No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው ተሾመ ሽፈራው ሀብታሙ እርቅይሁን ብርሀኑ መንግስቱ ነፃነት ተገኝ አመልካቾች፡- 1ኛ. የክርስቶስ አካል ቤተክርስቲያን - መጋቢ ተስፊልደት ሲሳይ - ቀርበዋል 2ኛ. መጋቢ ተስፊልደት ሲሳይ - ቀርበዋል ተጠሪ፡- ወ/ሮ አልማዝ ባዩ - ጠበቃ መኮንን ይማም - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በቤት ኪራይ ውል መነሻ ያልተከፈለ የኪራይ ገንዘብ ለማስከፈል እና ቤት ለመረከብ የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች ተከሳሾች ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ በህዲር 04 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዲ 03 የቤት ቁጥር 479 ሙለ ጊቢውን በቆርቆሮ ብቻ ከተሰራ መለስተኛ አዲራሽ፤ አንድ ክፍል ቆርቆሮ ቤት እና በቆርቆሮ የተሰራ የጥበቃ ቤት አመልካቾች በወር ብር 12,000 በመክፈል ከጥቅምት 25 ቀን 2011 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለመጠቀም ተስማምተው የኪራይ ውል አድርገናል። ነገር ግን አመልካቾች ከሚያዝያ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የኪራይ ገንዘብ በከፉል ያልከፈለ ሲሆን ከሐምል እስከ ነሐሴ 2012 ዓ.ም ያለውን ደግሞ ሙለ የኪራይ ገንዘብ አልከፈለም። በመሆኑም አመልካቾች የሚቀርባቸውን ውዝፍ የኪራይ ገንዘብ በድምሩ 64,000 ከፍለው ቤቱን እንዱያስረክቡ እና እስኪያስረክቡ ላለው ጊዜ በወር 12,000 ብር የኪራይ ገንዘብ እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካቾች በየካቲት 03 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው ውድቅ የተደረገ ሲሆን ፍሬ ነገሩን በተመለከተ ከተጠሪ ጋር የኪራይ ውል ብንፈጽምም ቤቱ ከነሙለ ይዞታው በተጠሪ እጅ ነው የሚገኘው። አመልካቾች ቤት እና ይዞታውን አልተረከብንም።
የኪራይ ገንዘብ እና ቤት እንዱለቀቅለት የሚጠይቅ ወገን በመጀመሪያ የቤቱ እና የይዞታው ሕጋዊ ባለቤት መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል። 1ኛ አመልካች የራሴን ቤት ኪራይ ከፍዬ የምለቅበት ምክንያት የለም። በመሆኑም ክሱ ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ አመልካቾች ነሐሴ 25 ቀን 2011 ዓ.ም በተፈጸመ የቤት ኪራይ ውል መነሻነት እስከተወሰነ ጊዜ የኪራይ ክፍያ እየከፈለ የነበረ መሆኑን አልካደም። በኪራይ ውለ ላይም በግልጽ አመልካቾች ቤቱን መከራየታቸው ተመልክቶ እያለ እና የኪራይ ገንዘብ እየከፈለ በቆዩበት ቤቱን አልተረከብንም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም። በመሆኑም አመልካቾች ሳይከፍለ የቀሩትን የኪራይ ገንዘብ ብር 56,000 ሉከፍለ እና ቤቱን ለቀው ሉያስረክቡ ይገባል። እንዱሁም አመልካቾች ቤቱን እስኪያስረክቡ ያለውን የኪራይ ገንዘብ ተጠሪ የመጠየቅ መብታቸው የተጠበቀ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በውለ ላይ የተጠቀሰው ካርታ በተጠሪ ስም የተመዘገበ መሆኑን እና በይግባኝ ባዮች ቁጥጥር ስር የሚገኙት በቆርቆሮ የተሰሩ ቤቶች በተጠሪ ስም በተመዘገበው ካርታ ላይ በተጠቀሰው 135.5 ካሬ ሜትር ይዞታ ውስጥ እንደሚገኙ በክፍለ አስተዲደር ተጣርቶ የቀረበ በመሆኑ አመልካቾች የኪራይ ገንዘብ ከፍለው ቤቱን ሉለቁ ይገባል በመባለ የተፈጸመ የፍሬ ነገርም ሆነ የህግ ስህተት የለም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።
አመልካቾች በሚያዝያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር ቅሬታ ያቀረቡት የስር ፍርድ ቤቶችን በውሳኔ በመቃወም ለማሳረም ሲሆን የቅሬታው ይዘት ባጭሩ 2ኛ አመልካች የ1ኛ አመልካች አገልጋይ ነኝ። 1ኛ አመልካች ደግሞ የራሷ ሕጋዊ ሰውነት ያላት የእምነት ተቋም ናት። 2ኛ አመልካች 1ኛ አመልካችን ወክዬ ባደረኩት ሕጋዊ ተግባር በግላ በኃላፉነት ልጠየቅ አይገባም። የቤት ኪራይ ውል ያደረግን ቢሆንም ቤቱን እስከዛሬ ድረስ አልተረከብንም። 1ኛ አመልካች አሁን የሚጠቀምበት ይዞታ የተጠሪ አይደለም። አመልካቾች ከሚመለከተው አካል የይዞታ ማስረጃ ለማግኘት በሂደት ላይ ነን። በስር ፍርድ ቤቶች የይዞታ ክርክር አቅርበን ተገቢው ማጣራት ከተደረገ በኋላ የደረሰቡት ድምዲሜ ተገቢ ስላልሆነ ሉታረም ይገባል በማለት ጠይቀዋል።
የአመልካቾች የሰበር ቅሬታ በሰበር አጣሪ ችልት ተመርምሮ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የክርክር መነሻ የሆነውን እና አመልካቾች እንዱያስረክቡ የተወሰነውን ቤትና ቦታ መጠን በካሬ ተለይቶ የተወሰነ ስለመሆን አለመሆኑ በጭብጥነት በመያዝ በአስተዲደሩ ተጣርቶ እንዱቀርብ ትእዛዝ ተሰጥቶ የወረዲው አስተዲደርም የቦታውን ትክክለኛ ይዘት እና ስፊት ለማወቅ የሚያስችል መሳሪያ የላላቸው መሆኑን በመጥቀስ በክፍለ ከተማው መሬት ልማትና አስተዲደር ጽህፈት ቤት በኩል ተጣርቶ እንዱቀርብ የሚል መግለጫ ሰጥተዋል። ይህንን መግለጫ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ የተሰጠበትን እና 1ኛ አመልካችም ህጋዊ ሰውነት ያለው ሆኖ እያለ 2ኛ አመልካች ተከሳሽ ተደርጎ ውሳኔ የተሰጠበትን አግባብነት ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱያቀርቡ ትእዛዝ ተሰጥቷል።
ተጠሪ በሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ ቤቱ በተጠሪ ስም የተመዘገበ የግል ቤቴ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። ለክሱ መነሻ የሆነው የኪራይ ውል በመሆኑ ውሳኔው የኪራይ ግንኙነትን የሚመለከት ብቻ መሆኑ ተገቢ ነው። በስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ ተጣርቶ በተሰጠ ውሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለላለ ቅሬታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
አመልካቾችም በሐምል 1 ቀን 2014 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታቸውን አጠናክረዋል።
የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም 2ኛ አመልካች መከሰሳቸው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? እና አመልካቾች የኪራይ ገንዘብ ከፍለው ለክርክሩ መሰረት የሆነውን ቤት ሉያስረክቡ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለትን ነጥቦች በጭብጥነት በመያዝ የግራ ቀኙን ክርክር በስር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እንዱሁም ከተገቢው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል።
በመጀመሪያም 2ኛ አመልካች ከ1ኛ አመልካች ጋር በአንድነት መከሰሳቸው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?
የሚለውን ጭብጥ ስንመለከት 2ኛ አመልካች 1ኛ አመልካችን በመወከል ባከናወንኩት ሕጋዊ ተግባር በግላ ልከሰስ አይገባም በማለት ተከራክረዋል። ከሳሽ ከተከሳሽ ላይ የሚጠይቀውን ጥቅም ወይም መብት በማረጋገጥ አቤቱታ ካላቀረበ በቀር በማናቸውም ሰው ላይ ክስ ሉያቀርብ እንደማይችል በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33/3 ላይ ተመልክቷል። 1ኛ አመልካች የራሷ የህግ ሰውነት ያላት የእምነት ተቋም መሆኗ በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። ህጋዊ ሰውነት ያለው አካል ሕጋዊ ተግባራትን የሚያከናውነው ህጋዊ ውክልና ባለው የተፈጥሮ ሰው መሆኑ ግልጽ ነው። 2ኛ አመልካችም የ1ኛ አመልካች አገልጋይ በመሆናቸው 1ኛ አመልካችን ወክለው ህጋዊ ተግባራትን የሚያከናውኑ ስለመሆኑ አከራካሪ ፍሬ ነገር አይደለም። ለክርክሩ መሰረት የሆነውን የኪራይ ውልም ከተጠሪ ጋር 1ኛ አመልካችን ወክለው የፈጸሙት 2ኛ አመልካች ናቸው። ውክልና ማለት ደግሞ ተወካዩ በወካዩ ስም ሆኖ ህጋዊ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል ስልጣን ሲሆን ተወካዩ ከውክልና ስልጣኑ ሳያልፍ የሚያከናውናቸው ተግባራት ተጠያቂነትን የሚያስከትለ ከሆነ ተጠያቂ የሚሆነው ወካዩ ስለመሆኑ ከፍ/ሕ/ቁጥር 2199 እና ከተከታዮቹ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። በዚህም መሰረት 2ኛ አመልካች 1ኛ አመልካችን ወክለው ከተጠሪ ጋር ለክርክሩ መሰረት የሆነውን የኪራይ ውል ያደረጉ ቢሆንም በኪራይ ውለ መሰረት የኪራዩ ገንዘብ ባለመከፈለ እንዱሁም የውለ ጊዜ ሲያበቃ ቤቱ ባለመለቀቁ ተጠያቂ ልትሆን የምትችለው 1ኛ አመልካች ናት። 2ኛ አመልካች የ1ኛ አመልካች ሕጋዊ ወኪል በመሆናቸው 1ኛ አመልካች በምትከሰስበት ጉዲይ 2ኛ አመልካችም በግል የሚከሰሱበት ህጋዊ ምክንያት የለም። በመሆኑም ጉዲዩ የተጀመረበት ፍርድ ቤት 2ኛ አመልካች ልከሰስ አይገባም የሚል መቃወሚያ ሲያቀርቡ ከላይ በተገለጸው ምክንያት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33/3 መሰረት 2ኛ አመልካች ሉከሰሱ አይገባም በሚል ከክርክሩ ውጪ ማድረግ ሲገባው 2ኛ አመልካችንም ለክሱ ተጠያቂ ማድረጉ እንዱሁም ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የስር ፍርድ ቤትን ስህተት ማረም ሲገባው ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የውክልና ድንጋጌ በመጥቀስ 2ኛ አመልካችን ከ1ኛ አመልካች ጋር ለክሱ ኃላፉ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይባል ብለናል።
በመቀጠል ያልተከፈለ የኪራይ ገንዘብ እንዱከፈል እና ለክርክሩ መሰረት የሆነውን ቤት ተጠሪ ሉረከቡ ይገባል ተብል የመወሰኑን አግባብነት ስንመለከት ተጠሪ ያልተከፈለ የኪራይ ገንዘብ እንዱከፈል እና ለክርክሩ መሰረት የሆነው ቤት እንዱለቀቅ እንዱወሰንላቸው የጠየቁት በ1ኛ አመልካች እና በተጠሪ መካከል በነሐሴ 25 ቀን 2011 ዓ.ም በተደረገ የኪራይ ውል መሰረት አልተፈጸመልኝም በሚል ነው።
1ኛ አመልካችም ይህ ውል መደረጉን ሳትክድ በኪራይ ውል ላይ የተጠቀሰውን ቤት ከተጠሪ ስላልተረከብኩ የኪራይ ገንዘብ ልከፍል አይገባም። እንዱሁም እየተጠቀምኩ ያለሁት በራሴ ቤት ስለሆነ ለተጠሪ ላስረክብ አይገባም በማለት ተከራክራለች። በመሆኑም ለግራ ቀኙ ክርክር እልባት ለመስጠት በመጀመሪያ መጣራት ያለበት ነጥብ 1ኛ አመልካች በኪራይ ውለ ላይ የተጠቀሱትን ቤቶች ከተጠሪ ተረክባለች ወይስ አልተረከበችም የሚለው ይሆናል። ጉዲዩ የተጀመረበት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ 1ኛ አመልካች የኪራይ ውል ፈጽማ የኪራይ ገንዘብ እየከፈለች ከቆየች በኋላ ቤቶቹን አልተረከብኩም በማለት የምታነሳው ክርክር ተቀባይነት የለውም የሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል።
ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩለ 1ኛ አመልካች በኪራይ ውለ ላይ የተጠቀሱትን ቤቶች ከተጠሪ ተረክባለች ወይስ አልተረከበችም የሚለውን ለማጣራት አሁን በ1ኛ አመልካች ይዞታ ስር የሚገኙት ቤቶች በተጠሪ ካርታ ውስጥ የሚገኙ ስለመሆን አለመሆኑ በሚመለከተው የመንግስት አካል ተጣርቶ እንዱቀርብለት ትእዛዝ ሰጥቶ በ1ኛ አመልካች ይዞታ ስር የሚገኙት ቤቶች በተጠሪ ካርታ በተጠቀሰው ይዞታ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸው ተረጋግጦ እንደቀረበለት የውሳኔው ግልባጭ ያሳያል።
ለክርክሩ መሰረት የሆነው የኪራይ ውል ቢሆንም 1ኛ አመልካች በኪራይ ውል ላይ የተጠቀሱትን ቤቶች አልተረከብኩም፤ የምጠቀመውም በተጠሪ ቤቶች አይደለም በሚል ስለተከራከረች በኪራይ ውለ ላይ የተገለጹት ቤቶች በተጠሪ ህጋዊ ይዞታ ውስጥ የሚገኙ ስለመሆን አለመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተጣርቶ እንዱቀርብ በማዘዝ እና ተጣርቶ የቀረበለትን ማስረጃ በመመዘን 1ኛ አመልካች በኪራይ ውለ ላይ የተጠቀሱትን ቤቶች ከተጠሪ አልተረከብኩም የምትለውን ክርክር ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤትን ድምዲሜ ተቀብሎል።
እንደሚታወቀው ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ሀ እና በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 የተሰጠው የዲኝነት ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸውን የመጨረሻ ውሳኔዎች ማረም ነው። በዚህ ሥልጣኑ ተከራካሪ ወገኖች ማስረጃ ለመቀበል፣ ለመስማትና ለመመዘን ሥልጣን ለተሰጣቸዉ የስር ፍርድ ቤቶች ያቀረቡትን ማስረጃዎች የመመዘን ጉዲይ ዉስጥ በመግባት ማስረጃዎችን በመመርመርና በመመዘን አከራካሪ የሆነዉ የፍሬ ነገር ጭብጥ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥልጣን ሰበር ችልቱ አልተሰጠዉም ማለት ነው። ሆኖም የማስረጃ አቀራረብን፣ አግባብነትን፣ ተቀባይነትን እና ማስረጃ አቅርቦ አንድን ፍሬ ነገር የማስረዲት ሸክም መርህ (Production, relevancy, admissibility and burden of proof of evidence)እንዱሁም የማስረጃ ምዘናን ወይም የማስረዲት ደረጃን (standard of proof or weight of evidence) የሚመለከቱ መሰረታዊ መርሆዎች ተጥሶ የተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ ሲኖር መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሚሆን በሰበር ሰሚ ችልት የሚታረም ይሆናል። በተያዘው ጉዲይ 1ኛ አመልካች በኪራይ ውል ላይ የተጠቀሰውን ቤት የተረከበች መሆን አለመሆኑን ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የስር ፍርድ ቤቶች የቀረቡትን ማስረጃዎች መዝነው 1ኛ አመልካች በኪራይ ውለ ላይ የተጠቀሱትን ቤቶች ተረክባለች የሚል ድምዲሜ ላይ ደርሰዋል። የስር ፍርድ ቤቶች ለቀረቡት ማስረጃዎች ተገቢውን ዋጋ ባለመስጠት ወይም መሰረታዊ የማስረጃ ምዘና መርህ ጥሰት መፈጸማቸውን የክርክሩ ሂደት አያሳይም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች 1ኛ አመልካች በኪራይ ውለ መሰረት ቤቶቹን ተረክባለች በማለት የደረሱበትን የፍሬ ነገር ድምዲሜ ይህ ችልት እንዲለ የሚቀበለው ይሆናል።
1ኛ አመልካች በኪራይ ውለ መሰረት ቤቶቹን ተረክባለች ከተባለ በኪራይ ውለ ላይ የተጠቀሰውን የኪራይ ገንዘብ የመክፈል እና የውለ ጊዜ ሲያልቅ አከራይ ለሆኑት ተጠሪ ቤቶቹን የማስረከብ የውል ግዳታ አለባት። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች 2ኛ አመልካችን ለክሱ ኃላፉ ማድረጋቸው ሉታረም የሚገባው ቢሆንም ከ1ኛ አመልካች አንጻር የሰጡት ውሳኔ ግራ ቀኙ ያደረጉትን የኪራይ ውል እና የቀረቡትን ማስረጃዎች መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በስተቀር በዚህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
1ኛ. በፋደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ብይን፤ በነሐሴ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በመጋቢት 07 ቀን የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1 መሰረት ተሻሽሎል።
2ኛ. 2ኛ አመልካች በግል መከሰሳቸው ተገቢ አይደለም ብለናል።
3ኛ. 1ኛ አመልካች ያልተከፈለ የኪራይ ገንዘብ ከፍላ ለክርክሩ መሰረት የሆነውን ቤት እንድታስረክብ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ጸንቷል።
4ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ትእዛዝ 1ኛ.በዚህ መዝገብ በሚያዝያ 19 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችልት የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።ይጻፍ።
2ኛ. የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመዝገብ ተመላሽ ይደረግ።
No topics extracted.