No summary available.
መ/ ህዲር 28 ቀን 2011 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ረጋሳ መልካሙ ተጠሪዎች፡- 1ኛ/ ካየሶ ክርባ 2ኛ/ አቶ ብርሀኑ ተስፊዬ መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ በመሆኑ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ፍርድ።
በዚህ መዝገብ የቀረበዉ ጉዲይ ከይዞታ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዲት መከላከል የሚመለከት ነዉ።የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የአሁኑ አመልካች ሲሆን የክሱ ይዘት ባጭሩ አመልካችና ተጠሪ በይዞታቸዉ በድንበር የሚዋሰኑ ሆኖ በምስራቅ በኩል ተጠሪዎች የተከለት ባሕርዛፍ ቅርንጫፍና ስሩ በአመልካች ጫት፣ቡና እና እንሰት ተክልች ላይ ጉዲት ያደረሰ ስለሆነ ዛፈን እንዱያነሱ እንዱወሰን የሚል ሲሆን በተጠሪዎች በኩል የቀረበዉ መልስ በመካከላቸዉ የእግር መንገድ ስላለ በአመልካች ንብረት ላይ የደረሰ ጉዲት አለመኖሩንና ባህርዛፍ ከተተከለ ረጅም ጊዜ ስለሆነ ክሱ ያለአግባብ የቀረበ ነዉ በማለት ተከራክረዋል።ክርክሩን በመጀመሪያ የዲኝነት ስልጣን የተመለከተዉ የአለታ ጩኮ ወረዲ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ምስክር ከሰማ በኋላ የተጠሪዎች ባህርዛፍ የአመልካች ተክልች ላይ ጉዲት አድርሷል ወይስ አላደረሰም? የሚለዉን የወረዲዉ ግብርና ባለሙያ አጣርቶ መግለጫ እንዱያቀርብ ትእዛዝ በመስጠት ባለሙያዉ ባቀረበዉ መግለጫ የተጠሪዎች ባህርዛፍ በአመልካች ንብረት ላይ ጉዲት እንዲደረሰና ለወደፉትም ትልቅ ጉዲት እንደሚያደርስ ስለገለጸ ፍርድ ቤቱም ይሕንኑ መሰረት በማድረግ በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 1212/1 ና 2/መሰረት ተጠሪዎች ባህርዛፈን ቆርጠዉ እንዱያነሱ ዉሳኔ ሰጥቷል።ተጠሪዎች በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝተዉ ለሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዉ ፍርድ ቤቱም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ በአንድ በኩል የተጠሪዎች ምስክሮች ባህርዛፈ ጉዲት አላደረሰም በሚል ተከላክለዋል በሚል በልላ በኩል ደግሞ በሲዲማ ባህል በረጅም ጊዜ ደጆ ስለሆነ ዛፈ አይቆረጥም በማለት የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔን ሽሯል።አመልካች በበኩለ ይህንኑ በመቃወም ለደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም።
ለዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ ተጠሪዎች በወሰን ላይ 40 ሜትር ርዝመት ላይ የተከለት ባህርዛፍ የአመልካች መተዲደሪያ ቡና፣እንሰት እና ጫት በስር እና በቅርንጫፍ ጉዲት ማድረሱ እንዱቆርጡለት በሽማግላ ጠይቆ እንቢ በማለታቸዉ ክስ ስለመመስረቱና በስር ፍርድ ቤት ጉዲት ስለመድረሱ በባለሙያ ጭምር መረጋገጡን ገልጾ የበላይ ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ተገቢ ባለመሆኑ እንዱታረም የሚል ነዉ።የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የተጠሪዎች ባህርዛፍ በአመልካች ንብረት ላይ ጉዲት ማድረሱ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ በራሳቸዉ ይዞታ ላይ ነዉ በሚል ወረዲ ፍርድ ቤት ዉሳኔ የመሻሩን አግባብነት ከፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 1212 አንጻር ለመመርመር በሚል ጭብጥ ተይዞ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ተደርጓል።በተጠሪዎች በኩል የቀረበዉ መልስ ባጭሩ በሁለቱ መካከል ትልቅ የመኪና መንገድ ያለበት ስለሆነ በአመልካች ንብረት ላይ የደረሰ ጉዲት የለም በሚል የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንዱጸና ጠይቀዋል።አመልካችም የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥና የክርክሩ ይዘት ከላይ ባጭሩ የተገለጸ ሲሆን እኛም አቤቱታዉ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድርግ አግባብነት ካለዉ ህግ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ አመልካችና ተጠሪዎች በሚዋሰኑበት አቅጣጫ ተጠሪዎች ባህርዛፍ ተክል ያላቸዉ ስለመሆኑ አላከራከረም።አመልካች በበኩለ ከተጠሪዎች በሚዋሰንበት አቅጣጫ ተጠሪዎች ወሰን ላይ የተከለት ባህርዛፍ አመልካች የሚጠቀምበት ጫት፣ቡና እንሰት የመሳሰለት ተክልች በዚህ የተጠሪዎች ባህርዛፍ ስርና ቅርንጫፍ ጉዲት ስለደረሰበት እንዱቆርጡለት ዲኝነት ጠይቀል።በእርግጥ አመልካችም ሆነ ተጠሪዎች በየራሳቸዉ ይዞታ ላይ መሆናቸዉ አላከራከረም።ነገር ግን ተጠሪዎች በራሳቸዉ ይዞታ ላይ የተከለት ባህርዛፍ በስሩ እና በቅርንጫፍ ወደ አመልካች ይዞታ አልፍ በአመልካች ንብረት ላይ ጉዲት ቢያደርስ ህጉ የሰጠዉ መፍትሄ ምንድነዉ?
የሚለዉ መታየት አለበት።በፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 1212 ላይ እንደተደነገገዉ ማንኛዉም ሰዉ ወደ መሬቱ ላይ ተዘርግተዉ የገቡትን የጎረቤቱን ዛፍችና ቅርንጫፍች በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ እንዱቆርጥ በዲኛ ማስገደድ ይችላል።ከዚህ ባሻገር ከወሰኑ መስመር አልፍ በመሬቱ ዉስጥ የሚሄደትን ሉቆርጥ እንደሚችል ተመልክቷል።ከዚህ መገንዘብ የሚቻለዉ አንድ ባለንብረት ንብረቱን የመገልገል መብቱ የላላኛዉን ወገን ጥቅም እንዲይጎዲ በህግ የተጣለ ወሰን ያለበት ስለመሆኑ ነዉ።ይኸዉም ተጠሪዎች በራሳቸዉ ይዞታ ላይ በማናቸዉም ሁኔታ ዛፍ በመትከል ጭምር የመገልገል መብት ያላቸዉ መሆኑ በልላ በኩል እነሱ የሚጠቀሙበት ዛፍ ቅርንጫፍ ወይም ስሩ የጎረቤት ንብረት ላይ ጉዲት እንዲያደርስ እና ጉዲት የደረሰበት ሰዉ የሚኖረዉ መፍትሄ ህጉ በግልጽ የደነገገ ስለመሆኑ ነዉ።በመሆኑም በዚህ አግባብ ጥበቃ የተደረገለት ተጎጂ ወገን አንድም በራሱ ጉዲቱን የማስወገድ አሉያም በፍርድ ሃይል ጉዲቱ እንዱወገድ ዲኝነት የመጠየቅ መብት በሕግ የተጠበቀ መሆኑን እንገነዘባለን።
No topics extracted.
በተያዘዉ ጉዲይ ተጠሪዎች የሚከራከሩት በመካከላቸዉ ትልቅ መንገድ ስላለ ባህርዛፍቹ በአመልካች ንብረት ላይ ጉዲት አላደረሱም በማለት ነዉ።የተጠሪዎች ባህርዛፍ በቅርንጫፈም ሆነ በስሩ በአመልካች ንብረት ላይ ጉዲት አድርሷል ወይስ አላደረሰም የሚለዉ የፍሬነገር ክርክር በማስረጃ ነጥሮ የሚታወቅ ከመሆኑ አኳያ የወረዲዉ ፍርድ ቤት የግራቀኙ ምስከሮች ብቻ መሰረት አድርጎ ፍትሃዊ ዉሳኔ መስጠት ባለመቻለ የወረዲዉ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጽ/ቤት ባለሙያ ጉዲዩን አጣርቶ መግለጫ እንዱሰጥ አድርጎ ባለሙያዉም በተጠሪዎች ባህርዛፍ ቅርንጫፍና ስር የአመልካች ንብረት ላይ ጉዲት ስለመድረሱ ገልጧል።የወረዲዉ ፍርድ ቤት ይህንኑ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎች ባህርዛፈን እንዱቆርጡ ዉሳኔ ሰጥቷል።የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምስክሮችን ቃል መሰረት በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ መሻሩን መዝገቡ ያሥረዲል።ከመዝገቡ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለዉ የግራቀኙ ምስክሮች ቃል ገለልተኛነት እና ተአማኘነት ጥያቄ ዉስጥ በመግባቱ የወረዲዉ ፍርድ ቤት ጉዲዩ በገለልተኛ ባለሙያ እንዱጣራ አድርጓል።ይግባኝ ሰሚዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግን ይህንን የባለሙያ መግለጫ ላለመቀበል የሰጠዉ ግልጽና ህጋዊ ምክንያት ስለመኖሩ አልተገለጸም። ስለሆነም ምንም እንኳን በመካከላቸዉ መንገድ መኖሩ ቢገለጽም ባህርዛፍቹ በቅርንጫፍቻቸዉና በስሮቻቸዉ በአመልካች ንብረት ላይ ጉዲት ስለማድረሳቸዉ በወረዲ ፍርድ ቤት በባለሙያ ታይቶ የተረጋገጠ እዉነታ ነዉ።በመሆኑም ይህንን በባለሙያ ጭምር የተረጋገጠ ፍሬ ነገር የሚያሥለዉጥ ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወረዲዉን ፍርድ ቤት ዉሳኔ በመሻር ዉሳኔ መስጠቱም ሆነ የበላይ ፍርድ ቤቶች ይህንኑ ማጽናታቸዉ ህጉንና የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር ባለማገናዘብ የተሰጠ ፍርድ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተናል።በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/43103 ላይ በ14/03/2010 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ እና ይህንኑ በማጽናት የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና ሰበር ሰሚ ችልት እንደቅደም ተከተላቸዉ በመ/ቁ/71766 እና መ/ ላይ የሰጡት ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁ/348/1/መሰረት ተሽሯል።
የአለታ ጩኮ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/21358 ላይ በ12/10/09 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ ጸንቷል።ይጻፍ።
በዚህ ፍ/ቤት ለተደረገዉ ክርክር ግራቀኙ የየራሳቸዉን ወጪና ኪሳራ ይቻለ ብለናል።