No summary available.
ቀን፡- የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግሥቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ሙለጌታ ሩጋ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፍሬሕይወት ተፈራ - ጠበቃ መሰረት አያላው - ቀረቡ መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ። ተጠሪ ሕዲር 05 ቀን 2009 ዓ/ም በተጻፈ የክስ ማመልከቻ ከአመልካች ጋር የነበረን ጋብቻ በፍቺ ፈርሶ የጋራ ንብረታችን የሆነ በአዱስ አበባ ከተማ ቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 01 የቤት ቁጥር 3099 መኖሪያ ቤት እንድንካፈል ውሳኔ አርፍበታል። ተጠሪ በኢትዮጵያ የማልኖር በመሆኑ ፍርደን ማስፈጸምና ድርሻችን መካፈል አልቻልንም። አመልካች በጋራ ንብረቱን በመያዝ ከኪራይ የሚገኘውን ገቢ ለብቻቸው እየተጠቀሙበት በመሆኑ ክስ አቅርቤ እስከ ሐምል 06 ቀን 2001 ዓ/ም ድረስ ያለውን የኪራይ ገንዘብ እንዱያካፈለ ተወስኗል። አመልካች ከነሀሴ 06 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ የጋራ ንብረቱን እያከራዩ ያገኙትን ገቢ ያላካፈለኝ በመሆኑ የተጠሪን ድርሻ ብር 500,000.00 ከወለድ ጋር እንዱከፍለ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካች ያቀረቡት መልስ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው። በክሱ የተመለከተው ቤት የጋራ ንብረታችን ነው። ነገር ግን ቤቱ ያልተከፈለው ተጠሪ ባለመፈለጋቸው ነው።
ከነሀሴ 06 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ቤቱን አላካራየሁም። በአሁኑ ሰዓት ሁለት ክፍልች ብቻ በወር በብር 3,000.00 ተከራይተዋል። በአንድ ወቅት ውጭ ሀገር ስለነበርኩኝ ቤቱን ዘግቼ ማንም ሳይከራይ ቆይቷል። ያገኘሁት ምንም ብልጽግና የላለ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች ባቀረቡት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ለጋራ ንብረቱ ዔድሳት የወጣ ወጪ ብር 53,000.00 በመሆኑ ግማሽ ድርሻ ብር 26,500.00 እና የተጠሪ አባት የሚከራይ ቤት ይዘው ለአንድ ዓመት ስለኖሩ በኪራይ ገንዘብ ታስቦ ድርሻዬ ብር 30,000.00 ተጠሪ እንዱከፍለ በማለት ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ ባቀረቡት መልስ ቤቱ ስለመታደሱ የቀረበ ማስረጃ የለም። አመልካች በቤቱ ውስጥ ስለሚኖሩ በእኔ ምትክ አባቴ በቤቱ በነጻ መኖራቸው ተገቢ ነው፤ ኪራይ ገንዘብ ልከፍል አይገባም ብለዋል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ አመልካች የጋራ ሀበቱን በማከራየት ገቢ ያገኙ በመሆኑ የተጠሪ ደርሻ ብር 367,500.00 እንዱከፍለና ቤቱ ላይ ለዔድሳት የወጣ ወጪ ብር 26,500.00 ተጠሪ ለአመልካች ሉከፍለ ይገባል በማለት ወስኗል። አመልካች ያቀረቡትን ይግባኝ ተቀብል ያከራከረው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ክሱ ያላግባብ መበልጸግን መሰረት አድርጎ የቀረበ በመሆኑ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የይርጋ ድንጋጌ በፍ/ሕ/ቁ. 2143(1) የተመለከተው የሁለት ዓመት ይርጋ ጊዜ ስለሆነ ከነሀሴ 06 ቀን 2001 ዓ/ም እስከ ሕዲር 05 ቀን 2007 ዓ/ም ድረስ ያለው የገንዘብ ዲኝነት በይርጋ የታገደ ነው። በይርጋ ላልታገደው ጊዜ አመልካች ብር 100,000.00 ለተጠሪ ሉከፍለ ይገባል በማለት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን አሻሽል ወስኗል። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በበኩለ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ከጋራ ሀብት የተሰበሰበ ገቢ ድርሻ ገንዘብ እንጂ ያላግባብ መበልጸግን መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ የሁለት ዓመት ይርጋ ጊዜ መሰረት አድርጎ መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔን አጽንቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረብነውን መስቀለኛ ተቃውሞ በዝምታ ማለፈ ተገቢ አይደለም። ክሱ የቀረበው አመልካች ያላግባብ በልጽጓል በሚል ነው፤ ከተጠሪ ጋር የውል ሆነ የሕግ ግንኙነት የለንም። ቤቱ ስለመከራየቱ ማስረጃ ላልቀረበበት ጊዜ በሙለ ክፍያው መታሰቡ ስህተት ያለበት ነው። ከኪራይ ገንዘቡ ጋር የተያያዘ ማስረጃ እንዱቀርብ ጠይቀን ሳይቀርብና አመልካች እንዲይመሰክሩ ተደርጎ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን ተመልክቶ አመልካች ንብረቱን በተጠሪ ፈቃድ የያዝኩት ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ውደቅ ተደርጎ የኪራይ ገንዘብ ይክፈለ ተብል መወሰኑ ተገቢነቱን ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርቡ ያዘዘ ሲሆን ተጠሪ የሰጡት መልስ በፍቺ ውሳኔ ቤቱ ላይ ክፍፍል እስኪደረግ እንጂ ለዘለቄታው አመልካች እንዱገለገለበት ፈቃድ አልሰጠሁም። ከአመልካች ጋር የጋራ ባለሀብት ነን፤ ያላግባብ መበልጸግ ክስ የሚቀርበው ምንም መብት ሳይኖረው በያዘ ሰው ላይ ነው፤ ክሱ ያላግባብ መበልጸግን መሰረት አድርጎ የቀረበ አይደለም። የአመልካች መስቀለኛ ተቃውሞ በስር ውድቅ ተደርጓል። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። ውሳኔው ላይ የተፈጸመ ስህተት የለም ብለዋል። አመልካች ባቀረቡት የመልስ መልስ አመልካች ቃላቸውን የሰጡ መሆኑን ገልጸው ነገር ግን በጠበቃቻው ጥያቄ እንዲይጠየቁ ተደርጓል በማለትና የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር፣ የሰበር አጣሪ ችልት የያዘው ጭብጥ፣ በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው ተጠሪ ሕዲር 05 ቀን 2009 ዓ/ም በተጻፈ የክስ ማመልከቻ ከአመልካች ጋር በአዱስ አበባ ከተማ ቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 01 የቤት ቁጥር 3099 የጋራ መኖሪያ ቤት አለን። የጋራ ንብረቱን አመልካች እያከራዩ ያገኙትን ገቢ ያላካፈለኝ በመሆኑ የተጠሪን ድርሻ ብር 500,000.00 ከወለድ ጋር እንዱከፍለ የሚል ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካች የይርጋ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ጉዲዩ ንብረቱ የጋራ ሀብት መሆኑን አምነው ተከራከረዋል። የፍትሐብሕር ጉዲይ የቀረበለት ፍርድ ቤት በቀዲሚነት እንዱያከናዉን ከሚጠበቁበት ተግባራት ዉስጥ አንደ እና መሰረታዊዉ ለቀረበለት ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉ የህግ ክፍል የመለየት ተግባር (identification of applicable law) ነዉ። አስቀድሞ ይህን ማድረግ የቀረበዉ ክስ የክስ ምክንያት ያለዉ መሆን አለመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን ያለዉ መሆን አለመሆኑን እና ላልች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ካለ አስቀድሞ በመለየት መርምሮ ተገቢዉን ዉሳኔ ለመስጠት የሚያችለዉ ሲሆን፣ ጉዲዩ ወደ ሙለ የክርክር ሂደት (full scale trial) የሚገባ ከሆነም በጉዲዩ ላይ ትክክለኛ ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉን ጭብጥ ይዞ ክርክሩን በመምራት ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉን ድንጋጌ በአግባቡ ለይቶ ፍትሐዊ ዉሳኔ ለመስጠት ያስችላል። በአጠቃላይ አስቀድሞ በጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉን የህግ ክፍል መለየት ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ከክርክር አመራር ሥርዓት ጋር በተያያዘ በሥ/ሥርዓት ህጉ የተመለከቱትን ደንቦች እና ድንጋጌዎች መሰረት ባደረገ መልኩ ክርክሩን ይመራ ዘንድ ያስችለዋል። የክርክር አመራርን አስመልክቶ በህጉ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ጉዲዩን መምራት፣ የክርክር አመራሩ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ እንዱሆን በማድረግ የተከራካሪ ወገኖችን የመሰማት መብት እንዱከበር በማድረግ ሥነ ሥርዓታዊ ፍትሕ እንዱረጋገጥ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ፤ ለጉዲዩ ትክክለኛ ጭብጥ በመያዝ፣ ተቀባይነት እና አግባብነት ያለዉን ማስረጃ ለይቶ በማስቀረብ እና በመመርመር ወሳኝ የሆኑ ፍሬ ነገሮች ነጥሮ እንዱወጡ በማድረግ ብልም ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉን የህግ ድንጋጌ ለይቶ ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ በጉዲዩ ላይ ፍትሐዊ ዉሳኔ እንዱሰጥ ያስችላል።
በክስ አቤቱታ ላይ የሚገለጹ ነገሮችን አስመልክቶ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 222 ላይ ከሳሽ ለክሱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች እንዱሁም ተከሳሽ ለክሱ ምክንያት በሆነዉ ነገር ላይ በኃላፉነት የሚጠየቅበትን ሁኔታ ከሳሽ በግልጽ በክሱ ማካተት እንዲለበት፤ እንዱሁም የሚጠየቀዉ ዲኝነት በግልጽ መመልከት እንዲለበት በአንቀጽ 224 በአስገዲጅ መልክ ከደነገገባቸዉ ምክንያቶች ዉስጥ አንደ ክስ የቀረበለት ፍርድ ቤት ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለዉን የህግ ክፍል አስቀድሞ እንዱለይ ለማስቻል እንደሆነ ይታመናል። ክርክሩን በፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፉነት ሲሆን በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ዓላማዎች የሆኑትን እንደ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግ፣ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትህ፣ ክርክርን ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት የመሳሰለትን ማሳካት ስለማይቻል የተከራካሪዎችን መሰረታዊ መብት ይነካል።
ክርክር የሚወሰነው በተጠየቀው ዲኝነት አግባብ እንደሆነ የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 182(2) ላይ ተመልክቷል።
ፍርድ ቤቱም ከቀረበው ዲኝነት አኳያ ከግራ ቀኙ ክርክር በመነሳት በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 246 እና ተከታዮቹ መሰረት በተነሱት ጉዲዮች ጭብጥ መስርቶ ውሳኔ የመስጠት ኃላፉነት አለበት።
ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዲይ ስንመለከት፣ ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ፣ ተጠሪ ለክሱ መሰረት ያደረጉት የጋራ ሀብት ላይ የተገኘ ገቢ ያካፍለኝ የሚል በመሆኑ ክስ የቀረበው የፍ/ሕ/ቁ. 1257 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ለቀረበው የይርጋ መቃወሚያ ሆነ ለሥረ-ነገሩ ክርክር ተፈጻሚነት ያለው ይኸው የሕግ ክፍል ነው። የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱ ያላግባብ መበልጸግን መሰረት ያደረገ ነው በማለት የፍ/ሕ/ቁ. 2143(1) የይርጋ ድንጋጌን ተፈጻሚ አድርጓል። ያላግባብ መበልጸግ በፍ/ሕ/ቁ. 2162 እንደተመለከተው በንብረቱ መብት የላለው ሰው አላግባብ ንብረቱን በመያዝ ሲበለጽግ ኃላፉነት የሚከተልበት መሆኑን የሚደነግግ ነው። በተያዘው ጉዲይ አመልካች የንብረቱ የጋራ ባለሀብት እንጂ መብት ሳይኖራቸው ንብረቱን የያዙ ሰው ባለመሆናቸው ያላግባብ መበልጸግን መሰረት ተደርጎ ጉዲዩ ሉዲኝ የሚገባው አይደለም። በተጨማሪም የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለይርጋው ተፈጻሚ ያደረገው የፍ/ሕ/ቁ. 2143(1) መሰረት ተደርጎ በሰበር መዝገብ የተሰጠው ትርጉም ሲሆን ይሕ ትርጉም በሰበር መዝገብ (በቅጽ 22 እንደታተመ) የተለወጠና ያላግባብ መበልጸገን መሰረት አድርጎ የቀረበ ክስ ቢሆን እንኳን ይርጋ ጊዜው በፍ/ሕ/ቁ. 1845 የተመለከተው የ10 ዓመት ጊዜ በመሆኑ ውሳኔ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ ያቀረቡት ከጋራ ሀብት የተገኘ የኪራይ ገንዘብ ያካፍለኝ ክስ ሲሆን በፍ/ሕ/ቁ. 1170(2) እንደተመለከተው የንብረት ፍሬ ማለት ሀብቱ በየጊዜው የሚሰጠው አበልና ነገሩም እንደተመደበበት ጉዲይ ከዚህ ላይ ለመውሰድ ልማድ በሚፈቅደው መሰረት የሚገኝ ሁለ ሲሆን አመልካችና ተጠሪ ያላቸው የጋራ የማይንቀሳቀስ ንብረት ተከራይቶ የሚገኘው ገቢ በድንጋጌው ማዔቀፍ ውስጥ የሚወድቅ ነው። በፍ/ሕ/ቁ. 1264(1) መሰረት ካልተከፊፈለው የጋራ ንብረት ላይ የሚገኘው ፍሬ፣ ጥቅም ያልተከፊፈለ እንደሆነና በንዐስ ቁጥር ሁለት ላይ እንደተደነገገው እያንዲንደ የጋራ ባለሀብት በማንኛውም ጊዜ ክፍያ እንዱደረግ መጠየቅ ይችላል። ተጠሪም ያቀረቡት ክስ የጋራ ሀብቱ ላይ ከነሀሴ 06 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት ሕዲር 05 ቀን 2009 ዓ/ም ጊዜ ድረስ በኪራይ የተገኘውን ገቢ አመልካች ሉያካፍለኝ ይገባል የሚል በመሆኑና የጋራ ሀብት ላይ የሚገኝ ፍሬ ከጋራ ባለሀብቱ አንደ ወገን ክፍያ እንዱደረግ ሲጠይቅ የሚከፊፈል በመሆኑ ክሱ በይርጋ ሉታገድ የሚገባው አይደለም ብለናል።
የክሱን ሥረ ነገር በተመለከተ አመልካች የጋራ ሀብት መሆኑን አምነው የሚከራከሩ በመሆኑ የጋራ ሀብቱ ገቢ አስገኝቷል ወይስ አላስገኘም? ገቢ ካስገኘስ ምን ያህል ነው? የሚለውን በፍ/ሕ/ቁ. 2001(1) እና በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 259 እና 260 መሰረት የአንድን ፍሬ ነገር መኖር ጠቅሶ የሚከራከር ወገን ፍሬ ነገሩ ስለመኖሩ የማስረዲት ግዳታ ስላለበት የተጠሪ ግዳታ ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማትና በመመዘን የጋራ ሀብቱን በማከራየት የተገኘው የተጠሪ ድርሻ ብር 367,500.00 ስለመሆኑ ድምዲሜ ላይ ደርሷል። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በኢፋዱሪ ሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 80(3) ሆነ የፍደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ላይ በመጨረሻ ውሳኔ ላይ በተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንጂ ማስረጃው ተመዝኖ የተደረሰበትን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ላይ እንዱመለከት ሥልጣን አልተሰጠውም።
በሥር ፍርድ ቤት የማስረጃ ምዘና ሂደት የተፈጸመ የማስረጃ ሕግና ማስረጃ ምዘና መርሕ ጥሰት መኖሩን የክርክሩ ሂደት አያሳይም። ስለሆነም በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አልተቀበልነውም።
በልላ በኩል አመልካች ገቢ ቢኖር እንኳን የማካፈል ኃላፉነት የለብኝም በማለት የሚከራከሩ ሲሆን የሚጠቅሱት ምክንያት ደግሞ ተጠሪ በባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር ጊዜ ንብረቱን አመልካች እንዱገለገለበት ፈቅደዋል በማለት ነው። የባልና ሚስት ክርክር የተደረገበት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመዝገብ ላይ የተሰጠው ውሳኔ እንደተመለከትነው ተጠሪ የንብረት ክፍፍለ ቢቆይና አመልካች ቢገለገለበት ተቃውሞ የላላቸው ስለመሆኑ በክርክሩ ሂደት የገለጹ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ንብረቱን ግራቀኙ በዓይነት እንዱካፈለ ወይም በጋራ እንዱገለገለበት መወሰኑ ሲታይ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አመልካች ንብረቱን ለዘለቄታው በግል እንዱገለገለበት ፈቃድ የማይሰጥ በመሆኑ ክርክሩ ተቀባይነት የለውም ብለናል። በአጠቃላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር የሥር ፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔን ማጽናቱ ላይ የተፈፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ነሀሴ 13 ቀን 2012 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።
አፈጻጸሙ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል። ይጻፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.