No summary available.
መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ደጄኔ አያንሳ ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ ሀብታሙ እርቅይሁን አመልካች፡- 1ኛ. ሳምራዊት አረጋ ጠበቃ ደሳለኝ የኔአካል - ቀረቡ 2ኛ. መቅደስ የሻው (ሞግዚት ሳምራዊት አረጋ) ተጠሪ፡- ደረሰ ታደሰ - ቀርቧል **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የውርስ ንብረት ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክሱ በቀረበበት በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ወል ዞን መስተዲድር በወግዱ ወረዲ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ እና በሰበር ክርክሩ የላለት አብረሃም አሰፊ የተባለት ግለሰብ በተከሳሽነት ተከራክረዋል።
አመልካቾች የካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ተጠሪ እና 2ኛ ተከሳሽ የነበሩት አብርሃም አሰፊ የተባለት ግለሰብ አዋሳኙ እና መጠኑ በክሱ ላይ የተመለከተውን የሟች እናታቸው የሖነውን የእርሻ መሬት እና በ2013 ዓ.ም እና 2014 ዓ.ም የውርስ ይዞታ ከሆነው መሬት የተገኘውን የመሬት አላባ የውርስ ድርሻቸውን እንዱያካፍላቸው ፤ እንዱሁም የያዙብንን ከሟች እናታችን በኑዛዜ የተላለፈልንን 75 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ለቀው እንዱያስረክቡን በማለት ጠይቀዋል።
ተከሳሾቹም መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የሟች እናታችንን የእርሻ መሬት አልከለከልናቸውም ይውሰደ ፤ ሟች እናታቸው ከእናቷ የወረሰችው መሬት ሟች በህይወት እያለች 75 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት የሰራች ሲሆን ቀሪውን ይዞታ በሟቿ እና በሥር ተከሳሾች መካከል ተደርጎ በፍርድ ቤት በፀደቀ ስምምነት ለ1ኛ ተከሳሽ ቁመቱ 42 ሜትር ወርደ 6 ሜትር ፤ ለ2ኛ ተከሳሽ ቁመቱ 25 ሜትር ወርደ 8 ሜትር የሆነ ቦታ ለቤት መስሪያ በስምምነት ከተላለፈልን ውጭ በእጃችን የለም። እናታችን በሕይወት እያለች የተላለፈልን ይዞታ ልንጠየቅ አይገባም።
አመልካቾች በኑዛዜ ተላልፍልናል የሚለት ሽማግላ ውለን ካፀደቀው ወዱህ ስላላወቅነው ኑዛዜው ይፍርስልን። የ2013 ዓ.ም አላባን በአውድማ ተካፍለው የወሰደ ሲሆን የ2014 ዓ.ም እኩል አራሹ እጅ ስለሚገኝ እኛም አልወሰድንም በማለት ተከራከረዋል።
ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙ በተማመኑበት ጉዲይ ላይ ከፉል ፍርድ ሰጥቶ በአከራካሪዎቹ ጉዲዮች ላይ የአመልካቾችንና የሥር ተካሳሾችን ክርክር እና ማስረጃ ካዲመጠ በኋላ ለክርክር መነሻ የሆነው 75 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ሟች ለአመልካቾች በማስተላለፍ ያደረጉት ኑዛዜ የሥር ተከሳሾችን ከውርስ የነቀለበትን ምክንያት በግልጽ ስለማያመለክት ኑዛዜው ፈራሽ ሆኖ አመልካቾች በፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 839/3 ድንጋጌ መሰረት በኑዛዜ ጠቅላላ ስጦታ እንደተደረገላቸው ተቆጥረው ከሥር ተከሳሾች ጋር በጋራ እንዱካፈለ ወስኗል። አመልካቾች ኑዛዜው ፈርሶ አከራካሪውን 75 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ግራ ቀኙ እኩል ይካፈለ በማለት የተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ጉዲዩን የተመለከተው የደቡብ ወል መስተዲድር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ እናት ካላቸው ንብረት አንፃር አንድ ቤት ለአመልካቾች መናዘዛቸው ከውርስ መንቀልን ማስከተል አለማስከቱን ለማጣራት ያስቀርባል በማለት የሥር ተካሳሾችን ክርክር ሰምቶ ሟች ወ/ሮ የሮም አሰፊ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም በወግዱ ወረዲ ፍትህ ጽ/ቤት ባደረጉት ኑዛዜ አከራካሪውን 75 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት በፍትሐ ብሕር ህጉ ቁጥር 882 መሰረት የተናዘዙ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን የሥር ተከሳሾች በጽሐፍ መልሳቸውም ሆነ በቃል ክርክር ወቅት ኑዛዜው ከውርስ ይነቅለናል የሚል ክርክር አላቀረቡም። አቅርበዋል ቢባል እንኳን የሟችን ይዞታ መሬት ግራ ቀኙ እንዱካፈለ ከመወሰኑም ባሻገር ሟች የሮም አሰፊ ለሥር ተከሳሾች የቤት መስሪያ ቦታ የሰጧቸው መሆኑ ተረጋግጦ የውርስ ንብረት አይደለም የሚል ውሳኔ ተሰጥቷል። የቤት መስሪያ ቦታ የተሰጠው እና ኑዛዜ የተደረገው በተመሳሳይ አመት ከመሆኑ አንፃር የሟች ፍላጎት ሉፈፀም ስለሚገባው ኑዛዜ መሻር የለበትም። ኑዛዜው ፈርሶ ግራ ቀኙ እኩል ሉካፈለ ይገባል ሲል የወግዱ ወረዲ ፍርድ ቤት የሰጠውን የውሳኔ ክፍል በአብላጫ ድምጽ በመሻር የተቀረውን የውሳኔ ክፍል በማጽናት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኙት ተጠሪ ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ጉዲዩን የተመለከተው ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ በሰጠው ውሳኔ የሥር ተከሳሾች በሥር ፍርድ ቤት ኑዛዜው ፈራሽ ተደርጎ ቤቱ የጋራ እንዱባልላቸው ክርክር ያቀረቡ በመሆኑ ኑዛዜው በየትኛው ህጋዊ ምክንያት ፈራሽ ላሆን ይችላል የሚለው ጭብጥ ፍርድ ቤት በራሱ የሚመረምረው ጉዲይ ሆኖ እያለ የደቡብ ወል መስተዲድር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ኑዛዜው ከውርስ ይነቅለኛል በሚል ያቀረቡት ክርክር የለም ማለቱ አግባብነት የለውም። በልላ በኩል አመልካቾች ሟች ለሥር ተከሳሾች ከሰጠችው ንብረት ውጭ ላላ ንብረት ለሥር ተከሳሾች የሰጠች ለመሆኑ ያቀረቡት ክርክርም ሆነ ማስረጃ የላለ ሲሆን ሟች የቤት መስሪያ ቦታ ሰጥታለች ቢባል እንኳን በክርክር ሂደት በፍርድ ቤት ውሳኔ የተገኘ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሟች ካላቸው ንብረት ላይ በፈቃዲቸው በኑዛዜ እንዲስተላለፈት የውርስ ድርሻ የሚቆጠር ባለመሆኑ ሟች የተጠሪን ድርሻ ለይታ በኑዛዜ የሰጠች መሆኑ ባልተረጋገጠበት ወይም በፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 1123/3 መሰረት ለተጠሪ በቂ ውርስ ሀብት ድርሻ መኖሩ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ኑዛዜው ተጠሪን አይነቅልም መባለ ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሶ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የወረዲ ፍ/ቤት ውሳኔን አጽንቷል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት አመልካቾች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ችልቱም በሥር ተከሳሾች ኑዛዜው ይነቅለናል የሚል ግልጽ መከራከሪያ ባልቀረበበት ፍርድ ቤት በራሱ ማንሳት ይችላል ከተባለ አመልካቾች ሟች ካላቸው ንብረት አኳያ ኑዛዜው የሚነቅል መሆን አለመሆኑን አንስቶ የመከራከር መብት ማጣበብ አለማጣበቡን ፤ ተጠሪ ኑዛዜው ፈራሽ ላሆን ይገባል በማለቱ ምክንያት ብቻ አመልካች ኑዛዜው የማይፈርስበትን ማንኛውንም ምክንያት ፍርድ ቤቱ ሉያነሳብኝ ይችላል በሚል መላምት መልስ እንዱሰጥ በሚያደርግ መልኩ ፍርድ ቤት መንቀልን ማንሳት ይችላል የመባለን አግባብነት ፤ ይህም የሚታለፍ ከሆነ ይነቅላል አይነቅልም የሚለው ጭብጥ ክርክር ተደርጎበት በማስረጃ ተጣርቶ መወሰን አልነበረበትም ወይ የሚለውን ለማጣራት ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ በሰበር አቤቱታው ላይ መልስ እንዱሰጡ በማድረግ ጉዲዩ እንደመረመረው፡- ተጠሪ በሟች የተደረገው ኑዛዜ ፈራሽ ተደርጎ ለክርክር መነሻ የሆነው ቤት የጋራ እንዱባል በማለት ያቀረቡት ክርክር ኑዛዜውን የተቃወሙ መሆኑን የሚያመለክት ነው። ተጠሪ የሟች ልጅ መሆናቸው አከራካሪ እስካልሆነ ድረስ ኑዛዜው ከውርስ በዝምታ የሚነቅል መሆን አለመሆኑ ከአጠቃላይ የኑዛዜ ሰነድ ሕጋዊነት ጋር ተያይዞ የሕግ ግምቱ በፍርድ ቤቶች በፈፃሚ ከሚሆን በቀር አንደኛው ወገን ስለኑዛዜው መንቀል አለመንቀል በግል ክርክር እንዱያቀርብ የሚገደድበት ምክንያት አይኖርም።
ተጠሪ የቤት መስሪያ ቦታ ያገኙት በፍርድ ቤት በተደረገ ክርክር በውሳኔ እንጅ በሟች ፍላጎት በተደረገ ሥጦታ ካለመሆኑም በላይ በአመልካቾች በኩል ሟች በህይወት እያለች ለተጠሪ ድርሻ የሚሆን የቤት መስሪያ ቦታ በፈቀዶ ሰጥታዋለች የሚል ክርክር ያልቀረበ ሲሆን በዚህ አግባብ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር የለም። በሟች ወ/ሮ የሮም አሰፊ የተደረገው ኑዛዜ ተጠሪን ከውርስ የሚነቅል በመሆኑ ፈራሽ ሆኖ ለክርክሩ መነሻ የሖነው 75 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ግራ ቀኙ እኩል እንዱካፈለ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በሚል የይግባኝ ሰሚ ችልቱን ውሳኔ አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የወግዱ ወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት እንዱሁም የሰበር ሰሚ ችልቱ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ሆኖ ቅሬታው በአጭሩ፡- ተጠሪ በወረዲ ፍርድ ቤትም ሆነ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክርክር ከቀረበበት ቤትና ቦታ ልካፈል ይገባል ከማለት ውጪ ኑዛዜው ከውርስ ይነቅለኛል የሚል ክርክር ሳያቀርብ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሥር ፍርድ ቤት ያልተነሳን መከራከሪያ ማቅረቡ የፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 329 ድንጋጌን ይቃረናል በማለት ያቀረብነውን የሰበር አቤቱታ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ተቀብል ችልቱም በሥር ተከሳሾች ኑዛዜው ይነቅለኛል የሚል ግልጽ መከራከሪያ ባልቀረበበት ፍርድ ቤት በራሱ ማንሳት ይችላል ከተባለ አመልካቾች ሟች ካላቸው ንብረት አኳያ ኑዛዜው የሚነቅል መሆን አለመሆኑን አንስቶ የመከራከር መብት ማጣበብ አለማጣበቡን ፤ተጠሪ ኑዛዜው ፈራሽ ላሆን ይገባል በማለቱ ምክንያት ብቻ አመልካች ኑዛዜው የማይፈርስበትን ማንኛውንም ምክንያት ፍርድ ቤቱ ሉያነሳብኝ ይችላል በሚል መላምት መልስ እንዱሰጥ በሚያደርግ መልኩ ፍርድ ቤት መንቀልን ማንሳት ይችላል የመባለን አግባብነት፤ ይህም የሚታለፍ ከሆነ ይነቅላል አይነቅል የሚለው ጭብጥ ክርክር ተደርጎበት በማስረጃ ተጣርቶ መወሰን አልነበረበትም ወይ የሚለውን ለማጣራት ጉዲዩ ያስቀርባል ቢልም የያዛቸውን ጭብጦች በአግባቡ ሳይመረምር የሰጠው ውሳኔ ሕግን የተከተለ አይደለም።
ለአመልካቾች የተላለፈው ቤት እና ቦታ ሟች ካላት በርካታ መሬት እና ቦታ ላይ አነስተኛ በመሆኑና ተጠሪ ከውርስ ሀብቱ ከ1/4ኛ ድርሻ በላይ ያገኘ በመሆኑ ለአመልካቾች የተደረገው ኑዛዜ ከውርስ የማይነቅለው አይደለም። ሟች እናታችን በህይወት እያለች የቤት መስሪያ ቦታ የሰጠችው ሲሆን ከእርሻ መሬቱም ድርሻውን አግኝቶ እያለ አከራካሪው ቤት የሟች ብቸኛ ንብረት እንደሆነ የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት የለውም። ተጠሪ ኑዛዜው የማይፀናበትን ምክንያት በመጥቀስ በወረዲ ፍርድ ቤት ያቀረበው መከራከሪያ ሳይኖር የወግዱ ወረዲ ፍርድ ቤት እና ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደረሱበት ድምዲሜ የፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉን ቁጥር 329 ድንጋጌን የሚቃረን ከመሆኑም በላይ ሟች ለተጠሪ ባደረገችው ስጦታ ያገኘውን የቤት መስሪያ ቦታ የውርስ ሀብት አካል አይደለም ካለ በኋላ ሟች ባደረገችው ኑዛዜ ለአመልካቾች የተላለፈውን 75 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት የውርስ ሀብት ነው በማለት ግራ ቀኙ እኩል እንድንካፈል መወሰኑ ኢፍትሀዊ ነው በማለት ሟች ያደረገችው ኑዛዜ ለፈርስ አይገባም ተብል እንዱወሰን ጠይቀዋል።
በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 ቁጥር 6(1) መሰረት ለሰበር ሰሚው ችልቱ የተመራው አቤቱታ በሰበር ሰሚ ችልቱ ተመርምሮ የግራ ቀኙ እናት ሟች ወ/ሮ የሮም አሰፊ ያደረጉት ኑዛዜ ተጠሪን ከውርስ ስለሚነቅል ሉፈርስ ይገባል ተብል መወሰኑ ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክር መሰረት ያደረገ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ተብል ተጠሪ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል።
ተጠሪ ሐምል 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፍ ባቀረቡት መልስ በወረዲ ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር ተከሳሾች የነበሩት ተጠሪ እና ወንድማቸው የሆኑት 2ኛ ተከሳሽ ሟች እናታቸው በኑዛዜ በዝምታ የነቀለቻቸው መሆኑን በመጥቀስ ኑዛዜው እንዱፈርስ ስለመጠየቃቸው ፤ ሟች የግራ ቀኙ እናት ወ/ሮ የሮም አሰፊ በህይወት ዘመናቸው ያላቸው ሀብት አከራካሪው ባለ 75 ክዲን ቆርቆሮ ቤት ብቻ ያፈሩ ሲሆን አመልካቾች ሟች ከዚህ ውጭ ላላ ተንቀሳቃሽም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ያላቸው ለመሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክርክር እና ማስረጃ ሳይኖር እና ተጠሪ በውርስ ያገኘሁት አንዲች ንብረት በላለበት በደፈናው ከፍተኛ ግምት ያለው ንብረት እንደወርሰኩ በማስመሰል የቀረበው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም። አንድ ተናዛዥ ወደ ታች የሚቆጠር ተወላጅን ከውርስ ለመንቀል በኑዛዜው ውስጥ ምክንያት መጥቀስ ተገቢ መሆኑ በሕጉ ተመልክቶ እያለ ሟች የጠቀሱት ምክንያት አለመኖሩ ተረጋግጦ የተሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም። ከሟች አያታቸው በጎጆ መውጫነት በሰጣቸው መሬት ላይ ከሟች እናታቸው ወ/ሮ የሮም አሰፊ ጋር ተካሰው ባደረጉት እርቅ ስምምነት መሰረት ያገኙት ቦታ የሟች አለመሆኑ እየታወቀ ከሟች እናታቸው በስጦታ ወይም በኑዛዜ እንደተሰጠ ከፍተኛ ግምት እንዲለው የውርስ ሀብት አድርጎ የሚቀርበው ቅሬታ አግባብነት የላለው በመሆኑ ሟች ያደረጉት ኑዛዜ ከ1/4ኛ በላይ ጉዲት ከማድረስ አልፍ ሙለ በሙለ ከውርስ የነቀለኝ በመሆኑ ለሰበር አቤቱታው ምክንያት የሆነው ውሳኔ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። አመልካቾች የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክር እና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ሲል የያዘዉን ጭብጥ እና በስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
ኑዛዜ ተናዛዡ በህይወት እያለ ከእሱ ሞት በኋላ ንብረቱን በሙለ ወይም በከፉል ለሚፈልጋቸው ሰዎች የሚያስተላልፍበት እና ከውርስ የሚነቀለትን ሰዎች ለይቶ የሚያስቀምጥበት የቃል መግለጫ ወይንም ሰነድ መሆኑን ከፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 857(1) ፤ 892 ፤ 909 ፤ 949 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል። አንድ ተናዛዥ ልጁን ወይንም ወደ ታች የሚቆጠር ተወላጅን ያለ በቂ እና አሳማኝ ምክንያት ከውርስ ከነቀለ ኑዛዜው ፈራሽ እንደሚሆን የፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 938(1) ይደነግጋል። ኑዛዜ በሕጉ የተመለከቱ ፍርማሉቲዎችንና ሁኔታዎችን አሟላቶ እስከተገኘ ድረስ የተናዛዡ ፍላጎት ማሳያ በመሆኑ ሉከበር ስለሚገባ ፈራሽ መሆን አለበት የሚለው ተከራካሪ ወገን ሉፈረስ ይገባል የሚልበትን ምክንያት መግለጽ አለበት።
በተያዘው ጉዲይ ሟች ወ/ሮ የሮም አሰፊ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም በወግዱ ወረዲ ፍትህ ጽ/ቤት ባደረጉት ኑዛዜ አከራካሪውን 75 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት በፍትሐ ብሕር ህጉ ቁጥር 882 መሰረት ለአመልካቾች የተናዘዙ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን የሥር ተከሳሾች አከራካሪው 75 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት አመልካቾች በኑዛዜ ተላልፍልናል የሚለት ሽማግላ ውለን ካፀደቀው ወዱህ ስላላወቅነው ኑዛዜው ሉፈርስ ይገባል ከማለት ባለፈ በጽሐፍ መልሳቸውም ሆነ በቃል ክርክር ወቅት ኑዛዜው ከውርስ ይነቅለናል የሚል ክርክር ያላቀረቡ ሲሆን ፤ የወግዱ ወረዲ ፍርድ ቤት ኑዛዜው የሥር ተከሳሾች የተነቀለበትን ምክንያት በግልጽ ስለማያመለክት ፈራሽ ሆኖ አመልካቾች በፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 839/3 ድንጋጌ መሰረት በኑዛዜ ጠቅላላ ስጦታ እንደተደረገላቸው ተቆጥረው ከሥር ተከሳሾች ጋር በጋራ እንዱካፈለ የወሰነው የሥር ተካሳሾች ኑዛዜው ከውርስ የነቀለ በመሆኑ ሉፈርስ ይገባል የሚል ምክንያት ባላቀረቡበት ሲሆን ተከሳሾቹ በምክንያትነት የጠቀሱት ኑዛዜውን አለማወቃቸውን ሲሆን ኑዛዜን አለማወቅ ለኑዛዜ መፍረስ በምክንያትነት በሕጉ አልተመለከተም።
የሥር ተከሳሾች ኑዛዜው ፈራሽ ላሆን ይገባል በማለታቸው ብቻ ኑዛዜው ፈራሽ ላሆን የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት ተለይቶ የክርክር ጭብጥ ባልሆነበት አመልካቾች ኑዛዜው የማይፈርስበትን ማንኛውንም ምክንያት ፍርድ ቤቱ ሉያነሳብን ይችላል በሚል ግምት ክርክር እንዱያቀርቡ ማድረግ አግባብነት የላለው የክርክር አመራር ከመሆኑም በላይ አከራካሪውን 75 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ለአመልካቾች በኑዛዜ ማስተላለፍ የሟች ወ/ሮ የሮም አሰፊ ፍላጎት በመሆኑ ሉከበር ሲገባው የወግዱ ወረዲ ቤት ኑዛዜውን መሻሩ እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው እና ሰበር ሰሚው የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይህንን ውሳኔ ማጽናታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ተከታዩ ተወስኗል።
የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚው ችልት የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰበር መዝገብ 9 የሰጠው ፍርድ ፣ ውሳኔ እና ትዕዛዝ ፤ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዝገብ 5 ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ ፣ ውሳኔ እና ትዕዛዝ እንዱሁም የወግዱ ወረዲ ፍርድ ቤት መዝገብ ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ ፣ ውሳኔ እና ትዕዛዝ በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ - ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 ቁጥር 9(1/ለ) መሰረት ተሽሯል።
የደቡብ ወል መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰበር መዝገብ የሰጠው ፍርድ እና ውሳኔ እና ትዕዛዝ የሰበር ሥነ - ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 ቁጥር 9(1/ሀ) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ መዝገብ ላይ ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዛዝ ተነስቷል።
ውሳኔው ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በችልት ተነቧል።