።
የስር ጣልቃ ገቦች የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በኩል የተሰጠ መልስ ደግሞ የ1ኛ ተጠሪ ሚስቶች እኛ እንጂ አመልካች አይደለችም። ቤቱም የተሰራው በእኛ ጥረት እንጂ አመልካች ለቤቱ ግንባታ ውስጥ ተሳትፍ የላትም በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የ1ኛ ተጠሪ ሚስቶች ናቸው፤ ቤቱ በተጠሪዎች የተሰራ በመሆኑ አመልካች ልትካፈል አይገባም ስለሆነም ግማሹ የ1ኛ ተጠሪ ሲሆን ግማሹን ደግሞ ጣልቃ ገቦች ለሁለት እኩል ይካፈለ በማለት ወስኗል።
አመልካች ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለደቡብ ወል ዞን አስተዲደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም። በመቀጠል አመልካች አቤቱታቸው ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቅሬታ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማና ከመረመረ በኋላ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በማሻሻል አመልካች በአከራካሪው ቤት የመካፈል መብት አላት በማለት በ1ኛ ተጠሪ ግማሽ ድርሻ ላይ አመልካች ግማሽ ድርሻ አላት፤ቀሪው የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ይፀናል ሲል ወስኗል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አመልካች ሐምል 25 ቀን 2008 ዓ.ም በፃፈት አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት በታዘዘው መሰረት መስከረም 27 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካችም አቤቱታቸው በማጠናከር የመልስ መልስ በመስጠት ተከራክረዋል። የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
አመልካች በ1991 ዓ.ም ከሁለም በፉት ከ1ኛ ተጠሪ ትዲር የመሰረቱ ሲሆን የነበረው ጋብቻ በፍቺ የፈረሰው በቀን 21/3/2008 ዓ.ም ነው። ላልቹ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጋብቻ የፈፀሙት ከአመልካች በኋላ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ በ1993 ዓ.ም 3ኛ ተጠሪ ደግሞ በ2000 ዓ.ም ነው። ለክርክር ምክንያት የሆነው ቤት የተሰራው በ2002 ዓ.ም መሆኑን በስር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ይህ ማለት ቤቱ የተሰራው በጋብቻ ወቅት መሆኑን ነው። በተጠሪዎች በኩል አመልካች ሚስት አይደለችም፤ለቤቱ ግንባታ አስተዋፅኦ አላደረገችም በማለት ያቀረቡት ክርክር የፍሬ ጉዲዩ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን የተሰጣቸው ያረጋገጡትን በዚህ ደረጃ መነሳቱ ተቀባይነት የለውም።
በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የባልና ሚስቱ ወይም የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት ሆኖ የሚገመት ስለመሆኑ የቤተሰብ ህጉ ያስገነዝባል። የጋራ ሀብት የሚያሰኘው በተጋቢዎች ከጋራ ጥረት ወይም በአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረትም የተፈራ ላሆን እንደሚችልና በአንደኛው ተጋቢ ስም ተመዝግቦ ቢሆንም እንኳ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ መሆኑ ከተረጋጋጠ እና በተለየ ሁኔታ ህጉ ባስቀመጠው አግባብ አንደኛው ተጋቢ የግል መሆኑን ካላስረዲ ጭምር መሆኑን የአብክመ ቤተሰብ ህግአንቀጽ 73/1/ እና 74/1/ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። በጋብቻ ወቅት የተፈራ መሆኑ ከመረጋገጡ በተጨማሪ ቤቱ በሚሰራበት ወቅት የሁለም ተሳትፍ የነበራቸው መሆኑን ከስር መዝገብ ተገንዝበናል። በዚህ ሁኔታ የተፈራ ንብረት እኩል መብት እያላቸው የአንደኛው ድርሻ ከላላው ወገን ድርሻ በተለየ ሁኔታ የተረጋገጠ ሳይኖር የሚያንስበት ህጋዊ የሆነ ምክንያት የለም። በአመልካች በኩል ቤቱ አመልካችና 1ኛ ተጠሪ እኩል እንድንካፈል ተደርጎ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ከ1ኛ ተጠሪ ድርሻ እንዱካፈለ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል። ከላይ እንደተገለፀው አከራካሪው ቤት የተፈራው የሁለም ጋብቻ ፀንቶ በነበረበትና የሁለም ተሳትፍ የነበራቸው መሆኑን በስር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ስለሆነም እኩል መብት ያላቸው በመሆኑ ክፍፍለ በተመለከተ እያንዲንዲቸው ከቤቱ 1/4ኛ ድርሻ አላቸው። የወረዲ ፍርድ ቤት ግማሹ የ1ኛ ተጠሪ ሲሆን ግማሹ ደግሞ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች እኩል እንዱካፈለ በማለት የሰጠውን ውሳኔ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በማሻሻል በ1ኛ ተጠሪ ግማሽ ድርሻ ላይ አመልካች ግማሽ ድርሻ አላት በማለት የተሰጠው ውሳኔ በውጤት ደረጃ አመልካችና ተጠሪዎች እኩል እንዱካፈለ የሚያደርግ ሆኖ አግኝተነዋል።
በመሆኑም በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ድርሻ ላይ ግማሽ ድርሻ አላት ተብል መወሰኑ በውጤት ደረጃ ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 03-13288 ግንቦት 3 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ውጤቱ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348/1/ መሰረት ፀንቷል።
አዋሳኝ ተጠቅሶ ክስ በቀረበበት ቤት ላይ አመልካች እና ተጠሪዎች እኩል እንዱካፈለ ብለናል።
በላልች ጉዲይ የተሰጠው ውሳኔ ክፍል አልተነካም።
በዚህ ችልት ለተደረገው ወጭ እና ኪሳራ የግራ ቀኙን ተከራካሪ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.