No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 03 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ፀሐይ መንክር ኑረዱን ከድር መላኩ ካሣዬ እስቲበል አንደዓለም አመልካች፡- አቶ ሽፊ ኢብራሂም፡- ጠበቃ አብደራዚት ረሽድ - ቀረቡ ተጠሪ፡- በሻደ ቱፊ ዋንታል፡- አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ ላቀርብ የቻለው አመልካች ጥር 20 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ.281388 በቀን 20/04/2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፀው በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ መነሻ ያደረገ ሲሆን አመልካች በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ።
የአሁን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአሁን አመልካች እና በስር 2ኛ፤3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ላይ ባቀረቡት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ በቀድሞው አጠራር ዞን 2 ወረዲ 24 ቀበላ 17 በአሁኑ አጠራር ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዲ 07 የቤት ቁጥር አዱስ ነዋሪ ሲሆን ይህንን ይዞታዬን ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ ይዤው በእርሻ ስራ እየተጠቀምኩበት የምገኝ አርሶ አደር ስሆን የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ካቢኔ በ2010 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ መሰረት በወረዲው የገበሬዎች ኮሚቴ፣ በወረዲው ግብርና አርሶ አደር ልማት ጽ/ቤት እና በወረዲው ካቢኔ ይዞታዬ ተለክቶ 3324 ካሜ የተጠሪ መሆኑ ተረጋግጦ ወደ ኮ/ቀ/ክ/ከተማ የመሬት ይዞታ አስ/ጽ/ቤት/ለስር 4ኛ ተከሳሽ/ ተልኮለት ካርታ ሰርቶ መስጠት ሲገባው ካሳ ሳይከፈለኝና ምትክ ቦታ ሳይሰጠኝ አመልካች እና ለስር 2ኛ ተከሳሽ በይዞታዬ ላይ ካርታ ሰርቶ ሰጥቷል። የስር 3ኛ ተከሳሽ የግንባታ ፈቃድ በመስጠት የአሁን አመልካች ይዞታዬን ነጥቀው በውስጡ የዕቃ ማስቀመጫ ስቶር እና አጥር በመስራት የሁከት ተግባር ጥር 28 ቀን 2013 ዓም የፈጠሩብኝ ስለሆነ የሁከት ተግባር እንዱወገድልኝ፤ካርታውና የግንባታ ፈቃደ እንዱመክንልኝ እና የተሰራው ስቶርና አጥር እንዱፈርስ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል።
አመልካች በሰጡት መልስም አከራካሪው ይዞታዬ የተሰጠኝ ከአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በልማት ተነሺ ስለሆንኩ ባለቤት እንደላለው እና ይዞታው የመንግስት ባድ ቦታ መሆኑ ተረጋግጦ ነው።ስለሆነም ተጠሪ በዚህ ይዞታ ላይ የሚጠይቁት መብትና ጥቅም ካለ ይዞታውን የሰጠኝን የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደርን ከሚጠይቁ በስተቀር አመልካችን የሚጠይቁበት አግባብ የለም በማለት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.33(2) መሰረት መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ተጠሪ ይዞታውን በይዞታቸው ስር አድርገውት የማያውቁ ለእርሻ አገልግልትም ውል የማያውቅ በመሆኑ የይዞታውን አዋሳኝ ሲገልፁም በደቡብ በኩል መንገድ ያዋስነዋል ብለው መግለፃቸው ይዞታውን ይዘው የማያውቁ መሆኑን ስለሚያሳይ፤አመልካች በይዞታው ላይ ካርታ ያለኝ በመሆኑ በይዞታው ላይ የተሻለ መብት እንዲለኝ ስለሚያሳይ አያስከስስም ተብል መዝገቡ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.231(1)(ሀ) መሰረት ሉዘጋ ይገባል፤ይዞታው ከተጠሪ እጅ ወጥቶ በአመልካች እና በስር 2ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ በመሆኑ ከእጃቸው በወጣ ንብረት ላይ የመፊለም ክስ ከሚያቀርቡ በስተቀር ጥያቄው በሁከት ይወገድልኝ ክስ ሉስተናገድ ስለማይገባ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ጉዲዩ ላይ በሰጡት መልስም አከራካሪው ይዞታ ከሀያ አመት በፉት በአዱስ አበባ ከተማ ውስጥ ከተያዙ የማህበር ይዞታዎች መካከል አንደ ሲሆን በኋላም ለልማት ተነሺዎች መሰጠት ተጀምሮ በአዱስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዲ 6 ውስጥ የሚገኘው መኖሪያ ቤቴ በመልሶ ማልማት ስለፈረሰ አስተዲደሩ ከስር 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ጋር በመነጋገር ቦታው ባድ ቦታ መሆኑን ከ6 ወር በላይ አጥንቶ በምትክነት የሰጠኝ በመሆኑ በይዞታው ላይ ግንባታ ያከናወንኩትም ተገቢውን የግንባታ ፈቃድ በመውሰድ በከተማው መሪ ፕላን መሰረት ስለሆነ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የስር ተከሳሾች ያቀረቡትን ክርክር በመስማትና ከሚመለከተው አካል ተገቢው ማስረጃ እንዱቀርብ አድርጎ በሰጠው ውሳኔም የወረዲ አስተዲደሩ አርሶ አደር ኮሚቴ ተጠሪ ህጋዊ ባለይዞታ መሆናቸውን ከመግለፁ በተጨማሪ ለኮልፋ ቀራኒዮ ክ/ከ/መ/ባንክና ማስተላለፍ ፅ/ቤት ደብዲቤ የላከ እና ይዞታውን በሚመለከት መብት ሉፈጠርላቸው ሂደት ላይ ሆኖ እያለ፤ለተጠሪ ምትክ ቦታ ወይም የካሳ ክፍያ ሳያዘጋጅ ወይንም የተጀመረውን የስነ ስርዓት ሂደት በመጠበቅ መብት ሳይፈጥርላቸው ለአመልካችና ለስር 2ኛ ተከሳሽ ማስተላለፈ ህገ ወጥ እና ሁከት ተግባር መሆኑን፤ የወረዲው አርሶ አደር ኮሚቴ ከፃፈው ደብዲቤ አንፃር 4ኛ ተከሳሽም ሆነ የሚመለከተው አካል አስተዲደራዊ ውሳኔ ላሰጥበት ይገባል፤አመልካችንና የስር 2ኛ ተከሳሽን በተመለከተ ባቀረቡት ማስረጃ አማካኝነት መብት የተፈጠረላቸው በመሆኑ ህጋዊ መብታቸውን በመመሪያና ደንብ መሰረት በመጠበቅ አስተዲደራዊ ውሳኔ ላሰጥበት ይገባል፤ስለሆነም አስተዲደራዊ ውሳኔ ላሰጥበት በሚገባው ጉዲይ በቀረበው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ባለይዞታው ማን እንደሆነ ሉወሰን የማይገባ በመሆኑ በይዞታው ላይ 4ኛ ተከሳሽ አስተዲደራዊ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ በህጋዊ መንገድ የሚመለከተውን አካል የመጠየቅ መብታቸውን በመጠበቅ ፍርድ ሰጥቷል።ይህ ውሳኔ ጉዲዩን በይግባኝ በተመለከተው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፀንቷል።
No topics extracted.
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም የስር ፍርድ ቤት በፍርድ ሀተታው ላይ በግልጽ አከራካሪው ይዞታ አስተዲደራዊ ውሳኔ ከሚሰጥበት በቀር ይዞታው የማነው የሚለው ሉወሰን እንደማይገባ ድምዲሜ ላይ ደርሷል።እዚህ ድምዲሜ ላይ የደረሰውም የወረዲው አርሶ አደር ኮሚቴ ለተጠሪ ከፃፈላቸው የድጋፍ ደብዲቤ ውጭ ከአመልካች እኩል የሚቆም ማስረጃ ስለላላቸውም መሆኑን በሀተታው ተካትቷል።ነገር ግን ከዚህ ፍፁም ተቃራኒ በሆነ መንገድ የስር ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ተራ ቁጥር 1 ላይ የከተማው አስተዲደር ተጠሪ በቦታው ላይ መብት እያላቸው ለአመልካች ማስተላለፈ የሁከት ተግባር ነው በማለት እርስ በእርሱ የሚጋጭ ተገቢነት የላለው ውሳኔ ሰጥቶብናል።ፍርድ ቤቱ ሁከት አለ ብል ሲያበቃ የስር 4ኛ ተከሳሽ ተጠሪን ጨምሮ ጉዲዪን በአስተዲደራዊ መንገድ መፍትሕ እንዱሰጥበት በመወሰን ጉዲዪን የበለጠ እርስ በእርሱ የሚጋጭ አድርጎብናል።
ከመነሻው የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ገና ሙለ በሙለ መብት ስላልተቋቋመላቸው ቦታው የማነው የሚለውን ለመወሰን የማይቻል መሆኑን ካመነበት ሕጋዊ ካርታ ላለን ለአመልካች መወሰን ወይም በቂ ማስረጃ አልቀረበም ብል መዝጋት ይችላል።የስር ፍርድ ቤት በተቃራኒው የሰጠው እርስ በእርሱ የሚጋጭ ውሳኔ የአመልካችን መብት በእጅጉ ጎድቶታል።የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንን ጉዲይ በአግባቡ ሳይመረምረው ይግባኙ አያስቀርብም ማለቱ መሰረታዊ ሕግ ስሕተት ነው።ስለሆነም የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ የሰጠው ውሳኔ እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማፅናት የሰጠው ብይን ባቀረብነው የሰበር አቤቱታ መሰረት ሙለ በሙለ እንዱሻርልን በማለት አመልክተዋል።
የስር ፍርድ ቤት አከራካሪ የሆነውን ይዞታ በተመለከተ በአስተዲደራዊ መንገድ እንዱታይ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ የተፈጠረው ሁከት ይቁም ሲል ውሳኔ መስጠቱ ህጋዊ መሆን አለመሆን ለማጣራት ጉዲዪ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ተጠሪ በሰጡት መልስም የስር ፍርድ ቤት ጉዲዪ በአስተዲደር ይታይ ያለው ከተፈጠረው የሁከት ተግባር አኳያ ሳይሆን አመልካች በአስተዲደር ጠይቆ እንዱወስድና ጉዲዪ በአስተዲደር እልባት የሚያገኝ ነው አለ እንጂ ተጠሪ በመመሪያ ቁጥር 20/2013 መሰረት እንዱሁም መመሪያውን ለማሻሻል በወጣው መመሪያ ቁጥር 1/2013 በቀን 01/02/2014 ዓ.ም ተሻሽል በወጣው መመሪያ አንቀጽ 9(16) አርሶ አደሩ በማንኛውም ጊዜ ያለ አግባብ መሬቱ ለላላ ሰው ተላልፍብኛል ብል ቅሬታ ለሚመለከተው አካል ሲያቀርብና ተጣርቶ ውሳኔ ሲሰጠው ቀደም ሲል በአርሶ አደር መሬት ላይ የተሰጠው ካርታ መክኖ መሬቱ ለአርሶ አደሩ ይመለሳል ብል የወጣ መመሪያ በመፃረር የስር 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች የተጠሪን ይዞታ ሳያሳውቁኝ ካሳና ምትክ ቦታ ሳይሰጡኝ ካርታ መስጠቱና አመልካች በተጠሪ ይዞታ ላይ ግንባታ ለመገንባት መንቀሳቀሱ የሁከት ተግባር ነው ተብል በስር ፍ/ቤት ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.1140-1149(1) መሰረት መወሰኑ እና የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ይህንን ማጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የለበትም ተብል ውሳኔው እንዱፀናልኝ በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል።
በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ፣ከተገቢው ሕግና ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል።የሁከት ይወገድልኝ ክስ እና የባለሃብትነት ክስ ሁለቱም ከንብረት መብት የሚመነጩ ቢሆኑም ከክርክሩ አድማስ እና በፍሬ ነገር ደረጃ ተከራካሪዎች ሉያረጋግጡት ከሚገባው መሰረታዊ ጭብጥ አኳያ የተለያየ መነሻ እና ውጤት ያላቸው ህጋዊ መብቶች ናቸው።
የአንድ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው ንብረቱን በተመለከተ በህግ ከተረጋገጡለት መብቶች ውስጥ አንደ በሀብቱ ላይ የተፈጠረው ህገ ወጥ ሁከት እንዱወገድለት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ማቅረብ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149(1) ይደነግጋል። በዚህ መልኩ ክስ የሚያቀርብ ሰው ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች ሁከት ተፈጠረበት የተባለውን ንብረት/ሀብት/ ባልተጭበረበረ መንገድ በእጁ አድርጎ በእውነት የሚያዝበት መሆኑን እና በዚሁ ይዞታው ላይ በተከሰሰው ሰው/አካል ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ሁከት የተፈጠረበት መሆኑን ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ/1140፣ 1146 እና 1149 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መረዲት ይቻላል። በዚህ አግባብ በቀረበ ክስ ላይ ሁከት ተፈጥሯል ተብል ውሳኔ የሚሰጠውም የተከሰሰው ሰው የላላ ሰው ይዞታ መያዙ አልያም በይዞታው ላይ ሁከት መፍጠሩ ሲረጋገጥ እና የሁከት ክስ የቀረበበት አካልም የሥራውን አደራረግ የሚፈቅድ ለእርሱ የሚናገርለት መብት መኖሩን በፍጥነት እና በማይታበል ዓይነት ሳያስረዲ ሲቀር ስለመሆኑ ከዚሁ ድንጋጌ ንዐስ ቁጥር 1 እና 3 ይዘት መረዲት ይቻላል።
በአንፃሩ የባለሃብትነት መብት የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት የሆነ ሰው ከንብረቱ ላይ መብት ሳይኖረው ከህግ አግባብ ውጭ ንብረቱን በእጁ ባደረገው ሰው ወይም ንብረቱን በያዘው አካል ላይ ክስ በማቅረብ የሚያስመልስበት ህጋዊ መብት (Right to bring Petutary Action) ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ/1206 ድንጋጌ ያስገነዝባል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ክስ የሚያቀርብ ሰው ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ንብረት በእጁ አድርጎ በእውነት የሚያዝበት ስለመሆኑ ማረጋገጥ አይጠበቅበትም። ይልቁንም በንብረቱ ላይ በህግ የተቋቋመ የባለሃብትነት መብት ያለው መሆኑን፤
ይህንኑ ንብረቱን ምንም መብት ወይም የተሻለ መብት የላለው ሰው/አካል/ የወሰደበት መሆኑን ማረጋገጥ ነው።
አሁን በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ያቀረቡ ሲሆን በዚህ ክሳቸውም በአከራካሪው ይዞታ ላይ የቀደመ የተረጋገጠ በአርሶ አደርነት ይዞታውን የመያዝ መብት እያላቸው አመልካች ይዞታቸውን ነጥቀው በውስጡ የዕቃ ማስቀመጫ ስቶር እና አጥር በመስራት የሁከት ተግባር የፈጠሩባቸው መሆኑን በመጥቀስ የሁከት ተግባሩ እንዱወገድላቸው፤ለአመልካች የተሰጠው ካርታና የግንባታ ፈቃደ እንዱመክንላቸው መጠየቃቸውን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ያሳያል።ከላይ እንደተመለከተው አመልካች የሁከት ይወገድልኝ ክስ በማቅረብ በይዞታው ላይ የተፈጠረው ሁከት እንዱወገድላቸው በህጉ አግባብ ሉጠይቁ የሚችለት ሁከት ተፈጠረበት የተባለውን ንብረት/ሀብት/ ባልተጭበረበረ መንገድ በእጁ አድርጎ በእውነት የሚያዝበት መሆኑን በቅድሚያ ሲያረጋግጡ ቢሆንም አሁን በያዝነው ጉዲይ አመልካች አከራካሪውን ለአመልካች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጠበትን 90 ካሜ ይዞታ በእጃቸው አድርገው ሲጠቀሙበት የነበረ መሆኑን ማስረዲታቸውን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ አያሳይም።
የወረዲው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ፅ/ቤት በ20/08/2013 ዓ/ም ተጠሪ የልማት ተነሺ አርሶ አደር መሆናቸውንና መንደር 5 ከቶታል ጀርባ የሚገኘው ቦታ ቀደም ሲል በእርሻ እና በግጦሽ ሲጠቀሙበት የነበረ መሆኑን ከመግለፅ ውጪ አመልካች የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያገኙበት ይዞታ በተጠሪ እጅ ሆኖ በእውነት የሚያዙበት ሆኖ በክሱ ላይ በተመለከተው ጊዜ አመልካች ይዞታውን በሀይል በመያዝ በህገ ወጥ መንገድ አጥር ያጠሩበትና መጋዘን የሰሩበት መሆኑን የተረጋገጠበት መሆኑን አያሳይም። ከዚህ ይልቅ በወረዲው የአርሶ አደር ኮሚቴዎች እና የወረዲው ዋና ስራ አስፈፃሚ በ08/10/2013 ዓ.ም የተያዘው ቃለ ጉባኤ ለአመልካች የተሰጣቸው ይዞታ ታጥሮ የሚገኝ መሆኑን የሚያመለክት መሆኑና በክፍለ ከተማው የመሬት ልማት ማኔጅመንት ፅ/ቤት የመሬት ይዞታ አስተዲደር ጽ/ቤት ባለሙያ ግራ ቀኙ በተገኙበት በማጣራቱ ሂደት የያዘው ቃለ ጉባኤ የአመልካች ይዞታ በአመልካች በቆርቆሮ ታጥሮ የተያዘ ይዞታ መሆኑን መግለፁ አከራካሪው ይዞታ በተጠሪ እጅ ያልነበረና ያልተያዘ መሆኑን ያሳያል።
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ የሚያስችለውን በዚሁ ይዞታው ላይ በተከሰሰው ሰው/አካል ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ሁከት የተፈጠረበት መሆኑን የማረጋገጥ ግዳታን በተመለከትም አመልካች ለአከራካሪው ይዞታ ከተገቢው የአስተዲደር አካል የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና የግንባታ ፈቃድ በማግኘት ማከናወናቸው መረጋገጡም ሁለተኛው የህጉ መሰረታዊ መስፈርት ያልተሟላ መሆኑን ያሳያል።
እነዚህ ዝርዝር ሁኔታዎች ደግሞ ከመነሻውም ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በሁከት ይወገድልኝ የክርክር ስርዓት ቀርቦ ሉስተናገድ የማይገባው መሆኑን እያሳዩ የስር የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ የቀረበው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ባለይዞታው ማን እንደሆነ መወሰንን የሚጋብዝ መሆኑን እያመለከተ ይህ ከሆነ ደግሞ የግራ ቀኙ ክርክር ባለሀብትነትን በመፊለም ክስ እልባት ሉያገኝ የሚገባው መሆኑን በማመልከት የቀረበውን የሁከት ይወገድልኝ ክስ ውድቅ ሉያደርገው ሲገባ ይዞታውን የስር 4ኛ ተከሳሽ ለአመልካች ማስተላለፈ የሁከት ተግባር ነው በማለት መወሰኑና ከዚህም በማለፍ በስር 4ኛ ተከሳሽ ላይ ከተጠየቀው ዲኝነት ውጪ በአመልካች ይዞታ ላይ አስተዲደራዊ ውሳኔ እንዱሰጥ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንን ከክርክር አመራር ስነ-ስርዓት አንፃር በስር ፍርድ ቤት የተፈፀመን ግድፈት ሉያርም ሲገባ ማፅናቱ አግባብነት ያለው ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ተወስኗል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.290115 ጥቅምት 09 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እና ይህንን ፍርድ በማፅናት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 281388 በቀን 20/04/2014 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ብይን በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ በሁከት ይወገድልኝ ክስ ክርክር አግባብ ሉስተናገድ የሚችል አይደለም ብለናል።
ይህ ውሳኔ ተጠሪ በይዞታው ላይ አለኝ የሚለትን መብት ባለቤትነትን የመፊለም ክስ በማቅረብ ከማረጋገጥ የሚያግዲቸው አይደለም ብለናል።
የስር ፍርድ ቤት መዝገብ በመጣበት አኳኋን ይመለስ።
ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
ጉዲዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል።ይመለስ።