No summary available.
ሚያዝያ 28/2012 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ጳውልስ ኦርሺሶ ፀሐይ መንክር መላኩ ካሳዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- ወ/ሮ ፊጡማ አልቃድር ተጠሪዎች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዲይ የውርስ ሀብት በሆነ ይዞታ ላይ በአንደኛው ወራሽ ያለተቃውሞ የተሰራ ቤትን በተመለከተ ቤቱን የሰራው እና ልልች ወራሾች በተሰራው ቤት ላይ ስላላቸው የመብት አድማስ የሚመለከት ነው።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/03-90267 ላይ መጋቢት 20/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት በአሁን አመልካች የቀረበለትን የሰበር አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠውን የመጨረሻ ትዕዛዝ በመቃወም ነው።
የክርክሩ አመጣጥ እንዱህ ነው። የአሁን አመልካች በአሁን 1ኛ ተጠሪ ላይ በሰሜን ጎንደር መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 23/2002 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ ቦታ እና አዋሳኙ በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰውን እና ግምቱ ብር 100,000(አንድ መቶ ሺህ) የሆነ በካርታ ቁጥር 0398/2007 የተመዘገበ ቤት እና ግምቱ ብር 720(ሰባት መቶ ሃያ) የሆነ የባህር ዛፍ ፍልጥ የያዙባቸው መሆኑን በመግለፅ በፍርድ ኃይል ተገደው እንዱለቁላቸው እና ለተጠቀሙበትም ኪራዩ በብር 50 ታስቦ እንዱከፈላቸው ዲኝነት ይጠይቃለ።
የአሁን 1ኛ ተጠሪ ለዚሁ ክስ ሐምል 26/2002 ዓ.ም በሰጡት መልስ የአመልካች ወንድም ሚስት በመሆናቸው ክስ የቀረበበትን ቤት ከላልች ወራሾች እጅ በአደራ ጠባቂነት ከመቀበላቸው ውጭ በቤቱ ላይ መብት የላላቸው መሆኑን እና የቀረበው ግምትም የተጋነነ መሆኑን በመግለፅ “ልጠየቅ አይገባም” ብለዋል።
በዚሁ መሀል የአሁን ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለ ተጠሪዎች በጣልቃ ገብነት ቀረበው የክርክሩ አካል በመሆን ጥቅምት 29/2003 ዓ.ም የተፃፈ መልስ ሰጥተዋል። የመልሳቸው ይዘትም ክስ የቀረበበት ቤት የሟች እናታቸው ወ/ሮ ምናላ ውቡ መሆኑን፤ ቤቱን በአደራ ለ1ኛ ተጠሪ የሰጧቸው እራሳቸው መሆኑን፤ ንብረቱ የጋራ የውርስ ሀብት ሆኖ እያለ የአሁን አመልካች ብቸኛ ወራሽ አስምስለው ካርታ ያወጡ መሆኑን በመግለፅ “ንብረቱን እኩል ከምንካፈል በቀር ልንለቅ አይገባም” በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ከሰማ በኋላ ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ መስጠቱን፤ በጉዲዩ ላይ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ድርስ ክርክር ተደርጎ ሰበር ሰሚ ችልቱ በመ/ቁ/16162 ላይ የካቲት 12/2005 ዓ.ም ሉጣሩ የሚገባቸውን ነጥቦች ለይቶ ጉዲዩን ለከፍተኛው ፍርድ ቤት የመለሰ መሆኑን፤ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም በተያዘው ነጥብ ላይ ተገቢውን ማጣራት አድርጎ ሐምል 23/2007 ዓ.ም ውሳኔ መስጠቱን፤ በዚሁ ውሳኔ ላይ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ክርክር ተደርጎ ሰበር ችልት በመ/ቁ/01-38878 ላይ ጥር 30/2008 ዓ.ም በዋለው ችልት በድጋሚ “ሉጣሩ ይገባል” ያላቸውን ነጥቦች ለይቶ ጉዲዩን ለከፍተኛው ፍርድ ቤት የመለሰ መሆኑን፤ ከፍተኛው ፍርድ ቤትም በተያዘው ነጥብ ላይ “ተገቢ ነው” ያለው ማጣራት አድርጎ ታህሳስ 25/2010 ዓ.ም በዋለው ችልት ውሳኔ መስጠቱን፤ ይኸው ውሳኔ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ ከላይ በተጠቀሰው የመዝገብ ቁጥር እና ቀን በዋለው ችልት የፀና መሆኑን የመዝገቡ ታሪክ ያስረዲል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታህሳስ 25/2010 ዓ.ም የሰጠው እና ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ውሳኔ ይዘት በአጭሩ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/01-38878 ላይ እንዱጣራ ተብል በነጥብነት የተለየው 1ኛ/ ክርክር የተነሳበትን ቤት በተመለከተ የአሁን አመልካች ያቀረቡት ካርታ ህጋዊነት እንዱጣራ፤ 2ኛ/ ክርክር የተነሳበት ይዞታ የውርስ ሀብት ከሆነ ወራሾች በድርሻቸው ልክ እንዱከፊፈለ በማድረግ የመሰለውን እንዱወስን የሚል መሆኑን፤ በዚሁ አግባብ ክስ የቀረበበትን ቤት በተመለከለተ የዞኑ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከወረዲው መሪ ማዘጋጃ ቤት ጋር በመሆን አጣርተው እንዱያቀርቡለት ትዕዛዝ መሰጠቱን፤ በውጤቱም ቤቱ የተሰራበትን ቦታ ወ/ሮ ማንአለብሽ ውቡ የተባለት በ1987 ዓ.ም በባህላዊ ግዢ ወ/ሮ ውብነሽ ከተባለት ገዝተው እላዩ ላይ የነበረውን ቤት አድሰው እየኖሩበትና ግብርም በተከታታይ ሲከፍለበት የነበረ መሆኑን፤ ይዞታውን በምን አግባብ እንደያዙ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አሁን ክርክር የተነሳበትን ቤት አመልካች በ1993 ዓ.ም በራሳቸው ወጪ የሰሩ ለመሆኑ ማረጋገጡን፤ ካርታውን በተመለከተ በአመልካች እጅ ያለው እና ከአስተዲደር ክፍል በቀረበው መካከል ልዩነት ያለ መሆኑን፤ በዚህም አመልካች ካርታውን ያገኙበት መንገድ ከአስተዲደር ክፍለ አሰራር እና ደንብ ውጭ በመሆኑ ህጋዊ እንዲልሆነ፤ አመልካች ቤት የሰሩበት ይዞታ የግራ ቀኙ እናት በመሆኑ የውርስ ሀብት መሆኑን በመግለፅ የአሁን ተጠሪዎች የቤቱን ግምት ለአሁን አመልካች ከፍለው የውርስ ሃብት የሆነውን ይዞታ ግራ ቀኙ እኩል እንዱካፈለ የሚል ነው።
በአሁን አመልካች አቤቱታ አቅራቢነት በዚሁ ውሳኔ ላይ እንደ ቅደም ተከተላቸው ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ የቀረበላቸው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልት የአመልካችን አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 337 መሰረት ውድቅ አድርገዋል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው።
አመልካች ሰኔ 03/2011 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ “ተፈጽሟል” ያለትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችልት እንዱታረምላቸው ጠይቀዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ከተመረመረ በኋላ አመልካች በባድ ይዞታ ላይ ክርክር የተነሳበትን ቤት ሰርተው ካርታ ያወጡበት ለመሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ቀድሞ ቦታው የግራ ቀኙ አውራሽ ነበር በሚል ብቻ አመልካች ለሰሩት ቤት ግምት ተከፍሎቸው ቦታውን ይከፊፈለ የመባለ አግባብነት በፍ/ብ/ህ/ቁ/1179 እና ማንም ባልተቃወመበት በይዞታ ላይ ስለተሰራ ቤት ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ቀደም ሲል ከሰጠው ትርጉም አንፃር ለዚህ ችልት ቀርቦ እንዱጣራ በአጣሪ ችልት በመታዘዙ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ተደርጓል።
በዚሁ መሰረት 1ኛ ተጠሪ ለብቻቸው፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በጋራ ጥቅምት 20/2012 የተፃፈ መልስ ሰጥተዋል። 4ኛ ተጠሪን በተመለከተ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ለመሆኑ በመረጋገጡ እና ወራሾች ካለ ቀርበው እንዱከራከሩ ጥሪ የተደረገ ቢሆንም የቀረበ ባለመኖሩ የሰበር ክርክሩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
1ኛ ተጠሪ በሰጡት መልስ በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት መልስ አግባብ ቤቱን ከላልች ወራሾች በአደራ የተረከቡ እንጂ የሚጠይቁት መብት አለመኖሩን በመግለፅ በተከራካሪነት “ልጠራ አይገባም” ብለዋል።
ከማስቀረቢያ ነጥቡ አኳያ የ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች መልስ ይዘት በአጭሩ ክርክር የተነሳበትን ቤት ወላጅ እናታቸው አሮጌ ቤት ገዝተው አፍርሰው የሰሩት እንጂ አመልካች የሰሩት እንዲልሆነ፤
አመልካች ያቀረቡት ካርታም ህጋዊ ካለመሆኑም በላይ በከተማው ውስጥ ባላቸው ላላ ቤት ላይ የተሰጠ እንጂ አሁን ክርክር የተነሳበትን ቤት የሚመለከት እንዲልሆነ፤ ወላጅ እናታቸው በሰሩት ቤት ላይ ግምቱን ለአመልካች ከፍለው እንዱካፈለ በሚል የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ባይሆንም አመልካች እህታቸው በመሆናቸው በተሰጠው ውሳኔ ተጎጂ ቢሆኑም በይሁንታ የተቀበለ መሆኑን በመግለፅ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱፀና የሚጠይቅ ነው።
አመልካች በሰጡት የመልስ መልስ ክርክር የተነሳበትን ቤት በባድ ቦታ ላይ ተጠሪዎች ላይ ሳይቃወሟቸው በራሳቸው ወጪ ለመስራታቸው ተረጋግጦ እያለ ቤቱ የግል ሃብታቸው ነው ተብል መወሰን ሲገባው ግምቱ ተከፍሎቸው ከላልች ወራሾች ጋር እንዱካፈለ መወሰኑ አግባብ አለመሆኑን በመግለፅ በቀረበው አቤቱታ መሰረት እንዱወሰንላቸው ሞግተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ነጥብ አኳያ የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
ከክርክሩ አመጣር መረዲት እንደሚቻለው ክርክር የተነሳበት ቤት የተሰራበት ይዞታን በተመለከተ የውርስ ሀብት ነው ወይስ የአመልካች የግል ይዞታ ነው የሚለው ከአንዳም ሁለት ጊዜ እስከ ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ግራ ቀኙን ሲያከራክር የቆየ መሆኑን፤ በመጨረሻም ጉዲዩን በመጀመሪያ የዲኝነት ስልጣኑ የተመለከተው የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚሁ ነጥብ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ሰምቶ እንዱሁም ስለይዞታው ጉዲዩ ከሚመለከተው አስተዲደር ክፍል በትዕዛዝ ካጣራ በኋላ ቤቱ የተሰራበት ይዞታ መሰረቱ የግራ ቀኙ አውራሽ መሆኑን፤ በዚሁ ይዞታ ላይ ክርክር የተነሳበትን ቤት አመልካች የሰሩ ለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ማረጋገጡን በፍርድ ሀተታው ላይ በግል አስፍሯል።
እንግዱህ በኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 80(3) እና በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁር 25/1988 አንቀፅ 10 መሰረት ለዚህ ሰበር ችልት የተሰጠው የዲኝነት ስልጣን በማናቸውም የመጨረሻ ውሳኔው ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ካለ ማረም እንጂ ማስረጃን የመመርመር አና የመመዘን ሥልጣን አይደለም። በመሆኑም የዚህ ሰበር ችልት ተግባር የሚሆነው ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር በግብዓትነት በመውሰድ ፍሬ ነገሩ መሰረት ተደርጎ በተሰጠ የህግ ትርጉም ውስጥ የተፈፀመ መሰረታዊ ስህተት ካለ መፈተሽ ነው።
አሁን በቀረበው ጉዲይ ማስረጃን በመመርመር እና በመመዘን ፍሬ ነገርን የማጥራት ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክርክር የተነሳበት ይዞታ የውርስ ሃብት መሆኑን እና በዚሁ ይዞታ ላይ የአሁን አመልካች በራሳቸው ወጪ ክርክር የተነሳበትን ቤት ስለመስራታቸው በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል። በፍሬ ነገር ደረጃ ይህ ተረጋግጦ ባለበት አመልካች “ይዞታው የእኔ ነው” በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ማስረጃን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ችልቱ አልተቀበለውም።
“ቤቱ የተሰራበት ይዞታ የውርስ ሀብት ነው” ከተባለ ወራሾች በዚህ ይዞታ ላይ ያላቸውን መብት እና ስለ መብቱ አፈፃፀም ያለውን የህግ ማዕቀፍ ማየቱ ተገቢ ይሆናል። በዚሁ መሰረት የውርስ ሀብት አከፊፈል እስከሚፈፀም ድረስ በወራሾች መካከል ውርሱ ሳይነጣጠል የሚቆይ መሆኑን እና ወራሾቹ በዚህ ባልተከፊፈለ የውርስ ሀብት ላይ ያላቸው መብት በፍትሐ ብሕር ህጉ ስለ የጋራ ባለሃብትነት በሚመለከተው የህጉ ድንጋጌዎች የሚወሰን ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ/1060(1) እና (2) ድንጋጌ ያስገነዝባል። ስለ የጋራ ባለሃብትነት የሚደነግገው የፍትሐ ብሕር ህጉ አንቀፅ 8 ምዕራፍ አንድ ደግሞ በአንድ ሀብት ላይ የጋራ ባለሃብት የሆኑት ሰዎች መብት እና ግዳታ የሚወሰነው የጋራ ባለሃብቱ በተቋቋመበት ውል እና የህጉን ግልፅ ድንጋጌን እስካልተላለፈ ድረስ በጋራ ባለሃብቶቹ መካከል በሚደረግ የውል ስምምት መሰረት ስለመሆኑ፤ በዚህ መልኩ የተደረገ ስምምነት ከላለ ወይም ስምምነት ቢኖርም ያልተሟላ እና ብቁ ባልሆነበት ጊዜ ደግሞ የእያንዲንደ የጋራ ባለሃብት ድርሻ ሀብት እኩል እንደሆነ የሚገመት ስለመሆኑ እና የመብቱ አፈፃፀምም በዚሁ መልኩ የሚመራ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ/1258፣ 1259 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
በዚሁ አግባብ አሁን ክርክር የቀረበበት ቤት የተሰራበት ይዞታ የውርስ ሀብት በመሆኑ እና በወራሾች መካከል ያልተከፊፈለ በመሆኑ አመልካች እና ላልች ወራሾች በይዞታው ላይ እኩል መብት ከሚኖራቸው በቀር የአንደ ወራሽ ድርሻ መጠን ተለይቶ “ይህ ያክል ነው” የሚባል አይሆንም። በእንደዚህ ዓይነት ይዞታ ላይ በአንደ ወራሽ የሚደረግ የትኛውም ግንባታ በልላ ሰው ይዞታ ላይ ስለሚደረግ ግንባታ በሚመለከተው የፍትሐ ብሄር ህጉ የሚመራ ይሆናል።
የራሱ ባልሆነ ይዞታ ላይ ቤት/ህንፃ/ የሰራ ሰውን በተመለከተ የቤቱ ሰሪ ስለሚኖረው የመብት አድማስ በፍ/ብ/ህ/ቁ/1178 እና 1179 ስር ተደንግጓል። በዚሁ መሰረት የራሱ ባልሆነ ይዞታ ላይ ቤት የሰራ ሰው የሚኖረው መብት ቤቱ ሲሰራ ባለይዞታው በሚኖረው እውቀት እና ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን፤ ቤቱ ባለይዞታው እየተቃወመ ተሰርቶ ከሆነ ቤቱን የሰራው ሰው ምንም ዓይነት መብት በሰራው ቤት ላይ የላለው መሆኑን፤ ሆኖም ቤቱ የተሰራው ያለተቃውሞ ከሆነ የሰራው ሰው የቤቱ ባለቤት የሚሆን ስለመሆኑ እንደቅደም ተከተላቸው ከፍ/ብ/ህ/ቁ/1178(1) እና 1179(1) ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች የወራሾች የጋራ በሆነ ይዞታ ላይ ክርክር የተነሳበትን ቤት በ1993 ዓ.ም በራሳቸው ወጪ የሰሩ ለመሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። በእርግጥ በዚህን ጊዜ የግራ ቀኙ አውራሽ በህይወት የነበሩ ለመሆኑ የታወቀ ነገር የለም። አውራሻቸው በህይወት ኖሩም አልኖሩም አመልካች በይዞታው ላይ ቤቱን ሲሰሩ ከአውራሻቸውም ሆነ ከላልች ወራሾች ቤቱ እንዲይሰራ የቀረበ ተቃውሞ የነበረ ለመሆኑ የቀረበ ክርክርም ሆነ የተረጋገጠ ነገር የለም። ይህ ከላለ አመልካች ያለተቃውሞ ቤቱን የሰሩ ለመሆኑ ግምት የሚያስወስድ በመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ/1179(1) በሚያዘው መሰረት ቤቱ የአመልካች የግል ሀብት ይሆናል። ቤቱ የአመልካች የግል ሀብት ከሆነ ላልች ወራሾች የቤቱን ዋጋ ከፍለው ከአመልካች ጋር የሚካፈለበት የህግ አግባብ የለም። ጉዲዩ ይህ በሆነበት የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለአመልካች የቤቱ ግምት ተከፍል ከላልች ወራሾች ጋር እኩል እንዱካፈለ በሚል መወሰኑ እና በየደረጃው ያለት የክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ ውሳኔ ማፅናታቸው የፍትሐ ብሄር ህግ ቁጥር 1179(1) ድንጋጌን መሰረት ያላደረገና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
በአማራ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ጎንደር ዞን መስተዲድር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/01-04881 ላይ ታህሳስ 25/2010 ዓ.ም ተሰጥቶ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/03-90267 ላይ መጋቢት 20/2011 ዓ.ም በዋለው ችልት የፀደቀው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
ክርክር የተነሳበትን ቤት አመልካች በራሳቸው ወጪ ያለምንም ተቃውሞ የጋራ በሆነ የውርስ ይዞታ ላይ የሰሩ በመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1179(1) በሚፈቅደው መሰረት ቤቱ የአመልካች የግል ሀብት ነው።
ክርክር የተነሳበት ቤት ከተገነባበት እና ቤቱ ካረፈበት ቦታ ውጭ ያለውን ይዞታ በተመለከተ አመልካች እና ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች እኩል የወራሽነት መብት አላቸው በማለት ተወስኗል።
ይህ ውሳኔ አመልካች በአፈፃፀም ወቅት የመውጫ እና መግቢያ መብት እንዱከበርላቸው የሚያቀርቡትን መብት ከመጠየቅ አያግዲቸውም።
የዚህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.