No summary available.
ታህሳስ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ዳኞች፡- ሰለሞን አረዲ ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- ኒው ክሬሽን ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን - ጠበቃ-ገ/እግዚያብሄር ሙናቸው - ቀረቡ ተጠሪ፡- ጭላል ኢንተርፔራይዝ ኃ/የተ/የግል ማህበር - ጠበቃ - ስራ አስኪያጅ አሰፊ ደገፈ - ቀረቡ መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠ።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካች የስር ጣልቃ ገብ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበር። በዚህ ፍርድ ቤት ተከራካሪ ያልሆኑት አቶ መኩሪያ ታፈሰ እና ወ/ሮ ሣራ ኖርድ የስር ተከሳሾች ናቸው። ተጠሪ ያቀረበው ክስ በአዱስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 9 የቤት ቁጥር 485 የሆነና በ3252 ካሬ ሜትር ላይ የሚገኝ መኖሪያ ቤት በብር 19,000,000.00 (አስራ ዘጠኝ ሚሉዮን ብር) ተከሳሾች መጋቢት 01 ቀን 2007 ዓ/ም ለተጠሪ ሽጠዋል። ገንዘቡን ተቀብለው የውል ግዳታቸውን ስላልፈጸሙ ቤቱንና ቤቱን የተመለከተ ሰነድ እንዱያስረክቡ፣ የሥም ማዛወሪያ ክፍያ እና አስፈላጊ ላላ ግዳታ እንዱፈጽሙ እና የውለን መቀጫ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እንዱከፍለ ዲኝነት ጠይቋል።
ተከሳሾች ያቀረቡት መልስ ውለ በውል አዋዋይ ፉት አልተደረገም። ተጠሪ አዋክቦ ውለን ቢያስፈርመንም ቤት ሆነ ሰነድ አልተረከበም። ከውለ ገንዘብ ውስጥ ብር 5,500,000.00 በቼክ ለመክፈል የሰጠ ቢሆንም ቼኩ ስንቅ የለውም የተባለ ስለሆነ ተጠሪ የውል ግዳታውን አልተወጣም።
ውለም የፈረሰ ስለመሆኑ በጽሁፍና በፕስታ ቤት አማካኝነት ቢላክለትም ፈቃደኛ አልሆነም። ውለ ስለፈረሰ ቤቱን ለ3ኛ ወገን በቀድሞ ዋጋ ሽጠን አስረክበናል። ተጠሪ የውል ግዳታውን ስላልተወጣ ውለ ይፈጸም ማለት አይችልም ሲለ አቅርበዋል።
አመልካች በክርክሩ ጣልቃ በመግባት ክርክር ያስነሳውን ቤት ሚያዚያ 11 ቀን 2007 ዓ/ም ከተከሳሾች ገዝተናል። የተጠሪ ውልም በፍ/ሕ/ቁ. 2878 መሰረት በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ላይ ስላልተመዘገበ አመልካች ላይ ውጤት የለውም። ተጠሪ የውል ግዳታውን ስላልተወጣና ቤትና ሰነድ ስላልተረከበ ውለ ፈራሽ ነው። ቤቱን ተረክበን ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የማሻሻያ ተግባር እያከናወን እንገኛለን። ተጠሪ ለተከሳሾች የሰጠው ቼክ በቂ ስንቅ የለውም የተባለው በስህተት ነው በማለት ባንኩ የጻፈው ማስረጃ ባላቸው ድብቅ ግንኙነት የተፈጸመ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም ይባልልን ብለዋል።
ተጠሪ ለአመልካች ክርክር የሰጠው መልስ ክፍያውን ሚያዚያ 12 ቀን 2007 ዓ/ም የተፈጸመ በማስመሰል ያቀረቡት ተቀባይነት የለውም። ሲፑኦ ይዘው ሲሄደ ሚያዚያ 13 ቀን 2007 ዓ/ም በፍርድ ቤት እግድ ምክንያት ሲፑኦውን ይዘው ተመልሰዋል። አመልካች ቤቱን ለቤተ አምልኮ እንፈልገዋለን ልቀቅልን ብለዋል። ለተከሳሾች የተሰጠው ቼክ በቂ ስንቅ የለውም ብል ባንኩ የጻፈውን ደብዲቤ አብረው ከተከሳሾች ጋርም መወስዲቸው ቤቱ ለተጠሪ መተላለፈን እያወቁ የገዙት መሆኑን ያሳያል። ቼኩ በቂ ስንቅ እያለው ተከሳሾች አለመውሰዲቸው ለመጠቃቀም ፍላጎት ስላላቸው ብቻ ነው። ብር 5,500,000.00 አልተከፈለም ቢባል እንኳን ውል ለማፍረስ በቂ ምክንያት አይደለም። በተናጠል ውለን ለማፍረስ የሚያስችል ስምምነት የለንም። ቤቱ ሚያዚያ 12 ቀን 2007 ዓ/ም እንዱታገድ ስለታዘዘ በአመልካች እጅ ሉገባ አይችልም ብሎል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ የተጠሪ ውል ያልተመዘገበ ቢሆንም በተለመደው አሰራር አመልካች ይህንኑ ቤት ከመግዛቱ በፉት እዚህ ቤት ላይ ያለውን የመብት ጥያቄ ሳያጣራ ይህን ሁለ ገንዝብ አውጥቶ የሽያጭ ውል ይፈጽማል ብል መገመት አይቻልም። የተጠሪ ምስክሮች የአመልካች አባላትና ኮሚቴ ይህንን ቤትና ቦታ ለአመልካች ቤተ አምልኮነት መፈለጋቸውን በመግለጽ እንዱተውለት በአካልም ሆነ በስልክ መጠየቃቸውንና ተጠሪ ግን ለመተው ፈቃደኛ አለመሆኑን መግለጹን የመሰከሩ ሲሆን የአመልካች ምስክሮችም ተከሳሾች ቤቱን ለላላ ሰው የሸጡት መሆኑን ነገር ግን የሚጠብቁት ነገር እንዲለ የገለጹላቸው መሆኑን፣ ውለ ከተፈጸመ በኋላ ሚያዚያ 12 ቀን 2007 ዓ/ም ውልና ማስረጃ ሲሄደ ቤቱ መታገደን ካወቁ በኋላ ተጠሪን ለምን እንዲሳገደውና እንዱተውላቸው መጠየቃቸውን መግለጻቸው አመልካች በሚያዚያ 11 ቀን 2007 ዓ/ም የፈጸመችው ውል ባለማወቅና በቅን ልቦና ሳይሆን ተጠሪ ቤቱን መጋቢት 01 ቀን 2007 ዓ/ም መግዛቱን እያወቀች የፈጸመችው መሆኑን ተረድተናል።
No topics extracted.
የተጠሪ ውል ያልተመዘገበ ነው ለተባለው የአመልካችም ውል ያልተመዘገበ ነው። የፍ/ሕ/ቁ. 2878 ለ3ኛ ወገኖች ማሳወቅ ዓላማ ያለው ሲሆን 3ኛ ወገኖች ውለን ያውቁት እንደነበር ማረጋገጥ እስከተቻለ ድረስ አለመመዝገቡ የሚያመጣው ለውጥ የለም። አመልካች የሚጠበቅባትን ጥንቃቄ ሳታደርግና ከተጠሪ ጋር ቀድሞ የተደረገ ውል መኖሩን እያወቀች በመደረብ የፈጸመችው ውል ስለሆነ ተጠሪ እና ተከሳሾች የፈጸሙት የሽያጭ ውል ስላልተመዘገበ ብቻ አመልካች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ማለት አይቻልም።
ከተከሳሾች አንጻር የተጠሪን ውል አልካደም። ብር 5,500,000.00 ለተከሳሾች ከተጠሪ የተሰጠው ቼክ በቂ ስንቅ እንደነበረው ተረጋግጧል። ባይኖረው እንኳን አብዛኛው የውለ ግዳታ የተፈጸመ በመሆኑ ውል ለማፍረስ በቂ ምክንያት አይደለም። ስለሆነም ክስ የቀረበበትን ቤትና የቤቱን ሰነድ ተከሳሾች ለተጠሪ እንዱያስረክቡ እና ተጠሪ ያልተመነዘረውን ቼክ ገንዘብ ብር 5,500,000.00 እንዱከፍል ወስኗል። መቀጮ እንዱከፈል የተጠየቀውን ዲኝነት ውደቅ አድርጓል። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች ያቀረበችውን ይግባኝ ባለመቀበል ቅሬታውን ሰርዟል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ቤቱን ተጠሪ ስለመግዛቱ ከክርክሩ በፉት ማወቃችን የሚያስረዲ ማስረጃ አልቀረበም። 3ኛ ወገንን በውል ለመቃወም በፍ/ሕ/ቁ. 1723 እና በፍ/ሕ/ቁ. 2878 መሰረት የተመዘገበ መሆን አለበት። ቤትና ሰነድ ከተያዘ ቅን ልቦና እንዲለ ሉወሰድ ይገባል። የማስፊፉያ ስራ ወጪ አውጥተንበታል። የተጠሪ ምሰክሮች የድርጅቱ ባለቤትና ድርሻ ያላቸው ልጃቸው ናቸው። ከውል አዋዋይ አካል ውጭ የተደረገ ተመሳሳይ ውል ሲገኝ ገንዘብ አከፊፈል፣ ቤትና ሰነድ ርክክብ እና እድሳት ወጪ ጋር ተገናዝቦ መታየት አለበት የሚል ነው።
የሰበር አጣሪ ችልት አመልካች ቤቱንና አስፈላጊ ሰነድ የተረከቡ መሆኑን እየገለጹ ባለበት ሁኔታ የተሻለ መብት ያለው ማነው የሚለውን ከፍ/ሕ/ቁ. 1161 እና ከሰበር መዝገብ አንጻር ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርብ በማዘዙ ተጠሪ ያቀረበው መልስ የተጠሪን ውል አላውቅም ቢለም ማስረጃ ተሰምቶ ውለን እንደሚያውቁ ተረጋግጧል። ቤቱንም እስከ ግንቦት 04 ቀን 2007 ዓ/ም ድረስ በሻጭ እጅ እንደነበር በሚመለከተው ጽ/ቤት ተረጋግጧል። በአፈጻጸም የተረከብኩት ከተከሳሾች ነው። የውለን ክፍያ ለሻጭ አልከፈለም። ሰነድም አልረተከቡም፤ ቢረከቡ ኖሮ በማስረጃነት ያቀርቡት ነበር። ቤቱ በእጃቸው ስላልነበረ እድሳት አድርጊያለሁ የሚለት ተቀባይነት የለውም።
ውሳኔው ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክሯል። አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታዋን በማጠናከር ተከራክራለች።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ክርክሩ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ተከትል የተመራ መሆን አለመሆኑን በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው ተጠሪ ክርክር ያስነሳውን ቤት በስር ፍርድ ቤት ተከሳሾች ከነበሩት ከአቶ መኩሪያ ታፈሰ እና ወ/ሮ ሣራ ኖርድ መጋቢት 01 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ ውል የገዛ ሲሆን እንደ ውለ ባለመፈጸሙ ሻጮች የሆኑት የስር ተከሳሾች በውለ መሰረት ቤቱን እና የቤቱን ሰነድች ሆነ ላላ አስፈላጊ ተግባር እንዱፈጽሙ ክስ አቅርቧል። ውለ የፍ/ሕ/ቁ. 1723 በሚያዘው አግባብ በውል አዋዋይ ፉት ያልተደረገ ቢሆንም የስር ተከሳሶች ውል መኖሩን ያመኑ በመሆኑ በተጠሪ እና በተከሳሾች መካከል ሕጋዊ የሆነ የፀና ውል አለ ማለት ይቻላል። የፀና ውል ካለ ደግሞ ሻጭ በውል የገባውን ግዳታ፤
በፍ/ሕ/ቁ. 1731(1) እንደተደነገገው ውል በተዋዋዮች መካከል እንደሕግ የሚቆጠር ስለሆነ እና ውል እንዱፈጸም የተጠየቀው የማይንቀሳቀስ ንብረት በመሆኑ ተጠሪ ልዩ ፍላጎት ንብረቱ ላይ እንዲለው ግምት ስለሚወሰድ፤ የመፈጸም ግዳታ አለበት። በዚህ አግባብም የሥር ፍርድ ቤት ተከሳሾች የነበሩት ውለን እንዱፈጽሙ የተወሰነ መሆኑን ተረድተናል።
በልላ በኩል አመልካች ይህንኑ ቤት ሚያዚያ 11 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ ውል ከስር ተከሳሾች ገዝታለች። የተጠሪ ውል ይፈጸምልኝ ክርክር መብቴን ይነካል በማለትም በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41 መሰረት ጣልቃ ገብታ ተከራክራለች። በመሆኑም ግራ ቀኙ ተከራካሪዎች ቤቱን ከገዙ በቤቱ ላይ የተሻለ መብት ያለው ማን ነው? የሚለው በጭብጥነት ተይዞ እልባት ሉሰጠው የሚገባ ይሆናል። አመልካች ሆነ ተጠሪ ያደረጉት የማይንቀሳቀስ ንብረት ግዥ ውል የፍ/ሕ/ቁ. 1723 በተመለከተው አግባብ በውል አዋዋይ ፉት ያልተደረገ እና በፍ/ሕ/ቁ. 2878 አግባብ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ የተመዘገበ አይደለም።
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41 መሰረት ጣልቃ የሚገባ ተከራካሪ ክርክሩ መብቱን የሚነካው እና በጉዲዩ ላይ የተረጋገጠ መብት ያለው መሆኑን ማሳየት አለበት። በልላ በኩል አመልካች የምትከራከረው ተጠሪ ለመረከብ ዲኝነት የጠየቀበትን ቤት የተመለከተ ሰነድ ሆነ ቤቱን ተረክቤያለሁ በማለት ነው። እንዱህ ከሆነ ተጠሪ በሦስተኛ ወገን እጅ ያለ ንብረትን ተዋዋዮች ተገደው እንዱፈጽሙ መጠየቅ ይችላል ወይስ አይችልም? የሚለውን ጭብጥ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል።
የሥር ፍርድ ቤቶች እነዚህን ክርክሮች በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 246 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት በጭብጥነት በመያዝ አጣርተው የመወሰን ኃላፉነት አለባቸው። አመልካች ቤቱን እና አስፈላጊ ሰነድችን ሚያዚያ 12 ቀን 2007 ዓ/ም በሰነድ የተረከበችና የማሻሻያ ግንባታ የጀመረች መሆኑን በመግለጽ የተከራከረች ሲሆን የሥር ተከሳሾችም ቤቱን ለአመልካች አስረክበናል ብለዋል። ተጠሪ በበኩለ ክስ ካቀረበበት ሚያዚያ 12 ቀን 2007 ዓ/ም በኋላ ግንቦት 04 ቀን 2007 ዓ/ም በስር ፍርድ ቤት በተደረገ ማጣራት ቤቱ በስር ተከሻሾች እጅ እንደነበር በፍትሕ ጽ/ቤት በኩል ተረጋግጧል፤ በአፈጻጸም ሂደትም የተረከብኩት ከተከሳሾች ነው በማለት ተከራክሯል።
የፍትሐ ብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተከራካሪዎች በእኩል የመደመጥ መብት እንዱከበር እና እውነትን የመፈለግ ዓላማ ያለው በመሆኑ እና ዓላማው እንዱሳካ የማድረግም ኃላፉነት የፍርድ ቤቱ ነው።
ስለሆነም የቀረበውን የፍሬ ነገር ክርክር ተከራካሪዎች ባቀረቧቸው የሰው ሆነ የሰነድ ማስረጃዎች በማጣራት እና በተጨማሪም በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 264 መሰረት ለክርክሩ አወሳሰን ጠቃሚ የሆነ ማስረጃ ፍርድ ቤቱ የማስቀረብ ስልጣን እና ኃላፉነት ያለበት በመሆኑ ጉዲዩ ተጣርቶ ተመዝኖ ሉወሰን ይገባ ነበር። የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ቤቱን ስትገዛ ተጠሪ ቤቱን አስቀድሞ መግዛቱን እያወቀች ውለን የፈጸመች መሆኑ ውለ መብት አይሰጣትም በማለት ድምዲሜ የደረሰ ቢሆንም አመልካች እና ተጠሪ ሁለቱም በአንድ ንብረት ላይ ያደረጉት የማይንቀሳቀስ ንብረት ግዥ ውል በፍ/ሕ/ቁ. 1723 በተመለከተው አግባብ በውል አዋዋይ ፉት ያልተደረገ እና በፍ/ሕ/ቁ. 2878 አግባብ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ያልተመዘገበ በመሆኑ ቤቱ በማን እጅ ይገኛል? ቤቱን የተመለከቱ ሰነድችን ማን ይዟል? የሚለትን አጣርቶ ማን የተሻለ መብት አለው? የሚለውን አብሮ በመመዘን መወሰን ሲገባው ማለፈ ስህተት ያለበት ነው። ክርክር ያስነሳው ቤት ሦስተኛ ወገን በሆነችው አመልካች እጅ ካለ ተጠሪ ተዋዋዮች ተገደው እንዱፈጽሙ መጠየቅ ይችላል ወይስ አይችልም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መወሰን ሲገባው ማለፈ ውሳኔው ላይ መሰረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ግድፈት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ታህሳስ 25 ቀን 2011 ዓ/ም እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክርክር ያስነሳው ቤትና ቤቱን የተመለከቱ ሰነድችን በማን እጅ ይገኛል የሚለውን በማጣራት እና አስቀድሞ ከተሰማው ማስረጃ ጋር በመመዘን ማን የተሻለ መብት አለው? ክርክር ያስነሳው ቤት ሦስተኛ ወገን በሆነችው አመልካች እጅ ካለ ተጠሪ ተዋዋዮች ተገደው እንዱፈጽሙ መጠየቅ ይችላል ወይስ አይችልም? የሥር ተከሳሾች ውለን ተገደው መፈጸም የማይችለ ከሆነ ሕጋዊ ውጤቱ ምንድን ነው? የሚለትን ጭብጦች በመመርመር የሥር ተከሳሾችንም ወደ ክርክሩ በማስገባት የመሰለውን እንዱወስን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት ጉዲዩን መልሰናል።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ። የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔው መሰረት እንዱፈጽም አዘናል። ይጻፍ
ሀምላ 10 ቀን 2011 ዓ/ም በዚህ ችልት የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ
የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ ይመለስ።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።