No summary available.
መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ደጄኔ አያንሳ ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ ሐብታሙ እርቅይሁን አመልካች፡- ወ/ሮ ኤልሳቤጥ እሸቱ - ቀርበዋል ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ወ/ሮ ማህደር እሸቱ - ቀርበዋል 2ኛ. አቶ ጌታሁን እሸቱ - አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የኑዛዜ ይፍረስ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክሱ በቀረበበት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ፣ ተጠሪዎች ደግሞ በተከሳሽነት ተከራክረዋል። የክርክሩ አመጣጥ በአጭሩ፡- አመልካች ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ የክስ አቤቱታ አባታቸው በ1975 ዓ.ም ስለሞቱ የሟች አያታቸው ወ/ሮ ደምሹ ትክሴ ተተኪ ወራሽ መሆናቸውን እና ሟቿ ከመሞታቸው ሁለት ቀን በፉት ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም አድርገውታል በተባለው ኑዛዜ መነሻነት ተጠሪዎች የውርስ ሀብቱን እንደከለከሎቸው በመግለፅ ፤ ሟች አድርገውታል የተባለው ኑዛዜ ከ1/4ኛ በላይ ጉዲት ያደረሰባቸው በመሆኑ ፈራሽ ተብል ያለኑዛዜ ወራሽ ናቸው ተብል እንዱወሰን ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መልስ የኑዛዜ ይፍረስልኝ ጥያቄው በወቅቱ ስላልቀረበ በፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 973 መሰረት በይርጋ ይታገዲል የሚል መቃወሚያ አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም መቃወሚያውን እንደመረመረው በፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 973/3 እና 974/1 ድንጋጌ መሰረት ኑዛዜ እንዱፈርስ መቃወሚያ ማቅረብ የሚቻለው መቃወሚያ አቅራቢው የኑዛዜውን ይዘት ባወቀ ወይንም ውርስ አጣሪው የውርስ ሀብት ድልድል ባሳወቀ በ3(ሶስት) ወር ጊዜ ውስጥ ሲሆን ፤
ኑዛዜው ተነቦ እንደሆነ አልያም ኑዛዜ አድራጊው በሞተ 5(አምስት) ዓመት ውስጥ መሆን አለበት።
ስለሆነም የ5(አምስት) ዓመት የይርጋ ድንጋጌ የሚመለከተው የኑዛዜውን ይዘት ያላወቀውን ወራሽን ነው። አመልካች የሚቃወሙት ኑዛዜ መኖሩን ከሰኔ ወር 2010 ዓ.ም አንስቶ የሚያውቁ መሆኑን በክሳቸው ስለገለጹ የ5(አምስት) ዓመት ይርጋው እሳቸውን የማይመለከት ከመሆኑም በላይ የፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 1123/3 ድንጋጌም ለጉዲዩ አግባብነት የላለው በመሆኑ ኑዛዜ መኖሩን ካወቁ ከ4 አመት በኋላ አመልካች ያቀረቡት ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት ክሱን ውደቅ በማድረግ መዝገቡን ዘግቶታል። አመልካች በዚህ ብይን ቅር ተሰኝተው ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ይግባኙን ባለመቀበል በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
የሰበር ቅሬታው የቀረበው የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን በመቃወም አመልካች ያቀረቡት የይግባኝ አቤቴታ በይግባኝ ሰሚው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጽናቱን በመቃወም በሰበር ለማስለወጥ ነው።
የሰበር ቅሬታው በአጭሩ፡- የፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 973 ድንጋጌ ተፈፃሚነት የሚኖረው ኑዛዜው በአካል ወይም በተወካይ ሲነበብ ለነበሩ ሲሆን የፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 974 ድንጋጌ ደግሞ በኑዛዜው መነበብ ሥነ ሥርዓት ያልነበሩ ወይም ያልተወከለ ሰዎችን የሚመለከት ለመሆኑ በሰበር መዝገብ (በቅጽ 15 እንደታተመው) አስገዲጅ ውሳኔን ሰጥቷል። አመልካች ሟች አያታቸውን ደምሹ ትክሴ ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም ያደረገችው ኑዛዜ ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ሲነበብ በአካል ያልነበርኩ መሆኑ በተጠሪዎች ያልተካደ ከመሆኑም በላይ በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። አመልካች ኑዛዜ መኖሩን ያወቅኩት የውርስ ሀብት ተጣርቶ ድርሻዬን እንዱያካፍለኝ በተጠሪዎች ላይ በመዝገብ ሳቀርብ ሆኖ ፍርድ ቤቱም ኑዛዜው ላይ የሚቀርበው ክርክር ታይቶ ውሳኔ ካገኘ በኋላ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብት ጠብቆ መዝገቡን ዘግቷል። በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኑዛዜውን በመቃወም ያቀረብኩት አቤቱታ ታይቶ ውሳኔ ካገኘ በኋላ ጉዲዩ የቀረበለት ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መጣራት አላባቸው የሚላቸውን ጭብጦች ይዞ ጉዲዩ ወደ አዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ቤት ግንቦት 10 ቀን 2013 ዓ.ም በመመለሱ ለሰበር ቅሬታው መሰረት የሆነው ክስ በፍትሐ ብሕር ሕግ ቁጥር 974 ድንጋጌ መሰረት የይርጋ ጊዜው 5(አምስት) መሆን ሲገባው ከ4(አራት ዓመት) በኋላ የቀረበ ክስ ነው ተብል በክርክር ሂደት ላይ የነበርኩ መሆኑ እየታወቀ በይርጋ ቀሪ መሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ስህተቱ ሉታረም ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 ቁጥር 6(1) መሰረት ለሰበር ሰሚው ችልቱ የተመራው አቤቱታ በሰበር ሰሚ ችልቱ ተመርምሮ አመልካች ኑዛዜ መደረጉን(መኖሩን) እንደማያውቁ በፍሬ ነገር ደረጃ ከመረጋገጡ አንፃር በሥር ፍርድ ቤት የተወሰደው የይርጋ እርዝማኔ ተገቢነት እንዱሁም አመልካች በኑዛዜው በተደረገው ክፍፍል ጉዲት አድርሶብኛል በማለት የሚከራከሩ በመሆኑ ያቀረቡት ክስ በይርጋ የሚታገድ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት መዝገቡ ያስቀርባል ተብል ተጠሪዎች ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል።
No topics extracted.
ተጠሪዎች ለሰበር አቤቱታው ህዲር 14 ቀን 2016 ዓ.ም የተጻፈ 3(ሶስት) ገጽ መልስ ያቀረቡ ሲሆን የክርክራቸው ይዘት፡- አመልካች የ1ኛ ተጠሪን የኑዛዜ ወራሽነት በመቃወም በመዝገብ አቤቱታ ያቀረቡት በሰኔ ወር 2010 ዓ.ም ሳይሆን በሚያዝያ 29 ቀን 2011 ዓ.ም ነው።
ሟች ያደረጉት ኑዛዜ ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ስለሚነበብ(ስለሚፈስ) አመልካች እንዱገኙ በተደጋጋሚ ተደውልላቸው እና ተነግሯቸው ለመቅረብ ፈቃደኛ ስላልሆኑ በፍትሐ ብሕር ህጉ 973/1 እና 974/3 ድንጋጌ መሰረት ቀሪ ሆኗል። አመልካች የሟች የልጅ ልጅ ተተኪ ወራሽ እንጂ ልጅ ስላልሆኑ በኑዛዜ ድርሻ ላይ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችለ ባለመሆኑ በግራ ቀኙ መካከል የይርጋ ክርክር በመካከላችን ሉነሳ የሚችልበት ሕግ አግባብ የለም። በይዞታ ውስጥ ከሟች የግል ንብረቶች በተጨማሪ በ1ኛ ተጠሪ የተሰሩ የንግድ ሱቆች ያለ ሲሆን ቀሪውን ንብረት ሟች ለአራት የኑዛዜ ወራሾች ተናዘዋል። ለኑዛዜ ተቀባዮች የተሰጠው ንብረት ዋጋ መጠን ተለይቶ ጉዲት መኖር አለመኖሩ ባልታወቀበት አመልካች ጉዲት ድርሶብኛል በማለት በደፈናው የሚያቀርቡት ክርክር የህግ መሰረት ስለላለው አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ እንዱሰጣቸው ጠይቀዋል።
አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና መሰረታዊ የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም በሰበር ችልቱ ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በፍትሐብሕር ሕጉ ቁጥር 1807/ረ/ ድንጋጌ መሰረት ይርጋ ግዳታዎችን ቀሪ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ አንደ ነዉ። ድንጋጌው የውል ህግን የሚመለከት ቢሆንም “ግዳታዎች” ማለቱ የውል ግዳታን ብቻ ላለመሆኑ አመላካች ሲሆን ከቁጥር 1677(1) ድንጋጌ አንፃርም ሲታይ ላልች ግዳታዎችንም ይጨምራል። ይርጋ የመብት ጥያቄ በህጉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ባለመቅረቡ በጊዜ ማለፍ ቀሪ የሚሆንበት ፣ ተጠያቅነትን በማስቀረት ያልነበረ መብትን የሚያጎናጽፍ ነው።
ይርጋ ዲተኛ መብት ጠያቂዎችን መብት የሚያሳጣ በአንፃሩ ባለዕዲዉ ሁልጊዜ ያለበትን ዕዲ እያሰበ በስጋት እንዲይኖር ነፃ የሚያወጣ ነው። በጊዜ ማለፍ ምክንያት ኃላፉነት ወርድልኛል የሚለው ሰው ኃላፉነት እንዲለበት የማይክድ በክርክሩ በተከሳሽነት የሚሰየመው ሰው ነው። ሕጉ ይህን መብት አንስቶ የመከራከር ዕድል ለባለዕዲው የተሰጠ ሆኖ መከራከሪያውን ማንሳት የሚችለው በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መልክ ነው። የይርጋ መቃወሚያ ተጠቃሚ የሆነ ሰው በፍ/ሥ/ሥ ሕጉ ቁጥር 244(2) (ሰ) መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ለማንሳት መብት ያለው ቢሆንም ይህን መብቱን መተው እንደሚችል የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1856 ያስገነዝበናል።
ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 244(2)(ሰ) እንዱሁም ከቁጥር 245 ድንጋጌዎች መረዲት እንደሚቻለውም ክሱ በይርጋ የታገደ መሆኑን የሚገልጽ መቃወሚያ ሲቀርብ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ ተቀብል ላላው ተከራካሪ ወገን በጉዲዩ ላይ የሚያቀርበውን ክርክር ከሰማ በኋላ ውሳኔ ለመስጠት ተገቢ መስል የሚገምተው ማስረጃ እንዱቀርብለት በማድረግ መቃወሚያው በተገቢና በቂ ማስረጃ መደገፈን በመመርመር ተገቢ መስል የታየውን ብይን ላሰጥ ይገባል። በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር የይርጋ መከራከሪ መብቱን ያልተጠቀመ ተከሳሽ መብቱን እንደተወው ስለሚገመት ዳኞች ክርክሩን ማንሳት ስለማይችለ ፍሬ ነገሩን መርምረው ውሳኔ ይሰጣለ።
የፍትሐብሕር ሕጉ ቁጥር 1851 ይርጋ የሚቋረጥባቸውን ምክንያቶች ይዘረዝራል። ይርጋ ከተቋረጠ እንደ አዱስ የሚቆጠር መሆኑን ከቁጥር 1852 ድንጋጌ መረዲት ይቻላል።
ኑዛዜን በመቃወም የሚቀርበው ማናቸውም መቃወሚያ መታየት ያለበት አግባብነት ካለቸው የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች አንፃር ነው። አንድ ኑዛዜ ፈራሽ ነው በሚል ስለሚቀርብ መግለጫ እና ክስ እንዱሁም መግለጫ እና ክሱ ላቀርብ ስለሚገባበት የጊዜ ገደብ በፍትሐ ብሕር ሕግ ቁጥር 973 እና 974 ተደንግጎ ይገኛል። የፍትሐ ብሕር ሕግ ቁጥር 973 ድንጋጌ ኑዛዜው ፈራሽ ነው የሚል መቃወሚያ ያላቸው ኑዛዜው ሲነገር /ሲፈስ/ የነበሩትን ሰዎች የሚመለከት ነው። ይህም ኑዛዜው ሲነበብ የነበሩ ወይም የተወከለ ሰዎች ኑዛዜው አይፀናም ወይም በኑዛዜው የተነገረ ቃል አይፀናም የሚለትንና የመሳሰለትን የሚቃወሙ ቢሆን ይህን ማድረግ ያለባቸው ኑዛዜው ከተነበበበት አንስቶ እስከ አስራ አምስት ቀን ድረስ እንደሆነ ያመለክታል። የፍትሐ ብሕር ሕግ ቁጥር 973 (1) ድንጋጌ ክስን ሳይሆን መግለጫን የሚመለከት ነው። የንብረት ድልድል የማያውቅ ወራሽ መግለጫ የማቅረብ ግዳታ የለበትም። ከዚህም በተጨማሪ ክስን የማቅረብ ሃሣብ መግለጫው በጽሐፍ ካልሆነና ለአጣሪው ወይም ለዳኞች ወይም በውርስ ላይ የተነሣውን ነገር ለመጨረስ ለተመረጡት የሽምግልና ዳኞች እንዱደርስ ካልተደረገ በቀር እንደማይፀና /መቃወሚያ አለ ለማለት እንደማይቻል/ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 973/2/ ተደንግጓል። በመጨረሻም መግለጫው ከተሰጠበት ቀን አንስቶ እስከ ሦስት ወር ድረስ ክስ ካልቀረበ መብቱ ከነጭራሹ እንደሚቀር በንኡስ ቁጥር /3/ ተመልክቷል። ኑዛዜ መኖሩን ማወቅ እና በኑዛዜው የተደረገውን ክፍፍል ይዘት ማወቅ ልዩነት ያለው መሆኑን ልብ ማለት ይገባል። ኑዛዜው ሲነበብ(ሲፈስ) በአካል ወይም በተወካይ ላልተሳተፈ ወይንም በላለበት ኑዛዜ የፈሰሰ ሰዎች በፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 973 የተመለከተው ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው የውርስ አጣሪው ስለ ክፍያ ፤ ድልድል አመዲደብ ሃሳብ ከነገራቸው ቀን አንስቶ መሆኑን የፍትሐ ብሕር ሕግ ቁጥር 974(1) ድንጋጌ ያመለክታል። አንድ ሰው ኑዛዜው መነበቡን (መፍሰሱን) ያውቃል ለማለት በአካል ወይንም በተወካይ ኑዛዜው ሲነበብ ወይም ሲፈስ መገኘት አልያም ስለ ክፍያ ፤ ድልድል አመዲደብ ሃሳብ በአጣሪው የተነገረው እንደሆነ መሆኑን ከፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 973 እና 974(1) ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል። ኑዛዜ ከፈሰሰበት ወይም ሟቹ ከሞተበት ከአምስት ዓመት በኋላ ስለኑዛዜው መጽናት፤ ስለክፍያው አመዲደብ አጣሪው ያቀረበውን ሃሳብ መቃወሚያ ላቀርብበት እንደማይገባ ፍፁም(absolute) ይርጋ በፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 974(2) ሥር ተመልክቷል። ኑዛዜ ሲነበብ(ሲፈስ) በአካል ያልነበሩ ፤ ያልተወከለ አልያም ስለ ክፍያ ፤ ድልድል አመዲደብ ሃሳብ በአጣሪው ያልተነገራቸው ሰዎችን የሚመለከተው ይርጋ በፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 974(2) ሥር የተመለከተው ፍፁም(absolute) ይርጋ መሆኑን ይህን ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ (ያልታተመ) ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም አስገዲጅ ውሳኔን ሰጥቷል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ(ሲፈስ) በአካል ወይንም በተወካይ ያልተገኙ ፤ ስለ ክፍያ፤ ድልድል አመዲደብ ሃሳብ በአጣሪው ያልተነገራቸው ነገር ግን ያለኑዛዜ የውርስ ድርሻቸውን ለመካፈል በ2010 ዓ.ም ክስ ሲያቀረቡ ተጠሪዎች የኑዛዜ ወራሽነት ማስረጃ መውሰዲቸውን ሰምቶ ኑዛዜው እንዱሰረዝላቸው ክስ ያቀረቡ መሆኑን ከክርክሩ ሂደት መረዲት ተችሎል። አመልካች የኑዛዜውን መኖር በ2010 ዓ.ም ሰምተው እያለ ከ4(አራት) ዓመት በኋላ ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም የቀረበው ክስ በ3(ሶስት) ወር የይርጋ ቀሪ ነው በማለት የአመልካችን የክሰ አቤቱታ በይርጋ ውድቅ ማድረጋቸው የፍትሐ ብሕር ሕጉን ቁጥር 973 እና 974(1) ድንጋጌዎች እንዱሁም በሰበር መዝገብ የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም የተላለፈ ነው። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት ችልት የሚሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉምን በመተላለፍ የሚሰጥ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመሆኑ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2(4(ሸ)) ይደነግጋል።
በመሆኑም አመልካች ኑዛዜዉ ሲነበብ ያልነበሩ ስለሆኑ በጉዲዩ ላይ ተፈጻሚነት ያለው ይርጋ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.974 (2) ሥር የተመለከተው የአምስት አመት ሲሆን ሟች ከመሞታቸው ሁለት ቀን በፉት ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ እንዱፈርስላቸው ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ያቀረቡት ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.974 (2) ሥር የተመለከተው የአምስት ዓመት የጊዜ ገደብ ከማለፈ በፉት ሆኖ እያለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.973 (2) እና 974 (1) መሰረት በ3 ወር ይርጋ የሚታገድ ነዉ በማለት የሥር ፍርድ ቤቶች ያሳለፈት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
ይግባኝ ሰሚው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ብይን ፣ እንዱሁም የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ህዲር 3 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ብይን በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ - ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 ቁጥር 9(1/ሀ) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ያቀረቡት የኑዛዜ ይፍረስልኝ አቤቱታ በይርጋ ቀሪ የሚሆን አይደለም በማለት ተወስኗል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በብይን የዘጋውን የመዝገብ አንቀሳቅሶ የፍሬ ነገር ክርክሩ አይቶ ውሳኔ እንዱሰጥ መዝገቡ በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ - ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 ቁጥር 9/2 መሰረት ተመልሶለታል።
ውሳኔው ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በችልት ተነቧል።