No summary available.
ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ደጀኔ አያንሳ ብርቅነሽ እሱባለው ሐብታሙ እርቅ ይሁን ብርሃኑ መንግስቱ አመልካች፡- ወ/ሮ እላኒ መኮንን - ተወካይ አቶ ተፈሪ በየነ ተጠሪ፡- አቶ ጢቆ ደግፋ - አልቀረቡም መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው። በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች የካቲት 04 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.
ሕዲር 28 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዲዩ የከተማ ይዞታን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ቢሾፍቱ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት ነው። በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፤ አቶ ዲኛቸው ቦጋለ የተባለ ግለሰብ ተከሳሽ፤ የአሁን አመልካች ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል።
የአሁን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አዋሳኙ በክሱ የተገለጸ በቢሾፍቱ ከተማ ጎርባ ቀበላ ውስጥ የሚገኝ 1.5 ጥማድ መሬት ከደርግ ጊዜ ጀምሮ ግብር እየገበርኩ እራሴም አከራይቼም ስጠቀምበት የነበረ ነው፤ በተጠሪ እና በአመልካች መካከል የነበረው የመሬት ኪራይ ውል በ2008 ዓ.ም ተጠናቆ መሬቱን ለመጠቀም ስሄድ ተከሳሹ መብት ሳይኖረው ከልክልኛል፤ በሕገ ወጥ መንገድም ይዞብኛል፤ ስለሆነም በሕገ ወጥ መንገድ የገነባውን ቤት እና አጥር አፍርሶ ይዞታውን እንዱያስረከብ ይወሰነልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የስር ተከሳሽ በሰጡት መልስ የያዝኩት መሬት የለም፤ ክስ የቀረበበት የመኖሪያ ቤት እና ቦታ በ1994 ዓ.ም አመልካች የገዛችው ሆኖ በጥበቃ ተቀጥሬ የምጠብቀው እንጂ በጉልበት የያዝኩት አይደለም ባለንብረቷን መጠየቅ ስለሚቻል ክሱ አይመለከተኝም በማለት መልስ ሰጥቷል።
የአሁን አመልካች ባቀረቡት የጣልቃ ገብነት ክርክር 20 ቅጠል ቆርቆሮ መኖሪያ ቤት ያረፈበት 1250 ካ.ሜ የግል ይዞታዬ ነው፤ ቤት እና ይዞታውን በቀን 06/10/1994 ዓ.ም ከተጠሪ የገዛሁት ነው፤ መሬቱ የእርሻ መሬት ሳይሆን በአሁኑ ወቅት በቢሾፍቱ ከተማ ጎርባ ቀበላ ውስጥ የሚገኝ መኖሪያ ቤት ነው፤
ክስ የቀረበበት ይዞታ ተጠሪ የሸጠልኝ ብቻ ሳይሆን ከላልች ሰዎች የገዛሁትን ንብረት እና ይዞታ በአሁኑ ወቅት አልምቼ የያዝኩትን በአንድ ላይ በማጠቃለል አቅርቦታል፤ ክሱን በተመለከተ 1250 ካ.ሜ አዋሳኙ በምስራቅ የአቶ አሉ አሰፊ እና ወ/ሮ መስታወት መርጋ ይዞታ፤ በሰሜን የህዝብ መንገድ፤
በምዔራብ የአቶ ዮሴፍ ገመቹ መኖሪያ ቤት፤ በደቡብ የአለምሸት ኃይለጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት ያዋስኑታል፤ ላላ ድንበር የለውም፤ ይህንን ደግሞ ሸጦልኛል፤ አቶ አሉ አሰፊ እና ወ/ሮ መስታወት መርጋ በፍርድ ቤት ተካሰው ንብረታቸውን ሸጠው እንዱካፈለ በመታዘዙ በቀን 01/09/1994 ዓ.ም ንብረቱ በሚገኝበት ቀበላ በኩል በ1000 ካ.ሜ ቦታ ላይ የሚገኘውን 30 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ሸጠውልኛል፤ በዚያው አጠገብ ላላ ይዞታ አለኝ፤ በተንኮል አጠቃል አቅርቦታል፤ ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ቤት እና የድሮ ቤት በመስራት የመንግስት ግብር የከፈልኩበት በቦታ መለያ በባለቤቴ አቶ ንጉሴ ዱንቃ ስም የተመዘገበ ነው፤ ክሱም በይርጋ ይታገዲል በማለት ተከራክረዋል።
ተጠሪ እና የስር ተከሳሽ በአመልካች /በጣልቃ ገብ/ ክርክር ላይ መልስ እንዱሰጡበት ታዞ ባለመቅረባቸው መልስ ለማቅረብ ፍላጎት እንደላላቸው ተቆጥሮ መብታቸው የታለፈ መሆኑን መዝገቡ ያመለክታል።
ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ እና ከሚመለከተው የአስተዲደር አካል ስለጉዲዩ ተጣርቶ እንዱቀርብለት ካደረገ በኋላ ተከሳሽ ከጣል ቃገብ / ከአመልካች / ጋር በቀን 07/06/2008 ዓ.ም የጥበቃ ውል ፈጽመው ተቀጥሮ ሲሰራ መቆየቱ ስለተረጋገጠ ንብረቱን በኃይል ይዟል ተብል የሚያስከስሰው ነገር የለም፤ ክርክር ያስነሳው 1000 ካ.ሜ ይዞታ የባልና ሚስት ንብረት ሲሆን በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዱካፈለ በተደረገው መሰረት በቀን 01/09/1994 ዓ.ም ከአቶ አሉ አሰፊ እና መስታወት መርጋ በመግዛት ሕጋዊ አድርገዋል፤ በቀን 06/10/1994 ዓ.ም በተጠሪ እና በጣል ቃገብ / አመልካች / መካከል በተደረገው ውል በ 1250 ካ.ሜ ላይ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት በማዲበሪያ ዔዲ በመያዙ ለአመልካች የተሸጠ ሲሆን ቀበላው ይህንኑ ያረጋገጠው ጉዲይ ነው፤ የአመልካች ምስክሮች አመልካች ክርክር ያስነሳውን ቦታ በሕጋዊ መንገድ ከቤት ጋር ከገዛች በኋላ የተለያየ ተክል እና ባሕርዛፍ በመትከል ትልቅ የድሮ እርባታ ቤት ሰርታበት ከ1994 ዓ.ም አንስቶ አየተጠቀመችበት የምትገኝ መሆኑን አረጋግጠዋል፤ ተጠሪ አከራካሪውን መሬት በኮንትራት ሰጥቻለሁ ያለ ቢሆንም ይህን የሚደግፍ ማስረጃ አላቀረበም፤ ከቀበላው ጽ/ቤት በቀን 03/03/2013 ዓ.ም የተጻፈው ደብዲቤ እና ተያይዞ የቀረበው ቃለ ጉባኤ አከራካሪው መሬት ከ1994 ዓ.ም በፉት በአቶ አሉ አሰፊ እጅ የነበረ እና አሁን ደግሞ ባልና ሚስት ሸጠውት በወ/ሮ እላኒ መኮንን / አመልካች / እጅ እንደሚገኝ፤ የተጠሪ መሬት በቤት ሽያጭ አማካኝነት በአመልካች እጅ የገባ መሆኑን እና ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ አመልካች የምትገብርበት መሆኑን በመግለጽ ምላሽ ልኳል፤ የተጠሪ ጠበቃ የኮንትራት ውለን እንዱያቀርብ ፍርድ ቤቱ ቢፈቅድም ማቅረብ ስላልቻለ መብቱ ታልፎል፤ ተጠሪ የመኖሪያ ቤት ቦታውን በሕጋዊ መንገድ ለአመልካች ከሸጠ በኋላ ተከሳሹ እንዱጠብቅላት በውል ስምምነት ቀጥራ በሚጠብቀው ግለሰብ ላይ ያቀረበው ክስ መብት በላለው ንብረት ላይ ያቀረበው ስለሆነ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።
ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም እቴነሽ መኮንን የተባለ ግለሰብን መልስ ሰጪ አድርገው ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል። ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የመዝገቡ መልስ ሰጪ ምስክሮች የግዢ እና የሽያጭ ውለን እንደሚያውቁ አሳማኝ በሆነ ሁኔታ አስረድተዋል፤ ከተለያዩ አካላት በትዕዛዝ ተጣርቶ የቀረበው ማስረጃም ይህንኑ የሚረጋግጥ ነው፤
ውለ የተደረገው በ1994 ዓ.ም በመሆኑ እና በገጠር መሬት ላይ የተሰራውን ቤት የገዛ ሰው አፍርሶ ያነሳል ተብል የተደነገገው ደግሞ በ1999 በወጣው ሕግ በመሆኑ በሕገ ወጥ መንገድ የተደረገ ግዢ ነው ማለት አይቻልም፤ አሉ አሰፊ እና ከባለቤቱ የተገዛው በቀበላ አስተዲደር እውቅና ስለመሆኑ ተረጋግጧል፤ የባለይዞታነት ማስረጃው በባለቤቷ ስም መኖሩ የግብር ክፍያው በሚስት ስም መሆኑ የባልና ሚስት ይዞታ የጋራ ስለሆነ እርስ በእርሱ አይስማማም በማለት የቀረበው ክርክር የሕግ ድጋፍ የለውም፤ አከራካሪው መሬት በክርክሩ እንደተገለጸው ሳይሆን 2752.50 ካ.ሜ መሆኑን እና መልስ ሰጪዋ ከተጠሪ እና አሉ ከተባለ ግለሰብ የገዛችው ድንበርተኛ መሆኑ የቢሾፍቱ ከተማ መሬት አስተዲደር ከሰጠው ምላሽ ተረጋግጧል፤ መልስ ሰጪ በሕጋዊ መንገድ ከገዛችው የመሬት ይዞታ ውጪ ያለው 462.50 ካ.ሜ መሆኑ ተረጋግጧል፤ መልስ ሰጪ ይህ መሬት የእርስዋ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አላቀረበችም፤ ጠበቃዋ በፍርድ ቤቱ ባቀረበው ክርክርም ይዞታውን ከቤት ጋር ገዝተው በሕጋዊ መንገድ የያዙትን መሬት ብቻ የሚመለከት መሆኑን በመግለጽ የተከራከረ በመሆኑ 462.50 ካ.ሜ ይዞታ የመልስ ሰጪዋ አይደለም፤ ስለሆነም መልስ ሰጪ ከይግባኝ ባይ ከአሉ ገዝታ በሕጋዊ መንገድ የያዘችው መሬት ተያይዞ የሚገኝ መሆኑ የተረጋጠ በመሆኑ ለክርክሩ ምክንያት ከሆነው 2712.50 ካ.ሜ መሬት ውስጥ 462.50 ካ.ሜ ለተጠሪ እንድትለቅ ሲል የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል ወስኗል።
ተጠሪ በመቀጠል የአሁን አመልካችን በመልስ ሰጪነት በመሰየም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም አቤቱታቸው ተቀባይነት አላገኘም።
ተጠሪ በመቀጠል ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የአሁን አመልካችን በተጠሪነት በመሰየም የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። አቤቱታው የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን ውሳኔ አሻሽል አከራካሪውን ይዞታ ተጠሪ ከአቶ አሉ አሰፊ እና ከወ/ሮ መስታወት መርጋ የገዛችው መኖሪያ ቤት በ 1000 ካ.ሜ ላይ አርፍ የሚገኘው የላልች ሰዎች ይዞታ መሆኑ መረዲት ስለተቻለ ተጠሪ መጠየቅ አይችልም፤ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በ1994 ዓ.ም ክርክር ባስነሳው ቤት ላይ የተፈጸመው የግዢ እና ሽያጭ ስምምነት የሕገ መንግስቱን እና የሕጉን ተጻራሪ መሆኑን ስለተረዲን የሚጸና ውል አይደለም፤ ስለሆነም አመልካች የያዘችውን ይዞታ እና ንብረት ለተጠሪ መልቀቅ አለባት በማለት አሻሽል የወሰነ ሲሆን አመልካች ከውልም ሆነ ከውል ውጪ የያዘችውን ይዞታ 462.50 ካ.ሜ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተወሰነውን ጨምሮ አዋሳኙን እና ስፊቱን በባለሙያ ለይቶ ካጣራ በኋላ ፍትሐዊ ውሳኔ እንዱሰጥበት በማለት ጉዲዩን ለወረዲው ፍርድ ቤት መልሶለታል።
አመልካች የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይህን ውሳኔ በመቃወም የቀረበ ሲሆን ይዘቱም፡- ጥያቄው የመሬት ኮንትራት ሰጥቼዋለሁ የሚል እንጂ አመልካች በቦታው ላይ ቀድሞ ገዝቼ የነበረውን ቤት እና አድሼ እና ጨምሬ የሰራሁትን ቤት አያጠቃልልም፤ ላታይ ይገባቸው የነበሩት ነጥቦች ይዞታው የእርሻ ቦታ ነው ወይስ ቤት ያረፈበት ግቢ፤ በውል በኪራይ ተሰጥቷል ወይስ አልተሰጠም፤ ቤቱ የሚገኘው በከተማ ክልል ነው ወይሰ በገጠር ክለል የሚለት ሉሆኑ ይገባ ነበር፤
የእርሻ ቦታ መሆኑን እና ባድ መሬት በውል በኮንትራት መስጠቱን የማስረዲት ሸክሙ የተጠሪ ላሆን ይገባ ነበር፤ ይዞታውን ስትገዛ የገጠር መሬት ነበር በማለት ለ20 ዓመታት ከኖርኩበት ቤት እንድፈናቀል መደረጉ ግፍ ነው፤ ይዞታው የእርሻ ነው ቢባል እንኳን ከ12 ዓመት በኋላ የቀረበው ክስ በይርጋ ይታገዲል፤ ቤቱን የገዛሁት በ1994 ዓ.ም ሆኖ በኋላ በወጣው አዋጅ ቁጥር 130/1999 መታየቱ አግባብ አይደለም፤ ውለ አልተመዘገበም የተባለ ቢሆንም በወቅቱ ተመዝግቦ ለ12 ዓመታት የባለይዞታነት ወረቀት ከቀበላ እስከ ወረዲ ተሰጥቶኛል፤ አሁንም ለ8 ዓመታት በቢሾፍቱ ከተማ ተመዝግቦ ቤቶቹን ገንብቼ እና አሳድሼ ስጠቀም ነበር፤ ተጠሪ ለ20 ዓመታት አልተቃወመኝም፤ ፍርድ ቤቱ ለውሳኔው መሰረት ያደረጋቸው ሕጎች ለጉዲዩ አግባብነት የላቸውም፤ አግባብነት አላቸው ቢባል እንኳን መሬትን መሸጥ የሚከለክለ እንጂ ቤቱን መሸጥ አይከለክለም፤ አከራካሪው መሬት የእርሻ መሬት አይደለም፤ በአንድ ወቅት ሁለም ከተማዎች የገጠር መሬት እንደነበሩ ይገመታል፤ ይዞታው የተጠሪ ነው ቢባል እንኳን በቀረው ቤት እና ይዞታ ላይ ካሳ ተሰጥቶታል፤ ውለ ሕጋዊ አይደለም በማለት የተሰጠው ውሳኔ ባልተጠየቀ ዲኝነት የተሰጠ ውሳኔ ነው፤ ስለሆነም ይህ ታልፍ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪው ችልት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ የፍሬ ነገር ክርክርን በተመለከተ በማስረጃ አጣርተው የመወሰን ስልጣን የተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የመሻሩን አግባብነት ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ቀርቧል።
ተጠሪ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጡት መልስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች በቦታው ላይ መኖሪያ ቤት ሰርታ አልኖረችበትም፤ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የክልለን የገጠር መሬት ሕግ መሰረት በማድረግ የአመልካችን ክስ ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ነው፤ አመልካች በቦታው ላይ መኖሪያ ቤት ሰርታ አልኖረችም፤ አመልካች እንድትለቅ በተወሰነው ቦታ ላይ ምንም ቤት የለም፤ ቤተሰብ በባድ መሬት ላይ እንደማይኖርም ታውቃለች፤ አመልካች ገዛሁ የምትለው ቤት በገጠር መሬት አስተዲደር ውስጥ የነበረ ነው፤ የገጠር መሬትን መግዛት አይቻልም፤ በ12 ዓመት ይርጋ ክሱ ውደቅ ላደረግ ይገባል በማለት የቀረበው ክርክር በስር ፍርድ ቤት አልተነሳም፤ ፍርድ ቤቱ አመልካች አለኝ የምትለውን ውል ሕጋዊነት መርምሮ መወሰኑ ተገቢ ነው፤ አከራካሪው መሬት የእርሻ መሬት ስለመሆኑ አልተካደም፤
አሁን በከተማ ስር መሆኑ አርሼ እንዲልጠቀም የሚከለክለኝ አይደለም፤ መሬቱ በከተማ ስር ቢገባም አመልካች በሕገ ወጥ መንገድ ከያዘችብኝ መሬት ውጪ ሁለም መሬት በእጄ ነው፤ እየተከራከርን ያለነው በ 1000 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ሳይሆን በቀሪው ይዞታ ላይ ነው፤ 1000 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈውን ቤት ከእነ አቶ አሉ አሰፊ የገዛችው ስለሆነ አመልካች ቅሬታ የለኝም፤ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሽያጭ ውለን ሕጋዊነት መርምሮ መወሰኑ ወደ ፍሬ ነገር ገብቷል አያስብለውም፤ ስለሆነም ውሳኔው ሉጻና ይገባል የሚል ነው።
አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።
ይህ ችልትም በሰበር አጣሪው ችልት ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤
ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የማይሸጥ እና የማይለወጥ ሆኖ ባለቤትነቱም የሕዝብና የመንግስት መሆኑን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40(3) ይደነግጋል። መንግስት የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም በሚመለከት ህግ የሚያወጣ መሆኑን ከሕገ መንግስቱ 51(5), 52(2) (መ) እና 55 (1) (ሀ) ድንጋጌዎች የሚያመለክቱ ሲሆን፤ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎቹን መሰረት በማድረግ በፋደራልም ሆነ በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠርና የከተማ መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም በሚመለከት በርካታ ሕጎች ወጥተው ሲሰራባቸው የቆዩ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብሉክ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/1997 እና የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 እና አዋጁን ለማስፈፀም የወጣው ደንብ ቁጥር 151/2005 እንዱሁም ፤ የከተማ ቦታን በሉዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ ቁጥር 721/2004፣ የኦሮሚያ ክልል የከተማ ቦታን በሉዝ ለማስተዲደር የወጣው ደንብ ቁጥር 182/2005 እና መመሪያ ቁጥር 4/2008 በሥራ ያለ ተጠቃሽ ሕጎች ናቸው። እነዚህ ሕጎች የገጠር እና የከተማ መሬት የሚገኝበትን አግባብ ፣ የመሬት ተጠቃሚው ያለው መብት ወሰን ፣ እና ላልች ዝርዝር ነገሮችን የያዙ ናቸው። የገጠር መሬት የመጠቀም መብት በሕጋዊ መንገድ ያገኘ ሰው ከይዞታው ያለመፈናቀል መብት ያለው መሆኑን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40(4) እና የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 ቁጥር 6(1- 6) ይደነግጋለ። ዜጎች የግል ንብረት የማፍራት መሰረታዊ መብት ያላቸው ሲሆን ባለሀብትነት ከሁለም የንብረት መብቶች የሰፊ በሕግ ብቻ የሚገደብ መሆኑን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40(1) እና የፍትሐ ብሓር ህጉ ቁጥር 1204 እና 1205 ያመለክታለ።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ለሥር የቢሾፍቱ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ በቢሾፍቱ ከተማ ጎርባ ቀበላ የሚገኝ አዋሳኞቹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን ስፊቱ አንድ ተኩል ጥማድ የሆነው ለአሁን አመልካች አከራይቶ ሲጠቀምበት የነበረውንና የኪራይ ጊዜው በ2008 ዓ.ም ተጠናቆ በእጁ የገባውን የሥር ተከሳሽ በሕገ ወጥ መንገድ የገነባውን ቤት እና አጥር አፍርሶ እንዱለቅልኝ የሚል ነው። የሥር ተከሳሽም አዋሳኙ ተጠቅሶ ክስ የቀረበበት ይዞታ የአሁን አመልካች የገዙት መኖሪያ ቤት እና ቦታ ሆኖ የሥር ተከሳሹ የጥበቃ ሰራተኛ እንጂ ባለንብረት ባለመሆኑ፤ ባለንብረት የሆኑትን አመልካች መጠየቅ ሲገባው በእሱ ላይ ክስ መቅረቡ አግባብነት የለውም በማለት ተከራክሯል። የአሁን አመልካች በጣልቃ ገብነት አቤቱታቸው አከራካሪውን ይዞታ ሰኔ 6 ቀን 1994 ዓ.ም ከ17 ዓመት በፉት 20 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ያረፈበትን 1250 ካ.ሜ ከአመልካች የገዙት ሲሆን ቀሪውን 30 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ያረፈበትን 1000 ካ.ሜ ባልና ሚስት ከሆኑት አቶ አሉ አሰፊ እና ወ/ሮ መሰረት መርጋ የገዙት ሲሆን ፤ ክሱ በቀረበበት ጊዜ የገጠር ሳይሆን በቢሺፍቱ ከተማ ጎርባ ቀበላ ውስጥ የሚገኝ ፤ ከ1994 ዓ.ም አንስቶ በእጃቸው ያለ እና ተጨማሪ ግንባታ ገንብተው ግብር የሚገብሩበት የግል ይዞታ እና ቤታቸው ላይ የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ተከራክረዋል። ተጠሪ በጣልቃ ገብነት አቤቱታው ላይ መልስ እንዱሰጡ በተያዘው ቀጠሮ መጥሪያ ደረሷቸው ስላልቀረቡ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል።
አመልካች አከራካሪውን ቤት እና ይዞታውን ከተጠሪ በግዥ ነው የገኘሁት በማለት ያቀረቡትን ክርክር ተጠሪ መቃወማቸውን መዝገቡ አያመለክትም። የቢሾፍቱ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤትም ተጠሪ ለአመልካች አሳልፍ በሸጠው ንብረት ላይ ክስ የማቅረብ መብት የለውም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል። ይግባኝ ሰሚው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተጠሪ እንደ ክስ አቀራረባቸው ማስረዲት አለመቻላቸውን ውሳኔው ያትታል።
በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40 (1) እና (2) እንዱሁም የፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 1204 ድንጋጌ መሰረት ባለሀብትነት መሰረታዊ እና ከሁለ የሰፊ በህግ ከተመለከቱት ሥርዓቶች ውጪ ሉገደብ የማይችል መብት ነዉ። ባለሀብትነት ማስተላለፍያ መንገድች የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1184 እና ተከታዮቹ ሥር ተደንግጓል። ባለሀብትነት ቀሪ ላሆን የሚችልባቸው መንገድችም የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1188 እና ተከታዮቹ ሥር ተመላክቷል።
እጃችን ባለው ጉዲይ በአመልካችም እንደታመነው ከአከራካሪው ይዞታ እና ንብረት ውስጥ 20 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት ያረፈበትን ስፊቱ 1250 ካ.ሜ የሆነውን መሬት ከ17 ዓመት በፉት ሰኔ 6 ቀን 1994 ዓ.ም ከተጠሪ በግዥ የተላለፈላቸው መሆኑ ነው። የአከራካሪው ይዞታ እና ቤት ባለሀብት ማነው? የሚለው ጭብጥ ሲመረመር ተጠሪ በንብረቱ ላይ ያላቸው መብት ቀሪ መሆን፤ አመልካችም በአከራካሪው ንብረት ላይ በሕጉ አግባብ የተላለፈላቸው የባለሀብትነት መብት መኖሩን ለመመርመር በግራ ቀኙ መካከል የተደረገውን የግዥ ውል ማየቱ የግድ ይላል። ከውለ ጋር አብሮ መታየታ ያለበት ውለ ሲደረግ መሬቱ ሲሰጥ ከነበረው አገልግልት አንፃር የገጠር ነው ወይም የከተማ? ክርክሩ ሉመራ የሚገባው በከተማ መሬት ሕግ ወይም የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ? የሚለ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ያሻል።
ምንም እንኳን ውለ ሲደረግ መሬቱ የገጠር የነበረ ቢሆንም ክሱ በቀረበበት ጊዜ ይዞታው በቢሾፍቱ ከተማ አስተዲደር ሥር የሚገኝ ለከተማ አገልግልት የዋለ መሆኑን ከክርክሩ መረዲት ተችሎል። የተጠሪ ክስ የነበረውም የከተማ ይዞታዬ ይለቀቅልኝ የሚል ነው። ይዞታው በቢሾፍቱ ከተማ አስተዲደር ሥር ከገባበት ጊዜ ጀምሮ መሬቱ የከተማ እንጂ የገጠር ባለመሆኑ ክርክሩ በገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ሕግ ላታይ የሚችልበት አግባብ አይኖርም። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችልትም መሬቱ በገጠር አስተዲደር ክልል ሥር እያለ የተደረገ የውል ሕጋዊነት መታየት ያለበት ክርክሩ በተነሳበት ጊዜ መሬቱ በሚተዲደርበት ሕግ መሆኑን በሰበር መዝገብ ላይ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
አከራካሪው ይዞታ እና ቤት በአመልካች እና ተጠሪ መካከል ሰኔ 6 ቀን 1994 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል ወደ አመልካች ተላልፍ አመልካች ያለ ምንም ተቃውሞ እየተጠቀሙበት ፤ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ሲገብሩበት በቆዩበት ወቅት አግባብነት ያለውን የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ሕግን በመተላለፍ አላግባብ የያዙትን የገጠር መሬት እንዱለቁ የቀረበ ክርክር በላለበት፤ መሬቱ አስቀድሞ ይሰጥ የነበረው አገልግልት ተቀይሮ ለከተማ አገልግልት በቢሾፍቱ ከተማ አስተዲደር ሥር ከገባ በኋላ ፣ ከገጠር መሬት ይዞታ ያለመፈናቀል ሕገ መንግስታዊ ጥበቃው ለአርሶ አደሩ ሆኖ ክስ በቀረበ ጊዜ ከገጠር መሬት ይዞታ ላይ የተፈናቀለ አርሶ አደር በላለበት ውል ሲደረግ የነበረው ሁኔታ ተቀይሮ ባለበት የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ሕጉን አላግባብ በመለጠጥ እና የከተማ መሬት ሕግ ተፈፃሚነት ወሰን በሚያጣብብ መልኩ የተሰጠው ውሳኔ የሚነቅፍ ነው።
የከተማ መሬት መሰረቱ የገጠር መሬት ቢሆንም ፤ ጉዲዩ መታየት ያለበት ክሱ በቀረበ ጊዜ በሥራ ላይ ያለው የከተማ መሬትን ለማስተዲደር የወጣው ሕግ ወይስ ውለ በተፈፀመ ጊዜ የነበረው የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም ህግ ?
የሚል ሆኖ መሬቱ ከተማ አስተዲደር ሥር ከገባ በኋላ ለቀረበ ክስ መሬቱ በገጠር ቀበላ ሥር በሚገኝበት ጊዜ የተደረገውን የገጠር ቤት ሽያጭ ውል መሰረት በማድረግ የተጠሪ ባለሀብትነት በፍትሐ ብሓር ሕጉ ቁጥር 1189 መሰረት ቀሪ ሆኖ ፤ በፍትሐ ብሓር ሕጉ ቁጥር 1184, 1189, 2875 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት በግዥ የተላለፈላቸውን ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት እና ይዞታ አመልካች እንዱለቁ የተሰጠው ውሳኔ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40(1) እና የፍትሐ ብሓር ህጉ ቁጥር 1204 እና 1205 መሰረታዊ ንብረት የማፍራት መብታቸውን የሚገድብ የፍደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ቁጥር 2(4) (ሀ) እና (ሸ) የሚጣረስ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ቀጣዩ ተወስኗል።
በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ ሕዲር 28 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፤ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ
ውሳኔው የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም በችልት ተነቧል።
No topics extracted.