የውል ስምምነት ሰነድ ርዔሱ የመኖሪያ ቤት ቀብድ ውል ስምምነት የሚል ሆኖ ይዘቱም ተዋዋይ ወገኖች ውለን በውል እና ማስረጃ ፅ/ቤት ለወደፉት ቀርበው ሲዋዋለ ሻጭ ቀሪውን ገንዘብ በመቀበል ቤትና ይዞታውን ለገዢ ለማስረከብ መስማማታቸውን እንጂ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ ውል በሰፈረው ሃሳብ መሰረት ተዋዋይ ወገኖች ውልና ማስረጃ ቀርበው የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል ስምምነት አመለኖሩንና እንዱሁም ተደርጓል የተባለው የመኖሪያ ቤት ቀብድ ውል ስምምነትም ቢሆን የሻጭ ባልሆነና ከካርታ ውጪ ያለ የመንግስት ይዞታ ጭምር ላይ የተደረገ ከሆነ ከአመሰራረት ጋር በተያያዘ ተደራራቢ የህግ ክፍተት ያለበትና በጥቅለ የህጉን መሰፈርት በጠበቀ እና በተሟላ መልኩ የተቋቋመ ባለመሆኑ የህግ ጥበቃ የማይደረግለት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1723(1)፣1678(ለ)፣1715(1)፣2266፣2879 እና ላልችም በቅድሚያ በተዋዋይ ወገኖች መካከል በህግ አግባብ የተቋቋመ ውል ኖሮ ነገር ግን ሻጩ ወይም ቀብደን የተቀበለው ወገን ይህ በመካከላቸዉ በህጉ አግባብ የተቋቋመዉን እና የፀናውን ውል በራሱ ፍቃድ ማፍረስ ከፈለገ የተቀበለውን ቀብድ አጠፋታ ለላላኛው ወገን መልሶ በመክፈል ውለን በነፃነት ማፍረስ የሚችል ሲሆን ነገር ግን በግራ ቀኙ መካከል በሃሳብ አቶ ሰለሞን ደቻሳ እና አቶ አየለ አበቴ እና ጅማሮ የቀረ ረቂቅ እንጂ በህጉ አግባብ የተደረገ ቤት ሽያጭ ውል በላለበት ሁኔታ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1815 (1) ስር እንደተመለከተው ተዋዋይ ወገኖች ውለታው ከመደረጉ በፉት እንደነበሩበት ሁኔታ እንዱመለሱ በማደረግ ሻጭ የተቀበለውን ገንዘብ ብቻ ለገዢ እንዱመልስ ይደረጋል እንጂ ረቂቅ ውለን መሰረት በማድረግ የተቀበለውን ገንዘብ አጠፋታ ሉከፍል የሚገደድበት የህግ አግባብ የላለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ.1883 እንዱሁም 1885(2)
No summary available.
የሰ/መ/ ቀን፡- 29/09/2015 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ረታ ቶልሳ እንዲሻ አዲነ ቀነዓ ቂጣታ ኑረዱን ከድር አመልካች፡- አቶ ሰለሞን ደቻሳ ተጠሪ፡- አቶ አየለ አበቴ መዝገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ሲሆን በዚሁ መሰረት ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
መዝገቡ ተከፍቶ ላቀርብ የቻለው አመልካች ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 27/11/2013 ዓ.ም እና የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 11/08/2014 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት በማመልከታቸዉ ነው።
ጉዲዩ ከቤት ሽያጭ ውል ጋር የተያያዘ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን በስር ፍ/ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል።
አመልካች በ27/11/2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ አመልካች ከተጠሪ ጋር በቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 10 የቤት ቁጥር አዱስ ከሆነው ከክፍለ ከተማው ጋር ሉዝ ከተዋዋለበት ይዞታ ላይ 440 ካ.ሜ የይዞታ መጠንና አምስት በብልኬት የተገነቡ ቤቶች ያለበትን እንዱሁም ከካርታ ውጪ በይዞታቸው የሚገኘውንና አንድ ክፍል ብልኬት ቤትና የቆርቆሮ ቤት ያለበትን በግምት 300 ካ.ሜ.ወደፉት ወደ ይዞታቸው የሚካተትና ከይዞታቸው አስቆርጠው ለአመልካች የሚያስረክቡት ቤትና ይዞታ በብር 4,224,000.00( አራት ሚልዮን ሁለት መቶ ሃያ አራት ሺህ አምስት መቶ ብር) ሸጠውላቸዋል።ለዚህም ነሐሴ 02 ቀን 2012 ዓ.ም የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል መፈራረማቸውን፤
ከውለ በፉት ብር 800,000፣የውለ ቀን ብር 200,000 እንዱሁም ከውለ በኃላ በተለያዩ ቀናት የገንዘብ መጠኑ ብር 624,000 ከፍያለሁ፣ ብር 37,189.90 ለአጥርና የበር ስራ ቀሪ ክፍያ በአመልካች የንግድ ባንክ አካውንት ገቢ አድርጊያለሁ፤ በተጨማሪም በሽያጭ በተስማሙበት ይዞታ ላይ አጥርና በሮች ላስገነቡበት ብር 342,000 በምስክር ፉት በጥሬ ገንዘብ መክፈላቸውን፤ ሆኖም ተጠሪ ነሐሴ 2 ቀን 2012 ዓ.ም በተደረገው የመኖሪ ቤት ሽያጭ ዉል መሰረት ለመፈጸም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ተጠሪ ለአመልካች የሸጡትን ቤትና ይዞታ ለአመልካች እንዱያስተላልፈና ለስም ዝውውሩ አስፈላጊ የሆኑ ተግባሮችን እንዱፈጽሙ ውሳኔ እንዱሰጥላቸው ጠይቀዋል።
ተጠሪ በቀን 15/08/2013 ዓ.ም በተጻፈ መልስ ነሐሴ 2 ቀን 2012 ዓ.ም የተደረገው ውል ላይ ውለ ስልጣን ባለው አካል ፉት ግራ ቀኙ ቀርበው ለመፈጸም ቢስማሙም ሻጭ ከመነሻውም ለገዢ ሉያስተላለፈት በማይችለት ጉዲይ ላይ ብቻ ሳይሆን መብታቸው ባልሆነ ሀብት ጭምር ላይም የተደረገ ውል በመሆኑ ውለ ሉፈጸም የማይችል ነው፤ ውለም ረቂቅ ውል በመሆኑ በዚህ ውል አማካኝነት ተጠሪ እንድፈጽም ልገደድ አይገባም፤ ውለ የዉል አጻጻፍ ፍርምን፤ ያልተከተለ በመሆኑ ፈራሽ ነው፤
አመልካች ከካርታ ውጪ 300 ካ.ሜ ቤትና ይዞታ ለመረከብ ያቀረቡት ጥያቄ ተጠሪ በዚህ ቦታ ላይ የሚያዙበት መብት የላለውና የመንግስት ይዞታ ነው፤ አመልካቸው ውለታ ፈጸምኩበት የሚለት ቤትና ይዞታ ስመሀብት የላለውና ሰነድ አልባ ነው፤ ተፈጸመ የተባለው የቤት ሽያጭ ውል በሙለም ሆነ በከፉል የሻጭ ሀብት ባልሆነ ላይ በመሆኑ ሉፈጸም የሚችል ውል የለም ተብል ውሳኔ እንዱሰጥና ተዋዋዮች ወደነበሩበት ሉመለሱ የሚገባ መሆኑን፤ተጠሪ ውለን በህግ አግባብ ተፈጻሚ ለማድረግ ባደረጉት ሂደት የቦላ ክ/ከተማ መሬት አስተዲደር ጽ/ቤት ከካርታ ውጪ ውል የተፈጸመበት 300 ካ.ሜ መሬት በይዞታቸው እንደማይካተት ስላሳወቃቸው የውለ ዓላማ ህገ ወጥ ሆኖ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነ ፍ/ቤቱ ሉፈጸም የሚችል ውል የለም ብል እንዱወስንልን፤በአመልካች የቀረቡት የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችም የሀሰት ሰነድችና ውለን ሉያስረደ የሚችለ ሰነድች ስላልሆኑ ሰነድቹ ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በበኩለ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ አመልካች መብት አስገኝቶልኛል በማለት ያቀረቡት ዉል ስምምነት ሰነድ የሽያጭ ውል ሳይሆን የቀብድ ውል እና ወደፉት በውልና ማስረጃ ቀርበው ለመዋዋል ስምምነት ያደረጉበት እንጂ የሽያጭ ውል ባለመሆኑ እና ይህ አይነት ስምምነት ደግሞ በህግ ፉት ዋጋ ያለው ሆኖ ሉጸና የሚችል ስምምነት ነው ብል ውጤት ለመስጠት የሚቻል ባለመሆኑ አመልካች ይህን በህግ ፉት ሉፀና የማይችለውን ውል መነሻ በማድረግ ተጠሪ ቤትና ይዞታውን ያስረክቡኝ እንዱሁም ስመሀብት ያዙሩልኝ በማለት ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም፤ተጠሪ ከአመልካች የተቀበለትን ገንዘብ ክሱ ሲሰማ ባመኑት መሰረት ብር 1,724,000 ለአመልካች ሉከፍለ ይገባል፤ ውጪና ኪሳራን በተመለከተ የየራሳቸዉን ይቻቻለ ሲል ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋደራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ፍ/ቤቱም ግራቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኃላ ተጠሪ ለአመልካች እንዱከፍለ ውሳኔ ካረፈበት ገንዘብ ውጪ ለአጥርና የበር ስራ ብር 37,189.90 እና ብር 342,000 አመልካች ወጭ በማድረግ ለተጠሪ ከፍለዋል? አልከፈለም? ተጠሪ ይህንን ገንዘብ ሉመልሱ ይገባል? አይገባም? በሚለው ጭብጥ ላይ አከራክሮ ውሳኔ እንዱሰጥ ወደ ስር ፍ/ቤት መልሶ በላልች ጉዲዮች ላይ ግን የከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት ወስኗል።
አመልካች ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት የሰበር አቤቱታም ይሄንኑን ውሳኔ በመቃወም የቀረበ ሲሆን ይዘቱም ባጭሩ፡- ተጠሪ ክደው የተከራከሩት በይዞታቸው አድርገው እየተጠቀሙበት የነበረውንና ህጋዊ ባለይዞታ ያልሆኑበትን 300 ካ.ሜ በተመለከተ እንጂ ከአመልካች ጋር ውል የፈጸሙበትን እና ህጋዊ ባለይዞታ የሆኑበትን 440 ካ.ሜ ይዞታ ባለመሆኑ የስር ፍ/ቤት ባመኑት መሰረት ለአመልካች ይህንን ይዞታ እንዱያስረክቡ ሉወስን ይገባ የነበረ መሆኑን፤ የስር ፍ/ቤት ውለ የቀብድ ውል ነው በሚል በተከራካሪ ወገኖች ያልተነሳ ክርክርን በማንሳት ውለ የቀብድ ውል ነው ሲል የደረሰበት ድምዲሜ ስህተት መሆኑን፤ ፍ/ቤቱ ውለ የቀብድ ውል ነው ካለም በቀብድ ውል ድንጋጌ መሰረት አመልካች የከፈለትን ገንዘብ አጠፋታ እንዱከፈላቸው ሉወስን ሲገባ ይህን አለመደረጉ ስህተት ነው የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ በሰበር አጣሪው ችልት ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት በግራቀኙ መካከል የተደረገው ስምምነት የሽያጭ ውል ሳይሆን የቀብድ ውል ነው በማለት ድምዲሜ ላይ ከደረሰ በኃላ ተጠሪ በቀብድ ውል ምክንያት የተቀበለትን ክፍያ አጠፋታ መክፈል አለባቸው? ወይስ የለባቸውም?
የሚለውን ሳይወሰን ያለፈበትን አግባብነት ከፍህ/ቁ.1885 እና ተያያዥ ጉዲዮች ለማጣራት የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል።
ተጠሪም በበኩለ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ ሐምል 19 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ ከሰበር አጣሪ ችልት ማስቀረቢያ ጭብጥ አንፃር ያቀረበዉ መልስ ይዘት ዝርዝሩ ሲታይ፡- የፍ/ህ/ቁ 1885(2) ተፈጻሚ የሚሆነው ቀብድ የተቀበለው ወገን የተቀበለውን ቀብድ አጠፋታ በመክፈል ውል ለማፍረስ የፈለገ እንደሆነ እንጂ ውለ ሕገ ወጥ በመሆኑ በሚፈርስ ውል ላይ አለመሆኑን፤ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ተፈጸመ በተባለው ውል ላይ ያቀረቡት ተቃውሞ ውል አልተፈጸመም የሚል ሳይሆን ሽያጩ ከተከናወነበት 440 ካ.ሜ ይዞታቸው ላይ 300 ካ.ሜ ይዞታ የራሳቸው ያልሆነና የመንግስት መሬት ላይ በመሆኑ ውለ ሕገ ወጥ እና ሉፈፀም የማይችል በመሆኑ በዚህ ምክንያት ሉፈርስ ይገባል የሚል ክርክር መሆኑን፤ የቦላ ክ/ከተማ የመሬት ልማት ማኔጅመንትም ሆነ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር መሬት ልማት ጽ/ቤት በሽያጭ ውለ ላይ የተካተተው 300 ካ.ሜ ይዞታ የመንግስት ይዞታ መሆኑን ማረጋገጣቸውን፤ ይህ ደግሞ የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 40(3) በተቃረነ መልኩ የተፈጸመ ውል በመሆኑ ሉፈርስ ይገባል የሚል ድምዲሜ ላይ ሉያደርስ የሚገባ እንጂ ተጠሪ ውል አፍርሰዋል በሚል የቀብደን አጠፋታ ሉከፍለ ይገባል ተብል ድምዲሜ ላይ የሚያደርስ አለመሆኑን፤የፍ/ብ/ህ/ቁ.1885 ተፈጻሚ ላሆን የሚገባው አመልካችና ተጠሪ በውለ ላይ ህጋዊ ውል ስምምነት የፈጸሙ እንደሆነና ተጠሪ ግን ውለን ለማፍረስ የፈለገ እንደሆነና የቀብደን አጠፋታ በመክፈል ውለ እንዱፈርስለት የጠየቀ እንደሆነ እንጂ ዉለ ራሱ ህገ-ወጥ በመሆኑ ምክንያት በፍ/ቤት ውሳኔ የፈረሰ እንደሆነ አይደለም የሚል ነው።
አመልካች የሰበር አቤቱታውን የሚያጠናክር ነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቦ ከመዝገቡ ጋር እንዱያያዝ ተደርጓል።
ከስር ጀምሮ በግራ ቀኙ የቀረበዉ ክርክር፣በስር ፍ/በቶች የተሰጠ ዉሳኔና እንዱሁም ባጠቃላይ የጉዲዩ አመጣጥ እና ይዘት ከፍ ሲል ባጭሩ የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም ጉዲዩ ያስቀርባል ሲባል በሰበር አጠሪ ችልቱ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንፃር በስር ፍ/ቤቶቹ ዉሳኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን ከግራ ቀኙ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለዉ መልኩ መርምረናል።
በመጀመሪያ ደረጃ በጭብጥነት ወደተያዘዉ ዋና ጉዲይ በቀጥታ ከመግባታችን በፉት ለመነሻ ያህል ቤትን ጨምሮ ባጠቃላይ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ባለቤትነት መብትን በዉል ለማቋቋምም ሆነ ከአንደ ወደ ላላ ለማስተላለፍ የሚደረጉ ዉልችን በተመለከተ ህጉ በዚህ ረገድ የወሰደዉን አቋም በትክክል የተመለከትን እንደሆነ ስለ ዉልች አመሰራረት አጠቃላይ ጉዲይን የሚገዛዉ ፍትሓብሄር ህጉ ክፍል አንቀፅ 1723(1) ድንጋጌ ስር የማይንቀሳቀስ ንብረቶች ባለቤትነት ወይም በአንድ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የአላባ ጥቅም ወይም የመያዣ ወይም የላላ አገልግልት መብት ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የሚደረጉት ውልች ሁለ በፅሁፍ እና በሚገባ አኳኃን በፍ/ቤት መዝገብ ወይም ውል ለመዋዋል ስልጣን በተሰጠው ፉት መሆን እንዲለባቸው አስገዲጅነት ባለው መልኩ መደንገጉን መገንዘብ ይቻላል።
ከዚህ አንፃር ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ለክሱ ምክንያት ያደረገው እና በማስረጃነትም ከክሱ ጋር አያይዞ ያቀረበው ውል ስምምነት ሰነድ ርዔሱ የመኖሪያ ቤት ቀብድ ውል ስምምነት የሚል ሆኖ ይዘቱም ግራ ቀኙ ተዋዋይ ወገኖች ውለን በውል እና ማስረጃ ፅ/ቤት ለወደፉት ቀርበው ሲዋዋለ ሻጭ ቀሪውን ገንዘብ በመቀበል ቤትና ይዞታውን ለገዢ ለማስረከብ መስማማታቸውን እንጂ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ ውል በሰፈረው ግራ ቀኙ ሃሳብ መሰረት ግራ ቀኙ ውልና ማስረጃ ቀርበው የተደረገ ቤት ሽያጭ ውል ስምምነት አመለኖሩንና እንዱሁም ይህ ከፍ ሲል በተገለፀው አኳኃን በግራ ቀኙ መካከል ተደርጓል የተባለው የመኖሪያ ቤት ቀብድ ውል ስምምነትም ቢሆን የተጠሪ ባልሆነና ከካርታ ውጪ ያለ 300 ካ.ሜ መንግስት ይዞታ ጭምር ላይ የተደረገ መሆኑን የስር /ቤቶች ውሳኔ ግልባጭ በግልፅ ያስረዲለ።
እንግዱህ አመልካች ይህ ላቀረቡት ዲኝነት ጥያቄያቸው እና ክርክራቸው መሰረት ያደረጉት ውለ ይዘት ይህ ከሆነ ከዚህ በቀላለ መገንዘብ እንደሚቻለዉ ግራ ቀኙ የቤት ሽያጭ ውል ገና ለወደፉቱ ዉል እና ማስረጃ ምዝገባ እና ማረጋገጫ ፅ/ቤት ቀርበዉ ለመፈፀም ሲሆን ሆኖም ይህን ባለመፈፀማቸዉ ምክንያት የግራ ቀኙ ሃሳብ በጅማሮ እና ረቂቅ ደረጃ የቀረ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ይህ ረቂቅ የተባለው ውል ሰነድም ቢሆን የተጠሪ (ሻጭ) ባልሆነና መብቱን ለላላ ማስተላለፍ በማይችለው 300 ካ.ሜ ካርታ ውጪ ባለ ይዞታ ላይ ጭምር የተደረገ ከመሆኑ ጋር ጉዲዩ በአንድ ላይ ተዲምሮና ተገናዝቦ ሲታይ ዉለ ከአመሰራረት ጋር በተያያዘ ተደራራቢ የህግ ክፍተት ያለበትና በጥቅለ የህጉን መሰፈርት በጠበቀ እና በተሟላ መልኩ የተቋቋመ ባለመሆኑ ዉለ በዚህ ምክንያት የህግ ጥበቃ ላደረግለት የሚገባ አይደለም(የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723(1)፣ 1678(ለ)፣1715(1)፣2266፣2879 እና ላልችንም ይመለከታል)።
ስለሆነም ተጠሪ ውለን መሰረት በማድረግ ቤትና ይዞታውን እንዱያስረክብ እንዱሁም ስመ ሀብቱን ወደ አመልካች ለማዞር ሉገደድ አይችልም ሲለ የስር ፍ/ቤቶች የደረሱበት መደምደሚያም ሆነ በዚህ ረገድ የሰጡት ውሳኔ ክፍል ህጉን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የሚነቀፍ አይደለም።በመሆኑም አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡት ሰበር ቅሬታ እና ክርክር በዚህ ምክንያት ተቀባይነት ያለዉ አይደለም።
በመቀጠል የዚህን ሰበር ችልት ምላሽ ይሻል በሚል በሰበር አጣሪ ችልቱ በጭብጥነት ወደተያዘዉ ዋና ሰበር ክርክር ነጥብ ወደ ሆነዉ ተጠሪ የተቀበለትን ቀበድ አጠፋታ ሉከፍለ ይገባል? ወይስ ይገባም?
የሚለውን ስንመለከት ደግሞ በመሰረቱ አንደ ተዋዋይ ወገን ለላላኛው ተዋዋይ ወገን ቀብድ መስጠቱ በማያከራክር ሁኔታ ውል መደረጉን አረጋጋጭ እንደሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1883 ስር በህጉ የተደነገገዉ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ይህ በህግ የተቋቋመዉን ዉል ላላ ተቃራኒ ስምምነት ከላለ በቀር ቀብድ የተቀበለ ተዋዋይ ወገን ይህንኑን የተቀበለዉን ቀብድ አጠፋታ በመክፈል ዉለን ለማፍረስ እንደሚችል እንዱሁ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1885(2) ስር የተደነገገ ሲሆን ከእነዚህ ከተጠቃሹ ህጉ ድንጋጌዎች ይዘትና አቀራረፅም መገንዘብ የሚቻለው በቅድሚያ በተዋዋይ ወገኖች መካከል በህግ አግባብ የተቋቋመ ውል ኖሮ ነገር ግን ሻጩ ወይም ቀብደን የተቀበለው ወገን ይህ በመካከላቸዉ በህጉ አግባብ የተቋቋመዉን እና የፀናውን ውል በራሱ ፍቃድ ማፍረስ ከፈለገ የተቀበለውን ቀብድ አጠፋታ ለላላኛው ወገን መልሶ በመክፈል ውለን በነፃነት ማፍረስ የሚችል መሆኑን ሲሆን በያዝነው ጉዲይ ግን ሲጀመር በግራ ቀኙ መካከል በሃሳብ ደረጃ እና ጅማሮ የቀረ ረቂቅ እንጂ በህጉ አግባብ የተደረገ ቤት ሽያጭ ውል በላለበት ሁኔታ ተጠሪ ረቂቅ ውለን መሰረት በማድረግ የተቀበለውን ገንዘብ አጠፋታ ሉከፍል የሚገደድበት የህግ አግባብ ካለመኖሩም ባሻገር ስር ፍ/ቤት በዚህ ረገድ የቀረበ ዲኝነትም ሆነ ክርክር በላለበት ሁኔታ ይህ ከስነ-ስርዓት ህጉ አንፃርም ሲታይ ተቀባይነት ያለዉ አይደለም(የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.182 ይመለከታል)።
ስለሆነም አመልካች በዚህ ረገድ የጠቀሳቸው ቀብድን የሚመለከቱ ፍትሐብሕር ህጉ አንቀፅ.1883 እና 1885 ድንጋጌዎች ለተያዘው ሰበር ክርክር ጉዲይ አግባብነት ስለላላቸዉ ተጠሪ የተቀበለዉን ገንዘብ አጠፋታ እንዱከፍል ሉያስገድደ የሚችለ አይደለም።
ሲጠቃለል ለዚህ ሰበር ችልት ክርክር ምክንያት የሆነው ዉል በህግ አግባብ የተቋቋመ ሳይሆን ይልቁንም ቀድሞም ቢሆን በህግ አግባብ ያልተቋቋመ፣ በህግ ፉት የማይፀና እና በተዋዋይ ወገኖች ላይ መብትና ግዳታን የማይፈጥር ፈራሽ ከመሆኑ አኳያ ግራ ቀኙ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1815 (1) ስር እንደተመለከተው ውለታው ከመደረጉ በፉት እንደነበሩበት ሁኔታ እንዱመለሱ በማደረግ ማለትም ተጠሪ በዉለ መነሻ ከአመልካች የተቀበለውን ገንዘብ ብቻ ለአመልካች እንዱመልስ ይደረጋል እንጂ አጠፋታ ባለመሆኑ በዚህ ረገድ በስር ፍ/ቤቶች የተደረሰዉ መደምደሚያ ሀሳብም ሆነ የተሰጠው ውሳኔ ክፍል በአግባቡ ነው ልባል ከሚችል በቀር የሚነቀፍና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በማለት ተከታዩ ተወስኗል።
1.የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.213653 በ11/8/2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት፤ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይሄንን ጉዲይ በተመለከተ በኮ/መ/ቁ.269209 በ27/11/2013 ዓ.ም የሰጠዉን ፍርድ፤በማሻሻል የሰጠዉ ፍርድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348(1) መሰረት ፀንቷል።
2.ግራ ቀኙ የዚህን ሰበር ችልት ክርክር ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
የማይነብብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.