No summary available.
መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ደጀኔ አያንሳ ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ ሐብታሙ እርቅ ይሁን አመልካቾች፡-
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካቾች መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የፍደራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.
የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ ኑዛዜ ይፍረስልኝ በሚል የቀረበን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋደራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በስር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁን አመልካቾች ደግሞ ተጠሪዎች በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አክስቴ የሆነችው ሟች ወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 07 የቤት ቁጥር 003 ውስጥ ስትኖር ልጅ ሳትወልድ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች፤ የወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና ወንድም የሆነው ሟች አባቴ አቶ ታደሰ ወልደሃና የሞተው ከአክስቴ ቀድሞ ነው፤ የአባቴ ተተኪ ወራሽ መሆኔን አረጋግጫለሁ፤ ላላ አክስቴ የሆነችው ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና ቤቱን እያስተዲደረችልኝ በጋራ ከኪራይ የሚገኘውን ገንዘብ እየሰጠችኝ ስንጠቀም ቆይተን ጥር 06 ቀን 2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፤ የውርስ ማጣራትም ሆነ የድርሻ ክፍፍል ያልተጠየቀበት በክሱ ላይ የተገለጸውን ቤት የውርስ ድርሻ ክፍፍል እንዱደረግበት በፋደራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችልት ጠይቄ እየታየ ባለበት አመልካቾች ሟች አማከለች ወልደሃና በልጅ ልጅነት ስላሳደገችን ኑዛዜ ተደርጎልናል በማለት ጣልቃ ገብተዋል፤ ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና የራስዋ ባልሆነ የአክስቴ ሟች ደብሪቱ ወልደ ሃና የነበረ ከሟች አማከለች ወልደሃና ጋር በጋራ እየተጠቀምንበት የነበረ ንብረት ላይ ያደረገችው ኑዛዜ ነው፤ ከንብረቱ ላይ ሟች አማከለች ወልደሃና በሕይወት እያለች ድርሻዬን እንድትሰጠኝ በተደጋጋሚ ብጠይቃትም ስታመላልሰኝ ቆይታ ድርሻዬን ሳትሰጠኝ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች፤ የውርስ ሀብት የሆነውን ንብረት ውርስ ሳይጣራ እና ሳታሳውቀኝ ስመ-ሀብቱን ወደራስዋ በማዞር የእሷ ብቻ ባልሆነ ንብረት ላይ ኑዛዜ ማድረጓን አረጋግጫለሁ፤ ሟች አማከለች ወልደሃና በህመሟና በመሞቷ ምክንያት ከመስከረም 2014 ዓ.ም ጀምሮ ይከፈለኝ የነበረው ኪራይ ስላልተከፈኝ በልላ መዝገብ ክስ መስርቻለሁ፤ ተጠሪ የውርስ ሀብት ድርሻዬን እየተጠቀምኩኝ ስለሆነ ሟች ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና ለአመልካቾች የተናዘዙት ኑዛዜ እንዱሻርልኝ እና 1/2ኛ ድርሻዬ እንዱሰጠኝ እና ለአመልካቾች የተሰጠው ካርታ እንዱመክን ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አመልካቾች በሰጡት መልስ የመጀመርያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በብይን ውድቅ ተደርጓል፤
በፍሬ ነገሩ ላይ ደግሞ አከራካሪው ቤት ከጅምሩ የወ/ሮ አባይነሽ አበጋዝ የነበረ ነው፤ ወ/ሮ አባይነሽ አበጋዝ ለወ/ሮ ደብሪቱ ወልደ ሃና በአዱስ አበባ አውራጃ ፍርድ ቤት ቀርበው በግልጽ ኑዛዜ አውርሰዋል፤ የአመልካቾች አውራሽ ወ/ሮ አማከለች ወልደሃናም ይህንን ንብረት ከሕዲር 3 ቀን 1992 ዓ.ም ጀምሮ ሲያስተዲድሩ ቆይተው ወራሽነታቸውን ሐምል 30 ቀን 1993 ዓ.ም አረጋግጠዋል፤ ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና የካቲት 30 ቀን 2009 ዓ.ም በሰነድች ማረጋገጫ ቀርበው ንብረቱን ለአመልካቾች አውርሰዋል፤ የተጠሪ የተተኪ ወራሽነት ማረጋገጫ የኑዛዜ ወራሽነትን አያረጋግጥም፤ ተጠሪ የኪራይ ገንዘብ እንዱሰጣቸው የጠየቁት በምን አግባብ እንደሆነ አልገለጹም፤ የኪራይ ገንዘብ ተከፍሎቸውም አያውቅም፤ ተጠሪ ክስ ባቀረበበት ጉዲይ ላይ መብት ስለላላቸው ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስጃ ከመረመረ በኋላ ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና ያደረጉት ኑዛዜ በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት የተደረገ እና ምንም እንከን የላለበት ነው፤
ለአመልካቾች በኑዛዜ የተላለፈው አከራካሪው ቤት ቀደም ሲል የወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና የነበረ ነው፤
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና ሐምል 30 ቀን 1993 ዓ.ም ባገኙት የወራሽነት ማስረጃ አከራካሪውን ቤት ከወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና በውርስ ያገኙት መሆኑን ያሳያል፤ ወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና የተጠሪ አክስት ተጠሪም ተተኪ ወራሽ መሆናቸውን በመ. በቀን 13/05/2014 ዓ.ም የተሰጠው እና በማስረጃነት የቀረበው የፍርድ ቤት ውሳኔ ያሳያል፤ ይህ ማስረጃ ያልተሰረዘ እና ወራሽነታቸውን የሚያረጋግጥ ነው፤ ሟች ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና ለአመልካቾች ያደረጉት ኑዛዜ በራሳቸው ድርሻ ላይ ብቻ ሳይሆን በተጠሪም ድርሻ ላይ በመሆኑ ኑዛዜው ፈራሽ ላሆን ይገባል ሲል ወስኗል።
አመልካቾች ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ይግባኛቸው ተሰርዟል።
አመልካቾች መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይህን ውሳኔ በመቃወም የቀረበ ሲሆን ይዘቱም፡- የስር ፍርድ ቤት ያልተሰረዘ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም ማለት አይቻልም በማለት የሰጠው ውሳኔ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰ.መ. የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነው፤ የኑዛዜ አውራሻችን የንብረቱን ስመ ሀብት ወደ ራሷ በማዞር እስከዔለተ ሞቷ ድረስ ለ 22 አመታት ስትጠቀምበት እንደነበር ተረጋግጧል፤ ተጠሪ ከአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ያገኙት የወራሸነት ማስረጃ የድርሻ ባለቤትነትን የማያሳይ ከመሆኑም በላይ በውርስ አጣሪ ተጣርቶ አልተረጋገጠም፤ የተጠሪ የወራሽነት ማስረጃ ለውርስ ማጣራት አቤቱታው እንደመነሻነት የሚያገለግል እንጂ የጋራ ወራሽነትን ለማስረዲት የሚውል አይደለም፤ ተጠሪ የጋራ ባለሃብት የሆነችበት የሕግ መሰረት በማስረጃ አላረጋገጠችም፤ ንብረቱ የአመልካቾች እና የተጠሪ የጋራ ሃብት ነው በማለት የተሰጠው ውሳኔ ማስረጃን በአግባቡ በመመዘን የተሰጠ አይደለም፤ ስለሆነም እነኚህ ሁኔታዎች ታልፈው ሟች ያደረጉት ኑዛዜ ሉፈርስ ይገባል በማለት በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችልት የአመልካቾችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ አመልካቾች የውርስ ንብረቱን ካርታ አውጥተው ከ20 ዓመታት በላይ ሲጠቀሙበት ከነበሩት ሰው በውርስ ሳያገኙ ተጠሪ የተተኪ ወራሽ ነኝ በማለት ያቀረቡት የወራሽነት ምስክር ወረቀት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ከሰጣቸው አስገዲጅ ውሳኔዎች አንጻር መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩ ለዚህ ችልት ቀርቧል።
ተጠሪ ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ያቀረቡት መልስ ይዘት ባጭሩ፡- አከራካሪው ቤት ከአመልካቾች ጋር በጋራ ይዘን ስለማስተዲደራችን በመ. ጥቅምት 25/2015 ዓ.ም በተሰጠ ብይን ተረጋግጧል፤ ሟች ያደረጉት ኑዛዜ እንዱፈርስ የተወሰነው ከአመልካቾች አውራሽ ጋር በጋራ በመሆን አከራካሪውን ቤት ስለመያዛችን ተረጋግጦ ነው፤ አመልካቾች ካርታ ያወጡት በወራሽነት ማስረጃ እንጂ ውርሱ ከተጣራ በኋላ አይደለም፤ የስር ፍርድ ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገው የተጠሪን የወራሽነት ማስረጃ ብቻ አይደለም፤ ስለሆነም ውሳኔው ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
አመልካች በሰጡት የመልስ መልስ ያቀረቡትን አቤቱታ በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። ይህ ችልትም ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ህጎች ጋር በማገናዝብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ ሑደት መገንዘብ የቻልነው ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አከራካሪ የሆነው ቤት ቀደም ሲል የወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና እንደነበር፤ ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና ሐምል 30 ቀን 1993 ዓ.ም ባገኙት የወራሽነት ማስረጃ አከራካሪውን ቤት ከወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና በውርስ እንዲገኙት፤
ወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና የተጠሪ አክስት ተጠሪም ተተኪ ወራሽ መሆናቸውን የሚያሳይ በመ.
በቀን 13/05/2014 ዓ.ም የተሰጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ በማስረጃነት እንደቀረበ፤ ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና ያደረጉት አከራካሪውን ቤት አስመልክቶ ለአመልካቾች ያደረጉት ኑዛዜ እንከን የላለበት መሆኑን አረጋግጦ ተጠሪ በማስረጃነት ያቀረቡት የወራሽነት ማስረጃ ያልተሰረዘ በመሆኑ እና ሟች ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና ለአመልካቾች ያደረጉት ኑዛዜ በራሳቸው ድርሻ ላይ ብቻ ሳይሆን በተጠሪም ድርሻ ላይ በመሆኑ ኑዛዜው ፈራሽ ላሆን ይገባል ሲል ከሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰ መሆኑን ነው።
አመልካቾች ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ባቀረቡት ክርክር በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ነው በማለት በዋነኝነት የሚከራከሩት የስር ፍርድ ቤት ለተጠሪ የተሰጠው የወራሽነት ማስረጃ ያልተሰረዘ በመሆኑ አመልካቾች የተጠሪን ወራሽነት አስመልክቶ የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም በማለት የሰጠው ውሳኔ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰ.መ. የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነው በሚል ነው። ስለሆነም ተጠቃሾቹ ውሳኔዎች ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምረናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰ. እና በላልችም መዛግበት የሰጠው ውሳኔ በአንድ ወገን አቤቱታ አቅራቢነት የተሰጠ ማስረጃ በማስረጃነት በቀረበበት በማናቸውም ጊዜ ተዓማኒነት እና ክብደት ያለው ማስረጃ መሆኑን ለማሳየት ክርክር ላቀርብበት እና ተቃራኒ ማስረጃ ተሰምቶ ውድቅ ላደረግ እንደሚችል በመግለጽ በየትኛም እርከን ላይ ለሚገኙ ፍርድ ቤቶች አስገዲጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት በተጠሪ በኩል የቀረበውን ማስረጃ ስላልተሰረዘ አመልካቾች የተጠሪን ወራሽነት በሚመለከት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም ማለቱ ተጠቃሹን የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ የሚቃረን ሆኖ አግኝተነዋል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አመልካቾች በተጠሪ በኩል የቀረበው የወራሽነት ማስረጃ በሚመለከት ወራሽነቷ የተረጋገጠበት እንጂ የሕግም ሆነ የኑዛዜ ወራሽ መሆናቸውን አያሳይም በማለት ከመከራከራቸው በቀር ተጠሪ የሟች ወራሽ አለመሆናቸውን ለማሳየት የሚያስችል ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ የተከራከሩ መሆኑን የስር ውሳኔ አያሳይም። በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. ጥር 13 ቀን 2014 የተሰጠው ውሳኔ ደግሞ ተጠሪ የሟች ወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና ወራሽ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። ስለሆነም አመልካቾች የተጠሪን ወራሽነት በሚመለከት ለዚህ ችልት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በመቀጠል ሟች ያደረጉት ኑዛዜ እንዱፈርሰ በማለት በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምረናል።
በኢትዮጵያ ውርስ ሕግ የሟች ውርስ ያለ ኑዛዜ፣ በኑዛዜና በከፉል ኑዛዜና በከፉል ያለ ኑዛዜ የሚፈፀም ስለመሆኑ፤ ሟች በኑዛዜ የሚያስተላልፈው ንብረትም የራሱን ንብረት ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 829 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
በያዝነው ጉዲይ አከራካሪ የሆነው ቤት የወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና እንደነበር እና ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና ሐምል 30 ቀን 1993 ዓ.ም ባገኙት የወራሽነት ማስረጃ አከራካሪውን ቤት ከወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና በውርስ እንዲገኙት፤ ተጠሪ በበኩላቸው የወ/ሮ ደብሪቱ ወልደሃና ተተኪ ወራሽ መሆናቸውን የሚያሳይ በመ. በቀን 13/05/2014 ዓ.ም የተሰጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ በማስረጃነት ያቀረቡ ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተረጋጠ ፍሬ ነገር ነው። ይህም ተጠሪ እና ሟች ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና የአከራካሪው ቤት ወራሾች መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። ተጠሪ እና ሟች ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና የአከራካሪው ቤት ወራሾች ከሆኑ ደግሞ ሟች ወ/ሮ አማካለች ወልደሃና ቤቱን በኑዛዜ ማስተላለፍ የሚችለት በድርሻቸው ላይ ብቻ ነው። ሆኖም ሟች ወ/ሮ አማካለች ወልደሃና ባደረጉት ኑዛዜ አከራካሪውን ቤት ያስተላለፈት በድርሻቸው ላይ ብቻ ሳይሆን የተጠሪንም ድርሻ ጨምረው በመሆኑ ኑዛዜው ሉፈርስ የሚገባው ሙለ በሙለ ሳይሆን በተጠሪ ድርሻ ላይ ያደረጉት የኑዛዜ ክፍል ብቻ ነው። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ሟች ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 07 የቤት ቁጥሩ 003 የሆነውን ቤት አስመልከቶ የካቲት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ ሙለ በሙለ እንዱፈርስ በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍደራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሻሽሎል።
ሟች ወ/ሮ አማከለች ወልደሃና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 07 የቤት ቁጥሩ 003 የሆነውን ቤት አስመልከቶ የካቲት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በራሳቸው ድርሻ ላይ ብቻ የተደረገ ሳይሆን በተጠሪም ድርሻ ላይ ጭምር የተደረገ በመሆኑ የተጠሪን ድርሻ በሚመለከት የተደረገው የኑዛዜ ክፍል ብቻ ፈራሽ ሆኗል በማለት ወስነናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።