ሻጭ የቤት ሽያጭ ውል ከማድረጉ በፉት የቤቱ ባለቤትነት ላይ ሰነደንና ቤቱን እንዱያስረክብ ክስ ተመስርቶ ቤቱ ላይ እግድ ከመሰጠቱ በፉት ተከሳሽ/ሻጭ ቤቱን በሽያጭ ውል ለ3ኛ ወገን አስተላልፍ ይህ ገዥም በክርክሩ ሳይሳተፍ ሻጭ በክርክሩ ተረትቶ ቤቱን ለከሳሽ እንዱያስረክብ ውሳኔ የተሰጠ ቢሆንም የቤት ሽያጭ ውለ ሲፈፀም ገዥው አንድ ጠንቃቃ አቶ ደሣለኝ ሲሳይ እና እነ ወ/ሮ ድማም ተክለ (2 ሰዎች) በሕግ ሆነ በአሰራር ሉያደርገው የሚገባውን ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፉነት በመወጣት፣ ውለም የተፈጸመው ሻጭ ቤቱን ገዝቶ ሕጋዊ ሰነድ በቤቱ ላይ ካወጣበት በኋላ ሕጋዊ ባለቤት እንዲለው በማረጋገጥ በውል አዋዋይ ፉት የተደረገ ከሆነ ግብይቱ ሕግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የሕግ ጥበቃ ላደረግለት የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 1723(1) ገዥ ውለን የማይንቀሳቀስ ሀብት መዝገብ ላይ እንዱጻፍ በማድረግ ካርታ ያወጣበት ከሆነ ውለ ሦስተኛ ወገኖችን ላይም ውጤት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 2878 ንብረት በሻጭ ስም ከመመዝገቡ እና ወደ ገዥ በሽያጭ ውል በሰነድ ከመዛወሩ በፉት መብቱ የማን ነው የሚለውን ሻጭ የማጣራት ኃላፉነት በሕግ የላለበትና ንብረቱ ላይ በፍርድ ቤት እግድ ከመሰጠቱ በፉት የተዛወረ ከሆነ ከሳሽ ክስ ካቀረበ በኋላ ሽያጭ ውለ መደረጉ ሆነ የተሸጠበት ዋጋ የተደረገውን ግብይት ቀሪና ውጤት አልባ የማያደርገው ስለመሆኑ ገዥ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41 መሰረት ጣልቃ ገብተው ክርክር ያስነሳውን ቤት፣ ሻጭ በስማቸው ካርታ አውጥተው የያዙትን፣ ሥልጣን ባለው አካል የተመዘገበና ስመ-ሀብቱ ተላልፍ የባለቤትነት ማረጋገጫ ያወጣሁበት ነው በማለት ጣልቃ ገብ ከሆኑ፣ ምንም እንኳን ከሳሽ በንብረቱ ላይ መብት ያላቸው ስለመሆኑ በፍርድ የተረጋገጠላቸው ቢሆንም፣ ይህ መብታቸው ከመረጋገጡ በፉት ተከሳሽ/ሻጭ በስማቸው የነበረውን ንብረት ለሦስተኛ ወገን ለሆኑት ገዥ ያስተላለፈ በመሆኑ፤ ከሦስተኛ ወገን መብት አኳያ ንብረቱን ከሳሽ ሉረከቡ የማይችልና ክርክር ያስነሳው ንብረት ሕጋዊ ባለመብት ገዥ በመሆናቸው ከሻስ ንብረት ለመረከብ ያቀረቡት ክስ ውድቅ ላደረግ የሚገባ ስለመሆኑ
No summary available.
ቀን፡- 04/02/2014 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡- አቶ ደሣለኝ ሲሳይ ተጠሪ፡-
የሰበር አቤቱታ የቀረበው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በሚል ነው። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ እና 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል። 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ከባለቤቴ አቶ አዘነ በየነ ጋር የባንክና የዔቁብ ዔዲ ስለነበረብን በቡራዩ ከተማ ዉስጥ የነበረንን ቤት በቀን 24/08/1999 ዓ/ም በተደረገ ዉል ሽጠን በሱለልታ ከተማ ቁምቡሬ በተባለ ቦታ በካርታ ቁጥር ሱል/243/2005 ሆኖ የሚታወቀዉን ቤት የአሁን 2ኛ ተጠሪ ልጃችን ስለሆነ በስሙ ከአቶ ዲዊት አለሙ ላይ ገዝተናል። ይሁን እንጂ ባለቤቴ በሞት ሲለይ አመልካች ቤቱን ስለያዘብኝ ቤቱንና ሰነደን እንዱያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። 2ኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት በራሴ ገንዘብ የገዛሁት እንጂ የ1ኛ ተጠሪ አይደለም ብለዋል። አመልካች በክርክሩ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 41 መሰረት ጣልቃ በመግባት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት በቀን 28/01/2011ዓ/ም በተደረገ ዉል በብር 443,594.25 ከ2ኛ ተጠሪ ላይ ገዝቼ በስሜ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር ሱል/562/11 ከቀን 06/02/2011 ዓ/ም ጀምሮ አስመዝግቤ የያዝኩት ነው። ክርክር ያስነሳውን ቤት በግዥ ያገኘሁት ስለሆነ ሉከራከሩበት አይገባም ብለዋል። 1ኛ ተጠሪ ለጣልቃ-ገብ ማመልከቻ ባቀረቡት መልስ ቤቱን አመልካች የገዛው ክስ ካቀረብኩና እግድ እንዱሰጥ ከጠየቅሁ በኋላ ነው። 2ኛ ተጠሪም ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ነው የሸጠው፤ አመልካች መብት የላለው መሆኑን እያወቀ የገዛው ስለሆነ ክርክሩ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል። 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ንብረቱን ለአመልካች መሸጣቸውን በመግለጽ መልስ አቅርበዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመስማት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት የ2ኛ ተጠሪ አባት(የ1ኛ ተጠሪ ባለቤት) በ2ኛ ተጠሪ ስም ለራሳቸዉ ጥቅም በገንዘባቸዉ የገዙ ስለመሆኑ ምስክሮቻቸዉ አላስረደም። ቤቱ የተገዛዉ በ2ኛ ተጠሪ ስም በመሆኑና ተመዝግቦ የሚገኘዉም በ2ኛ ተጠሪ ስም ስለሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1195 መሰረት 2ኛ ተጠሪ የቤቱ ባለቤት እንደሆኑ ይገመታል። 1ኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ መብት ለማግኘት ቤቱ በ1ኛ ተጠሪ እና በባለቤታቸዉ ገንዘብ በአሁን 2ኛ ተጠሪ ስም መገዛቱን በማስረጃ በማረጋገጥ ግምቱን ማስተባበል ይጠበቅባቸዋል። ከዚህ አንጻር ማስረጃዉ ሲመረመር የቤቱ ባለቤት 2ኛ ተጠሪ እንደሆኑ የሚያስቆጥረዉን ግምት በማስረጃ አላስተባበለም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ ሚዛን በሚደፊ ሁኔታ ማስረጃዎቹ የሚያሳዩት 1ኛ ተጠሪ ከባለቤታቸዉ ጋር የነበራቸዉን እዲ ለመሰወር በማሳብ የነበራቸዉን ቤት ሽጠዉ በ2ኛ ተጠሪ ስም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት መግዛታቸዉን ነዉ።
በሕብረተሰቡ ዉስጥ ባለዉ ተጨባጭ ሁኔታ አባት በልጁ ስም ቤትም ሆነ ላላ ንብረት የሚገዛ መሆኑ የተለመደ ነዉ። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች 1ኛ ተጠሪ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1195 መሰረት ቤቱ በ2ኛ ተጠሪ ስም ሉመዘገብ የቻለበትን ምክንያት በማስረዲት ግምቱን አስተባብለዋል። አመልካች ንብረቱ በቅን ልቦና ከ2ኛ ተጠሪ አልገዙትም፤ 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ ክስ የመሰረቱት በቀን 23/01/2011 ዓ/ም ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ደግሞ አከራካሪዉን ቤት ለአመልካች በሽያጭ ያስተላለፈት በቀን 28/01/2011 ዓ/ም ክሱ ከተመሰረተ ከ5 ቀን በኋላ እንደሆነ የቀረበዉ ማስረጃ ስለሚያሳይና አስቀድሞ ከብር አንድ ሚሉዮን በላይ በሆነ ገንዘብ የተገዛዉን ቤት 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች በብር 445,000.00 እንደሸጡ በመግለጽ መከራከራቸዉ ሲታይ በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል በድብቅ ግንኙነት መኖሩን ያሳያል።
ስለሆነም ክርክር ያስነሳዉን ንብረት 1ኛ ተጠሪ በሞት ከተለዩት ባለቤታቸዉ አቶ አዘነ በየነ ጋር ያፈሩት ንብረት ነዉ በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በመሻር አመልካች ቤቱን ለመግዛት ለ2ኛ ተጠሪ የከፈለትን ገንዘብ ከ2ኛ ተጠሪ ላይ ከማስመለስ ዉሳኔዉ እንደማያግድ ገልጾ ወስኗል። አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ ባለመቀበል ሰርዟል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም 2ኛ ተጠሪ በስሙ ካርታ መያዙን፣ የሉዝ ውል መዋዋለን አይቼ በውል አዋዋይ ፉት በተደረገ ውል ገዝቼና ስመ-ሀብት አዛውሬ የያዝኩት ንብረት ነው። የ2ኛ ተጠሪ አባት በሕይወት እያለ 2ኛ ተጠሪ የሉዝ ውል ተዋዋል ያዛወረውን ድብቅ ግንኙነት መባለ ተገቢ አይደለም። ንብረቱን በምገዛበት ጊዜ በፍርድ ቤት እግድ አልተሰጠበትም። የቤቱ ዋጋ ብር 445,000.00 የተባለው የመሐንዱስ ዋጋ ግምት ነው፤ ቤቱን የሸጠልኝ በብር 1,200,000.00 ነው። ተጠሪዎች ያላቸውን ግንኙነት አላውቅም፤ በንብረቱ ላይ ያለኝ መብት ሉከበር ይገባል የሚል ነዉ። የሰበር አጣሪ ችልት አቤቱታውን መርምሮ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት 2ኛ ተጠሪ በስሙ የሚገኘውን ለአመልካች በሽያጭ አስተላልፈው ባለበት ሁኔታ ቤቱን እንዱለቁ የመወሰኑ አግባብነትን ተጠሪዎች ባለበት እንዱጣራ ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ንብረቱ ላይ ክስ ካቀረብኩ በኋላ እገድ እንዱሰጥበት ጥያቄ አቅርቤ በእግድ ማመልከቻው ላይ 2ኛ ተጠሪ አስተያየት እንዱሰጡበት ትዕዛዝ ተሰጥቶ፤ 2ኛ ተጠሪ ትዔዛዙን አልቀበልም ካለ በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ ባላቸው ግንኙነት፣ 2ኛ ተጠሪን ለመርዲት በዝቀተኛ ዋጋ የተሸጠው ንብረቱን ለማሸሽ ነው። በማጭበርበርና ከቅን ልቦና ውጭ የተደረገ ሽያጭ ስለሆነ የአመልካች ክርክር ተቀባይነት የለውም ብለዋል። 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ንብረቱ የራሴ ነው፤ ውል ለመዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፉት የባንክ ዔዲ እና የፍርድ ቤት እግድ እንደላለው ተረጋግጦ ለአመልካች በሽያጭ ውል የተላለፈና በስሙ አዛውሮ ባለሀብት የሆነበት ንብረት ነው ብለዋል። አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የግራ ቀኝ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር፣ የሰበር አጣሪ ችልት የያዘዉን ማስቀረቢያ ነጥብ መሰረት በማድረግ ዉሳኔው ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል።
እንደመረመርነው 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በሱለልታ ከተማ ቁምቡሬ በተባለ ቦታ በካርታ ቁጥር ሱል/243/2005 በ2ኛ ተጠሪ ስም ያለው ንብረት የ1ኛ ተጠሪና የሟች ባለቤቴ ስለሆነ ቤቱን ከነሰነደ 2ኛ ተጠሪ ሉያስረክበኝ ይገባል በሚል ባቀረቡት ክርክር መነሻነት የተጠሪዎች ክርክር እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ደርሶ በመዝገብ ሐምል 26 ቀን 2013 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ንብረቱ በ2ኛ ተጠሪ ስም የተገዛ ቢሆንም የተገዛበት ገንዘብና ባለቤትነቱ የ1ኛ ተጠሪና የባለቤታቸው ስለመሆኑ በመረጋገጡ ለ2ኛ ተጠሪ በሕግ የተሰጣቸው የባለሀብትነት ግምት ስለመስተባበለ በሥር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በማስረጃ ተረጋግጦ ንብረቱ የ1ኛ ተጠሪና የባለቤታቸው ተብል የተሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል። በዚህ የሰበር ችልት ውሳኔ ላይ አመልካች በክርክር ያልተሳተፈ በመሆኑ ንብረቱን ከ2ኛ ተጠሪ መግዛታቸው ውጤቱ በጭብጥነት ተይዞ አልተመረመረም። በዚህም ምክንያት አመልካች አሁን በተያዘው መዝገብ ላይ የሰበር አቤቱታቸውን ያቀረቡ በመሆኑ በተጠሪዎች ክርክር ንብረቱን ገዝቻለሁ በሚል ያቀረቡት የጣልቃ ገብነት ማመልከቻና ሕጋዊ ውጤቱን በቀጣይነት እንመለከታለን።
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41 መሰረት ጣልቃ የሚገባ ተከራካሪ ክርክሩ መብቱን የሚነካው እና በጉዲዩ ላይ የተረጋገጠ መብት ያለው መሆኑን ማሳየት አለበት። አመልካችም ጣልቃ የገቡት ክርክር ያስነሳውን ንብረት 2ኛ ተጠሪ በስማቸው ካርታ አውጥተው የያዙትን መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ ውል ገዝቼዋለሁ። ውለም ሥልጣን ባለው አካል የተመዘገበና ስመ-ሀብቱ ተላልፍ የባለቤትነት ማረጋገጫ ያወጣሁበት ነው። ስለዚህ የ1ኛ ተጠሪ ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ነው። 1ኛ ተጠሪ የሚከራከሩት አመልካች ቤቱን የገዛው ክስ ካቀረብኩና እግድ እንዱሰጥ ከጠየቅሁ በኋላ ነው። 2ኛ ተጠሪም ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ነው የሸጠው፤ አመልካች መብት የላለው መሆኑን እያወቀ የገዛው ስለሆነ ክርክሩ ተቀባይነት የለውም በሚል ነው። ከክርክሩ የተረዲነው 2ኛ ተጠሪ ቤቱን በስማቸው ከገዙ በኋላ ለአመልካች ውል ለመዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ሽያጭ ውል በማድረግ ባለሀብትነት መብትን አስተላልፈዋል።
አመልካች መብቱ የተላለፈላቸው ጥበቃ ላደረግለት በሚገባ ግብይት መሆን አለመሆኑን መመልከት ተገቢ ነው። አመልካች ግዥ ሲፈጽሙ አንድ ጠንቃቃ ገዥ በሕግ ሆነ በአሰራር ሉያደርገው የሚገባውን ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፉነት አለባቸው። የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ሕግ የተለየ ጥበቃ ስለሚያደርግ የሀብትነት ሰነድ ስለሚወጣበት፤ ሰነደ ስለሚገኝበት የሥራ ክፍል፣ ውለ ስለሚፈጸምበት እና ንብረቱ ስለሚተላለፍበት ሥርዓት የተገለጸውን መከተል ግዳታ ይጥላል። ሽያጭ ውል ሉፈጸምበት በሚችል የከተማ ክልል ውስጥ ያለ፣ ቦታው ላይ ቤት ያረፈበትና ስለቤቱ የሚመለከቱ ሰነድች በቤቱ ባለሀብት ሥም በማይንቀሳቀስ ሀብት ምዘገባ ክፍል መገኘቱና ውለን የፍ/ሕ/ቁ. 1723(1) በሚያዘው አግባብ ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፉት ማድረግ ይጠበቃል።
አመልካች ውለን የፈጸሙት 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ገዝተው ሕጋዊ ሰነድ በቤቱ ላይ ካወጡበት በኋላ ሕጋዊ ባለቤት እንዲለው በማረጋገጥ በውል አዋዋይ ፉት መሆኑ ሲታይ ግብይቱ ሕግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የሕግ ጥበቃ ላደረግለት የሚገባ ነው። አመልካች ውለን የማይንቀሳቀስ ሀብት መዝገብ እንዱጻፍ በማድረግ ካርታ ያወጡበት በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ. 2878 እንደተመለከተው ውለ ሦስተኛ ወገኖችን ላይም ውጤት ያለው ነው። ሕግን መሰረት ላደረገ ግብይት ፍርድ ቤት ሕጋዊ ጥበቃ በመስጠት ገበያው በሕግ እንዱመራ ሆነ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ጤናማ በሆነ ሁኔታ እንዱመራ የማድረግ ኃላፉነት አለበት። ንብረቱ በ2ኛ ተጠሪ ስም ከመመዝገቡ እና ወደ አመልካች በሽያጭ ውል በሰነድ ከመዛወሩ በፉት መብቱ የማን ነው የሚለውን አመልካች የማጣራት ኃላፉነት በሕግ የለባቸውም። ንብረቱ ላይ በፍርድ ቤት እግድ ከመሰጠቱ በፉት የተዛወረ ከመሆኑ አኳያ አመልካች ክስ ካቀረቡ በኋላ ሽያጭ ውለ መደረጉ ሆነ የተሸጠበት ዋጋ የተደረገውን ግብይት ቀሪና ውጤት አልባ አያደርገውም። ምንም እንኳን 1ኛ ተጠሪ በንብረቱ ላይ መብት ያላቸው ስለመሆኑ በፍርድ የተረጋገጠላቸው ቢሆንም ይህ መብታቸው ከመረጋገጡ በፉት 2ኛ ተጠሪ በስማቸው የነበረውን ንብረት ለሦስተኛ ወገን ለሆኑት ለአመልካች ያስተላለፈ በመሆኑ፤ ከሦስተኛ ወገን መብት አኳያ ንብረቱን 1ኛ ተጠሪ ሉረከቡ አይችለም ብለናል። ሥለሆነም ክርክር ያስነሳው ንብረት ሕጋዊ ባለመብት አመልካች በመሆናቸው 1ኛ ተጠሪ ንብረት ለመረከብ ያቀረቡት ክስ ውድቅ ላደረግ ሲገባ ይሕ ታልፍ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ ነሀሴ 07 ቀን 2012 ዓ/ም እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሚያዚያ 20 ቀን 2012 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
በፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ
No topics extracted.