No summary available.
ቀን፡- ጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሃኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች፡-
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው። የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዲነው አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ከሳሾች ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበር።
አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ወላጅ እናታችን ወ/ሮ ማሬ በዲኔ በ21/08/1990 ዓ/ም የሞቱ ሲሆን አመልካቾች የሟች ልጆችና ወራሾች ነን፤ በይርጋ ጨፋ ወረዲ በአዲሜ ቀበላ አስተዲደር ክልል ሥር ከአባታችን ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በጋራ ያፈሩት ቤት አላቸው። ንብረቱን ወራሾች በማናውቀው ሁኔታ በ15/05/2010 ዓ/ም በተጻፈ ውል 1ኛ ተጠሪ ለ2ኛ ተጠሪ በሽያጭ መኖሪያ ቤቱን ከነይዞታው አስተላልፎል። በፍ/ሕ/ቁ. 1715(2) መሰረት ውለ ፈርሶ ንብረቱን ለወራሾች እንዱመልሱ እንዱወሰንልን ሲለ ዲኝነት ጠይቀዋል።
1ኛ ተጠሪ የሰጡት መልስ ይዘት ውለ የተደረገው በ21/09/2009 ዓ/ም ነው። የተሸጠውም 20 በ17 ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት ነው። የሽያጭ ውለ ከባለቤቴ ወ/ሮ ምትኬ ደሮ እና ከላልች ሦስት ወራሾች ጋር በብር 50,000.00 የተደረገ ነው። 2ኛ ተጠሪም ንብረቱን ከገዛ በኋላ ማሻሻያ ሥራ ሰርቶበታል። የእናታቸው ድርሻ ከተሸጠ ውርሱ ተጣርቶና ድርሻ ተለይቶ ላቀርብ ሲገባ በዚህ አግባብ ያልቀረበ ክስ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው። 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ንብረቱን ገዝቻለሁ። የኔ ባይ ከመጣ ለመከራከርና ለማስቀረት ተዋዋዮች ግዳታ ገብተዋል። ንብረቱን የማደስና የማሻሻያ ሥራ ሰርቻለሁ። አመልካቾች ድርሻቸውን ከሻጮች ይጠየቁ እንጂ ውለ ሉፈርስ አይገባም ብለዋል። የይርጋ ጨፋ ወረዲ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ላይ በቅጽ 10 እንደታተመ በሰጠው ትርጉም መሰረት ጠንቃቃ ገዥ ያደረገው የሽያጭ ውል ሉፈርስ አይገባም። ወራሾች ድርሻቸውን ከሽያጭ ገንዘቡ ከሻጮች ሉቀበለ ይገባል በማለት ወስኗል። በየደረጃው የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን አጽንተዋል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘትም በተጠቀሱት የሰበር ችልት ውሳኔዎች ወራሾች ብቸኛ ወራሽ ነን በማለት ንብረቱን በስማቸው አዛውረው ያደረጉትን ሽያጭ የሚመለከት ነው፤ በተያዘው ጉዲይ የንብረቱ ሻጭ ወራሾች ሳይሆኑ 1ኛ ተጠሪ ናቸው።
የንብረቱ ሥመ-ሀብትም አልተዛወረም፤ በጋራ ስናስተዲድረው የነበረን ንብረት ነው 1ኛ ተጠሪ የሸጡት።
በውል አዋዋይ ፉት የተደረገ ውል አይደለም፤ ውለም ሕገ-ወጥ በመሆኑ ሉፈርስ ይገባል የሚል ነው።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን መርምሮ የሰበር ውሳኔዎች ተጠቅሰው ውለ ሉፈርስ አይገባም መባለ ሕጋዊነቱን ለመመርመር ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ አዟል። 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ይዘትም በሥር ፍርድ ቤቱ የተጠቀሰው የሰበር ውሳኔ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው ነው። አመልካቾች ንብረቱ ሲሸጥ ያውቃለ። ውሳኔው ተገቢ ነው የሚል ነው። 2ኛ ተጠሪ ደግሞ አመልካቾች ውለ ሲፈጸም እያወቁና ንብረቱ ማሻሻያ ሥራ ሲሰራበት እያዩ ቆይተው ያቀረቡት ክስ ተገቢነት የለውም። የተሸጠው ቤት እንጂ ቦታ አይደለም፤ ውለ ሕጋዊ ስለሆነ ሉፈርስ አይገባም። የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሉጸና ይገባል ብለዋል። አመልካቾች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር፣ በሰበር አጣሪ ችልት የተያዘው ጭብጥ፣ በሥር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ወላጅ እናታችን ሟች ወ/ሮ ማሬ በዲኔ ልጆችና ወራሾች ነን፤ በይርጋ ጨፋ ወረዲ በአዲሜ ቀበላ አስተዲደር ክልል ሥር ከአባታችን ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በጋራ ያፈሩት ቤት አላቸው። ንብረቱን ወራሾች በማናውቀው ሁኔታ በ15/05/2010 ዓ/ም በተጻፈ ውል 1ኛ ተጠሪ ለ2ኛ ተጠሪ በሽያጭ መኖሪያ ቤቱን ከነይዞታው አስተላልፎል፤ ውለ ፈርሶ ንብረቱን ለወራሾች እንዱመልሱ እንዱወሰንልን የሚል ነው። 1ኛ ተጠሪ 20 በ17 ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት ለ2ኛ ተጠሪ መሸጣቸውን ገልጸው ውርሱ ተጣርቶና ድርሻ ተለይቶ ያልቀረበ ክስ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ንብረቱን ገዝቻለሁ። ንብረቱን የማደስና የማሻሻያ ሥራ ሰርቻለሁ።
No topics extracted.
አመልካቾች ድርሻቸውን ከሻጮች ይጠየቁ እንጂ ውለ ሉፈርስ አይገባም ሲለ ተከራክረዋል።
ውል ሉመሰረት የሚገባው ችልታ ባላቸው፣ በተዋዋዮች ነጻ ፈቃድ፣ የሚቻልና ሕጋዊ በሆነ ዓላማና ጉዲይ ላይ በሕግ የተመለከተውን የውል አጻጻፍ ፍርም ተከትል ላሆን እንደሚገባ በፍ/ሕ/ቁ. 1678 ላይ ተመልክቷል። ውለ የአመሰራረት ጉድለት ካለበት ተዋዋዮች/መብት ያገኙ ሰዎች ሥምምነቱ ፈራሽ እንዱሆን በፍ/ሕ/ቁ. 1808 አግባብ ክስ ሉያቀርቡ ይችላለ። አመልካቾችም በዚህ አግባብ ውል ሰጭ የሆኑት አባታቸው በሙለ ንብረቱ ላይ ውለን ለመፈጸም መብት የላቸውም፣ በንብረቱ የሟች እናታችን ግማሽ ድርሻ ላይ ወራሾች ሳንፈቅድና ሳንስማማ የተደረገው ውል ፈራሽ እንዱሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪዎች የንብረቱ ግማሽ ባለድርሻ ወራሾች የሆኑት አመልካቾች አይደለም የሚል ግልጽ ክርክር የላቸውም። የሥር ፍርድ ቤትም አመልካቾች በንብረቱ ላይ ድርሻ ያላቸው መሆኑን በማረጋገጥ ከሽያጭ ገንዘቡ 1ኛ ተጠሪ ድርሻቸውን እንዱከፍሎቸው ወስኗል። አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም ከሽያጭ ገንዘቡ ሳይሆን ውለ ፈርሶ ንብረቱን መረከብ አለብን በሚል ነው።
2ኛ ተጠሪ በዚህ ችልት ደረጃ የሚከራከሩት አመልካቾች ውለ ሲፈጸም እያወቁና ንብረቱ ማሻሻያ ሥራ ሲሰራበት እያዩ ቆይተው አሁን ያቀረቡት ክስ ተገቢነት የለውም በማለት ነው። ከዚህ ክርክር በመነሳት 2ኛ ተጠሪ መብቱ የተላለፈላቸው ጥበቃ ላደረግለት በሚገባ ግብይት መሆን አለመሆኑን መመልከት ተገቢ ነው። 2ኛ ተጠሪ ግዥ ሲፈጽሙ አንድ ጠንቃቃ ገዥ በሕግ ሆነ በአሰራር ሉያደርገው የሚገባውን ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፉነት አለባቸው። የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ሕግ የተለየ ጥበቃ ስለሚያደርግ የሀብትነት ሰነድ ስለሚወጣበት፤ ሰነደ ስለሚገኝበት የሥራ ክፍል፣ ውለ ስለሚፈጸምበት እና ንብረቱ ስለሚተላለፍበት ሥርዓት የተገለጸውን መከተል ግዳታ ይጥላል። ሽያጭ ውል የሚፈጸምበት ንብረት ላይ በሕግ መብት ያላቸው ሰዎች እነማን እንደሆኑ፣ ቦታው ላይ ቤት ያረፈበትና ስለቤቱ የሚመለከቱ ሰነድች በቤቱ ባለሀብት ሥም በማይንቀሳቀስ ሀብት ምዝገባ ክፍል መገኘቱና ውለ የፍ/ሕ/ቁ. 2878 በሚያዘው አግባብ ንብረቱ በሚገኝበት ሥፍራ ባለው የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዝገባ ክፍል እንዱመዘገብ ይጠበቃል። 2ኛ ተጠሪ ውለን የፈጸሙት ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ሲሆን የንብረቱ ግማሽ ባለድርሻ ወራሾች የሆኑት አመልካቾች በሽያጭ ውለ አለመሳተፊቸው ከትክክለኛው ባለመብት ያልገዙ መሆኑን ያሳያል። አመልካቾች የሽያጭ ሂደቱን በጊዜው ያውቁ ነበር የሚለው የ2ኛ ተጠሪ ክርክርም ላልች ወራሾች እንዲለ እያወቁ ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርጉ የገዙት መሆኑን ያስገነዝባል። ውለም በማይንቀሳቀስ ሀብት ምዝገባ ክፍል የተመዘገበ አይደለም። ስለሆነም የተደረገው የሽያጭ ውል ተገቢውን ሕግና አሰራር ተከትል የተፈጸመ ባለመሆኑ ውለ ፈራሽ ላሆን ይገባል ብለናል።
በሥር ፍርድ ቤት የተጠቀሱት የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ የሰጣቸው ውሳኔዎችና አስገዲጅ ትርጉሞች የሽያጭ ውለ ጥበቃ እንዱደረግለት የሚያዘው ንብረቱ በሻጭ ስም ተዛውሮ የነበረና ገዥው ተገቢው ጥንቃቄ አድርጎ በሕግ በተመለከተው ሥርዓት ለተፈጸመ ግብይት ነው። በተያዘው ጉዲይ 2ኛ ተጠሪ ተገቢው ጥንቃቄ አድርገው የፈጸሙት የሽያጭ ውል ባልሆነበት ሁኔታ ውለ ሉፈርስ አይገባም ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ/ም፣ የጌዳኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሳስ 03 ቀን 2012 ዓ/ም እና የይርጋ ጨፋ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ መስከረም 06 ቀን 2012 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በይርጋ ጨፋ ወረዲ በአዲሜ ቀበላ አስተዲደር ክልል ሥር የሚገኘው ቤት በተጠሪዎች መካከል የተደረገው የሽያጭ ውል ፈራሽ ነው በማለት ወስነናል። 2ኛ ተጠሪ ንብረቱን ለአመልካቾችና ለ1ኛ ተጠሪ እንዱያስረክቡ ተወስኗል።
2ኛ ተጠሪ የሽያጭ ገንዘቡንና ለማሻሻያ ሥራ ያወጡት ወጪን በተመለከተ 1ኛ ተጠሪን ከመጠየቅ ይሕ ውሳኔ አያግድም።
በዚህ ችልት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ።