No summary available.
ጥቅምት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካች- ኤቦካ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ጠበቃ ገ/ክርስቶስ ለማ - ቀርበዋል ተጠሪ- በአ/አበባ ከተማ አስተዲደር የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፔራይዝ ነ/ፈጅ ታሪኳ ጌታቸው - ቀርበዋል **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የግንባታ ውልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ በሰንጋ ተራና ክራውን ሳይቶች ለሚያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የቆሻሻ ማስወገጃ /Garbage Chute/ ከነገጠማ ስራው ለመገንባት ከተጠሪ ጋር በቀን ሚያዝያ 10 ቀን 2008 ዓ.ም ባደረግነዉ ውል አመልካች በተጠቀሱት ሳይቶቸ ላይ ለሚገኙ 19 ህንፃዎች የቆሻሻ ማስወገጃ ሉገጥም፤ ተጠሪም ለዚሁ ስራ ለአመልካች ብር 13,690,000.60 ሉከፍል ተስማምተናል። በዚሁም መሰረት አመልካች በክራውን ሳይት በሚገኙ 12 ህንፃዎች ላይ የገጠማ ስራውን ያጠናቀቅኩ ሲሆን ተጠሪ ለዚሁ ስራ ብር 8,520,000.00 እንዱከፍለኝና የተሰራውን ስራ እንዱረከብ በተደጋጋሚ ብጠይቅም ፍቃደኛ አልሆነም። ስለሆነም ስራውን እንዱረከብና ገንዘቡን ከሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀዉን ዲኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ።
ተጠሪ በበኩለ ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ በውለ አንቀጽ 4(2) ስር በተመለከተው የውለ አካልና አባሪ በሆነው የጨረታ ሰነድ (Specification) መሰረት አመልካች የቆሻሻ ማስወገጃውን ገጥሞ ለማስረከብ ግዳታ ገብቷል። ስራውንም ሲሰራ መጠቀም ያለበት ግብዓት ብሪትሽ ስታንዲርድ ቢኤስ 1703 እና ቢኤስ 5906 ደረጃውን የጠበቀ 304 የማይዝግ /Stainless Steel/ ሆኖ ውፍረቱ 1.5 ሚሉ ሜትር መሆን እንዲለበት ቢቀመጥም አመልካች ግን ስራውን የሰራው ከውለ ውጪ ውፍረቱ 1 ሚሉ ሜትር እና ጋልቫናይዝድ በሆነ ወጥ ላሜራ ነው። በወቅቱም አመልካች በላከው የስራ እቅድ ላይ በሰጠነው አስተያየት ስራውን ለመስራት የሚጠቀመውን ግብዓት በተመለከተ ከውላችን ውጪ በመሆኑ እንደማንቀበለው በመግለፅ እቅደን ውድቅ ማድረጋችንን አመልካች ለመጠቀም ካቀደው ግብዓት የምዘና ውጤት ጋር በደብዲቤም ጭምር ገልፀንለታል፤ ስለሆነም አመልካች በውላችን መሰረት ላልሰራው ስራ የአገልግልት ክፍያ እንዱከፈለው ለመጠየቅ የሚያስችል የህግም ሆነ የውል መሰረት የለውም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ፣ እንዱሁም ስለጉዲዩ ተጨማሪ ማጣራት እንዲደረገ ከገለፀ በኋላ በወቅቱ ከድዛይን ዝግጅት ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ክፍተት ምክንያት በውለ ላይ የተመለከተውና ለቆሻሻ ማስወገጃ ገጠማ የሚውለው ግብዓት በቀላለ በገበያ ላይ የሚገኝ ስለመሆኑ ሳይጣራ ውል የተገባ መሆኑን እና በቀን መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ አመልካች ላቀረበው የግብዓት ለውጥ እቅድ (Specification) ተጠሪ መልስ አለመስጠቱ በዔቅደ እንደተስማማ የሚያስቆጥረዉ መሆኑን፤ ስለሆነም ምንም አንኳን አመልካች በህንፃዎቹ ላይ የቆሻሻ ማስወገጃ ለመግጠም የተጠቀመው ግብዓት በውለ ላይ የተመለከተውን የማይዝግ፣ ውፍረቱም 1.5 ሚሉ ሜትር ባይሆንም ለተጠሪ በላከዉ የግብአት ለዉጥ መሰረት ስራውን በልላ ግብዓት ያከናወነ በመሆኑ ተጠሪ ለተሰራዉ ስራ ዋጋዉን የመክፈል ኃላፉነት አለበት። የኃላፉነት መጠኑንም አስመልክቶ አመልካች የቆሻሻ ማስወገጃውን ለመግጠም በተጠቀመው ጋልቫናይዝድ ላሜራ ብረት ዋጋ ስላት ብር 6,739,786.00 መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑን ጠቅሶ ይህንኑ ገንዘብ ከቀን ከሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ተጠሪ ለአመልካች ይክፈል በማለት ወስኗል። ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩበት በኋላ አመልካች ስራውን በጋልቫናይዝድ ብረት እንደሚሰራ ያሳወቀበት እቅድ የውል ድርድር ሀሳብ ማስታወቂያ አይደለም፤ የውል ድርድር ሀሳብ ማስታወቂያ ነው እንኳን ቢባል ተጠሪ አመልካች በውለ ላይ የተጠቀሰውን ግብዓት ለውጦ የተጠቀመው ግብዓት በውለ ላይ ከተገለፀው ግብዓት ጋር ተመሳሳይና ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ በተስማሚነት ምዘና ድርጅት አስፈትሾ ውጤቱን እንዲወቀ ህዲር 05፣ ህዲር 16 እና ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም በፃፊቸው ደብዲቤዎች ስራው በውለ መሰረት ተስተካክል መሰራት እንዲለበት፤ ይህ ካልሆነ ግን ክፍያውን መፈፀም እንደማይችል ገልፆና በማስረጃም ጭምር አስደግፍ ተከራክሮ እያለ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ የአመልካችን እቅድ ባለመቃወሙ በዝምታ እንደተቀበለ ይቆጠራል ከሚል መደምደሚያ ላይ በመድረስ ስራው የተሰራው በተጠሪ ፍቃድና ይሁንታ ነው ሲል የሰጠው ውሳኔ የቀረበውን ክርክርና ማስረጃ መሰረት ያደረገ ነው ማለት አይቻልም፤ አመልካች ከውል ዉጪ ራሱ በፈቀደው የሰራውን ስራ ተጠሪ ተገድ እንዱረከብም ሆነ ክፍያውን ለመፈፀም ሉገደድ የሚችልበት የውልም ሆነ የህግ ግዳታ የለበትም በማለት የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሽሮታል። ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ተፈጽመዋል ያላቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችልት እንዱታረሙለት ጠይቋል። የአቤቱታው ይዘትም በአጭሩ ስራው የሚሰራበትን እቃ በገበያ ላይ አለማግኘታችንን ጠቅሰን በልላ ተመሳሳይ እቃ እንደምንሰራ ለተጠሪ ያሳወቅን ሲሆን ተጠሪ በተገቢው ጊዜ ውስጥ ምላሽ አለመስጠቱ በህግ አግባብ ጥያቄያችንን እንደተቀበለው ይቆጠራል፤ ቀድሞ የተደረገን ውልም መለወጥ እንደሚቻል በህግ በግልጽ ተደንግጓል፤ ተጠሪም በአመልካች እየተሰራ የነበረውን ስራ የራሱን ባለሞያዎች በመላክ የመስክ ላይ የስራ ጉብኝትና የጥራት ቁጥጥር ሲያደረግ ያቀረበው ተቃውሞ አልነበረም፤ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንኑ በመገንዘብ የተሰራው ስራና ዋጋ ገለልተኛ በሆነው የከተማና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በኩል ተጣርቶ እንዱቀርብለት ካደረገ በኋላ የሰጠው ውሳኔ ተሽሮ ተጠሪ በቤቱ ላይ የተሰራውን ስራ ጨምሮ ቤቶቹን ለሚመለከታቸው አካላት አስተላልፍ እያለ ለተጠሪ ክፍያ ሉከፈለው አይገባም፤ የሰራውን ስራ ከቤቶቹ ላይ አላቆ መውሰድ ይችላል ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
ጉዲዩም በሰበር አጣሪ ችልት ተመርመሮ አመልካች ስራውን የሰራው በውለ ላይ በተቀመጠው ስታንዲርድ መሰረት ባይሆንም የተሰራው ስራ በገለልተኛ ተቋም ባለሞያ ተረጋግጦ የቀረበውን የገንዘብ መጠን ተጠሪ ሉከፍል የሚገባ መሆን አለመሆኑን ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል ተብሎል። በዚሁም መሰረት ተጠሪ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ አመልካች ስራውን በተመሳሳይ እቃ ነው የሰራሁት ቢልም በውለ ላይ የተገለፀውና አመልካች ስራውን የሰራበት እቃ ተመሳሳይ አይደለም፤ በተመሳሳይ እቃ ስራውን መስራቱን የሚገልጽ መከራከሪያም በስር ፍርድ ቤት አላቀረበም፤ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለአመልካች ገንዘብ እንዱከፈለው የወሰነው አመልካች ስራውን በጋልቫናይዝድ ሜታል ለመስራት ጥያቄ ሲያቀርብ ተጠሪ በዝምታ እሺታውን ገልጿል በሚል ምክንያት ነው፤ ሆኖም ግን ፍርድ ቤቱ ተጠሪ አመልካች ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገበት፣ በክርክር ሂደትም ያነሳው እና በማስረጃት ያቀረበውን ጳጉሜን 02 ቀን 2008 ዓ.ም፣ ጥቅምት 21፣ ህዲር 05 እና ህዲር 16 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ እና ላልች በርካታ ደብዲቤዎችን ሳይመለከትና ሳይመረምር ነው፤
አመልካች ስራውን በልላ እቃ እንደሚሰራ በቀን 23/12/2008 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ አሳውቂያለሁ ቢልም ደብዲቤው በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1684 መሰረት የቀረበ አለመሆኑን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አረጋግጧል፤ አመልካቸ ለተጠሪ የላከው ደብዲቤ የስራ እቅድ እንጂ የውል ማሻሻያ አይደለም፤
አመልካች ስራውን የሰራበት ጋልቫናይዝድ ላሜራም ጥራቱ በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የተረጋገጠ አይደለም፤ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተጠሪ ስራው እንዱሰራለት ከተስማማበት የእቃ አይነት ውጪ ለተሰራ ስራ በገለልተኛ አካል አስገምቶ እንዱከፍል መወሰኑ ስህተት ነበር በማለት የአመልካች አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግለት ጠይቆ ተከራክሯል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቶ ተከራክሯል።
ከስር ጀምሮ የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታዉን ለማስቀረብ የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል። እንደመረመረዉም አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክስ ለጠየቀዉ ዲኝነት መሰረት ያደረገዉ ተጠሪ በሚያስገነባቸዉ ህንፃዎች የቆሻሻ ማስወገጃ ለመግጠም አመልካች በዉል በገባዉ ግዳታ መሰረት በክራውን ሳይት በሚገኙ 12 ህንፃዎች ላይ የገጠማ ስራውን ያጠናቀቀ ቢሆንም ተጠሪ ለዚሁ ስራ ዋጋ ብር 8,520,000.00 ለመክፈል ፍቃደኛ አለመሆኑን ሲሆን፣ ተጠሪ በበኩለ በግራ ቀኝ መካከል ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ዉል መኖሩን ሳይክድ ኃላፉነት የለብኝም በማለት የሚከራከረዉ በዉለ መሰረት አመልካች የቆሻሻ ማስወገጃ ስራዉን ለመስራት ጥቅም ላይ ሉያዉል የሚገባዉ በብሪትሽ ስታንዲርድ ቢ3 1703 እና ቢኤስኤስ 906 ደረጃዉ 304 ሆኖ ዝገት የማይነካዉ እና ዉፍረቱም 1.5 ሚ/ሜ የሆነ ብረት መሆን ሲገባዉ ከዉል ስምምነቱ ዉጪ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ እና የጥራት ልዩነት ባለዉ ጋልቫናይዝድ ሜታል ሺት ባለ 1 ሚ/ሜ ብረት የተጠቀመ መሆኑን በመጥቀስ ስለመሆኑ ለመገንዘብ ተችሎል። አመልካች የቆሻሻ ማስወገጃ ስራዉን ለመስራት ጥቅም ላይ ያዋለዉ ብረት በዉለ ላይ የተመለከተዉ ዓይነት አለመሆኑ በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ አመልካችም ይህን ፍሬ ነገር አይክድም። አመልካች ይህን ሳይክድ ስራዉ የተሰራበትን ገንዘብ ተጠሪ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት አጥብቆ የሚከራከረዉ ተጠሪ ስራዉ በተለዋጭ ማቴሪያል እንደሚሰራ ጭምር የተሰጠዉን የስራ ዔቅድ አለመቃወሙ የማቴሪያል ለዉጡን ተስማምቶ መቀበለን ስለሚያሳይ እና ስራዉም በተለወጠዉ ማቴሪያል ተሰርቶ የተጠናቀቀ መሆኑን በመጥቀስ ነዉ።
ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ፣ ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተዉ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ለተሰራዉ ስራ ዋጋዉን የመክፈል ኃላፉነት አለበት በሚል ድምዲሜ ላይ ሲደርስ የጠቀሰዉ መሰረታዊ ምክንያት በዉለ ላይ የተመለከተዉ ዓይነት ብረት በገበያ ላይ የላለ መሆኑን ተከትል አመልካች ነሐሴ 23 ቀን 2008 ዓ.ም እና መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ.ም ለተጠሪ በላከዉ የስራ ዔቅድ በህንፃዉ ላይ ለሚገጠመዉ የቆሻሻ ማስወገጃ ዔቃ በዉለ ላይ የተመለከተዉ ሳይሆን ጋልቫናይዝድ ስቲል ሽት መሆኑ እና ብረቱም በኢትዮጵያ ተስማሚነት እና ምዘና ድርጅት ተረጋግጦ ናሙናዉም ተልኮለት ተጠሪ እንዱጎበኘዉ መጠየቁን እና ተጠሪ ይህን ዔቅድ አስመልክቶ ምንም ዓይነት ተቃወሞ አለማቅረቡ ዔቅደን እና ስራዉ በተለወጠዉ ዔቃ የሚሰራ መሆኑን እንደተቀበለ ያሳያል የሚል ስለመሆኑ የዉሳኔዉ ይዘት ያስገነዝባል። ይሁንና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በበኩለ ተጠሪ አመልካች በዔቅደ ላይ የጠቀሰዉ እና ለስራዉ የተጠቀመበትን ዔቃ በተስማሚነት ምዘና ድርጅት አስፈትሾ ዉጤቱን ካወቀ በኋላ ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም፣ ህዲር 05 ቀን 2009 ዓ.ም፣ ህዲር 16 ቀን 2009 ዓ.ም እንዱሁም ከዚህ ጊዜ በኋላ ለአመልካች በተጻፈት ደብዲቤዎች ስራዉ በዉለ መሰረት ተስተካክል መሰራት እንዲለበት እና ይህ ካልሆነ አመልካች ክፍያዉን የማይፈጽም መሆኑን ለአመልካች መግለጹ ተረጋግጧል በሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል። አመልካች በዚህ ችልት ባቀረበዉ ክርክር ስራዉን በዉለ ላይ የተመለከተዉን ማቴሪያል ከገበያ ላይ ማግኘት ባለመቻለ በጋልቫናይዝድ ስቲል ሺት ማቴሪያል እንደሚሰራ ዝርዝር ዔቅድ አዘጋጅቶ ለተጠሪ ያሳወቀ መሆኑን እና ተጠሪ ለዚህ ምላሽ አለመስጠቱ የተሻሻለዉን ዉል በዝምታ መቀበለን የሚያሳይ ነዉ በማለት አጥብቆ የሚከራከር ቢሆንም አመልካች ለስራዉ የተጠቀመዉ እና በዔቅደ ያካተተዉን ማቴሪያል በተስማሚነት እና ምዘና ኤጀንሲ ካስመረመረ በኋላ አመልካች ይህን አስተካክል ስራዉን በዉለ በተመለከተዉ መሰረት እንዱያከናዉን ካልሆነ ግን ክፍያ እንደማይፈጽምለት በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ በተመለከቱት ቀናቶች የተፃፈን ደብዲቤ አስመልክቶ በግልጽ ክድ አይከራከርም።
እንግዱህ ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለዉ አመልካች ተጠሪ ለሚያስገነባቸዉ የቆሻሻ ማስወገጃ በማይዝግ ብረት ወይም ስቴንለስ ሜታል ሺት ለመስራት በዉለ ግዳታ የገባ ቢሆንም በተጨባጭ ስራዉን የሰራዉ በዓይነትም(በጥራትም) ሆነ በዋጋ በዉለ ላይ ከተመለከተዉ በሚያንሰዉ ጋልቫናይዝድ ብረት ስራዉን ማከናወኑ መረጋገጡን ነዉ። በመሰረቱ ዉል ተዋዋይ ወገኖች የእራሳቸዉን ጉዲይ በእራሳቸዉ ለመወሰን ያላቸዉን ነፃነት ተጠቅመው የሚደርጉት ስምምነት ሲሆን፣ ዉለ በህግ የተመለከቱትን አስፈላጊዉን መስፈርቶች ተሟልቶ እስከተደረገ ድረስ አንደኛዉ ወገን በዉለ የገባዉን ግዳታ በዉለ ላይ በተመለከተዉ ጊዜ እና ሁኔታ ለላላኛዉ ወገን የመወጣት ኃላፉነት አለበት። ዉል የህግ ደረጃ የተሰጠዉ ተግባር እንደሆነ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1731 ላይ የተመለከተዉም በዚሁ መሰረተ ሃሳብ መነሻነት እንደሆነ ይታመናል። ከተዋዋይ ወገኖች አንደኛዉ ወገን ግዳታዉን እንዱወጣ ላላኛዉን ወገን ማስገደድ የሚችለዉም በቅድሚያ በበኩለ የሚጠበቅበትን ግዳታ የተወጣ እንደሆነ ወይም ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ካረጋገጠ ብቻ ስለመሆኑም በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1757 እና 1771 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ገዲይ ስንመለከት አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን የቆሻሻ ማስወገጃ ገጠማ ስራ ለመስራት በዉለ የተስማማዉ ስቴንለስ ሜታል ሺት በሆነ ዔቃ ሆኖ እያለ ነገር ግን በዋጋም ሆነ በጥራት በዉለ ከተመለከተዉ በታች በሆነዉ ጋልቫናይዝድ ሜታል ሺት በሆነ ዔቃ መስራቱ በዉለ መሰረት የሚጠበቅበትን ግዳታ አለመወጣቱን የሚያሳይ ነዉ። አመልካች በዉለ ላይ ከተመለከተዉ ዉጪ በሆነ ላላ ዔቃ ስራዉን ያከናወነዉ ይህንኑ ጠቅሶ ተጠሪ እንዱያዉቅ በዔቀድ አካቶ ከላከለት በኋላ ተጠሪ መልስ ባለመስጠቱ እና ይህም የተሻሻለዉን ዉል ተጠሪ እንደተቀበለዉ የሚቆጠር መሆኑን በመጥቀስ የሚከራከር ቢሆንም፣ የስራ ዔቅድ ዉለን መሰረት በማድረግ አፈፃፀሙን አስመልክቶ ስራዉን በሚሰራዉ አካል የሚዘጋጅ የድርጊት መርሃ ግብር እንጂ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 1684(2) ላይ በተመለከተዉ አግባብ እንደ የዉል ማሻሻያ ሃሳብ የማይወሰድ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እንደ የዉል ማሻሻያ ሃሳብ (offer for amendment of contract) የሚቆጠር ነዉ ቢባል እንኳ ተጠሪ አመልካች ባቀረበዉ ዔቅድ ላይ የጠቀሰዉ ጋልቫናይዝድ ሜታል ሺት በተስማሚነት እና ምዘና ኤጀንሲ ካስመረመረ በኋላ አመልካች ስራዉን በዉለ መሰረት እንዱያከናዉን መጠየቁ እና ይህ ካልሆነ ክፍያዉን ለመፈጸም እንደማይገደድ ማሳወቁ አመልካች በዉለ ላይ ከተመለከተዉ ዉጪ ስራዉን በልላ ዔቃ እንዲይሰራ መቃወሙን የሚያሳይ ነዉ። ስለሆነም ተጠሪ አመልካች የላከዉን ዔቅድ በዝምታ ተቀብልታል ለማለት የሚቻል አይደለም። በመሆኑም አመልካች ወድ እና ፈቅድ ባደረገዉ ዉል ላይ በተመለከተዉ መሰረት የቆሻሻ ማስወገጃ ስራዉን በስቴንለስ ሜታል ሺት የመስራት ግዳታ እያለበት በእራሱ ጊዜ በመለወጥ በጋልቫናይዝደ ሜታል ሺት ዔቃ መስራቱ በዉለ መሰረት የሚጠበቅበትን ግዳታ መጣሱን ወይም አለመወጣቱን የሚያሳይ በመሆኑ ተጠሪ ለተሰራዉ ስራ ኃላፉ ላሆን የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም።
ከዚህ አንፃር ሲታይ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በአግባቡ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ስላልተገኘ ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይ/መ/ ላይ መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻለ።
No topics extracted.