No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) እንዲሻው አዲነ ተሾመ ሽፈራው መላኩ ካሳዬ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ወቅት አስቀድሞ ውርሱ ሲጣራ ተነስቶ ውሳኔ ያገኘ ክርክር በድጋሚ ሉነሳ የሚችል መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው። የሰበር ቅሬታ የቀረበው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም በመዝገብ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ነው። ጉዲዩ በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲጀመር የአሁን አመልካቾች ተከሳሾች ተጠሪዎች ደግሞ ከሳሽ ነበሩ።
ተጠሪዎች በታህሳስ 21 ቀን 2014 በተፃፈ አቤቱታ ባቀረቡት ክስ ከ1-3ኛ ተጠሪዎች እንዱሁም በዚህ አቤቱታ ላይ ያልተካተተው አቶ ደረጄ ቀፀላ የሟች እናታችን የወ/ሮ እላኒ ውድነህ ሕጋዊ ወራሾች ነን።
እንዱሁም 2ኛ ተጠሪ፣ 3ኛ ተጠሪ፣ 2ኛ አመልካች እና 3ኛ አመልካች የሟች አባታችን አቶ ሙለጌታ ታምሬ ህጋዊ ወራሾች መሆናችንን በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በተደረገ የውርስ ማጣራት አረጋግጠናል። ውርሱ ሲጣራ በቂርቆስ ክፍል ከተማ ወረዲ 04 የቤት ቁጥሩ 777 የሆነው የመኖሪያ ቤት የሟቾች ወ/ሮ እላኒ ውድነህ እና የሟች አቶ ሙለጌታ ታምሬ የጋራ ሀብትና በወራሾች መካከል እኩል የሚከፊፈል መሆኑ፤ በ1ኛ አመልካችና በሟች አቶ ሙለጌታ ታምሬ የጋብቻ ዘመን ለባንክ የተከፈለ ብር 25,540,50 የሁለቱ የጋራ ሀብት መሆኑን እና የገንዘቡ ግማሽ ለአቶ ሙለጌታ ታምሬ ወራሾች የሚከፊፈል መሆኑን ሰርቪስ ቤቶቹንም በተመለከተ ቀደም ሲል ለነበሩት ሰርቪስ ቤቶች የወጣው ብር 3204.50 ግማሹ በሟች በወ/ሮ እላኒ ወራሾች መካከል ግማሹ ደግም በሟች ሙለጌታ ታምሬ ወራሾቸ መካከል የሚከፊፈል መሆኑ ተረጋግጦ የውርስ አጣሪ ሪፕርት የፀደቀ ቢሆንም የውርስ ንብረቱ በወራሾች መካከል ክፍፍል ሳይደረግበት በአመልካቾች እጅ ሆኖ ብቻቸውን እየተጠቀሙበት ይገኛለ። በመሆኑም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 04 የቤት ቁጥር 777 የሆነ የመኖሪያ ቤት በወራሾች መካከል የድርሻ ክፍፍል ይደረግልን በማለት ጠይቀዋል።
አመልካቾች ለተጠሪዎች አቤቱታ በጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ የውርስ ክፍፍለ የተጠየቀው የውርስ አጣሪ ሪፕርቱን መሰረት በማድረግ ነው። የውርስ አጣሪ ሪፕርት ደግሞ እንደማስረጃ እንጂ እንደ ፍርድ ስለማይቆጠር አፈፃፀም ሉጠየቅበት አይችልም። የአጣሪ ሪፕርቱ ቢፀድቅም ስህተት አለበት። ክርክር የቀረበበት የቤት ቁጥር 777 ሟች አቶ ሙለጌታ ታምሬ 1ኛ አመልካችን ከማግባታቸው በፉት የተመሩት ቢሆንም ከጋብቻ በኋላ 1ኛ አመልካች በቤቱ ላይ መሰረታዊ ለውጥ አድርገውበታል።
ቤቱ የተሰራበትንም እዲ ከፍለዋል። በመሆኑም ቤቱ የ1ኛ አመልካች እና የሟች አቶ ሙለጌታ ታምሬ የጋራ ሀብት ላሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የስር የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራቀኙን ክርክር መርምሮ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 5፤244(2)ለ እና 245 (ለ) ከተደነገገው አኳያ እንዱሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ በውርስ ይጣራልኝ መዝገብ ቀርቦ እልባት የተሰጠው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በድጋሚ በውርስ አጣሪው ሪፕርት መሰረት እንካፈል በሚል ላላ መዝገብ ላይ በመቃወሚያነት ላቀርብ አይችልም በማለት የወሰነ በመሆኑ አመልካቾች በውርስ ማጣራቱ ቅሬታ ከነበራቸው ሪፕርቱ በይግባኝ እንዱስተካከል መጠየቅ ነበረባቸው። በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 04 የቤት ቁጥር 777 የሆነውን ቤት በተመለከተ 1ኛ አመልካች የጋራ ነው ሲለ ያቀረቡትን ክርክር አስቀድሞ በውርስ አጣሪ መዝገብ ላይ ተነስቶ እልባት የተሰጠበት በመሆኑ በድጋሚ መቅረቡ ተገቢነት የለውም።
ቤቱ የሟች ወ/ሮ እላኒ ውድነህ እና የሟች አቶ ሙለጌታ ታምሬ እንጂ የ1ኛ አመልካችና የሟች አቶ ሙለጌታ ታምሬ የጋራ ሀብት ስላልሆነ የሟች ወ/ሮ እላኒ ወራሾች አቶ ቴዎድሮስ ታዬ፣ ደረጄ ቀፀላ፣ ሉያ ሙለጌታ፣ ቤተልሄም ሙለጌታ 50% እኩል እንዱካፈለ ቀሪውን 50% ደግሞ የሟች አቶ ሙለጌታ ታምሬ ድርሻ ስለሆነ ወራሾቹ ሉያ ሙለጌታ፣ ቤተልሄም ሙለጌታ፣ እየሩሳላም ሙለጌታ እና ስነ-ጥበብ ሙለጌታ እኩል እንዱካፈለ እና ላልችን ንብረቶችም በውርስ አጣሪ ሪፕርት መሰረት እንዱከፊፈለ ወስኗል።
No topics extracted.
አመልካቾች ውሳኔውን ተከትል ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው ፍርድ ቤቱ ግራቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ አጽንቷል።
አመልካቾች በሀምላ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባቀረቡት የሰበር ቅሬታ የውርስ አጣሪ ሪፕርት እንደ አንድ ማስረጃ የሚያገለግል ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች እንደ ውሳኔ በመውሰድ በፍ/ብ/ሥ/ስ/ህ/ቁ/5 መሰረት በድጋሚ ክርክር የሚቀርብበት አይደለም በማለት መወሰናቸው፤ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ መጋቢት 2 ቀን 2007 ዓ.ም በሰጠው አስገዲጅ ትርጉም የውርስ አጣሪ ሪፕርት ከማስረጃነት ዋጋ ውጭ ላላ ዋጋ የላለው እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ ላቀርብበት እንደማይችል ወስኗል፤ የውርስ ማጣራት እና የውርስ ሀብት ክፍፍል ጭብጥና ፍሬ ነገር የተለያዩ ናቸው፤ የውርስ ማጣራት እንደ ውሳኔ ቢቆጠር ኖሮ በቀጥታ አፈፃፀም ይከፈትበታል እንጂ ለክስ የማስረጃነት ውጤት ባልኖረው ነበር፤ የውርስ ማጣራት ሪፕርቱ በመደበኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠበትና በድጋሚ ክርክር የማይቀርብበት ነው ከተባለም የስር ፍርድ ቤት ከመጀመሪያው ክሱን መቀበል ወይም ውሳኔ መስጠት አልነበረበትም፤ በአንድ ተከራካሪ ወገን የተቆጠረ ማስረጃ የማይሰማው ህጋዊ ምክንያት ሲኖር ብቻ በመሆኑ ምስክሮችን ሳናሰማ የተሰጠ ፍርድ የአመልካቾችን ማስረጃ የማሰማት መብታችንን ያላከበረ ነው፤ ክርክር የቀረበበት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 4 የቤት ቁጥር 777 የሆነው ቤት የቦታ ምሪት የተካሄደው 1ኛ አመልካችና አቶ ሙለጌታ ታምሬ ከመጋባታቸው በፉት ቢሆንም ቤቱ የአሁኑን ቅርፅ የያዘው እና የተጠናቀቀው ከጋብቻቸው በኋላ ነው፤
የተሰራውም ከባንክ በተገኘ ብድር ሲሆን እዲው ከነወለደ ብር 25,540,18 የተከፈለው በ1ኛ አመልካች ነው፤ በቤቱ ግንባታ ላይ የተጠሪዎች እናት ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ አላደረጉም፤ በንብረት መፈራት ምንም አስተዋፅኦ ያላደረገ ተጋቢ ንብረት እንዱካፈል ማድረግ በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 40 (1) ስር የተቀመጠውን የንብረት ባለቤትነት መብት የሚጥስ መሆኑን አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፤
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ውሳኔዎችን በመሻር የውርስ አጣሪ ሪፕርት በፍርድ ቤት ቢፀድቅም ባይፀድቅም እንደ ማስረጃ ተቃውሞ ቀርቦበት በተቃራኒ ማስረጃ ሉስተባበል የሚችል ነው ተብል ይወሰንልን። እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ያቀረብነውን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ በህግ መሰረት እንደገና ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩ ይመለስልን በማለት አቅርበዋል።
የሰበር አጣሪ ችልትም የአመልካችን ቅሬታ መርምሮ በፍርድ ቤት የፀደቀ የውርስ አጣሪ ሪፕርት ላይ በክፍፍል ጊዜ የሚነሳ ክርክር በፍ/ብ/ህ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/5 ድንጋጌ መሰረት በድጋሚ የቀረበ ስለሆነ ተቀባይነት ያለው አይደለም የተባለበትን አግባብ በሰበር መዝገብ ፤169570 ከተሰጡት ውሳኔዎች አንፃር ተገቢነቱ መጣራት ያለበት በመሆኑ ተጠሪዎች መልስ እንዱቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪዎች በህዲር 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ አመልካቾች በውርስ አጣሪ ሂደቱ ላይ አንድ አይነት መከራከሪያና አንድ አይነት ማስረጃ በማቅረብ እልባት ያገኘውን ጉዲይ እንደገና እንዱታይ ክርክር አቅርበዋል። የስር ፍርድ ቤት በውርስ ማጣራት ሂደቱ ላይ ክርክር ያደረጉት አንድ አይነት ተከራካሪዎች መሆናቸውን አሁንም ይዘው የቀረቡት ክርክር አንድ አይነት መሆኑን በመጥቀስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/5 ላይ የተመለከቱ መርሆዎችን የሚጥስ ነው በማለት ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ ነው።
የስር ፍርድ ቤት ድምዲሜ ላይ ከመድረሱ በፉት ዋናውን ውርስ የተጣራበት መዝገብ አስቀርቦ በክርክሩ የተነሳውን ፍሬ ነገርና ማስረጃ አንድ አይነት መሆኑን በሚገባ በማገናዘብ የሰጠው ውሳኔ ተገቢነት ያለው ነው። በስር ፍርድ ቤት ያቀረብነው አቤቱታ በፍርድ ቤት የፀደቀውን የውርስ አጣሪ ሪፕርት እንዱሁም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/.1020 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎች መሰረት የውርስ ሀብት ክፍፍል እንዱደረግልን እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 378 መሰረት ፍርድ እንዱፈፀምልን አይደለም። አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ምስክር ያልተሰማላቸው በውርስ ክፍፍለ ክርክር ላይ ያነሷቸውን መከራከሪያዎች በሙለ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ በማቅረባቸው የተለወጠ አዱስ ነገር የላለ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት ነው። በመሆኑም ችልቱ የአመልካቾችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ አድርጎ ያሰናብተን በማለት ጠይቀዋል።
አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ በታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም የተጻፈ አቅርበዋል።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን አኛም ያስቀርባል ሲባል የተያዘውን ጭብጥ ከግራቀኙ ክርክር፤ በስር ፍርድ ቤት ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እና ከተገቢው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነው የተጠሪዎች እናት እና ተጠሪዎችን ጨምሮ ከ2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች አባት የውርስ ሐብት ሲጣራ የአሁን 1ኛ አመልካች የክርክሩ ተሳታፉ ሆነው ለክርክሩ መሰረት የሆነው ቤት የተጠሪዎች እናት የውርስ ሐብት ድርሻ የለበትም። ቤቱ የ1ኛ አመልካች እና የሟች ሙለጌታ ታምሬ የባል እና ሚስት ንብረት ነው የሚል ክርክር አቅርበው ውርሱ በተጣራበት መዝገብ ላይ ይህ ክርክር በጭብጥነት ተይዞ እና ማስረጃ ተሰምቶ የውርስ ሐብት ነው በሚል ተረጋግጦ የውርስ አጣሪ ሪፕርት በማጽደቅ ውሳኔ መሰጠቱ በአመልካቾች የተካደ አይደለም። አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩት የውርስ አጣሪ ሪፕርት አፈጻጻም የሚጠየቅበት ሳይሆን እንደማስረጃ የሚያገለግል እና በልላ ማስረጃ ሉስተባበል የሚችል ነው የሚል ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ተጠሪዎች ያቀረቡት ጥያቄ በውርስ አጣሪ ሪፕርት መሰረት የውርስ ሐብት የክፍፍል ውሳኔ እንዱሰጥ እንጂ ቀጥታ በውርስ አጣሪ ሪፕርት መሰረት ያቀረቡት የአፈጻጸም ጥያቄ የለም። ስለዚህ የውርስ አጣሪ ሪፕርትን መሰረት አድርገው ተጠሪዎች አፈጻጸም እንደጠየቁ በማድረግ አፈጻጸም ሉጠይቁ አይችለም የሚለው የአመልካቾች ክርክር ተገቢነት ያለው አይደለም።
ላላው የአመልካቾች የውርስ አጣሪ ሪፕርት ከማስረጃ ያለፈ ውጤት የለውም የሚለው ክርክርም ቢሆን የውርስ አጣሪ ሪፕርት የጸደቀበት ውሳኔ ይዘት ማለትም በውርስ ማጣራቱ ሂደት ተሳታፉ የነበሩ ወገኖች ያነሷቸው ክርክሮች እና ክርክሮቹ በማስረጃ ተጣርተው ድምዲሜ የተደረሰባቸው መሆን ያለመሆኑ የሚወስነው ይሆናል። ይህም ማለት በውርስ ማጣራት ሂደት ተሳታፉ የነበሩ ወገኖች የተለያዩ ክርክሮችን አንስተው ውርሱ በተጣራበት መዝገብ ክርክሮቹ በጭብጥነት ተይዘው እና ማስረጃ ተሰምቶ ድምዲሜ ላይ ከተደረሰ የውርስ አጣሪ ሪፕርቱ የጸደቀበት ውሳኔ ከማስረጃ ያለፈ ውጤት ይኖረዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ እና በላልች መዝገቦች የህግ ትርጉም የተሰጠበት ጉዲይ ነው። በልላ በኩል የውርስ አጣሪ ሪፕርት ላይ ተሳታፉ ያልነበረ እና ክርክሩን ያላቀረበ ወገን ደግሞ በውርስ አጣሪ ሪፕርቱ ላይ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት መቃወሚያ ማቅረብ ሳይጠበቅበት በክፍፍል ወቅት ክርክሩን ማቅረብ ስለማይከለከል በዚህ ጊዜ የውርስ አጣሪ ሪፕርቱ የማስረጃ ዋጋ ብቻ ይኖረዋል። በመሆኑም በውርስ ማጣራት ሂደት ተሳታፉ የነበሩ ወገኖች በውርስ ማጣራት መዝገብ ላይ በክፍፍል ወቅት ሉነሳ የሚችል ክርክር ሁለ አስቀድመው አንስተው ክርክራቸው በማስረጃ ተጣርቶ ውሳኔ ከተሰጠ ይህ የውርስ አጣሪ ሪፕርት የጸደቀበት ውሳኔ ክርክር ተደርጎ ድምዲሜ ላይ ከተደረሰባቸው ነጥቦች አንጻር የመጨረሻ ውጤት ይኖረዋል ማለት ነው።
በዚህ መሰረትም አመልካቾች ለክርክሩ መሰረት የሆነው ቤት የ1ኛ አመልካች እና የሟች ሙለጌታ ታምሬ የባል እና ሚስት ንብረት ነው በሚል የሚያቀርቡት ክርክር አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ እና የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5 መስፈርትን ያሟላል ወይስ አያሟላም? የሚለውን ስንመለከት በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
5(1) ላይ እንደተመለከተው በሕግ ሥልጣን የተሰጠው ማናቸውም ፍርድ ቤት ክርክሩን ተቀብል የመጨረሻ ፍርድ ከሰጠ በኋላ ቀድሞ በፍርድ የተወሰነው ክርክር ሥረ-ነገርና የተያዘው ጭብጥ አንድ ዓይነት ከሆነ በክርክሩ ላይ የነበሩት ወይም ከተከራካሪዎቹ መብት ያገኙ ሦስተኛ ወገኖች በዚያው ነገር ሁለተኛ ክስ ማቅረብ አይችለም። ይህም ማለት በድንጋጌው መሰረት ጉዲዩ አስቀድሞ በፍርድ አልቋል ለማለት የተዘረዘሩት አራት መስፈርቶች በአንድነት መሟላት አለባቸው። የመጀመሪያው መስፈርት ጉዲዩን የተመለከተው በሕግ ሥልጣን የተሰጠው ማናቸውም ፍርድ ቤት መሆኑ ነው። በሕግ ሥልጣን የተሰጠው የሚለው አስቀድሞ ጉዲዩ የታየው በሕግ ዲኝነት ለመስጠት ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ወይም ዲኝነት ነክ አካል መሆኑን ለማመላከት ነው። ሁለተኛው መስፈርት አስቀድሞ በፍርድ ቤት የተሰጠው የመጨረሻ ፍርድ መሆን አለበት የሚለው ነው። ፍርድ ቤቱ ክርክሩን አይቶ ጉዲዩ ላይ የመጨረሻ እልባት ወይም ውጤት የሰጠበት መሆን እንዲለበት የሚያስረዲ መስፈርት ነው። ሦስተኛው መስፈርት አስቀድሞ ፍርድ ያረፈበት ጉዲይ ሥረ-ነገሩና ጭብጡ አሁን ከተያዘው ጉዲይ ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለበት የሚለው ነው። የክርክሩ መነሻ ጉዲይ አንድ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ፍርድ ቤቱ በጭብጥነት የመረመረው ጉዲይ አሁን በተያዘው ክርክርም በጭብጥነት ተይዞ የሚመረመር ከሆነ ውጤቱ አስቀድሞ ፍርድ ያረፈበት ይሆናል። ሥረ-ነገሩ ተመሳሳይ ሆኖ ነገር ግን የሚያዘው ወይም የተያዘው ጭብጥ የተለያየ ከሆነ በተያዘው ጭብጥ ላይ የቀደመ ፍርድ ባለመኖሩ ጉዲዩ በፍርድ እንዲለቀ ሳይቆጠር ክርክሩ ቀጥል ፍርድ ሉያርፍበት የሚችል ጉዲይ ነው። በሕጉ ላይ የተቀመጠው አራተኛው መስፈርት የተከራካሪዎች ወይም ከተከራካሪዎች መብት ያገኙ ሦስተኛ ወገኖች ተመሳሳይ መሆን እና በእነርሱ መካከል ያለ ክርክር መሆኑ ነው። የዚህ መስፈርት መነሻ ፍርድ የአስገዲጅነት ሀይል ሆነ ውጤት የሚኖረው በተከራካሪዎች መካከል ብቻ ነው የሚል ነው። ከተከራካሪዎች ውጭ ፍርደን በመያዝ መብት ማቋቋም ሆነ ማስፈጸም አይቻልም። ፍርድ ቤት ጉዲዩን የሚመረምረው ሆነ ፍርድ የሚሰጠው ከተከራካሪዎች መካከል የተሻለ መብት ያለው ማን ነው ከሚለው ነጥብ አኳያ ብቻ ነው።
በጉዲዩ ላይ ያላቸው መብት በፍርድ ቤቱ ሳይመረመር እና የመደመጥ ሆነ የመከላከል መብታቸው ሳይከበር ተከራካሪ ያልሆኑ ወገኖች ላይ ፍርደ አስገዲጅነት አለው ልባል አይችልም። የተከራካሪዎች ተመሳሳይነት የሚለው ከተከራካሪዎች በሕግ ሆነ በውል መብት የተላለፈላቸውን ሦስተኛ ወገኖች የመብታቸው ምንጭ የቀድሞው ክርክር ላይ ተከራካሪ በሆኑት ወገኖች ልክ በመሆኑ በእነዚህ ወገኖች ላይም ጉዲዩ አስቀድሞ በፍርድ እንዲለቀ የሚያስቆጥር ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ በውርስ ማጣራት መዝገብ ላይ አመልካቾች ለክርክሩ መሰረት የሆነው ቤት የ1ኛ አመልካች እና የሟች ሙለጌታ ታምሬ የባል እና ሚስት የጋራ ንብረት ነው የሚል ክርክር አቅርበው ይህ ክርክር በማስረጃ ተጣርቶ ተቀባይነት አለማግኘቱን የስር ፍርድ ቤት ለቅሬታ መነሻ በሆነው ውሳኔ ላይ አስፍሯል። በአመልካቾችም የተካደ አይደለም። ይህም ማለት አመልካቾች በውርስ ሀብት ክፍፍል ወቅት እያነሱ ያለት ክርክር አስቀድሞ ውርሱ ሲጣራ በጭብጥነት ተይዞ ውሳኔ ያገኘ ጉዲይ ነው። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት አመልካች ለክርክሩ መሰረት የሆነው ቤት ላይ የተጠሪዎች እናት ድርሻ የላቸውም በሚል ክርክር ያቀረቡት ለቀረበባቸው የክፍፍል ክስ መልስ ሲሰጡ በመሆኑ ከውሳኔ በፉት ክሱን በብይን ውድቅ የሚያደርግበት እድል ባይኖረውም በውሳኔ ወቅት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
5(1) መሰረት ጉዲዩ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው በማለት የአመልካቾችን ክርክር ውድቅ ማድረጉ እና ይኼው በይግባኝ መጽናቱ ሕጉን የተከተለ በመሆኑ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችልት በየካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም በመዝገብ እንዱሁም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም በመዝገብ የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የነበረው ክርክር ያስከተለውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻቻለ።