No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 26 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር) እንዲሻው አዲነ ተሾመ ሽፈራው መላኩ ካሳዬ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች፡- 1ኛ. አቶ መስፍን ባልቻ አሩሲ 2ኛ. አቶ ተሾመ ባልቻ አሩሲ 3ኛ. አቶ አለማየሁ ባልቻ አሩሲ 4ኛ. አቶ ግዛው ባልቻ አሩሲ 5ኛ.አቶ ብርሃኑ ባልቻ አሩሲ አመልካቾች/ጠ ጌታቸው ታደሰ - ቀረቡ 6ኛ. አቶ ሚሉዮን ባልቻ አሩሲ 7ኛ. ብርክቲ ባልቻ አሩሲ ተጠሪዎች 1ኛ. አቶ ሙለጌታ አለሙ - የተጠሪዎች ጠበቃ መስፍን አለማየሁ - ቀረቡ 2ኛ. አቶ ጌታቸው ወዲጆ 3ኛ. አቶ ደስታ ጌታቸው 4ኛ. ወ/ሮ ገነት ጌታቸው 5ኛ. አቶ ደበበ ጌታቸው 6ኛ. ወ/ሮ ካሰች አለሙ 7ኛ. አቶ ሳሙኤል ወርቁ 8ኛ. ወ/ሮ አስቴር ወርቁ 9ኛ. አቶ ጸጋዬ ወርቁ 10ኛ. ወ/ሮ መአዛ ወርቁ 11ኛ. አቶ በቀለ ኤደኤ 12ኛ. ወ/ሮ ጸሀይ ኤደኤ 13ኛ. አቶ ቀነኒ ኤደኤ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የውርስ ሐብትን ለማስለቀቅ በቀረበ ክስ ላይ የተነሳ የይርጋ ክርክርን የሚመለከት ነው። ለዚህ ሰበር ቅሬታ መነሻ የሆነው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በህዲር 20 ቀን 2015 ዓ.ም የስር ፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሰጠው ብይን ላይ የቀረበውን ቅሬታ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ በማድረግ የሰጠው ትእዛዝ ነው። ጉዲዩ በተጀመረበት በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ።
አመልካቾች በሐምል 26 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ ወላጅ አባታችን በጥር 12 ቀን 1993 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። አባታችን በመጋቢት 04 ቀን 1983 ዓ.ም በአፈጻጸም የተረከቡትን በቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 11 የሚገኝ ቤት እና የእርሻ መሬት ተጠሪዎች ባልታወቀ ምክንያት ስለያዙ በማንእጅ እንደሚገኝ ፍርድ ቤቱ አጣርቶ ተጠሪዎች ይዞታውን እንዱያስረክቡ ወይም ተጠሪዎች በይዞታው የተቀበለት ካሳ እና ምትክ ቦታ ካለ እንዱመልሱ ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎች በነሐሴ 07 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የውርስ ሀብት ነው የተባለው ንብረት ከሟች እጅ ከወጣ ከ30 ዓመት በላይ የሆነው በመሆኑ ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ሟች እስከ ጥር 12 ቀን 1993 ዓ.ም ድረስ የውርስ ሀብት ነው በተባለው ንብረት የተገለገለ ሲሆን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት ድረስ ያለው ጊዜ ሲቆጠር 20 ዓመት ይሆናል። የውርስ ሀብት ሕጋዊ ወራሽ ባልሆነ ሰው ተይዞብኛል የሚል ክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ 10 ዓመት ነው። አመልካቾች አባታቸው ሲሞቱ ልጆች መሆናቸውን እና አባታቸው ሲሞቱ የመጨረሻው ልጅ እድሜ 8 ዓመት የነበረ መሆኑን በመግለጽ የተከራከሩ ቢሆንም የስምንት አመት ልጅ 18 ዓመት የሚሞላው ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ነው። ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ቢቆጠር እንኳን ክሱ የቀረበው ከ10 ዓመት በኋላ ስለሆነ ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት የአመልካቾችን ክስ በብይን ውድቅ አድርጓል። አመልካቾች ይህንን ብይን በመቃወም የይግባኝ ቅሬታ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ሟች ሲሞቱ የአመልካቾች እድሜ ስንት እንደነበር የ8ኛ ክፍል የምስክር ወረቀት በማስቀረብ ካጣራ በኋላ የይግባኝ ቅሬታቸውን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 337 መሰረት ውድቅ በማድረጉ የሚከተለውን የሰበር ቅሬታ አቅርበዋል።
አመልካቾች በታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር ቅሬታ ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካቾችን እድሜ ለማጣራት ማስረጃ ያስቀረበው ተጠሪዎች የእድሜ ክርክር ባላቀረቡበት ነው። አመልካቾች አባታችን በክርክር የረታበት ማስረጃ እጃችን ላይ ስላልነበር የውርስ ሀብቱን ለመጠየቅ አልቻልንም። ንብረቱ የአባታችን መሆኑን ያወቅነው ክስ ከማቅረባችን ከአንድ ወር በፉት ነው። በመሆኑም ክሱ በይርጋ ይታገዲል መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልን በማለት ጠይቀዋል።
የሰበር አጣሪ ችልት የአመልካቾችን ቅሬታ መርምሮ ክሱ በ10 ዓመት ይርጋ ይቋረጣል መባለ ተገቢ መሆን እለመሆኑን ለማጣራት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ ትእዛዝ ተሰጥቷል።
ተጠሪዎች በመጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ በስር ፍርድ ቤት ክሱ በሚሰማበት ወቅት ሟች ሲሞቱ የመጨረሻው ልጅ እድሜ 8 ዓመት ነበር ይበለ እንጂ የሟች የመጨረሻ ልጅ የተወለደው ከ1983 ዓ.ም በፉት ነው። ፍርድ ቤቱ እውነታውን ለማጣራት ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 4 ማህደር በማስቀረብ ማየት ይችላል። በመሆኑም በስር ፍርድ ቤቶች ክሱ በይርጋ ይታገዲል በመባለ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ያስቀርባል ሲባል የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ በስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እና ከተገቢው ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
እንደመረመርነው ተጠሪዎች የአመልካቾች የውርስ ሐብት ይለቀቅልን ክስ በይርጋ ይታገዲል የሚለት ለክርክሩ መሰረት የሆነውን ቤት እና የእርሻ መሬት አባት ከሞቱ ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ይዘነዋል በሚል ነው። ተጠሪዎች ይህንን ቤት እና የእርሻ መሬት ሟች ከዚህ አለም በሞት ከተለዩበት ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ መያዛቸው በአመልካቾችም የታመነ ፍሬ ነገር መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት ብይን መረዲት ይቻላል። ይሁን እንጂ አመልካቾች አባታቸው ሲሞቱ የመጨረሻው ልጅ እድሜ 8 ዓመት የነበረ በመሆኑ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል እድሜ ላይ አልነበርም በማለት ክሱ በይርጋ እንደማይታገድ ገልጸው ተከራክረዋል። የውርስ ሐብት በያዘ ሰው ላይ ክስ ሲቀርብ ተፈጻሚነት የሚኖረው የይርጋ ድንጋጌ የፍ/ሕ/ቁጥር 1000 ሲሆን በዚህ ድንጋጌ የ3 ዓመት እና የ15 ዓመት የይርጋ ጊዜዎች ተመልክተዋል።
ይህ በፍ/ሕ/ቁጥር 1000 ላይ የተመለከተው የይርጋ ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚኖረው ወራሽ በሆኑ ተከራካሪዎች መካከል መሆኑን ነገር ግን ወራሽ በሆኑ እና ባልሆኑ ወገኖች መካከል ክርክሩ የሚደረግ ከሆነ ተፈጻሚነት ያለው የፍ/ሕ/ቁጥር 1000 ድንጋጌ ሳይሆን በፍ/ሕ/ቁጥር 1845 ላይ የተመለከተው የ10 ዓመት የይርጋ ድንጋጌ መሆኑን የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ (በቅጽ 11 የታተመ) እና በላልች መዝገቦች የህግ ትርጉም የሰጠበት ጉዲይ ነው።
በተጨማሪም ሟች ሲሞት ወይም የውርስ ንብረቱ በተከሳሽ ሲያዝ ህጻናት የነበሩ የሟች ወራሾች በመብታቸው መስራት እና ንብረቱ እንዱለቀቅ ክስ ማቅረብ የሚችለት እድሜቸው 18 ዓመት ሲሞላ ነው። የውርስ ንብረቱ ሲያዝ አካለ መጠን ላላደረሱ የሟች ልጆችም ተፈጻሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ 10 ዓመት መሆኑን እና ይህ የ10 ዓመት ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው እድሚአቸው 18 ዓመት ከሞላ ጊዜ ጀምሮ መሆኑን የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ በየካቲት 25 ቀን 2012 ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ(ያልታተመ) የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
በተያዘው ጉዲይ የተከራካሪዎች ማንነት ሲታይ አመልካቾች የሟች ወራሾች ሲሆኑ ተጠሪዎች ደግሞ የሟች ወራሾች አይደለም። ይህም ክርክሩ የሟች ወራሽ በሆኑ እና ባልሆኑ ወገኖች መካከል የሚደረግ መሆኑን ስለሚያሳይ የስር ፍርድ ቤት ተፈጻሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ 10 አመት ነው ማለቱ ተገቢ ነው። ይህ የ10 ዓመት ጊዜ ከመቼ ጀምሮ መቆጠር አለበት የሚለው ሲታይ ማስረጃ የመቀበል እና የመመዘን ስልጣን ያለው የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካቾችን የትምህርት ማስረጃ በማስቀረብ አመልካቾች 18 ዓመት የሚሞላቸው መቼ እንደሆነ በማጣራት 18 ዓመት ከሞላቸው ጊዜ ጀምሮ ክስ እስካቀረቡት ያለው ጊዜ ሲቆጠር ከ10 ዓመት በላይ በመሆኑ የአመልካቾችን ክስ በይርጋ ውድቅ በማድረግ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል። በመሆኑም የአመልካቾች ክስ በ10 ዓመት ይርጋ የታገደ ነው መባለ የተጠቀሱትን የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔዎች የተከተለ ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ስላልተገኘ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
1ኛ. የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በግንቦት 23 ቀን 2014 ዓ.ም እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በህዲር 20 ቀን 2015 ዓ.ም የሰጡት ብይን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል።
2ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት የነበረው ክርክር ያስከተለውን ወጪ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻቻለ።