No summary available.
መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ዳኞች፡- እትመት አሰፊ ደጄኔ አያንሳ ኑረዱን ከድር መላኩ ካሳዬ ሀብታሙ እርቅይሁን አመልካች፡- አቶ ተባረክ ዘሩ - ቀርቧል ተጠሪ፡- ወ/ሮ ጨዋነሽ በርቱ - አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የባልና ሚስት ንብረት ክርክር የሚመለከት ሆኖ ክሱ በቀረበበት የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት በፉንፉኔ ዙርያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ፣ ተጠሪ ደግሞ በከሳሽነት ተከራክረዋል። የክርክሩ አመጣጥ በአጭሩ፡- አመልካች የፍቺ ውሳኔን ተከትል ባቀረቡት የንብረት ዝርዝር ቡራዩ ከተማ አስተዲደር በመልካ ገፈርሳ ቀበላ ውስጥ የሚገኝ በ90 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈ በግራ ቀኙ የተፈራ አዋሳኞቹ በክሱ ላይ የተመለከተው 650,000.00(ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር የሚያወጣ መኖሪያ ቤት ተሸጦ ግማሽ ደርሻቸው እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል።
ተጠሪ በበኩላቸው ባቀረቡት መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆነው መኖሪያ ቤት የባልና ሚስት ንብረት ሳይሆን የእህታቸው የወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ መሆኑን ፤ ንብረቱ የግራ ቀኙ የጋራ ለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩን ፤ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል አቶ ፈቃደ በረዲ ከሚባል ሰው 430,000.00(አራት መቶ ሰላሳ ሺህ) ብር መገዛቱ ፤ አመልካች አከራካሪውን ቤት ለመግዛት የሚያስችል አቅም የላለው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ቤቱ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት አለመሆኑን ተረድቶ የአመልካችን አቤቴታ ውድቅ እንዱያደርግ ጠይቀዋል። ክርክሩ በተሰማበት ወቅት ለክርክሩ መነሻ የሆነው መኖሪያ ቤት በተጠሪ ስም መገዛቱንና በስማቸው መመዝገቡን ፤ በተጠሪ በኩል የቀረበው ማስረጃ የውሸት የመንደር ውል መሆኑን፤ ትክክለኛው ቤቱ የተገዛበት ውል አቶ ፈቃደ በረዲ እጅ ስለሚገኝ ማቅረብ እንደሚቻል ተከራክረዋል። ተጠሪ በበኩላቸው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት እህታቸው ወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ ከውጪ በላኩት ገንዘብ መገዛቱን፤
በእህታቸው ፈቃድ በቤቱ ውስጥ የሚኖሩ በመሆኑ በቤቱ ላይ መብት እንደላላቸው ተከራካረዋል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አከራካሪው ቤት የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት ነው ወይስ በተጠሪ እህት ስም የተገዛ ነው? የሚል ጭብጭ ይዞ የተከራካሪዎችን ማስረጃ ሰምቶ መዝገቡን እንደመረመረው በአመልካች በኩል የቀረቡት ሶስት ምስክሮች ግራ ቀኙ በአከራካሪው ቤት ውስጥ መኖራቸውን እንጂ ቤቱ የማን እንደሆነ አናውቅም ያለ ሲሆን የቤቱ ሻጭ የሆኑት አንደኛው ምስክር ግን ቤቱን የሸጡት ለተጠሪ መሆኑን ፤ ውለም በተጠሪ ስም መፃፈን ፤ ውልንም ለተጠሪ የሰጡ መሆኑን ገልፀዋል። በተጠሪ በኩል የቀረቡት ምስክሮች ቤቱ የተገዛው ለተጠሪ እህት ወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ ተብል መሆኑን አስረደተዋል። አመልካች ቤቱ የተገዛው በተጠሪ ስም መሆኑን ገልፆ የተከራከረ ቢሆንም ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈው የሽያጭ ውል የውል ተቀባይ አቶ ዓለሙ በርቱ መሆኑን የሚያመልክት ሲሆን አመልካች ቤቱ በተጠሪ ስም መገዛቱን የሚያመለክት ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም። ተጠሪ አከራካሪው ቤት የተገዛበት ገንዘብ ከአቶ ገታሜ ኢንጋኒ ወደ እሷ አካውንት የተላለፈ መሆኑን ገልፃ የተከራከረች ሲሆን የሽያጭ ውለ በተደረገበት ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም 400,000.00(አራት መቶ ሺህ) ብር ከአቶ ገታሜ ኢንጋኒ ወደ ተጠሪ አካውንት መተላለፈን የሚያመለክት ማስረጃ ቀርቧል። አመልካች አከራካሪው ቤት በተጠሪ ስም መገዛቱን እንጂ እንዳት እንደተገዛ ማስረዲት ያልቻለ ሲሆን በአንፃሩ ተጠሪ ቤቱ የተገዛበት ገንዘብ በምን አግባብ ወደ አካውንቷ እንደተላለፈ አስረድታለች። አከራካሪውን ቤት ባልና ሚስት ያፈሩ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አልቀረበም። በቡራዩ ከተማ አስተዲደር መልካ ገፈርሳ ቀበላ በ90 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ቤት ግራ ቀኙ በትዲር ውስጥ እያለ በጋራ ያፈሩት ንብረት ሳይሆን የተጠሪ እህት የሆኑት ወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ በወንድሟ አቶ ፍቃደ በርቱ ስም ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ስምምነት ከአቶ ፍቃደ በረዲ የተገዛ ስለሆነ ተከራካሪዎቹ በቤቱ ላይ ምንም መብት የላቸውም በማለት በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 33(2) መሰረት አመልካች ያቀረቡትን የቤቱ ግማሽ ድርሻ ይገባኛል ጥያቄን ውድቅ አድርጓል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ያቀረቡትን የይግባኝ አቤቱታ የፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት መሰረዙን ተከትል ለሁለተኛ ጊዜ አመልካች ያቀረቡትን የይግባኝ አቤቱታ የመረመረው ይግባኝ ሰሚው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ በሰጠው ውሳኔ ሻጩ አከራካሪውን ቤት ለተጠሪ ሽጦ ገንዘቡንም በባንክ ያስተላለፈችለት መሆኑን፤ የሽያጭ ውለንም ለተጠሪ የሰጠ መሆኑን መስክሯል። አመልካች እና ተጠሪ ክርክር በተነሳበት ቤት ውስጥ በአንድ ላይ እንደሚኖሩ በተጠሪ ባልተካደበት እና የቀረበው የሽያጭ ውልም ቤቱ በአቶ ዓለሙ በርቱ ስም እንጂ በወ/ሮ አመለወርቅ ስም የተገዛ መሆኑን የማያመለክት ሆኖ እያለ፤ አቶ ዓለሙ በርቱ ለወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ ቤት መግዛት የሚያስችለው ውክልና ሳያቀርብ እንዱሁም ወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 41 መሰረት ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተው ያልተከራካሩ ሲሆን አከራካሪው ቤት በተጠሪ ስም መገዛቱ እና የሽያጭ ገንዘብም በተጠሪ ስም ለመከፈለ ማስረጃ ስለቀረበ አከራካሪው ቤት ግራ ቀኙ በትዲር ውስጥ እያለ የተፈራ መሆኑ ተረጋግጧል በሚል የቡራዩ ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር ቤቱ የባልና ሚስቱ የጋራ ንብረት ነው በማለት እኩል እንዱካፈለ ወስኗል።
ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት ተጠሪ ባቀረቡት የሰበር ቅሬታ ጉዲዩን የተመለከተው የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችልት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ በሰጠው ውሳኔ ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቤቱ የተገዛበት ገንዘብ ምንጭ ሳይሆን ግራ ቀኙ በቤቱ ውስጥ ይኖሩ የነበረ መሆኑና ቤቱ የተገዛው በልላ ሰው ስም ቢሆንም ቤቱን ለመግዛት የሚያስችል የውክልና ማስረጃ አልቀረበም በማለት ቤቱ የጋራ ነው ሲል የደረሰበት ድምዲሜ ገንዘቡ በባለትዲሮቹ ልፊት የተገኘ ነው አይደለም የሚለውን ጭብጥ ሳይመረምር ውሳኔ የሰጠ ሲሆን በተቃራኒው የቡራዩ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ገንዘቡ የ3ኛ ወገን መሆኑን ማረጋገጡን ፤ አመልካች ቤቱ የተገዛበት ገንዘብ የተገኘው ግራ ቀኙ አቶ ገታሜ እንጋኒ ጋር ስንቆጥቡ የነበረ ነው በማለት ያቀረበው ክርክር አዱስ በመሆኑ በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 329 መሰረት ተቀባይነት የላለው መሆኑን ጠቅሶ ይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አከራካሪው ቤት የጋራ ነው ሲል የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የቡራዩ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል።
የሰበር ቅሬታው የቀረበው የቡራዩ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ ፤ የፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት በሰበር ለማስለወጥ ሆኖ የሰበር ቅሬታው በአጭሩ፡- በትዲር ውስጥ የተገዛ ቤት የኔ ነው ባይ 3ኛ ወገን ቀርቦ ባልተከራከረበት ተጠሪ አከራካሪው ቤት የ3ኛ ወገን ነው የሚል ክርክር ለማቅረብ የሚያስችል መብት ሳይኖራት ባቀረበችው ክርክር መነሻነት ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የጋራ ንብረት አይደለም ተብል መወሰኑ የሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ የሰጠውን አስገዲጅ ውሳኔን ይቃረናል።
ተጠሪ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት የአራካሪውን ቤት ግማሽ ባለድርሻ ናቸው በማለት የሰጠውን ውሳኔ ለመቃወም የሚያስችላቸው መብት ሳይኖራቸው ያቀረቡት አቤቱታ የፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 327 እና አዋጅ ቁጥር 216/2011 አንቀጽ 27 ድንጋጌን የሚቃረን ሆኖ እያለ ይህንን በመተላለፍ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው። የአከራካሪው ቤት ሻጭ ቀርቦ በሰጠው የምስክርነት ቃል ቤቱን የሸጠው ለተጠሪ መሆኑን፣ የቤቱ ሽያጭ ገንዘብ የተከፈለው ከአዋሽ ባንክ ወጪ ሆኖ በተጠሪ በኩል መሆኑንና የውል ሰነደም ያለው በተጠሪ እጅ መሆኑን ያስረዲ ሲሆን ወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ ለግዥ የዋለውን ገንዘብ ለተጠሪ መላኳ እንዱሁም አቶ አለሙ በርቱ በወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ ስም ቤት እንዱገዛ የተወከለበት ማስረጃ ባልቀረበበት አከራካሪው ቤት የወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ የግል ንብረት ነው ተብል መወሰኑ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ማስረጃ የመዘዘን ስልጣን ሳይኖረው ማስረጃን መዝኖ ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ ህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆኑን ጠቅሰው የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ተሽሮ የይግባኝ ሰሚ ችልቱ ውሳኔ እንዱፀናላቸው ጠይቀዋል።
የሰበር አጣሪ ችልቱ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 28(1) እንዱሁም በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 ቁጥር 6(1) መሰረት ለሰበር ሰሚው ችልት የተመራው የሰበር አቤቱታ በሰበር ሰሚ ችልቱ ተመርምሮ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት ለክርክሩ መነሻ ምክንያት የሆነው የ3ኛ ወገን(የተጠሪ እህት) ሳይሆን የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ የተጠሪን መብት ሉነካ የሚችልበት ሁኔታ በላለበት ተጠሪ ቤቱ የ3ኛ ወገን ነው ተብል ሉወሰን ይገባል በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችልት ተቀብል መወሰኑ ሥነ ሥርዓታዊ መሆን አለመሆኑ ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ ለሰበር ቅሬታው በሰጡት መልስ የቡራዩ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት አከራካሪውን ቤት አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ የፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማጽናቱን ተከትል ጉዲዩን የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔን በመሻሩ ተጠሪ ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሻሩ የሥነ ሥርዓት ሕጉን የተከተለ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ አይደለም። አመልካችና ተጠሪ ለክርክር መነሻ የሆነውን ቤት ለመግዛት አቅም የላላቸው መሆኑን ፤ ለቤቱ መግዣ የዋለው ገንዘብ ተጠሪ ወደ ሻጭ የሂሳብ ቁጥር ያስተላለፍኩት ወንድሜ አቶ ዓለሙ በርቱ የአዋሽ ባንክ አካውንት ስላልነበረው መሆኑን ፤
ከእህቴ ወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ የተላከው ገንዘብ በተጠሪ አካውንት ገብቶ ለሻጭ መተላለፈ በተጠሪ ምስክሮች መረጋገጡን ፤ ወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ ግራ ቀኙ በአከራካሪው ቤት ውስጥ እንዱኖሩ በመፍቀዶ ምክንያት አመልካች እንደጋራ ንብረት መጠየቁ ያልተገባ ብልጽግና ለማግኘት መሆኑን፤ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በቀጥታ የተጠሪ መብት የሚነካ ባይሆንም የባልና ሚስት ንብረት አይደለም በማለት ተጠሪ ያቀረብኩት ክርክር ተቀባይነት ማግኘቱ ሥነ ሥርዓታዊ አይደለም ቢባል እንኳን የሥር ፍርድ ቤቶች ወ/ሮ አመለወርቅ በርቱን የክርክሩ ተካፊይ ማድረግ የነበረባቸው ቢሆንም የተጋቢዎች ያልሆነውን ቤት የጋራ ንብረት አይደለም ብል መወሰናቸው የሚነቀፍ አለመሆኑን ፤ ቤቱ የባልና ሚስት የጋራ ነው ተብል ቢወሰን ተጠሪ ከላላ ሶስተኛ ወገን ለወሰድኩት ንብረት ተጠያቂ መሆናቸውን በመግልጽ የቡራዩ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱጸና ፤ ውሳኔው ሥነ ሥርዓታዊ አይደለም የሚባል ከሆነም መዝገቡ ወደ ሥር ፍርድ ቤት ተመልሶ ለክርክሩ 3ኛ ወገን የሆኑት እህታቸው ወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተው ጉዲዩ በአዱስ መልክ ታይቶ ውሳኔ እንዱያገኝ ጠይቀዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና መሰረታዊ የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችልቱም በሰበር ችልቱ ሉጣራ ይገባዋል ተብል የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
በፍትሐ ብሕር ሥና ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 39 ድንጋጌ መሰረት በክሱ ውስጥ መጣመር የሚገባው ሰው አለመጣመር ወይንም መከሰስ የማይገባውን ሰው በማጣማር የቀረበ ክስ ውድቅ የማያደረገው ሲሆን ፤ በክሱ ውስጥ ተሳታፉ መሆን የሚገባቸዉ ወገኖች መቅረትን በሚመለከት ወይንም ተካፊይ መሆን የሚገባቸው ወገኖች ተሳታፉ ሆኖ ሲገኙ ክርክሩ ከመጀመሩ በፉት ተቃውም መቅረብ ያለበት መሆኑን ይደነግጋል። ከባለ ጉዲዮቹ የሚቀርብ ክርክርን መሰረት በማድረግ ፍርድ ቤት በራሱ ተነሳሽነት ለውሳኔ አሰጣጥ አስፈላጊ የሆነን ሰው አባሪ ሆኖ በክርክሩ እንዱገባ ማድረግ እንደሚችል የፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 40(2) ይደነግጋል። በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የክርክር ተካፊይ የሚሆኑ ሰዎች ለክርክሩ የግድ አስፈላጊ የሆኑ (indispensable party) ባልተሳተፈበት ክርክር መብት እና ጥቅማቸው ወይንም ግዳታቸውን የሚነካ ተካፊይ ባልሆኑበት ክርክር የሚሰጠው ፍርድ ወይንም ውሳኔ ውጤት የማይኖረው ሰዎች ሲሆኑ ነው። በክሱ በተከሳሽነት ተካፊይ መሆን የሚገባውን ከሳሽ ያላጣመረው ቢሆንም ለቀረበዉ ክስ የመከላከያ መልስ እንዱሰጥበት በፍርድ ቤት ሉታዘዝ የሚገባ መሆኑ የፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 39(1) እና 40(2) ድንጋጌ ያስገነዝበናል።
ባለሀብትነት በሕግ ወይንም ባለጉዲዮች በሚያደርጓቸው ሕጋዊያን ተግባሮች የሚተላለፍ ሲሆን የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ባለሀብትነት ሲተላለፍ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ማስመዝገብ አስፈላጊ መሆኑን የፍትሐብሕር ሕጉ ቁጥር 1184 እና 1185 ያስገነዝበናል። በዚህ መልክ ሀብትነቱ ለላላ ሰው ሲተላለፍ ሀብትነት ቀሪ እንደሚሆን ከፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር 1189 ድንጋጌ መረዲት ይቻላል። የባለሀብትነት ምስክር ወረቀት የሚሰጠው በፍ/ሕ/ሕግ ቁጥር 1553- 1636 ድንጋጌዎች መሰረት ነው።
በተያዘው ጉዲይ ቡራዩ ከተማ አስተዲደር በመልካ ገፈርሳ ቀበላ ውስጥ የሚገኝ በ90 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈው ቤት በስማቸው ተገዝቷል በማለት የቀረበው ሰነድ የመንደር ውል በመሆኑ የተጠሪ እህት የሆኑት ወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ በክርክሩ በግድ መሳታፍ የሚገባቸውን (indispensable party) ስላልሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 39(1) እና 40(2) መሰረት ወደ ክርክሩ መግባት የሚገባቸው አይደለም።
አመልካች እና ተጠሪ ክርክር በተነሳበት ቤት ውስጥ በአንድ ላይ የሚኖሩ መሆኑ በተጠሪ አለመካደ ፤ የቀረበው የሽያጭ ውልም ቤቱ በአቶ ዓለሙ በርቱ ስም እንጂ በወ/ሮ አመለወርቅ ስም መገዛቱን የማያመለክት መሆኑን ፤ አቶ ዓለሙ በርቱ ለወ/ሮ አመለወርቅ በርቱ ቤት መግዛት የሚያስችል ውክልና አለመቅረቡ ፤ አከራካሪው ቤት በተጠሪ ስም መገዛቱ እና የሽያጭ ገንዘብም በተጠሪ ስም መከፈለንና የቤት ሽያጭ ውለም ለተጠሪ መስጠቱን የቤቱ ሻጭ የሆኑት ግልሰብ በሰጡት የምስክርነት ቃል መረጋገጡን መሰረት አድርጎ ይግባኝ ሰሚው የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ማስረጃ የመዘዘን ስልጣን ሳይኖረው ማስረጃን መዝኖ ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን ውሳኔ መሻሩ በሰበር መዝገብ (በቅጽ 9 እንደታተመው) የተሰጠውን አስገዲጅ ውሳኔን እንዱሁም የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ- መንግስት አንቀጽ 80(3/ለ) እና የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 216/2011 አንቀጽ 25(2/ረ) እና አንቀጽ 26/2 ድንጋጌዎችን የሚቃረን መሰረታዊ ህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ቀጣዩ ተወስኗል።
በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ - ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 ቁጥር 9(1/ለ) መሰረት ተሽሯል።
ይግባኝ ሰሚው የኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዝገብ ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ እና ትዕዛዝ ፤ በፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሥነ - ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 ቁጥር 9(1/ሀ) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ውሳኔው ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በችልት ተነቧል።
ፍ/ደ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.